Telegram Web Link
ጓደኛ አታብዛ!!

የሁሉም ሰው ጓደኛ ከሆንክ አስታውስ አንተ የራስህ ጠላት ነህ።ብዙ ጓደኛ ኖሮት ለራሱ በቂ ጊዜ የሚሰጥን ሰው ፈልግ፣ ያ7ኘውን ሰው በሙሉ ጓደኛ እያደረ7 የተጠቀመን ሰው ፈልግ፡፡ በፍፁም አታገኝም፡፡ የጓዷኛ ብዛት ችግር እንጂ ምንም የሚጠቅምህ ነገር የለውም፡፡ ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገደብ አብጅለት፡፡ በሰው ተከበህ ለራስህ ጠላት ከምትሆን ብቻህን ቀርተህ ለራስህ ወዳጅ ብትሆን ይሻላል፡፡ ጫወታው ጓደኛ ባበዛ ሳይሆን ጥራት ያላቸው ካንተ ባህሪና ማንነት ጋር የሚሔዱ፣ የሚጠቅሙህና የሚረዱህ ጥቂት የልብ ጓደኞችን ማፍራት ነው፡፡ ከራሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የማይወድ ሰው የጓደኞቹ ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ባይፈልግም እንኳን ሁሌም ራሱን የሚያገኘው እነርሱን ለማስደሰት ሲጥር ነው፡፡ ብቸኝነትን ይፈራልና እየተጠቀሙበትም ቢሆን ጎጂ ጓደኝነት (toxic friendship) ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይቆያል፡፡ ጓዷኝነት ካልጠቀመህ ብዛቱ ምን ያደርግልሃል? በዙሪያህ ብዙ ሰው ካለ በዋናነት የምታቃጥለው የራስህን ውድ ጊዜ ነው፡፡

ራስህን ታደግ! እርግጥ ነው ለብቻ መጓዝ ከባዱ ፖዞ ነው ነገር ግን ከእርሱ በላይ የሚያጠነክርህ ነገር የለም፡፡ በጫጫታና በአላስፈላጊ ድራማ መከበብ ማንንም ነፃ አውጥቶ አያውቅም፡፡ብዙ ጓደኛ ስላላቸው በሰዎች የሚወደዱ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዛ ጓደኞቼ የሚሏቸው ሰዎች እንደሚወዷቸው ለማረጋገጥ በደስታቸውና በሃዘናቸው ጊዜ የሚሰማቸውን ስሜት ማስተዋል ቢችል ብዙ ያተርፋል፡፡ ምቀኛም ሆነ ሌባ ከሩቅ አይመጣም፡፡ አብዝቶ የሚያውቅህ፣ የቅርብ ጓደኛዬ ነው አመነዋለሁ የምትለው ሰው ስለሚቀናብህ ብቻ ከጀርባህ ምን ሊሰራብህ እንደሚችል አታውቅም፡፡ ብዙ ጓደኛ ሲኖርህ ችግር አያጣህም፡፡ የእያንዳንዳቸውን ችግር ለመቅረፍ ስትሞክር የራስህ ችግር ሊያሰምጥህ ይደርሳል፡፡ ለእነርሱ ስትሯሯጥ ራስህን ትረሳለህ፣ ምናልባትም ባላሰብከው መንገድ ልትጠፋ ትችላለህ፡፡ በአንድም ሆነ በሌላ የማይጠቅምህ ጓደኝነት እየጎዳህ ነው ማለት ነው፡፡

ጓደኛ አታብዛ፣ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ቀንስ፡፡ ከእነርሱ የምታገኘውና ለእነርሱ በምትሰጠው ነገር ላይ ግንኙነትህን መስርት፡፡ በፍፁም ትርጉም አልባ ግንኙነት ውስጥ ተሳስተህ እንኳን እንዳትገባ፡፡ ጓዷኝነት የህይወት አቅጣጫህን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል፡፡ በጓደኛህ ትጠፋለህ በጓደኛህ ትድናለህ፡፡ በክፏ ቀን የሚዷርስህ ጓዷኛህ ነው፣ ደስታህንም እንደራሱ ደስታ የሚደሰትልህ እርሱ ነው፡፡ ከባድም ቢሆን ጓደኛህን በአግባቡ ምረጥ፡፡ ከቻልክ ቁጥራቸውን ቀንስ፣ የጋራ ነገር ከሌላችሁና የማያተርፍልህ ከሆነ ጓዷኝነቱ ይቅርብህ፡፡ ማንም ትርፍ አልባ ግንኙነት የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንተ ለራስህ ካላወቅክ ማንም መጥቶ የሚጠቅምህን ሊነግርህ አይችልም፡፡ በመሰለህ መንገድ ሳይሆን በሚጠቅምህ ትክክለኛ መንገድ ተጓዝ፡፡ የይሉኝታ ተጠቂ አትሁን፡፡ አንዳንዴ ጓደኛህን ምንም ያህል ብትወድውም ወደ ጥፋት መንገድ እየመራህ ከሆነ አንድም ለራስህ ብለህ ሌላም ራስህን አድነህ ዳግም ተመልሰህ እርሱን ታድነው ዘንድ እያዘንክ ትተወዋለህ፡፡ የምታውቀውን ሰው በሙሉ ጓደኛ ለማድረግ አትሞክር ይልቅ በቅድሚያ የራስህ ጓደኛ ሁን፡፡ በየትኛውም መንገድ ጥራትን እንጅ ብዛትን አትፈልገው ይቅርብህ፡፡ ጓደኛ ማለት አንተ በለለህበት አንተን ሆኖ የሚገኝልህ ሰው መሆኑን አትርሳ!! አሏህ የልብ ወዳጅ መልካም ጓደኛ ይስጣችሁ፡፡


ድንቅ ምሽት ይሁንልን!
ከአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ጋር ሙሉ ጊዜ መስራት ለምትፈልጉ ካላችሁበት ሆናችሁ በየትኛውም የስራ ዘርፍ ለመቀጠር በቴሌግራም @miyomi መልእክት ይላኩልን!
2025/07/04 07:05:08
Back to Top
HTML Embed Code: