Telegram Web Link
ነጃሺ ቲቪ እና አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

•••••“ኡመር” ፊልም በረመዳን በነጃሺ ቲቪ ሊቀርብ ነው

በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን አዘጋጅነትና በነጃሺ ቲቪ አቅራቢነት በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎመውን የታላቁን ሶሀባ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ፊልም ወደ ህዝብ ይቀርባል።

የትርጉም ፊልሞችን በአማርኛ በመተርጎም ግንባር ቀደም ከሆኑ ተቋማት አንዱ የሆነው አልፋሩቅ መልቲሚዲያ የተወዳጁን ነብይ ዩሱፍ(አለይሂ ሰላም)ን ፊልም ጨምሮ በርካታ ፊልሞችን ተርጉሞ ለህዝቡ አድርሷል።

አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ከትርጉም ስራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ኢስላማዊ ስራዎችን በማዘጋጀት በነጃሺ ቲቪ ለማስተላለፍ እና በጋራ አብሮ ለመስራት ስምምነት እንደተደረገ የነጃሺ ቲቪ ፕሮግራም ሀላፊ አቶ አሊ አሚን ገልፀዋል።

አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ የሚሰራቸውን ኢስላማዊ ፕሮግራሞችና የትርጉም ስራዎች ወደ ህዝበ ሙስሊሙ ተደራሽ ለማድረግ ነጃሺ ቲቪ አንዱ አማራጭ ሆኖ እንዳገኙት የጠቀሱት የአል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ዋና ስራ አሰኪያጅ አቶ ፋሩቅ ጋሊብ ናቸው።

አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ የሚያስተምሩና የሚያዝናኑ ፕሮግራሞችን ተመልካች ዘንድ በጥራት ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ስራ አሰኪያጁ ተናግረዋል።

በአል ፋሩቅ መልቲሚዲያ የተዘጋጀው የኡመር ኢብኑ ኸጣብ የትርጉም ፊልም በረመዳን ከተራዊ መልስ ፊልሙ በነጃሺ ቲቪ መተላለፍ እንደሚጀምር የነጃሺ ቲቪ ፕሮግራም ክፍል ሀላፊ አቶ አሊ አሚን አሰታውቀዋል።

ነጃሺ ቲቪ
ወደ ልዕልና
በዑመር ኢብኑልኸጣብ ረ.ዐ. ህይወት ላይ ያተኮረውና በዓለም ዑለሞች ህብረት እውቅና የተቸረው "ዑመር" ፊልም ከዛሬ ምሽት 3:30 ጀምሮ በነጃሺ ቲቪ መተላለፍ ይጀምራል!

ነጃሺ ቲቪ! ወደ ልዕልና!
እሁድ ምሽት ይጠብቁን
ያሸምሰል መዲና || ከድር አብደላ (አልሀድራ)
በቅርብ ቀን ይጠብቁን
''ላኢላሀ ኢለላህ''
አዲስ የመንዙማ አልበም በቅርብ ቀን ይጠብቁ

ላ ኢላሀ ኢለሏህ
ዘይኔ አሚና
ሳሂበል ሚዕራጅ
ሰላም አለይኩም ኑርሁሰይኒያ (አናጂና)
ሺሊላህ ያረሱላህ (ደዌ ሀድራ)

ግጥም
ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
ኡስታዝ አህመድ አደም
አብዱል ማሊክ ላሌ ጎራው
ሸህ ኢብራሂም ጫሌ
ዛሂድ ኢቅባል

ዜማ
ከመሻኢኮች
እና
ሷሊህ ሙሐመድ
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ!
የአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ!
የአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በታላቅ ደስታ ነው ይህንን የምስራች የምናበስረው! በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን( በመንዙማ እና ነሺዳ ዩትዩብ ቻናላችን) ብቻ ከ 200,000 በላይ ተከታዮች እና ከ 40 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን በማስመዝገብ ተደማጭነትን አትርፈናል!

በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ዩትዩብ ቻናል በማሚለቀቁ መንዙማ እና ነሺዳዎች ውስጥ ምን ያገኛሉ?
•  የጌታችንን አላህ (ሱ.ወ) እና የመልክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ውዳሴ የሚያቀርቡ መንዙማዎችን እና ነሺዳዎችን ያቀርባል።
•  የተለያዩ ኢስላማዊ አስተምህሮቶችን በስነ-ጥበብ ይገልፃል።
•  በ 3 አመታት ውስጥ ከ 500 በላይ ቪዲዮዎችን ፕሮዲውስ በማድረግ በራሱ እና በሌሎች ዩትዩብ ቻናል ላይ በመልቀቅ ተደራሽነቱን አስፍቷል።
ይህንንም መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ምርትዎን እና አገልግሎቶን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ታዳሚዎች ማድረስ ይችላሉ!
ከዋነው አልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን (ከመንዙማ እና ነሺዳ ቻናላችን )በተጨማሪ የሚከተሉትን ቻናሎቻችንን መጠቀም ይችላሉ፦
•  አልፋሩቅ ቶክ ሾው (Al-Faruk Talkshow)
•  አልፋሩቅ አል-ማዕሪፋ (Al-Faruk Al-Ma'arifa)
•  አልፋሩቅ ቁርኣን (Al-Faruk Quran)
ዛሬውኑ 0945144444 ይደውሉልን እና ምርትዎን እና አገልግሎቶን በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ዩትዩብ ቻናሎች በማስተዋወቅ ተደራሽነትዎን ያሳድጉ!
ለላቀ ኘሮዳክሽን ጥራት አልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን
2025/06/29 09:31:04
Back to Top
HTML Embed Code: