«ሰላም ዐለይኩም ነቢ»
ገጣሚያችን ዛሒድ ኢቅባል እና ዑስታዝ ሰኢድ አሕመድ በጋራ በመሆን የፃፉት መንዙማ ነው።
ከጥንት ከመሻኢኾቻን ዘመን ተወርሶ በዚህ ዘመን ማዲሆች እየተቀጠለ ያለውን የሰይዳችንን ውዳሴ ላይ የሚያጠነጥን፣ በውዳሴያቸው ስለሚገኙ በረከቶች፣ ስለ ፍቅራቸው፣ ስለ አፍቃሪው ሶሐባቸው የፍቅር ገድል ሌሎችም ተያያዥ ነጥቦች ይቃኛል።
በዘመኑ ተወዳጅ የሆኑት ማዲሆች…ድምፀ መረዋው ማዲህ ኢድሪስ ሙሐመድ፣ በስርቅርቅ ድምፁ የሚታወቀው ማዲህ ፉኣድ ሸምሱ እና ለስላሳ’ና ተወደጅ የሆነው ማዲህ ማህፊዝ አብዱ ተሳትፈውበታል።
እንዲሁም ሚናራ ፕርዳክሽን በጣም ቆንጆ አድርጎ ቪዲዮዉን ከሽኖታል::
አልፋሩቅ መልቲ ሚዲያም በሁሉም መልኩ ለታዳሚያን የሚመጥን አድርጎ አቅርቦታል። ዛሬ ምሽት 1:00 ለዕይታ ይበቃል!

❤20❤🔥2
እንኳን ለነብያችን ለሸፈዐችን ለከዉኑ ነጋሴ ለፋጥመቱ ዛህራ አባት ለመኸለቃችን ሰበብ ለሆኑት ለሙሂቦች አይነታ ሁሉም ለማየት ለሚመኛቸዉ ነብይ ለሁለቱም አገር ጠበቃችን አሏህ ለራሱ ሲል ለኸለቃቸዉ ለሚሳሳላቸዉ ዉዱ እና ምርጥ ነብይ ለአለሙ እዝነት ቢሆን እንጂ ለላካቸዉ ነብይ አሏህ ራሱ በክብር እና አቆላምጦ ቢሆን እንጂ በስማቸዉ ጠርቷቸዉ ለማያዉቁት ለተከበሩት ነብይ ከእናት አባት የበለጠ ለሚራሩልን ወንድሞቸ ናፈቁኝ ብለዉ ናፍቀናቸዉ ላለቀሱልን ነብይ የዉበታቸዉን ጥግ ሆነ እሳቸዉን መግልፅ ላልተቻሉት እሱን ስለሰጠኋቹ ተደሰቱ ብሎ ላዘዘን ምርጥ ነብይ ኡመቱ በማድረግ ከሁሉም እንድንልቅ ላደረጉን ሁሉ ነገራችን ለሆኑት ዘላላም አዲስ ለሆኑት እንደሳቸዉ አይነት ተኸልቆ ለማያዉቀዉ ወደፊትም ለማይኸለቀዉ እናትም የሱ አምሳያ ለማትወልደዉ ለአሚነት ልጅ አንዱ አምሳያዉ ለታጣዉ ዉዱ ነብይ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) 1500 ዐ.ሂ ዊላዳ በሰላም አደረስ።
❤12🥰4👍3
ሙሐመድ የሚል ስም እስካለበት ድረስ…ይኼም ሆነ ያኛው ዓለም ሊጨልም ቀርቶ አፍታ ሊደበዝዝ የተገባ አይደለም። ረሱለሏህ የማይከስም የማይደበዝዝ፣የማይጠፋም የሆነ ምሉዕ ብርኃንን አልብሰውታልና!
መልካም የመውሊድ ውሎ!✌️
✍️ @zahid Iqbal
መልካም የመውሊድ ውሎ!✌️
✍️ @zahid Iqbal
❤12👍3