በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ በመኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ በመኝታ ላይ የነበረ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ
ዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:45 ሰዓት ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ እየተገነባ ያለ ህንፃ ከስሩ ባለ መኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ በቤት ዉስጥ ተኝተዉ የነበሩ በጾታ ወንድ የሆኑ የ50 ዓመት ዕድሜ የተገመቱ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።
በስፍራዉ ፈጥነዉ የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ ሶስት ሰዎችን ከአደጋዉ መታደግ ችለዋል።
በአዲስ አበባ የግንባታ ስራ ላይ በተለይም በግለሰቦች የሚገነቡ ግንባታዎች የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ ባለመስራታቸዉ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ አደጋዎች እያጋጠሙ ይገኛል።
የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጉዳዩ የሚመለከታቸዊ አካላት ግንባታዎቹ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ተጠብቀዉ ስለመሰራታቸዉ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎችን መዉሰድና የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16😭12❤1🔥1👏1
ቀደም ባሉት ወራት በዋጋ ሽቅብ ይጎን የነበረው የሪል ስቴት ገበያ የዋጋ ቅናሽ እየታየበት ነው - ዋጋውን ጣሪያ የሰቀሉ ጭራሽኑ ጠያቂ አጥተዋል ።
ግዙፉ የሪል ስቴት ዘርፍ ዘገር ነቅናቂ ሆኖ የቀረበው ኦቪድ - በታሪክ ተመዝግቧል ...... ብራቮ ዮናስ ታደሰ !
በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት የካሬ ሜትር ዋጋ ወቅታዊ ነፀብራቅ ምን መልክ ይዟል ተብሎ ቢታይ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባስጠናው ጥናት የአንድ ካሬ ሜትር የሪል ስቴት መገንቢያ ዋጋ ከ 30,000 ብር እስከ 40,000 ብር - አለፍ ብሎም እስከ 50,000 ብር ነው ።
ነገር ግን ይህንን ዋጋ ብዙዎቹ የሪልስቴት አልሚዎች በፍፁም አይቀበሉትም ። ይልቁኑ እንደየ ሪልስቴት ግንባታው ደረጃ የሚለያይ ቢሆንም በአልሚዎች ጥናት የሪል ስቴት የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከ 63,000 ብር እስከ 70,000 ብር ይደርሳል።
የሪል ስቴት መገንቢያ ቦታ በሁለት መንገድ ይገኛል ። አንድም ከአስተዳደሩ ሁለትም ከግለሰቦች በግዥ ። ከግለሰቦች በግዥ የሚገኘው ውድ እንደመሆኑ በግንባታው ላይ የመሬት ዋጋ ፣ የሠራተኛ እና የመሳሰሉ ወጪዎች ሲጨመሩበት ዋጋውን ማናሩ አይቀርም ።
ኦቪድ ግሩፕ ገበያውን ከመቀላቀሉ በፊት አብዛኛዎቹ አልሚዎች ለገበያ ያቀረቡትን ሪል ስቴት በካሬ ከ 80,000 ብር እስከ 120,000 ብር ይጠሩ ነበር - በውጭ ምንዛሪ ደግሞ በካሬ ሜትር ከ 3,000 እስከ 4,000 ዶላር ድረስ ይጠራሉ - ከዚህም በላይ ዋጋ የሚጠራላቸው ቅንጡ ሪልስቴቶች እዚህም እዚያም እንዳሉ አሉ!
በአሁኑ ገበያ ግን በካሬ ሜትር 70,000 ብር እና ዙሪያውን ፣ በውጭ ምንዛሪም 2,000 እና ዙሪያውን እየተጠራ ይገኛል ። ከዚህ ባለፈም ከ10 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ማማለያ እየተሰጠ ነው ።
በዚህ መሀል ማን ሰንጥቆ መጣ !? ለሦስት አስርት ከግንባታ ተገልሎ የቆየው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በለውጡ ዳግም አንሰራራ - ረሻድ ከማል የሚባል ዶዘር መጣለት - ፌቤኮ ተገማች ባልሆነ መንገድ በዋና ዋና ግንባር ቦታዎች ሁነኛ ህንፃዎችን ገንብቶ ባልተጠበቀ ዋጋ ቤቶችን ገንብቶ ለገበያ ሲያቀርብ - ገበያው ከኢኮኖሚ ማንሰራሪያ ባሻገር ለብዙሃኑ ሃብት ሆነ ...
ግን ግን የግልና መንግስት አጋርነት ( PPP ) ከመንግስት በ 70/30 ቀመር መሬት የወሰዱ ሪል ስቴት አልሚዎች በስንት ብር ቢሸጡት ያዋጣቸው ይሆን !?
በ70 ሽህ ? መንግስት ከተገነባው ሪል ስቴት ድርሻውን ሲወስድ አልሚዎቹ የመገንቢያ ዋጋውን እንዴት አብቃቅተው አትራፊ ይሆኑ ይሆን - ልናይ ኋላ!
በልዩ ሁኔታ የሚታይ ቢሆንም የፐርፐዝ ብላክ ዋጋ ሳያስደምም የሚቀር አይደለም - የፐርፐዝ ብላክ ነገር እስካሁን መጨረሻው ባይለይም አምስት ቢሊየን ብር ቦታ ገዝቶ ፤ በ 60 ቢሊዮን ብር 113 ወለል ህንፃ ከነ አጀቡ ገንብቶ - ከአክሲዮን ድርሻ ጋር ፣ መቶ ካሬ ሜትር ቤት በ 1.5 ሚሊዮን ብር ፤ ቆየት ብሎም በ3.5 ሚሊዮን ብር ሂሳብ ( በካሬ ሜትር 15,000 ብር እና 35,000 ብር መሆኑ ነው ) መዋዋሉ ከትርፋማነት ቀመር ውጭ ነው ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ዘርፍ ለመኖሪያ ፈላጊው ጥሩ አማራጭ ገበያ እንዲሆን ካስፈለገ የመሬት አቅርቦት ፣ የፋይናንስ አማራጭ ፣ የሸማች መብት ጥበቃ ወሳኝነት አላቸው - በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቢሊየነሮች የገቡበት ዘርፍ መሆኑ ልብ ይሏል - የዚያኑ ያህልም የተካኑ ባለካልኩሌተሮችም ዘርፉን ተቀላቅለዋልና መፍዘዝ ጥሩ አይደለም !
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍41❤7🤔3
#ተዓምረ_Dog 🐕🚀🐕🚀🐕🚀🐕
😵 በሁለት ቀናት ውስጥ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ተቀላቅሏል::
🙀 Varified ነው
😳 #Tap ማድረግና #Task የለውም (ጊዜ አይወስድም)
😻 ስትጀምሩ ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበት ዓመት አስልቶ #Coin ይሰጣችኋል
🙀 "Who are you dawg?" የሚል ጽሁፍ ከመጣላችሁ አካውንታችሁ @Username የለውም ማለቱ ነው - አስገቡበት::
🙀 ብዙ ተከታይ ያላችሁ የራሳችሁን link በማጋራት ራሳችሁንም ሌሎችንም ጥቅሙ::
😻 ያልጀመራችሁ - ጊዜ አትውሰዱ:: በአቃራጭ የመጣ የማይደገም እድል ነው::
👇👇👇
https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=cfb5cSz1TdO8TWlQQe0jTw
😵 በሁለት ቀናት ውስጥ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ተቀላቅሏል::
🙀 Varified ነው
😳 #Tap ማድረግና #Task የለውም (ጊዜ አይወስድም)
😻 ስትጀምሩ ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበት ዓመት አስልቶ #Coin ይሰጣችኋል
🙀 "Who are you dawg?" የሚል ጽሁፍ ከመጣላችሁ አካውንታችሁ @Username የለውም ማለቱ ነው - አስገቡበት::
🙀 ብዙ ተከታይ ያላችሁ የራሳችሁን link በማጋራት ራሳችሁንም ሌሎችንም ጥቅሙ::
😻 ያልጀመራችሁ - ጊዜ አትውሰዱ:: በአቃራጭ የመጣ የማይደገም እድል ነው::
👇👇👇
https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=cfb5cSz1TdO8TWlQQe0jTw
👍11🤔2🙏1
Structural behavior of cantilever beams A famous photograph by Benjamin Baker, in which through a living model the cantilever structural principle on which the solution to the Firth Bridge over the Forth was based.
To illustrate the structural theory of a cantilever beam (Gerber), a human demonstration was carried out. The loads were represented by the person sitting in the middle of the span of the suspended span. The arms of the persons seated on both sides represented the traction at the joints; the wooden bars, the compression at the lower elements, and the bricks, the anchor points located at the pylons. The chairs represent the granite piles. Imagine the chairs 500 m apart and the men's heads as high as St. Paul's cross (London church, 104 m) their arms are represented by steel beams and the canes by 3.5 m diameter tubes at the base you get a good notion of the structure.
Heinrich Gerber applied in 1866 a theory that consisted in subdividing the continuous beam through ball-and-socket joints "which define a point of zero bending moment". This type of beam with intermediate joints is what is now known as a Gerber beam. The position where these hinges are located allows for influencing the behavior of the beam; therefore, it is not only used directly in some structures but in some projects, a real beam can be idealized by assimilating it to a Gerber beam, whose isostatic allows a simple approximate calculation.
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
To illustrate the structural theory of a cantilever beam (Gerber), a human demonstration was carried out. The loads were represented by the person sitting in the middle of the span of the suspended span. The arms of the persons seated on both sides represented the traction at the joints; the wooden bars, the compression at the lower elements, and the bricks, the anchor points located at the pylons. The chairs represent the granite piles. Imagine the chairs 500 m apart and the men's heads as high as St. Paul's cross (London church, 104 m) their arms are represented by steel beams and the canes by 3.5 m diameter tubes at the base you get a good notion of the structure.
Heinrich Gerber applied in 1866 a theory that consisted in subdividing the continuous beam through ball-and-socket joints "which define a point of zero bending moment". This type of beam with intermediate joints is what is now known as a Gerber beam. The position where these hinges are located allows for influencing the behavior of the beam; therefore, it is not only used directly in some structures but in some projects, a real beam can be idealized by assimilating it to a Gerber beam, whose isostatic allows a simple approximate calculation.
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍18👏3❤2
The load pathway for a concrete structure involves the transfer of loads from the point of application to the ground. Here are the typical five steps in this pathway:
1. Load Application:
- Loads such as gravity loads (dead and live loads), environmental loads (wind, earthquake), and other imposed loads are applied to the structure.
2. Load Distribution:
- These loads are distributed across the surface or point of application (e.g., floors, roofs) and transferred to structural elements like beams and slabs.
3. Load Transfer to Vertical Elements:
- The distributed loads are transferred from beams and slabs to vertical structural elements such as columns and walls.
4. Load Transfer to Foundation:
- The vertical elements, in turn, transfer the loads to the foundation of the structure. This can include footings, pile foundations, or mat foundations.
5. Load Transfer to the Ground:
- Finally, the foundation transfers the loads to the ground, where they are dispersed into the soil, ensuring the stability of the entire structure.
⚡️Each of these steps is crucial for maintaining the structural integrity and ensuring that the loads are safely transferred to the ground without causing failure or excessive deformation in any part of the structure.
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍25❤10
"ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ።
አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው።
የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው። እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል።
ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው
የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:-
፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ...
፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል....
በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ....
፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።
፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል።
፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።
ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ
የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል።
ለምሳሌ :-
፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣ የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ካደረገ።
፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ
፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ
፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ
፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ
ሐ) መውጫ በምሳሌ
ነገር ግን ከአምስቱ አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ።
ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል...
ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው።
በ ደሳለኝ ከበደ
(አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍47❤3🙏1
የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል።
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭36👍16❤1
#Ethio construction team በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለመላው ወገን መፅናናትን ይመኛል!!
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
😭37👍7❤1
👉 increases the strength of concrete and the durability of the building.
👉 reduces the permeability of concrete due to water evaporation.
👉 completes the cohesion and reaction of cement that continues for a period after pouring.
⚡️Watering the concrete with water after pouring is very important. It must be done for a period of at least one week, twice a day, to reach 70% of its resistance in a week.
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍36
💫The reasons for honeycomb in concrete:
1. Inappropriate workability of concrete.
2. Use of stiff concrete mix or the concrete is already set before placing.
3. Improper vibration of concrete in formwork.
4. Over reinforcement.
5. Use of larger size aggregates in excessive amounts.
6. Formwork is not rigid and watertight.
7. Concrete is poured from more than allowable height.
8. Congestion of steel is preventing the concrete to flow over all corners.
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍40❤8
የግንባታ ላይ አረንጓዴ ስፍራ ህግ
በ100 ሜትር ካሬ ይዞታ ላይ 2 በ2 ሜትር ስፋት ያለው ከግንባታ ነጻ መሬት እንዲኖር የሚደነግገው ህግ ጽሁፍ ተያይዟል።
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍16❤4
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት አንዱና ዋነኛው ትኩረት ማድረግ የሚገባው በሰው ልጆች ደህንነት ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግንባታዎች በሚገነቡበት በዋናነት ለሰውልጆች አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች የስራ ላይ ደህንነት ሥጋት የሌለባቸው እንዲሁም ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ለአካባቢ የተመቹ እና ደህንነታቸው የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮንስትራክሽን ስራ እንዲኖር ቁጥጥር በማድረግ ሂደት ትኩረት እንደሚሰጥ ቢነገርም ደህንነት በቁጥጥር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሁሉም የግንባታው ዘርፍ አካላት በየራሳቸው ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ነጥብ ነው፡፡
👷♀የግንባታ ሂደት ውስጥ የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ በግንባታ ስራው ላይ የሚሰማሩት የመስክ ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ እንዲሰሩ የሚያስፈልጋቸውን የግል የአደጋ መከላከያዎችን በማቅረብ ሰራተኞቹም የስራ ላይ ትጥቃቸውን በመጠቀም በስራ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ በህንጻ ግንባታ ሆነ በሌሎች ግንባታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡
የህንጻ ግንባታዎች ላይ በተለይም የግንባታ ስራ የእቃ መስቀያ፣ መወጣጫዎች እንዲሁም ወደ መንገድ እና ወደ አጎራባች ህንጻዎች፤ መኖሪያዎች፣መተላለፊያዎች የሚወርዱ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የግንባታ ግብዓቶች በሰው እና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ሆኖም በእነዚህ አደጋዎች የሚፈጥሩትን ኪሳራ የግንባታ ጊዜ ማስታወቂያዎች መከላከያዎች በማድረግ እንዲቀነሱ ማድረግ ይቻላል፡፡
🚧በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሙያተኞች ወደስራ ቦታቸው ሲገቡ አስፈላጊውን የደህንነት መጠበቂያ ባለማድረጋቸው የሚደርሱ የአካል እና የመንፈስ ስብራቶች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የራስ (የአናት) መከላከያ ቆብ፣ ጓንት፣ አስፈላጊ የደህንነት ጫማዎች፣ የመለያ አልባሳት ወ.ዘ.ተ ለደህንነት ዓላማ የተዘጋጁ ቁሶች እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለደህንነት በመስጠት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀላል የሚቀረፉ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች በብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
ግንባታ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ ኪሳራዎች ደግሞ በግለሰብ በማህበረሰብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ታሳቢ ቢያደርገውና ቅድሚያ ለደህንነት በማለት የመጀመሪያውን እርምጃ ለደህንነት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
(ኢኮባ)
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍25❤2
⚡️በኮንስትራክሽንፈ ኢንዱስትሪ የማጭበርበር አመለካከትና ተግባር የሚስተዋልበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩ
⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ
⚡️የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ
⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮች መካከል ተወዳዳሪነት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑ
⚡️ለኮንስትክሽን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሠንሠለት ያልተዘረጋ መሆኑ
🌟ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስፋፋትና መጠናከር የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥር የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት ሥርዓት የተጠናከረ ያለመሆን
🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ ያለመፈጠሩ
🌟የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት የተጠናከረ ያለመሆን
🌟ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥራዎች ጋር ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ
🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ወይም ፓኬጅ አዘጋጅቶ በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር
🌟ለባለሞያዎችና ስራተቋራጮች የሚደረግ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እጅግ አናሳ መሆን
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍34❤3
ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የላብና ደም አሻራ ያረፈበት የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የአይን ብሌኑም ጭምር ነው።
ተማሪው ፣ ሰራተኛው ፣ ወጣቱ ፣ አዛውንቱ ለዚህ ግድብ ካለው ላይ ፤ ከሚበለው ቀንሶ ሰጥቶ ያሰራው ለትውልድ የሚያወርሰው ሀብቱና ቅርሱ ነው።
ይህ ግድብ ሀገር ውስጥ በየጊዜው በሚፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ሀዘን፣ መከፋት፣ መበደል ሲመጣ እንኳን ሁሉም የውስጡን በውስጡ ይዞ " ሀገሬ ትቅደም " ብሎ ተጠናቆ በአይኑ ለማየት ሲል ብዙ ዋጋ የከፈለለት ነው።
በፖለቲካ አቋም፣ በሃሳብ፣ በአመለካከት እየተለያየ እንኳ የሀገሩን ጥቅምና ግንድቡን የሚነካበት ነገር ሲመጣ ሁሉን ጥሎ ሽንጡን ገትሮ የተራከረለት ፣ እስከመጨረሻው ድረስም ዋጋ የሚከፍልለት ነው።
ይህ ግድብ ገና ከመሰረቱ እንዳይገነባ ፤ ድጋፍም እንዳይመጣ ሲሯሯጡ የነበሩ ብዙ ናቸው።
እንዳይሳካ ያልፈነቀሉት ድንጋይ ፤ ያልሄዱበት ቦታ የለም። ግን አልሆነም ፤ ወደፊትም አይሆንም።
ዛሬም እነዚህ አካላት ለኢትዮጵያ እንደማይተኙ ግን ግልጽ ነው።
ኢትዮጵያ " የሰው ድርሻ አንድም አልነካም፤ የራሴን ግን እጠቀማለሁ " ማለቷ የሚያንጨረጭራቸው ሀገራት በግንባታው ወቅት ዛቻ ሲያዘንቡ ፣ እንዲቆም ለማስፈራራት ሲሞክሩ ፣ በአንድም በሌላ በዓለም አቀፍ መድረክ በውስጥ እና በይፋ ጫና ለማድረግ ሲሰሩ እንደከረሙ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ብዙ ብዙ ቢሞክሩም መክነው ቀርተዋል። አሁንም ግን ጩኸታቸው እንደቀጠለ ነው።
ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረትም እንደዛው እንደቀጠለ ነው።
አንዴ " የመሬት መንቀጥቀጥ ቢመጣ አይፈርሳል " ፤ አንዴ " ጥራቱ አስተማማኝ አይደለም ይደረመሳል " ፤ አልሆን ሲላቸው " በአየር እንመታዋለን ፣በቦንብ እናጋየዋለን " በማለት ብዙ ሲያወሩ ከርመዋል።
ከወሬ የዘለል ግን ምንም ማድረግ አይችሉም።
እዛው ያሉበት ሆነው የፈለጉትን ማሰብ ይችላሉ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እያለ ግን ማድረግ መንካት ግን ፈጽሞ አይቻልም።
#Ethiopia
#GERD
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍37
የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት።
ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው።
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍22❤1
