⚡️ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።
እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።
ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።
ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።
ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡
(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

❤27👍5😭3
ProcurementGuidanceidentificationandtreatmentofAbnormallyLowBidsandProposals.pdf
2.3 MB
አንድ ለጨረታ የገባ ዋጋ የተሰበረ ነው (abnormally/unusually low) የሚባለው መቼ ነው? የተሰበረ ዋጋ ሲያጋጥም ምን እናደርጋለን?
በአዲሱ የፌደራል የግዥ አፈፃፀም መመሪያ አፈፃፀም መመሪያ 1073/2017 አንቀፅ 123 መሠረት:
ለዕቃ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከገበያ ዋጋ አንጻር ከ30% (ሰላሳ በመቶ) ያነሰ ሲሆን ፤ ለምክር እና ከምክር ውጭ የሆነ የአገልግሎት ግዥ በተጫራቹ የቀረበው ዋጋ ከገበያ ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እና፤ (እዚህ ላይ በእንግሊዘኛ በተቀመጠው "also more than twenty percent (20%) lower than other bid prices." የሚል አካቷል)
🏗 ለግንባታ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከምህንድስና ግምት ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡
ይህ በሚያጋጥምበት ጊዜ ምን አይነት የማጣራት እና ግምገማ ሂደቶችን ማለፍ እንዳለበት የመመሪያው አንቀፅ 123 ዝርዝር ሃሳቦችን አካቷል።
ይህን ሂደት በተመለከተ በዓለም ባንክ የተዘጋጀው "Guide to the identification and treatment of Abnormally Low Bids and Proposals" የሚለው መመሪያ ጠቃሚ ማብራሪያ ይሰጣል።
https://www.tg-me.com/ethioengineers1

❤44👍15🙏4🔥1😍1