Telegram Web Link
⚡️ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።

እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።

ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።

ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።

ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡

(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
27👍5😭3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ቪዲዮ ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት

ጥቅል የኤሌክትሪክ ነው ብለው የሸጡላቸውን ተመልከቱ።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
🤔2013🙏5👍4😍3
ProcurementGuidanceidentificationandtreatmentofAbnormallyLowBidsandProposals.pdf
2.3 MB
አንድ ለጨረታ የገባ ዋጋ የተሰበረ ነው (abnormally/unusually low) የሚባለው መቼ ነው? የተሰበረ ዋጋ ሲያጋጥም ምን እናደርጋለን?

በአዲሱ የፌደራል የግዥ አፈፃፀም መመሪያ አፈፃፀም መመሪያ 1073/2017 አንቀፅ 123 መሠረት:

ለዕቃ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ  ከገበያ ዋጋ አንጻር ከ30% (ሰላሳ በመቶ) ያነሰ ሲሆን ፤ ለምክር እና ከምክር ውጭ የሆነ የአገልግሎት ግዥ በተጫራቹ የቀረበው ዋጋ ከገበያ ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እና፤ (እዚህ ላይ በእንግሊዘኛ በተቀመጠው "also more than twenty percent (20%) lower than other bid prices." የሚል አካቷል)

🏗 ለግንባታ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከምህንድስና ግምት ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡

ይህ በሚያጋጥምበት ጊዜ ምን አይነት የማጣራት እና ግምገማ ሂደቶችን ማለፍ እንዳለበት የመመሪያው አንቀፅ 123 ዝርዝር ሃሳቦችን  አካቷል።

ይህን ሂደት በተመለከተ በዓለም ባንክ የተዘጋጀው "Guide to the identification and treatment of Abnormally Low Bids and Proposals" የሚለው መመሪያ ጠቃሚ ማብራሪያ ይሰጣል።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
44👍15🙏4🔥1😍1
2
#AddisAbaba

👆ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) በተመለከተ የተሻሻለ ውሳኔ ተላልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) እና ተያያዥ የግንባታ ፈቃድ መመሪያዎችን አስመልክቶ የተሻሻለ ያለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ህንፃዎች ከይዞታ ወሰን የሚኖራቸው ርቀት (Set Back Regulation) በተመለከተ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወቃል።

በመመሪያው ላይ ግልፅ ያልሆኑና በአሰራር ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ ካቢኔው ሰኔ 10/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሶስተኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመወያየት ማሻሻያ ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር።

የተሻሻለው ውሳኔ ማስተለፍ ያስፈለገው የሴትባክ ህግ አፈፃፀም ሂደት ላይ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ ከግንባታ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከአልሚዎችና ፕላን ፈፃሚ ተቋማት በኩል በተደጋጋሚ የሚቀርቡ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያስችል ዘንድ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመመሪያው ላይ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ለከተማዋ ፕላን እና ልማት ቢሮ የተጻፈው ደብዳቤ " የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት በ1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ እንዲያፀድቅ የቀረበውን ራሱን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ጥናት ካቢኔው ተወያይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንድታደርጉ" ሲል ይገልጻል።

በእዚህም መሰረት ከ 28/12/17 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ የከተማዋ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ፣ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዲሁም  ለሁሉም የክፍለ ከተማ የፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የካቢኔውን ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ መመሪያ አውርዷል።

የተሻሻለው ውሳኔ መሰረት ግንባታዎች ከዋና መንገድ፣ ከንኡስ ዋና መንገድ ፣ከሰብሳቢ መንገድ እንዲሁም ከውስጥ ለውስጥ መንገድ ሊኖራቸው ስለሚገባ የወሰን ጠርዝ ርቀት ከተያያዘው ዶክመንት ይመልከቱ።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
19😍1
⚡️እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር ፣ የደስታና የስኬት ዘመን ያድርግልን

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
10
👉የግንባታ ኢንደስትሪው ሀብቶች

💫1.የገንዘብ ሀብት /Financial Resource or fund/:-

የግንባታ ሥራው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጠይቀው የገንዘብ ወጪ ነው፡፡ ይህም ከተቀማጭ በቀጥታ፣  በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ከብድር፣ወይም ከስጦታ ወይም ከሌላ ህጋዊ ከሆነ የገንዘብ ምንጭ የሚገኝ ሊሆን የሚችል ሲሆን የግንባታ ፕሮጀክት ለማከናወን ከሚያስፈልጉ ሀብቶች አንዱ መሰረታዊውና ዋነኛው ነው፡፡

💫2. የሰው ሃይል ሀብት /Human Resource/Labour or Workmanship/:-

እነዚህም ከዘርፉ ቀጥተኛ የሰለጠኑ ባለሞያዎች/Proffesionals/ ፣ በፕሮጀክት አመራር ውስጥ አጋዥ ወይም ደጋፊ የሥራ ዘርፍ ባለሞያዎችንና እስከታችኛው እርከን የሚወርዱ የሥራው ቀጥታ ተሳታፊ የሆኑ በከፊል የሰለጠኑና/Semi skilled/ ስልጠና የሌላቸው የጉልበት ሰራተኞችን/Unskilled/ ሁሉ ያጠቃለለ ነው፡፡የሰው ሃይል ሀብት ለግንባታ ሥራ ከሚመደበው የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት ከ5-7% የሚሆነውን የሚቋደስ ነው፡፡

💫3. የመረጃ ሀብት /Information Resource/:-

ይህ ዓይነቱ ሀብት ከፕሮጀክት ጥናት ጀምሮ በዲዛይን ሥራ ብሎም ወደግንባታ ሥራ ለመግባትና፣ በፕሮጀክት ሥራ ክንውን ወቅት በሚደረጉ ጉዞዎች ሁሉ አስፈላጊና ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ደህንነት መረጋገጥ የሚጠቅሙ፣ የግንባታ ሥራን  አዋጭና በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚረዱ መረጃዎች ናቸው፡፡
መረጃዎች ሳይሰበሰቡ የሚደረግ የዲዛይንና የግንባታ ሥራ ሁሉ አጠራጣሪ ወይም አስጊነቱ የማይካድ ነው፡፡

💫4. አካላዊ /ግዘፍ ሀብቶች/Physical Resources/:-

አካላዊ ወይም ግዘፍ ሀብቶች የሚባሉት የግንባታ ግብዓት ዕቃዎችና የግንባታ ሥራ ማሽነሪዎች /Materials and Machinaries/ ናቸው፡፡ እነዚህ ሀብቶች ከፍተኛ ግዢ የሚካሄድባቸውና፣ የአንድ ፕሮጀክት አብዛኛውን የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት የሚቋደሱ ወይም የሚይዙት ናቸው፡፡ለምሳሌ የግንባታ ግብዓቶችን ብቻ አንኳን ብንመለከት ከ50-65% የሚሆነውን የግንባታ ሥራ በጀት የሚይዙ ናቸው፡፡

💫5. የአገልግሎትና አስተዳደራዊ አቅርቦቶች ሀብቶች /Survices and Management/:-

የመሬት አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የስልክ መገናኛ አገልግሎት አቅርቦቶችና የመሳሰሉትን የሚያካትት ሆኖ የግል ወይም የመንግስት አገልግሎት አቅራቢ ተቋማትን አስተዳደራዊ ፈቃድ የሚጠይቁና የሚቀርቡ፤ የግንባታ ሥራዎች ጥራት፣ ቅልጥፍናና የተሻለ አዋጭነት ባለው መልኩ እንዲከናወንና እንዲጠናቀቅ የሚረዱ ሀብቶች ናቸ
ው፡፡

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
14👍1👏1🙏1
እስከዳረ የቱረክ ብሎኬት ማምረቻ
ባለ 15 | ባለ 10 | ባለ 20_


📍ጥራታቸውን የጠበቁ
📍በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመረቱ
📍በተመጣጣኝ ዋጋ
📍ትንሹ ማዘዝ የሚቻለው ብዛት 600

📞 ለመረጃ እና ለማዘዝ: 0970096060
Tel
egram: @Eskedarcon


Website:www.eskedarconstruction.com
Location: https://maps.app.goo.gl/Yde11MBHoUTh3do78?g_st=it
5
👉የክፍያ መዘግየት መላ

💫በኮንስትራክሽን ግንባታ ወቅት የኮንትራክተሮች ራስ ምታት ከሚሆኑ ጉዳዮች ዋነኛው የግንባታ ክፍያ መዘግየት እና በተቀመጠው ውል መሠረት ተገቢ ክፍያዎች አለመፈጸም በቀዳሚነት የሚቀመጥ ነው፡፡

📌አስገንቢው ድርጅት ወይም ግለሰብ የሚፈልግበትን ክፍያ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ አለመክፈሉን ተከትሎ ግንባታዎች እንዲጓተቱ፣ ሠራተኞች ደመወዛቸውን በወቅቱ እንዳያገኙ ከማድረጉም በላይ፣ የባንክ ዕዳ በወቅቱ እንዳይወራረድ በማድረግ የሚያስከትለው ችግር እና ኪሣራ በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡

ይህን ውጣ ውረድ ለመቅረፍ ብቸኛው አማራጭ በህግ አግባብ፣ በውሉ መሠረት እንዲተዳደር እና እንዲፈጸም ማድረግ ሲሆን፣ ኮንትራክተሮች ወይም ክፍያ ጠያቂዎች ሊከተሏቸው የሚገባቸው አሠራሮች Infracon Media በዚህ መልኩ አጠናቅሮታል፡፡

በውሉ መሠረት መብት እና ግዴታን ጠንቅቆ ማወቅ


▶️በዚህ ሁኔታ ውስጥ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ክፍያን በፍጥነት ለመቀበል የሚያስችሉ፣ ከተዛማጅ ዕዳ የሚከላከሉ እና ክፍያዎች በዘገዩ ቁጥር በከፋዩ ላይ ሊጣሉ የሚችሉ የወለድ ክፍያ ህጎችን ጠንቅቆ ማወቅ እና በውሉ ላይ ማስፈር ይገባል፡፡

ቋሚ የሆኑ የክፍያ ጊዜያዎችን የተመለከተ ስምምነት መፈጸም


▶️በተቻለ መጠን የክፍያ ጊዜን በተመለከተ ዝርዝር ጊዜን መመደብ እና በወረቀት ላይ ማስፈር ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ማድረግ የገንዘብ ፍሰትን ለማወቅ፣ ደንበኛው የክፍያ ጊዜውን እንዲያስታውስ እና እንዲከፍል ለማድረግ፣ ይህ ባልተፈጸመ ጊዜ ስምምነቱን በመጥቀስ እንዲከፍል ለመጠየቅ ይረዳል፡፡

ስምምነቱን ከህግ ባለሙያ ጋር መፈጸም


▶️ቀዳሚው በስምምነቱ መሠረት የራስህን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ክፍያ በውሉ መሠረት ካልተፈጸመ ውሉን ባስፈጸመው የህግ ባለሙያ (ጠበቃ) አማካኝነት የውሉን መረጃ በማያያዝ ክፍያው እንዲፈጸም ለመጠየቅ አለማመንታት እና በድፍረት ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

ሰነዶችን በተደራጀ መንገድ መያዝ እና ማስቀመጥ


▶️ደረሰኞችን እና ተዛማጅ መረጃዎችን በአግባቡ መያዝ እና መሰነድ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እንዲያመራ የሚያደርግ አለመግባባት ሲፈጠር፣ በቀላሉ ፋይል ለመክፈት፣ አሰሪው ወደ ኃላ ዞር ብሎ እንዲያስብ እና ወደ ስምምነት እንዲመለስ የሚያደርግ ዕድልን ይፈጥራል፡፡

ክስ ለመመስረት አለማመንታት


▶️መደበኛ ክፍያዎች በአግባቡ ተፈፃሚ የማይሆኑ ሲሆን እና ይህንኑ ተከትሎ ተናግረው፣ ነዝንዘው እና አስጠይቀው ምላሽ ሲያጡ እና ክፍያውን ሊፈፀም ሳይችል ሲቀር ምንም ሳያመነቱ ክስ ይመስርቱ፡፡ አንዳንዶቹ ካላቸው ዝና እና ስም አንፃር ብከሰስ ምን እባላለሁ? የሚል ፍራቻ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በህግ ፊት ሁሉም እኩል መብት ስላለው የእርስዎ አስተያየት፣ የተዋዋሉት ውል ላይ ብቻ ማተኮር ይገባዋል፡፡ ከዚህ በመነሳት በህግ አግባብ ፍርድ ቤት ቀርበው መብትዋን በማስከበር እና ክፍያውን ከመቀበል ባለፈ ለሌሎች ክብር ብለው የራስዎን መብት ማጣት አይገባዎትም፡፡ 

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍87😭1
2025/10/20 03:15:06
Back to Top
HTML Embed Code: