የዱባዮ ቡርጂ አል አረብ ጂሜይራህ፣ በአለማችን ውስጥ ከሚገኙ ቅንጡ ሆቴሎች መካከል አንዱ ነው።

ይህ ሆቴል ከአለማችን ሠማይ ጠቀስ ሆቴሎችም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይሁን እንጂ፣ ከዚህ ረጅም ሕንፃ ውስጥ 39 ከመቶ የሚሆነው የሕንፃው አናት ክፍል ጥቅም አልባ (non occupied) ሲሆን፣ ሕንፃውን ለመገንባት 7.6 ቢሊየን ዳላር ወጪ ተደርጓል።

ቡርጂ አል አረብ፣ ያረፈው በሰው ሰራሽ ደሴት ላይ ከመሆኑም በላይ፣ ሕንፃው ከመሬት ጋር የሚገናኘው በድልድይ ነው።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥያቄ

🏗ወስን ተጠግቶ ለሚገነባ ግንባታ አዋሳኙ ባለመብት በአዋሰኝ በኩል ያለዉን የህንፃ ገፅ ለመስራት የመከልከል መብት አለው ወይስ የለዉም ?

#መልሱን_ቀጠይ_እመለስበታለሁ ❗️

🏗 ሳይት ላይ ያጋጠማችሁን ማገራት ለምትፈልጉ @Ethiocon143bot


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ethio Construction
💥ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/ 1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate) • ከ 20% እስከ 30%  ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ • ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡ • አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤…
Advance payment ለምን ይከፈላል?

በውል ላይ ካልተቀመጠ advance መከፈል ግዴታ አይደለም
ነገር ግን FIDIC አንቀጽ 14.2 ላይ Advance ለስራ ተቋራጭ የሚከፈል ከወለድ ነፃ የሆነ ብድር መሆኑን ይገልፃል::
ይህም ማለት  ተቋራጭ advance ካልተከፈለው በራሱ ገንዘብ ስርቶ payment ሲጠይቅ ግን ወለዱን የመጠየቅ መብት ይኖረዋል::


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
L- connection of tie beam

1- Rebars must cross like the fingers of a hand.

2- Put an additional rebar around the outer corner.

3- Extend hooked bars from the inside to the outside.


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ማሽን ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ባለሀብት ይጥፋ?

በዚህ ዘመን ኮንስትራክሽን ማለት ይበልጡኑ ቴክኖሎጂ እና ማሽነሪ ነው። ከዚያም አመራርም አለ። በመሆኑም፣ ጥራት ያለው ግንባታን በተያዘለት ጊዜና በጀት ጨርሶ ለማስረከብ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ወሳኝ ናቸው።

ከታች በፎቶ የተቀመጠው የእግረኛ መንገዶችና የሕዝብ መሰብሰቢያ ግልጽ ቦታዎች ላይ ግንባታ ለማከናወን ጠቃሚነቱ ወደር የለውም።

ይህ ማሽን ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ባለሀብት ቢጠፋ እንኳ፣ ማሽኑን መንግሥት ቢያስመጣው በተለይ ለኮሪደር ልማትና ተያያዥ  የፕሮጀክቶች ሥራዎችን በፍጥነት ለመጨረስ ተኪ የሚገኝለት አይደለም።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዳማ

በአዳማ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ የሁለት ሰራተኞች ህይወት ማለፉን የከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት አደጋው ትናንት በከተማው ደጋጋ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀጠና አራት አካባቢ የደረሰ ነው፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም ሌሎች ሁለት የጉልበት ሰራተኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ  እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ሕንፃ አሰሪዎች ለሚያሰሯቸው ሰራተኞች የስራ ደህንነት ሊጠብቁና  ዋስትና ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሳዛኝ_ዜና

ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው።

እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር።

የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል።

#FirstSafety

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጥቂት ቀናት ውስጥ በጃፓን አሮጌውን መንገድ ለመጠገን አዲስ ድልድይ ለመገንባት ተችሏል።

🏗ይህ ሊሆን የቻለው በጃፓን ውስጥ ብቻ ነው !


Via:- infera Ethiopia

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባህር ዳር

በባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ መጠናቀቁ ተሰምቷል።

ድልድዩ 380 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ የጎን ስፋቱም 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል።

5ሜትር የእግረኛ መሄጃ የተሰራለት ሲሆን በሁለቱም አቅጣጫ ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚሆን መስመርን ያካተተም ነው።

ድልድዩ 65,683 ኪሜ የሚሸፍነው፤ ከግብፅ ተነስቶ፤ በሱዳን በማቋረጥ ኬንያ እና ታንዛንያን አልፎ እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚያገናኘው የኔትዎርክ መንገድ አካልም ነው።

ቀድሞ የነበረው ድልድይ ከ60 ዓመታት በላይ ለማህረሰቡ የትራንስፖርት ማመላለሻ መንገድ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ለአዲሱ ቦታውን የሚያስረክብም ይሆናል።

ግንባታው በአንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን  ብር  የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ

የድልድዩ_ግንባታ_ስራ፡-

📌ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን  ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡
ይህ ድልድይ ኤክስትራ ዶዝድ የሚባል ስያሜ የተሰጠው ተንጠልጣይ ድልድዮች (ሰስፔንሽን) ከሚባሉት ድልድዮች የተለየና ይልቁን የመኪና ተሸካሚው ዴክ ከፊትና ከሁዋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (በገመዶች የተወጠረ) ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካይነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፡፡

ይህ አይነቱ ድልድይ የረጃጅም ኬብል ስቴይድ (በገመድ የተወጠረ) ድልድዮችና  የረጃጅም ቦክስ ገርደር አይነት ድልድዮች ውሁድ ሆኖ ስፋታቸው ከ 250 ሜትር እከ 500 ሜትር በሚደርሱ ወንዞች ላይ አመቺና ወጪ ቆጣቢ ሆነው እንዲሰሩ በመጀመሪያ በፈረንሳይ ሀገር የተፈለሰፈ በቀጣይ ግን በብዛት ጃፓን ሀገር ስራ ላይ የዋለ የድልድይ አይነት ነው፡፡

የተጠናቀቀው የድልድዩ የምህንድስና ሰነዶች እንደሚያመለክቱት የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ (piers) 7 ሜትር  ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሀና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፡፡

ለድልድይ ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ
#ዋና_ዋና_ግብዓቶች

✳️የተለያዩ የጥንካሬ ደረጃ (Grade C-30, C-40, C-50, and C-55) ያላቸው አርማታ 54,138.68 ሜ.ኩ

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የአርማታ ብረት 9,241.45 ቶን

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የማንጠልጠያ  እና መወጠሪያ 474.37 ቶን  

👍የድልድይ ግንባታ ሥራውን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ከተሠሩት
#የተለየ_የሚያደርገው

🔰የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጅ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ

🔰ድልድዩ በከተማ ውስጥ እንደመሠራቱ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የቱሪሰት መስህብ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማገናዘብ ቅንጡ ተደርጎ መሠራቱ

🔰በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራት የተገጠመ መሆኑ ይገኙበታል፡፡

❇️
#የኘሮጀክቱ_ሁለንተናዊ_ፋይዳ

በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት  በመስጠት ላይ የሚገኘውን  ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን  የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡

ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል።

ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘጋጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም  ከስጋት ነጻ  ያደርጋቸዋል፡፡

ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች  ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡

ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ  አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡

📌አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናወኑም ይረዳል ፡፡


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/05/14 10:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: