Telegram Web Link
በሰብአዊ መብቶች ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የተካሄደ ውይይት
...

ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት መሥራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትኩረታቸውን በሰብአዊ መብቶች ላይ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት የሚሠራበትን “የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ” አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ውይይት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋና መሥሪያ ቤቱ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ በሴቶች እና በሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞች እና በአረጋውያን፣ በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት፣ በመገናኛ ብዙኃን እና በሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።

መድረኩ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎን ከድርጅቶቹ ተወካዮች እና ኃላፊዎች ጋር ያስተዋወቀ ሲሆን ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ሊኖረው የሚገባውን የትብብር ሥራ በተደራጀ እና ሥርዓት ባለው መልኩ ለመምራት ባዘጋጀው የስትራቴጂክ አጋርነት መምሪያ (Strategic Partnership Guideline) መሠረት ሲሠራባቸው የቆዩ ዘርፎችን በተመለከተ ማብራሪያ ቀርቧል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31555

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👏1
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱን በተመለከተ
...

ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና ከታገዱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ ቆይቷል

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ 3 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችን በድጋሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከልን ማገዱ ይታወሳል።

ኢሰመኮ ታኅሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች በሲቪል ምኅዳሩ እና በማኅበር የመደራጀት መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል። በተጨማሪም ኢሰመኮ በድርጅቶቹ እገዳ ላይ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ያከናወነ ሲሆን የደረሰባቸውን ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት አጋርቷል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31567

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ  ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሴቶች የእኩልነት መብት
...

በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 3

አባል ሀገራት በሁሉም መስክ በተለይም በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ መስኮች የሴቶችን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥና ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ሴቶች ከወንዶች እኩል በሰብአዊ መብቶቻቸው እና መሠረታዊ ነጻነቶቻቸው መጠቀም እንዲችሉ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ አለባቸው።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 35(3)

ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው፤ በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው።

🔗 https://ehrc.org/?p=31576

#Ethiopia🇪🇹 #IWD2025 #ForAllWomenAndGirls #InternationalWomensDay #RingTheBellForGenderEquality #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1👍1👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሕፃናት በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት እና ትምህርት
...

የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 27(3)

ወላጆች እና ለሕፃኑ ኃላፊነት ያለባቸው ሌሎች አካላት የሕፃኑን ለእድገቱ ተስማሚ የሆነ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት እንዲያሟሉ ለማገዝ፣ አባል ሀገራት እንደየሀገራዊ ሁኔታቸው እና ዐቅማቸው ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ። አስፈላጊ በሆነ ጊዜም በምገባ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ ረገድ ቁሳዊ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ የድጋፍ መርኃ ግብሮችንም ያዘጋጃሉ።

የአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፣ አንቀጽ 11(3)(መ)

አባል ሀገራት የሕፃናትን የመማር መብት ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ ሁሉንም ተገቢ እርምጃዎች ይወስዳሉ። በተለይም በትምህርት ቤት ተገኝቶ ትምህርትን በቋሚነት መከታተልን ለማበረታታት እንዲሁም የተማሪዎችን ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔ ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።

🔗 https://ehrc.org/?p=31650

#Ethiopia🇪🇹 #ForEveryChild #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
2
#ትግራይ፦ ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔዎችን መውሰድ ያስፈልጋል
...

ኢሰመኮ ከመደበኛ የክትትልና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር ችግሩ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን በሚያረጋግጥ መልኩ በውይይት እንዲፈታ ጥረት ያደርጋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ እና ውጪ በሚገኙ እና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪዎች መሆናቸውን በሚገልጹ አካላት መካከል ከተከሰተው አለመግባባት ጋር ተያይዞ በክልሉ ለወራት የዘለቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣው ውጥረት በክልሉ አጠቃላይ ሰላም እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያለውን አንድምታ እየተከታተለ ይገኛል።

በተለይም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ጊዜያዊ እገዳ ማስተላለፋቸውን እንዲሁም የህወሓት ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጹት አካላት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የጊዜያዊ አስተዳደሩን የመንግሥት ተቋማት ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከክልሉ ነዋሪዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ ባሻገር በሰዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ አደጋ እና ሥጋት ፈጥረዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31769

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
ለ5ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ተሳታፊዎች የተሰጠ የማስጀመሪያ ስልጠና
...

ውድድሩ ተማሪዎች ስለ ሰብአዊ መብቶች ዕውቀትና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳ ነው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለ5ኛ ጊዜ ለሚያካሂደው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር የማስጀመሪያ ስልጠና የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በ12 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዓላማ የውድድሩን አጠቃላይ ገጽታ ማስገንዘብ እና በዚህ ዓመት ለውድድር የተመረጠውን የሰብአዊ መብቶች ርዕሰ ጉዳይ ለተወዳዳሪ ተማሪዎች እና አሰልጣኝ መምህራን ማስተዋወቅ ነው።

በዚህ ስልጠና ከአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ደሴ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ግልገል በለስ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ለኩ፣ መቐለ፣ ሜጢ፣ ሚዛን፣ ሰመራ እና ወልቂጤ ከተሞች ከ105 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወከሉ ተወዳዳሪ ተማሪዎች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ አስተባባሪዎች፣ አሰልጣኝ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና የተማሪ ወላጆች ተሳትፈዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31799

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
በኢሰመኮ የቅብብሎሽና ቅንጅት ማእቀፍ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተደረገ ውይይት
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች ተጓዳኝ ድጋፍ ለመስጠት እስካሁን እየተገበረ በሚገኘው የቅብብሎሽና ቅንጅት ማእቀፍ ላይ የተሠራውን የዳሰሳ ጥናት መነሻ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዓላማ በሥራ ላይ ያለውን የቅብብሎሽ አሠራር በተሻለ መልኩ ለማደራጀት እና ለማጠናከር በዳሰሳ ጥናቱ ግኝቶች ላይ እንዲሁም ኢሰመኮ ወደፊት ለሚተገብረው መደበኛ የቅብብሎሽ ሥርዓት ከባለድርሻ አካላት ግብአት ማሰባሰብ ነው።

በውይይቱ ለተጎጂዎች ድጋፍ የሚሰጡ ከ35 በላይ የሚሆኑ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትን ጨምሮ በሴቶች፣ በሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞች እና በሌሎች ዘርፎች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩም በዳሰሳ ጥናቱ የተለዩ ቁልፍ ግኝቶች የቀረቡ ሲሆን ኢሰመኮ ተጎጂዎችን ከሕግ፣ ከሥነ ልቦና፣ ከመጠለያ፣ ከማኅበራዊ ወዘተ. ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ማገናኘት መቻሉ፤ ተጎጂዎች በተቻለ መጠን ለዳግም ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ፤ ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ ከማድረግ አንጻር መልካም ሥራ ማከናወን መቻሉ ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተቀናጀ እና በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ኢሰመኮ ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጠናከረ መደበኛ የቅብብሎሽ ሥርዓት (Referral System) መዘርጋቱ በይበልጥ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31843

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ከአድሎአዊ የዘር ልዩነቶች የመጠበቅ መብት
...

ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 1

ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ክብርና መብቶች ይዘው ነጻ ሆነው ተፈጥረዋል።
ሁሉንም ዐይነት አድሎአዊ የዘር ልዩነቶች ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 1 (1) እና 5

“አድሎአዊ የዘር ልዩነት” ማለት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በባህላዊ ወይም በሌላ በማንኛውም ሕዝባዊ የሕይወት መስክ የሰብአዊ መብቶችን እና የመሠረታዊ ነጻነቶችን እኩል ዕውቅና፣ ተጠቃሚነት ወይም ትግበራ ዋጋ የማሳጣት ወይም የመጉዳት ዐላማ ወይም ውጤት ያለው በዘር፣ በቀለም፣ በትውልድ ወይም በብሔር ወይም በዘር ሐረግ ላይ የተመሠረተ ልዩነት ማድረግ፣ ማግለል፣ መገደብ ወይም ማበላለጥ ነው።

አባል ሀገራት ሁሉንም ዐይነት የዘር አድልዎ የመከልከል እና የማስወገድ እንዲሁም ማንኛውም ሰው በዘር፣ በቀለም፣ በብሔር ወይም በዘር ሐረግ ልዩነት ሳይደረግበት በሕግ ፊት እኩል የመሆን መብቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።

🔗 https://ehrc.org/?p=31825

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት 

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
60 Years of the International Convention on the Elimination of All Forms of Racial Discrimination (ICERD)
...

What is ICERD? What are the key features of ICERD? What is CERD/the Committee? Mechanisms used by CERD/the Committee to monitor state actions and advise. Is Ethiopia party to ICERD? How can human rights actors engage with ICERD?

The International Convention on the Elimination of All Forms of Racial Discrimination (ICERD) is one of the earliest United Nations (UN) treaties aimed at eradicating racial discrimination globally. ICERD emerged in the 1960s amid global struggles against colonialism, apartheid, and systemic racism, and was adopted on 21 December 1965 by the UN General Assembly, entering into force on 4 January 1969. As of today, 182 States are parties to the Convention, reflecting its wide acceptance as a cornerstone of international human rights law.

🔗 https://ehrc.org/?p=31884

#Ethiopia #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
የውሃ መብት
...

ውሃ ለሕይወት እና ጤና መሠረታዊ የሆነ ውስን የተፈጥሮ ሀብት ከመሆኑም በተጨማሪ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ ተጠብቆ እንዲኖር እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ መብቶቹን እንዲጠቀም ለማስቻል መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታ ሲሆን በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችም ጥበቃ የሚደረግለት መብት ነው። የውሃ ሀብት ጥበቃና ልማት ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና ተጨባጭ ተግባራትን ለማበረታታት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. ከ1993 ጀምሮ በየዓመቱ መጋቢት 13 የዓለም የውሃ ቀን ሆኖ ይከበራል። ይህም ማብራሪያ ቀኑን በማስመልከት የውሃ መብት ምንነት፣ ጥበቃ፣ ይዘት እና የመንግሥታት ግዴታዎችን አስመልክቶ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተዘጋጀ ነው።

የውሃ መብት ምንድን ነው?

የውሃ መብት ሁሉም ሰው ለግሉ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት በቂ የሆነ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተቀባይነት ያለው፣ በአካል ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ/affordable የሆነ ውሃ የማግኘት መብት ሲሆን በውስጡ ሌሎች ነጻነቶችን/freedoms እና መብቶችን/entitlments እንደሚይዝ የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ኮሚቴ የውሃ መብትን አስመልክቶ የሰጠው አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 15 ያስረዳል።

🔗 https://ehrc.org/?p=31898

#Ethiopia🇪🇹 #WorldWaterDay #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
International Day for the Right to Truth concerning Gross Human Rights Violations and for the Dignity of Victims
...

On this International Day, EHRC emphasizes the importance of victims’ right to truth

On this International Day for the Right to Truth Concerning Gross Human Rights Violations and for the Dignity of Victims (24 March), the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) reiterates the importance of victims’ right to the truth. Victims include persons who individually or collectively suffered physical or mental harm, substantial impairment of their fundamental rights, through acts or omissions that constitute gross violations of international human rights law, or serious violations of international humanitarian law.

🔗 https://ehrc.org/?p=31939

#Ethiopia🇪🇹 #StandUp4HumanRights #TruthAndDignity #JusticeForAll #RightToTheTruth #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የመደራጀት መብት
...

የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 22 (1) (2)

ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በማኅበር የመደራጀት ነጻነት አለው፡፡ ይህም ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የሠራተኛ ማኅበራትን የማቋቋም እና አባል የመሆን መብትን ይጨምራል።

በሕግ ከተደነገገው እና በዴሞክራሲያዊ ማኅብረሰብ ውስጥ ለብሔራዊ ደኅንነት፣ ለሕዝብ ሰላምና ጸጥታ ጥቅም ወይም የሕዝብን ጤናና ሥነ ምግባር ወይም የሌሎችን መብቶችና ነጻነቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ ከሆነው በቀር በዚህ መብት አጠቃቀም ላይ ምንም ዐይነት ገደብ አይደረግበትም፡፡

🔗 https://ehrc.org/?p=31952

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት 

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ጥበቃ
...

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 6 (1) እና (2) 

አባል ሀገራት አካል ጉዳተኛ ሴቶችና ሴት ልጆች ለተደራራቢ አድልዎ የተዳረጉ መሆናቸውን ዕውቅና ይሰጣሉ፤ ይህንንም ከግንዛቤ በማስገባት በሁሉም ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ሙሉ እና እኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እርምጃዎችን ይወስዳሉ።

አካል ጉዳተኛ ሴቶች በዚህ ስምምነት በተደነገጉት ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ አባል ሀገራት የሴቶችን የተሟላ ልማትና ዕድገት ዕውን ለማድረግ እና ለማብቃት የሚያስችሉ ተገቢ እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳሉ።

🔗 https://ehrc.org/?p=32014

#Ethiopia🇪🇹 #DisabilityInclusion #DisabilityRights #CommitToChange #GDS2025 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የጤና አገልግሎት ተደራሽነት
...

የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 12 (1) እና (2)(መ) 

አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ሊደረስበት የሚችለውን ከፍተኛውን የአካል እና የአእምሮ ጤና ደረጃ የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ። 

የዚህን መብት ሙሉ ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ አባል ሀገራት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በሕመም ጊዜ ሁሉንም የሕክምና አገልግሎት እና ክትትል አቅርቦት መኖሩን የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን መፍጠርን ይጨምራል። 

የኢትዮጵያ  ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 41(4) 

መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል። 

🔗 https://ehrc.org/?p=32142

#Ethiopia🇪🇹 #AccessToHealth #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
#ትግራይ፦ ወደ ቀድሞ የመኖሪያ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተከናወነ ክትትል
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ከቆዩ በኋላ በደቡባዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች ወደሚገኙ የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ከነሐሴ 19 እስከ ጷጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 11 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ክትትሉ የተደረገው ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም በክልሉ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ክትትሎችን በማከናወን በተለያዩ ጊዜያት መግለጫዎችን እና ሪፖርቶችን ይፋ ሲያደርግ እንዲሁም ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ የሚያደርገውን ክትትልና ውትወታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሲገልጽ በቆየው መሠረት ነው።

ጋዜጣዊ መግለጫ፦ https://ehrc.org/?p=32253

ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ፦ https://ehrc.org/download/?p=32255

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: በሥነ-ጥበብ ሐሳብን የመግለጽ እና የፈጠራ ነጻነት
...

የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2) እና የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 15 (1) (ሐ)

ማንኛውም ሰው በሥነ-ጥበብ መልክ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት አለው።

አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ከሥነ-ጽሑፋዊ ወይም ከሥነ-ጥበባዊ የሥራ ውጤቱ የሚመነጨውን የሞራል እና ቁሳዊ ጥቅም የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 41 (9)

መንግሥት የባህልና የታሪክ ቅርሶችን የመጠበቅ እና የመንከባከብ እንዲሁም ለሥነ-ጥበብ መስፋፋት አስተዋጽዖ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

🔗 https://ehrc.org/?p=32361

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍31
Advancing the Business and Human Rights Agenda in Ethiopia
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) in collaboration with the Ministry of Justice, the Danish Institute for Human Rights and Friedrich-Ebert-Stiftung, organized a two-day series of workshops on April 8-9, 2025, focused on the development of Ethiopia’s National Action Plan (NAP) on Business and Human Rights and its methodologies. The events brought together members of the National Action Plan Technical Committee, including representatives from government ministries, the Confederation of Ethiopian Trade Unions, the Confederation of Ethiopian Employers’ Associations and civil society organizations. International partners in attendance included the United Nations Office of the High Commissioner for Human Rights, the Danish Institute for Human Rights and Friedrich-Ebert-Stiftung.

🔗 https://ehrc.org/?p=32408

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝ ላይ በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...

የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝ ከመደበኛው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በተለየ የሕግ ማዕቀፍ ሊደገፍ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝን በተመለከተ በ2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ይፋ ባደረገው የክትትል ሪፖርት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ዙሪያ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የጤና ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማት፣ በሴቶችና እና በሕፃናት መብቶች ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ሶማሊ፣ ክልሎች እና ከሸገር ከተማ አስተዳድር የተውጣጡ አቻ ተቋማት ተሳትፈዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32439

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ አካባቢ
...

የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ስምምነት ቁጥር 155 –  የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤና ስምምነት፣ አንቀጽ 16 

አሠሪዎች በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ የሥራ ቦታዎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች እና የአሠራር ሂደቶች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ምንም የጤና ሥጋት የማያስከትሉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል።

አሠሪዎች ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ ሲወስዱ፣ በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ ኬሚካላዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ-ሕይወታዊ ንጥረ-ነገሮች እና መሣሪያዎች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለጤና አደጋ የሌላቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል።

የአደጋ ሥጋትን ወይም አሉታዊ የጤና ተጽዕኖዎችን ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሠሪዎች በቂ የደኅንነት መጠበቂያ ልብሶችንና መሣሪያዎችን እንዲያቀርቡ ሊደረጉ ይገባል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32514

#Ethiopia🇪🇹 #DecentWork #SocialJustice #ThisWayToSocialJustice #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ለማካተት እና ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ዙር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ እና ባሕር ዳር ከተሞች የተውጣጡ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል፡፡ ክትትሉ በአዲስ አበባ፣ በአምቦ፣ በባህር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በባኮ፣ በጋምቤላ፣ በሆሳዕና፣ በመቐለ፣ በሰበታ እና በሻሸመኔ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ በክትትሉ የተለዩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በትምህርት ወቅት የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች የቀረቡ ሲሆን ምንም እንኳን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተሻሻሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም የትምህርት ቤቶቹ መማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎች እንዲሁም የውስጥ እና የውጭ አካባቢ የተደራሽነት ክፍተት ያለባቸው መሆኑ፣ በአዲሱ የትምህርት ካሪኩለም መሠረት የተዘጋጁ የመማሪያ መጽሐፍት በምልክት ቋንቋ እና በብሬል ተተርጉመው አለመቅረባቸው እንዲሁም በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር ከተጠቀሱ ተግዳሮቶች መካከል ናቸው።

🔗 https://ehrc.org/?p=32542

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
2025/10/27 05:44:55
Back to Top
HTML Embed Code: