ዐውደ ጥናት፦ በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የሥራ ፍልሰት አስተዳደር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) “የሌሎች ሀገራትን መልካም ተሞክሮ በመቅሰም እና የባለድርሻ አካላት ትብብርን በማጠናከር በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የሥራ ፍልሰት አስተዳደርን ማጎልበት” በሚል ርዕስ ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ዐውደ ጥናት አካሂዷል። በዐውደ ጥናቱ የመንግሥት አካላት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት፣ በስደት ተመላሾች የተቋቋሙ ማኅበራት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ዐውደ ጥናቱ የሀገራት መልካም ተመክሮዎችን በመውሰድ በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የሥራ ፍልሰት አስተዳደርን ለማጠናከር ስትራቴጂያዊ ስልቶችን እና መፍትሔዎችን ለመለየት ያለመ ነው።
በዐውደ ጥናቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተወካይ የኢትዮጵያ ሥራ ፍልሰት አስተዳደር ተግዳሮቶች እና ዕድሎች፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ክፍተቶችን እና ድክመቶችን ስለመፍታት፣ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር ስላለው የኤሌክትሮኒክስ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS)፣ የሥራ ዕድሎችን ለሥራ ፈላጊዎች በማቅረብ እና በውጭ ሀገር ሥራ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሰዎች መረጃን አደራጅቶ በማቅረብ ረገድ ያለውን ጠቀሜታ አብራርተዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33789
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

❤1👍1
ስልጠና፦ በስደተኞች ለሚመሩ ድርጅቶች እና ለስደተኞች ተወካዮች
...
የስደተኞች መብቶች ጥበቃን ለማጎልበት የስደተኛ ማኅበረሰብ ተወካዮችን እና ማኅበራትን በማጠናከር አሳታፊ የሆኑ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች እና አሠራሮችን መተግበር ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሉተራን የዓለም ፌዴሬሽን (LWF) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ለሚገኙ በስደተኞች የሚመሩ ድርጅቶች እና ለስደተኞች ተወካዮች የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰኔ 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ሰጥቷል። በስልጠናው በስደተኞች የሚመሩ ድርጅቶች ኃላፊዎች እና አባላት እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የከተማ ስደተኛ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዓለም አቀፍ መርሖችን እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን ጨምሮ ስለ መሠረታዊ የስደተኞች መብቶችና ግዴታዎች ተሳታፊዎች ያላቸውን ዕውቀት እና ግንዛቤ ማሳደግ ነው።
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በስደተኞች የሚመሩ ማኅበራት ሚናዎች እና ኃላፊነቶች፣ በስደተኞች መብቶች እና ጥበቃ፣ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች አሳታፊነት እና አካታችነት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት እና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር የሚከወን ቅንጅታዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ማብራሪያዎች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር በተግባር የተደገፈ ውይይት ተደርጓል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33799

👍4❤2
በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥበቃ እና በሲቪክ ምኅዳር ላይ የተካሄደ የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ ኮንፈረንስ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ በሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎች በተለይም በሲቪክ ምኅዳሩ እና በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥበቃ ላይ ያተኮረ ብሔራዊ ኮንፈረንስ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ አካሂደዋል። ብሔራዊ ኮንፈረንሱ በ2017 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩ አሳሳቢ እና ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡና በሰብአዊ መብቶች ላይ አተኩረው ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመምከር ያለመ ነው።
በብሔራዊ ኮንፈረንሱ በሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ፣ በሽግግር ፍትሕ፣ በሴቶች እና ሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብቶች እና መሰል ዘርፎች ላይ ሀገራዊ መሻሻል ለማምጣት ኢሰመኮ፣ ሲቪል ማኅበራትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት መሠራት ባለባቸው ሥራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥበቃ እና ከሲቪክ ምኅዳሩ ጋር በተያያዘ በ2017 ዓ.ም. የነበሩ ክስተቶች ላይ ያከናወነው ጥናት፣ በግልጽ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ እንዲሁም በክትትልና ምርመራ የተለዩ ግኝቶች በዝርዝር ለኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ቀርበዋል። በተጨማሪም በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሥራቸው ወቅት ስለሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች እና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አስተያየቶች በግልጽ አቅርበዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33807

❤1
ለአካል ጉዳተኛ የመንግሥት ሠራተኞች በሚቀርብ ተመጣጣኝ ማመቻቸት ላይ የተካሄደ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ለሚሠሩ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሚቀርበውን ተመጣጣኝ ማመቻቸት አስመልክቶ ባከናወነው ጥናት የተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ምክክር አካሂዷል። ጥናቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም ከፌዴራል መንግሥት በተመረጡ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ላይ የተካሄደ ነው፡፡
በምክክሩ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌዴራል መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ከኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን እና ከኦሮሚያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በምክክር መድረኩ ተመጣጣኝ ማመቻቸትን በተመለከተ በፌዴራል ተቋማት እና በክልሎች የተደነገጉ የሕግ ማዕቀፎች ያለባቸው ክፍተት፣ በየተቋማቱ በሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና የሰው ሃብት ባለሙያዎች ዘንድ የሚታይ የግንዛቤ እና የአመለካከት ክፍተት፣ ተመጣጣኝ ማመቻቸትን የተመለከተ የኦዲት ሥራ፣ መመሪያዎች እና ፎርማቶች አለመኖር፣ ዝቅተኛ የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ተሳትፎና ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘት እና ሌሎች ኢሰመኮ ባከናወነው ጥናት የተለዩ ግኝቶች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
🔗 https://ehrc.org/?p=33870

❤3
#ድሬዳዋ እና #ሐረሪ፦ የታራሚዎች እና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል ግኝቶችና የምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ባካሄደው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና በ2016 ዓ.ም. በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከሰኔ 21 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በድሬዳዋ እና በሐረር ከተሞች ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ከድሬዳዋ ፖሊስ እና ማረሚያ ቤት፣ ከከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት፣ ከፍትሕና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ፣ ከሴቶችና ሕፃናት ቢሮ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት እና ከጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ እንዲሁም ከሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት አስተዳደር ኮሚሽን፣ ከማረሚያ ቤት አስተዳደር፣ ፖሊስ ኮሚሽን እና በሥሩ ከሚገኙ 11 ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ከፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት፣ ከምክር ቤት፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ፣ ከሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ከጤና ቢሮ እና ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች፣ ተወካዮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33904
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ባካሄደው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና በ2016 ዓ.ም. በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከሰኔ 21 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በድሬዳዋ እና በሐረር ከተሞች ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ከድሬዳዋ ፖሊስ እና ማረሚያ ቤት፣ ከከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት፣ ከፍትሕና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ፣ ከሴቶችና ሕፃናት ቢሮ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት እና ከጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ እንዲሁም ከሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት አስተዳደር ኮሚሽን፣ ከማረሚያ ቤት አስተዳደር፣ ፖሊስ ኮሚሽን እና በሥሩ ከሚገኙ 11 ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ከፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት፣ ከምክር ቤት፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ፣ ከሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ከጤና ቢሮ እና ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች፣ ተወካዮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33904
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
❤1
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በልዩ አዳሪ እና ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ አራተኛ ዙር ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በመቐለ ከተማ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ክትትል የተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ኢሰመኮ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊ መብቶችን አስመልክቶ በአዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ባሕር ዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ባኮ፣ ጋምቤላ፣ ሆሳዕና፣ መቐለ፣ ሰበታ እና ሻሸመኔ ከተሞች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ያካሄደ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙር የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እንዲሁም ሦስተኛውን ዙር በሃዋሳ ከተማ ማካሄዱ ይታወቃል።
በቀረበው የክትትል ሪፖርት በክልሉ ያለው ከፍተኛ የሆነ የበጀት እጥረት፣ የትምህርት ቤቶች ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ምቹ አለመሆን እና የተደራሽነት ውስንነት፣ በአካቶ ትምህርት ቤቶች የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ አለመኖር፣ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸው፣ በጦርነቱ አካል ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች ለማስተናገድ በቂ የሆነ በጀት አለመኖር ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ዋና ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33915

#ትግራይ፣ #ሶማሊ፦ ግጭት በተካሄደባቸው እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የትምህርት ተገኝነትን በተመለከተ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድኅረ ግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ የትግራይ ክልል እና የተፈጥሮ አደጋዎች ባሉባቸው የሶማሊ ክልል አካባቢዎች የትምህርት ተገኝነት እና ተያያዥ የሕፃናት መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የትግራይ እና የሶማሊ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ትምህርት ቢሮዎችና ጽሕፈት ቤቶች ኃላፊዎች፣ በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ 17 ትምህርት ቤቶች መምህራን እና ርዕሰ መምህራን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ኢሰመኮ በክትትሉ የለያቸው ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዚሁ መሠረት በትግራይ ክልል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የቤተ-መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ እና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ማእከላት መልሶ ግንባታ ወይም ጥገና ያልተደረገላቸው በመሆኑ ፣ የማስተማሪያ እና የመማሪያ ግብዓቶች እጥረት መኖር እንዲሁም በተወሰኑ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች መጠለያነት ስለሚያገለግሉ የሕፃናትን በተለይም የአካል ጉዳተኞችን እና ሴቶችን ደኅንነት የጠበቀ፣ ምቹ አለመሆናቸው ተጠቅሷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33929

ኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነርን እና የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነርን ላበረከቱት ቀና የሰብአዊ መብቶች አገልግሎት ያመሰግናል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ኢሰመኮን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 15 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ አስቀድመው በጽሑፍ ማቅረባቸውን እና ምክር ቤቱም አሠራሩን ተከትሎ ጥያቄያቸውን መቀበሉን ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
ራኬብ መሰለ በኢሰመኮ ከፍተኛ አማካሪነት የኮሚሽኑን ተቋማዊ ማሻሻያ እና መዋቅራዊ ለውጥ በኃላፊነት ከአንድ ዓመት በላይ ሲመሩ ከቆዩ በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ባደረገው ልዩ ስብሰባ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ ቀን ርግበ ገብረሐዋሪያ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት የሴቶች እና የሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር ኃላፊነትን ደርበው እያገለገሉ ቆይተዋል። ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እንዲሁም ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ በኢሰመኮ በነበራቸው ቆይታ በትጋት፣ በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ አገልግለዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33936
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ኢሰመኮን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 15 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ አስቀድመው በጽሑፍ ማቅረባቸውን እና ምክር ቤቱም አሠራሩን ተከትሎ ጥያቄያቸውን መቀበሉን ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
ራኬብ መሰለ በኢሰመኮ ከፍተኛ አማካሪነት የኮሚሽኑን ተቋማዊ ማሻሻያ እና መዋቅራዊ ለውጥ በኃላፊነት ከአንድ ዓመት በላይ ሲመሩ ከቆዩ በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ባደረገው ልዩ ስብሰባ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ ቀን ርግበ ገብረሐዋሪያ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት የሴቶች እና የሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር ኃላፊነትን ደርበው እያገለገሉ ቆይተዋል። ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እንዲሁም ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ በኢሰመኮ በነበራቸው ቆይታ በትጋት፣ በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ አገልግለዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33936
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
❤2
ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የተካሄደ ሁለተኛ ዙር ስልጠናዊ ውይይት
...
በሰብአዊ መብቶች ላይ በጋራ መምከር እና አጋርነትን ማጠናከር ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ ጉልህ ሚና አለው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶቹ እንዲሁም ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ዙሪያ ሐምሌ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች አባላት ጋር ሁለተኛ ዙር ስልጠና እና ውይይት አካሂዷል።
የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢሰመኮ ልዩ ልዩ የሰብአዊ መብቶች ሥራ መሪዎች የተሳተፉበት የመጀመሪያው ዙር ሥልጠናዊ ውይይት ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደ መሆኑ ይታወሳል።
ስልጠና እና ውይይቱ ኢሰመኮ ከምክር ቤቱ ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ለማሳደግ፣ በአዋጅ በተሰጡት ተግባራትና ኃላፊነቶች ላይ ግልጽነት ለመፍጠር፣ እያከናወናቸው የሚገኙ ዋና ዋና ተግባራትን ማስገንዘብ እና ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በመፍጠር የምክር ቤቱን ቀጣይነት ያለው አዎንታዊ እገዛ ለማግኘት ያለመ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=33941

#ደቡብምዕራብኢትዮጵያ፦ የታራሚዎች እና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የታራሚዎች እና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በ2017 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና በ2016 ዓ.ም. ለክልሉ የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤን ጭምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ የዐቃቤ ሕግ ኃላፊ፣ የፖሊስ እና የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና በፍትሕ ዘርፍ ላይ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ኢሰመኮ በ2016 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል መሠረት ለክልሉ ፖሊስ እና ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ሪፖርት በሥራ ኃላፊዎች ቀርቧል። የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ሁኔታ መኖሩ የተመላከተ ሲሆን ለመተግበር ጊዜ የሚፈልጉ ምክረ ሐሳቦችንም አስፈላጊውን ሁኔታ በማሟላት ለመፈጸም ቅድመ ዝግጀት መኖሩ ተመላክቷል።
በ2017 ዓ.ም. በፖሊስ እና በማረሚያ ቤቶች የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33977
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የታራሚዎች እና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በ2017 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና በ2016 ዓ.ም. ለክልሉ የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በጅማ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤን ጭምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ የዐቃቤ ሕግ ኃላፊ፣ የፖሊስ እና የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና በፍትሕ ዘርፍ ላይ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ኢሰመኮ በ2016 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል መሠረት ለክልሉ ፖሊስ እና ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ሪፖርት በሥራ ኃላፊዎች ቀርቧል። የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ሁኔታ መኖሩ የተመላከተ ሲሆን ለመተግበር ጊዜ የሚፈልጉ ምክረ ሐሳቦችንም አስፈላጊውን ሁኔታ በማሟላት ለመፈጸም ቅድመ ዝግጀት መኖሩ ተመላክቷል።
በ2017 ዓ.ም. በፖሊስ እና በማረሚያ ቤቶች የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33977
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: በሰዎች ከመነገድ ወንጀል የመጠበቅ መብት
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 18 (2)
ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው።
በሰዎች በተለይም በሴቶችና ሕፃናት የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመግታትና ለመቅጣት የወጣ ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 3 (ሀ)
በሰዎች መነገድ ማለት ሰዎችን በማስፈራራት ወይም ኃይል በመጠቀም ወይም በሌላ በማንኛውም ዐይነት መንገድ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማጭበርበር፣ በማታለል፣ ሥልጣንን ወይም የተጎጂን ተጋላጭነት አላግባብ በመጠቀም፣ ወይም በሌላ ሰው ላይ ቁጥጥር ያለውን ሰው ፈቃድ ለማግኘት ክፍያ ወይም ጥቅማጥቅም በመስጠት ወይም በመቀበል ሰዎችን ለብዝበዛ ዐላማ የመመልመል፣ የማጓጓዝ፣ የማሸጋገር፣ የመቀበል ወይም የማስጠለል ድርጊት ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34011
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

#ሲዳማ፦ በተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በሲዳማ ክልል በ15 ፖሊስ ጣቢያዎች እና በይርጋለም ማረሚያ ቤት በሕግ ጥበቃ ሥር የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በሻሸመኔ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ የክልሉ የጤና፣ ትምህርት እና ፍትሕ ቢሮዎች፣ የማረሚያ ቤቶች እና ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የዞኖች እና የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በውይይት መድረኩ በኢሰመኮ ክትትል የተለዩ እመርታዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ክትትል በተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች ከታዩ መሻሻሎች መካከል ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት ጊዜ የተጠረጠሩበት ወንጀል እና የተያዙበት ምክንያት የሚገለጽላቸው መሆኑ፣ የተጠርጣሪዎች መረጃ አያያዝ መሻሻሉ፣ በተጠርጣሪዎች ላይ አካላዊ ጥቃት/ድብደባ እንዲሁም ሌላ ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም አዋራጅ አያያዝ አለመፈጸሙ፣ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ጫናና ማስገደድ ቃላቸውን መስጠታቸው፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር እንዲገናኙ መደረጉ፣ በራሳቸው ወጪ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸው እንዲሁም በፍርድ ቤት የሚሰጡ ትእዛዞች ተፈጻሚ መሆናቸው በውይይቱ ተጠቅሷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34022

#ማእከላዊኢትዮጵያ፦ በፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የተከናወነ ክትትል ግኝቶችን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 በጀት ዓመት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥር በሚገኙ በተመረጡ 49 ፖሊስ ጣቢያዎች እና በ7 ማረሚያ ቤቶች በሕግ ጥበቃ ሥር የሚገኙ ሰዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ባደረገው ክትትል ግኝቶች ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በሻሸመኔ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በምክክር መድረኩ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ከክልሉ ምክር ቤት፣ ከጤና ቢሮ፣ ከፖሊስ እና ማረሚያ ኮሚሽን፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከወረዳና ዞን የተወከሉ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በወይይት መድረኩ ላይ ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው የፖሊስ እና የማረሚያ ቤት ተቋማት የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና ጥበቃ ሁኔታ ላይ የታዩ መልካም እመርታዎች፣ መሻሻል የሚያስፈልጋቸው አሳሳቢ ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበርን ለመከታተል የሚያስችል የድርጊት መርኃ ግብር በኮሚሽኑ በኩል ተዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ቀርቧል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34029
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 በጀት ዓመት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥር በሚገኙ በተመረጡ 49 ፖሊስ ጣቢያዎች እና በ7 ማረሚያ ቤቶች በሕግ ጥበቃ ሥር የሚገኙ ሰዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ባደረገው ክትትል ግኝቶች ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በሻሸመኔ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በምክክር መድረኩ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ከክልሉ ምክር ቤት፣ ከጤና ቢሮ፣ ከፖሊስ እና ማረሚያ ኮሚሽን፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከወረዳና ዞን የተወከሉ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በወይይት መድረኩ ላይ ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው የፖሊስ እና የማረሚያ ቤት ተቋማት የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና ጥበቃ ሁኔታ ላይ የታዩ መልካም እመርታዎች፣ መሻሻል የሚያስፈልጋቸው አሳሳቢ ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበርን ለመከታተል የሚያስችል የድርጊት መርኃ ግብር በኮሚሽኑ በኩል ተዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ቀርቧል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34029
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
❤2
በንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ላይ የተካሄደ የዐቅም ግንባታ ስልጠና
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም (Danish Institute for Human Rights (DIHR)) እና ከኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮረ የዐቅም ግንባታ ስልጠና ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። መድረኩ በንግድ ዐውድ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመለየት፣ ለመከላከል እና ለመቀነስ የሚያስችሉ የጥንቃቄ ሂደቶችን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሖችን (United Nations Guiding Principles on Business and Human Rights) እንዲሁም በዝግጅት ሂደት ላይ የሚገኘውን የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር በተመለከተ የንግዱን ማኅበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ነው።
በስልጠናው አስመጪ እና ላኪዎች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አምራቾችን ጨምሮ በተለያዩ የንግድ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጀቶች እንዲሁም የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም እና የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በስልጠናው የተባበሩት መንግሥታት የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሖች መሠረታዊ ይዘቶችን አስመልክቶ በተለይም የንግድ ተቋማት ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ኃላፊነትን የተመለከተ ገለጻ ተደርጔል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34034

❤4
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ ተጠያቂነትን ማስፈን እና ተጎጂዎችን መካስ ያስፈልጋል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ባለ 152 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት በሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። ለ4ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ሪፖርት በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ ባሉ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የተስተዋሉ ቁልፍ እመርታዎችን፣ አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ምክረ ሐሳቦችን እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያካተተ ነው።
ይህ ዓመታዊ ሪፖርት ኢሰመኮ በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች በተቋቋሙ የሥራ ክፍሎቹ በሰበሰባቸው ማስረጃዎች፣ ባከናወናቸው የክትትል እና ምርመራ ላይ መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው። በዚህም መሠረት ሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕን ጨምሮ የሲቪል እና የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ፣ የሴቶች እና የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች መብቶች፣ በኢሰመኮ የተስተናገዱ በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎችን ከመወጣት አኳያ ያለችበት ሁኔታን የሚያሳዩ ጉዳዮች በዝርዝር ተካተዋል።
ሙሉ ሪፖርት: https://ehrc.org/download/?p=34091
ጋዜጣዊ መግለጫ: https://ehrc.org/?p=34088

የሳምንቱ #HumanRights Concept: በሕይወት የመኖር መብት
...
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 6
ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው። ይህ መብት በሕግ ሊከበር ይገባል፤ ማንኛውም ሰው ያላግባብ ሕይወቱን ሊነፈግ አይገባም።
የተ.መ.ድ. አጠቃላይ ትንታኔ ቁ. 36 (በሕይወት የመኖር መብት)
አባል ሀገራት ሕግ የማስከበር ተልዕኮ የተሰጣቸውን ወታደሮች ጨምሮ ሕግ አስከባሪ ኃላፊዎቻቸው ሕይወትን ያላግባብ እንዳይነፍጉ ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎችን በሙሉ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34177

ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዘላቂ መፍትሔዎች ቀጠናዊ ሴክሬታሪያት (The Regional Durable Solutions Secretariat (ReDSS)) ጋር በመተባበር ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ አተገባበርን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አባላት፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተፈናቃዮች ከሚያስተናግዱ ክልሎች የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ጥበቃን እና ድጋፍን የተመለከቱ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ ማዕቀፎች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃና ድጋፍ ረቂቅ ብሔራዊ ሕግ ይዘትና ያለበት ደረጃ፣ የኢሰመኮ የክትትል ግኝቶች፣ ዘላቂ መፍትሔ የማፈላለግ ተግባራት ያሉበት ሁኔታ፣ በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰተዋሉ አሳሳቢ ጉዳዮችና ምክረ ሐሳቦች፣ የዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ብሔራዊ ስትራቴጂ ከተዘጋጀበት ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራት፣ የታዩ ለውጦች፣ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34206

❤5
በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (International Media Support) ጋር በመተባበር በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ ውይይቱ በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ሕጎችን ለባለድርሻ አካላት ለማስገንዘብ እና በአፈጻጸሙ ላይም የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው።
በመድረኩ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ የሕግ ማዕቀፎች፣ በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ የተደረጉ የቅርብ ጊዜ ለውጦች፣ ክፍተቶች፣ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊነቶች፣ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት እና ሐሳብን የመግለጽ መብት ላይ ኢሰመኮ ባከናወናቸው ክትትሎች የተለዩ ግኝቶች፣ የመብቶቹ መከበር ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለው ሚና፣ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነቶች እና የሚጣሉባቸው ገደቦች፣ በጋዜጠኞች መብቶች ጥበቃ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በጋዜጠኝነት እና የማኅበረሰብ አንቂነት መካከል መደበላለቅ እንደሚስተዋል፣ ሐሰተኛ ስሞችን በመጠቀም በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የጥላቻ ንግግር እንደሚሰራጭ፣ ጋዜጠኞች በወንጀል ተግባር ተጠርጥረው በሕግ ሲጠየቁ በሙያቸው ምክንያት እንደታሰሩ ተደርጎ መረጃ የማስተላለፍ ሁኔታዎች መኖራቸው በውይይቱ ተገልጿል፡፡
🔗 https://ehrc.org/?p=34218

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ የክትትል ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. በቃሊቲ የሴቶች ማረፊያ እና ማረሚያ ማእከል፣ በቂሊንጦ የቀጠሮ ማረፊያ ማእከል፣ በከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት እና በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች ታራሚዎች እና የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦችን መሠረት በማድረግ ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ከአራቱ ማረሚያ ቤቶች የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በውይይት መድረኩ ኢሰመኮ በ2017 በጀት ዓመት በ4 የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን እና የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚመለከት ባከናወነው ክትትል የተለዩ ጠንካራ ጎኖች እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34238

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሃይማኖትና የእምነት ነጻነት
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 27(1)
ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የኅሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው። ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፤ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመግለጽ፣ የመከተል፣ የመተግበር እና የማስተማር መብትን ያካትታል።
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 18(2 እና 3)
ማንም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመከተል ወይም የመያዝ ነጻነቱን በሚነካ አኳኋን ሊገደድ አይገባም።
የራስን ሃይማኖት ወይም እምነት የመግለጽ ነጻነት ሊገደብ የሚችለው በሕግ በተደነገገው መሠረትና የሕዝብን ደኅንነት፣ ጸጥታ፣ ጤና ወይም ሞራል ወይም የሌሎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለማስከበር አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34274

👍4❤3