Telegram Web Link
አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል። በ23ኛ ሳምንት ምድብ “ለ” ተጠባቂ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከአንድ የውድድር ዘመን በኃላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ አርባ…

https://www.fanabc.com/archives/244536
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞቻችን እና የከተማ አስተዳደራችን ተቋማት የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ…

https://www.fanabc.com/archives/244539
Live stream finished (40 minutes)
እነ ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ክስ መመስረቻ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ክስ መመስረቻ ለዐቃቤ ህግ ተፈቅዷል። የክስ መመስረቻውን የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ በቀሲስ በላይ መኮንን ፣ያሬድ ፍስሃ እና ዳባ ገናና በተባሉ 3 ተጠርጣሪዎች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/244543
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ባሕርዳር ገባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ባሕርዳር ከተማ ገብቷል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የጣና ሐይቅ ፈርጧ፣ የበርካታ ደሴቶች መናኸሪያ፣ የጢስ አባይ ፏፏቴ መገኛ እና የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆነችው ውቢቷ ባሕርዳር ገብተናል ብለዋል። ልዑኩ ባሕር ዳር ሲደርስም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና…

https://www.fanabc.com/archives/244552
የኢስላማባድ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የቢዝነስና ንግድ ጉዞ እንዲሳተፍ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር እና የኢስላማባድ ፕሬዚዳንት የንግዱ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ በሚካሄደው 2ኛው የቢዝነስና ንግድ ጉዞ እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡ አምባሳደር ጀማል በከር በኢስላማባድ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ ፎረም ከፕሬዝዳንቱ አህሳን ዛፋር ባክታዋሪ ጋር በመሆን መርተውታል። በኢስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው…

https://www.fanabc.com/archives/244555
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት በስተላለፉት መልዕክት÷ ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ መደጋገፍ የእለት ተእለት ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች…

https://www.fanabc.com/archives/244561
በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከል መረጃና ስታቲክስ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ÷ አደጋው በሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11 ሰዓት 40 ላይ መከሰቱን…

https://www.fanabc.com/archives/244564
ማስታወቂያ!
እንኳን አደረሳችሁ!
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡፡
ማይክሮሶፍት በኢንዶኔዥያ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ለመደገፍ ቢሊየን ዶላሮች መመደቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማይክሮሶፍት በኢንዶኔዥያ ከኮምፒዩተር አገልግሎት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር የተያያዙ መሠረተ ልማቶችን ለመደገፍ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ለመመደብ መዘጋጀቱ ተገልጿል። የአሜሪካው ግዙፍ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳቲያ ናዴላ ዕቅዱን ይፋ ያደረጉት ከጥቂት ቀናት በፊት በጃካርታ ባደረጉት ቆይታ በማይክሮሶፍት ግንባታ ዙሪያ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት…

https://www.fanabc.com/archives/244573
የሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠይቋል፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ዓረቢያ የንግድ ም/ቤቶች ፌደሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም አምባሳደር ሌንጮ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ገልጸው÷ ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱና ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።…

https://www.fanabc.com/archives/244567
የጸሎተ ሐሙስ "ሕፅበተ እግር" ስነ ስርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የትህትና እና አክብሮት መገለጫ የሆነው የጸሎተ ሐሙስ ‘ሕፅበተ እግር" ስነ ስርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከናውኗል፡፡

ዕለቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የቤተክርስቲያኗ ጳጳሳት፣ ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት በመንበረ-ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተክርስቲያን ተካሂዷል።

የሃይማኖቱ ተከታዮችም ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትን የጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቅዳሴ፣ በስግደት እና በሕፅበተ እግር አክብረዋል።

በቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ካህናት አባቶች በዕለተ ሐሙስ በዕውቀት፣ በዕድሜ፣ በክብር፣ በስልጣን ትልቅ ነኝ ሳይሉ ከዲያቆናት እስከ ምዕመናን ድረስ ዝቅ ብለው እግር …

https://www.fanabc.com/archives/244580
የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ2017 ዓ/ም በጀት ሰሚ መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ2017 ዓ/ም በጀት ሰሚ መድረክ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

የበጀት ሰሚ መድረኩን የመሩት አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት ÷ የ2017 ዓ/ም የበጀት ዝግጅቱ ዓላማ የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው በ2016 እስከ 2ዐ18 ዓ/ም የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ማስፈጸምና የመንግስትን ፈጣን፣ ፍትሃዊና ዘላቂ የዕድገት ፖሊሲን ማረጋገጥ ነው፡፡

በዛሬው የመጀመሪያ የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ2017 ዓ/ም በጀት ሰሚ መድረክ የስራና ክህሎት፣ የቱሪዝም፣ የባህልና ስፖርት እንዲሁም የገቢዎች …

https://www.fanabc.com/archives/244585
በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማና አዳማ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በፕሪምየር ሊጉ የ23ኛ ሣምንት መርሐ ግብር በዛሬው እለት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አዳማ ከተማ ነቢል ኑሪ ባስቆጠራት ጎል ሻሸመኔ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/244596
Live stream finished (1 hour)
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አመራሮችና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮችና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን መቀላቀላቸው ተገለጸ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ፣ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር እና ሚኒስትር ዴኤታዋች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና የጽሕፈት ቤቱ ሰራተኞች ናቸው በንቅናቄው የተሳተፉት፡፡

በዚህም በጠቅላላው ብር 247 ሺህ 900 ብር በማዋጣት…

https://www.fanabc.com/archives/244599
በአቃቂ የገበያ ማዕከል በተከሰተ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ተቃጠሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት 3 ሠዓት ከ10 ደቂቃ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጠሉ፡፡

እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰውና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠርም አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ፣ ሁለት የውኃ ቦቴ እና 44 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መሠማራታቸው ተገልጿል፡፡
2024/05/17 22:40:03
Back to Top
HTML Embed Code: