🖊
ከዘመድ አዝማድ እርቄ
መርጨ ካንችው ብዛመድ
ቡን አደረግሻት ህይወቴን
ልክ እንደ ጓሮ አመድ።
"ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኸ"
ቢሆንብኝም ነገሩ
"ሞኝ ቅቤ በውሃ ይቀልጣል"
ቢል ቢሳለቅም ሀገሩ
በገራገር ብኩን ልቤ
ሁሉንም ነገር ዛሬ ተረዳሁ
ምንም ቢሆን ግን ድርጊቱ
በሞኝነቴ እኔ ተጎዳሁ።
ቤተሰብ ይሁኑ ሸር ያድርጉ 👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ባለ ሱቋ😁
ሀበሻ vibe👑 @viberealfeel
ባለ ሱቋ 🤫

አንዲት ሴት ተበረች ሱቅ የነበራት😁
ከሁሉም አብልጬ እጅግ ማፈቅራት😍
ከመውደዴ ብዛት - ከማፍቀሬ ብዛት እንዳያት ጓጉቼ
እገዛት ነበረ ቤቴ የሞላውን ሱቋከ ገብቼ

መርፌ እንኳን ገዝቼ🙄
መልስ አልቀበልም መቶ ብር ሰጥቼ
የማልፈልገውን ስገዛ_ስገዛ
ቲፕ ነው እያልኩኝ ደሞዜን ሰጥቻት በዋዛ ፈዛዛ🙃
ኖሬ_ኖሬ_ኖሬ
ምን አለ ባልገዛው ከሱቋ ገብቼ
እንድል ሆኛለሁኝ እኔው በሰራው እኔው ተፀፅቼ🙂

ምንልል መሰላቹ...😌
ያቺ የምወዳት ባለሱቋ ፍቅሬ
ዛሬ ላይ የለችም
እርቃ ሄዳለች ከኛ ሰፈር ወጥታ😞
ለምን?🥹
በኔ ብር በኔ ቲፕ ትልቅ ሆቴል ከፍታ 🤨
ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🌀የኑሮ ኳስ ሜዳ🌀
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሀል ዳኛ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ይሯሯጣል
ይራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል
ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱ ያንዱን ላይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ይገባል
......................................
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ሰው የራሱን 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ
.........................................
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሀሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም....
ውሸት እውነት እንጂ እውነት ውሸት የለም

ሼር ይደረግ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
"በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"

በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ

" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)

" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)

" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6

ውድ አባቶቼ እናቶቼ ወንድም እህቶቼ፡ህፃናት የተዋህዶ ልጆች


በሀገርም
ውስጥ
ከሀገርም
ውጭ
ያላችሁ
በስደት
በእስራት
በጎዳና
በጭንቅ
በአልጋ
በዱር
በበረሃ
በዋሻ
ያላችሁ
በሙሉ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሠኛችሁ የተዋህዶ ልጆች

እንኳን

ለጌታችን እና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ በዓል
በሰላም እና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ
























ባ ለ ው ለ ታ ች ን

ጌ ታ ች ን

አ ም ላ ካ ች ን

መ ዳ ኒ ታ ች ን

ኢየሱስ ክርስቶስ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም








በቸርነቱ





ፍቅርንም ይስጠን ሰላሙን ያድለን አይነ ልቦናችንንም ያብሪልን

የሰላም የደስታ የፍቅር የበረከትየአንድነት በዓል ይሁንልን።
🙏አሜን!!!
🙏አማን!!!
🙏 አማን!!!

https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
የእኩለ ሌሊት ወፍ
🖊


መቃብር መሳይ ትንሽየ ከአፈር የተሰራች ጉብታ (መደብ) ላይ ታቻምና የነሃሴ ብርድ የገደለብንን የፍየል ሌጦ አንጥፌ ጋደም ብያለው። አንድ ዙር ተኝቼ ስነቃ እኩለ ሌሊት ላይ አንድ ድምፅ ሰማሁ። ልዩ ለዛ ያለው የወፍ ድምፅ። መቼም ልጅ የነገን ጨዋታ ነው የሚናፍቅና ነጋ መስሎኝ ብድግ አልኩኝ። ቤቱ በጨለማ እንደታነፀ ነው። ተመልሼ ጋደም አልኩኝ።
የወፏ ጩኸት ግን ቀጥሏል። ልብ ሰጥቼ ሰማሗት። የማያውቁትን ሰው የሚያስናፍቅ አንደበት ነው።
" መጣሽ ቀረሽ!?" የሚል ናፍቆት የወረሰው እህህ ባይ አይነት ጩኸት፤ ወፎች በሌሉበት ጨካ ውስጥ እየኖረች ወገን የናፈቃት አይነት ቅላፄ ፤ በወፎች ተከባ ወፍ የሚናፍቃት ቀና ልብ ያላት ወፍ ዝማሬ አይነት። ምናለፋችሁ… በሃሳብ ሽምጥ ያስጋልባል ድምጿ።

ይች ወፍ ከ25 ዓመት በሗላ ድጋሜ ሰማሗት። ሌሊቴን በረዘችው። በትዝታ አስዋኘችኝ።
ይሔው ድምጿ…" መጣሽ ቀረሽ!? መጣሽ ቀረሽ!?…"
ጥሪዋን ቀጥላለች። እኩለ ሌሊት ላይ ከአንቅልፌ ነቅቼ እከተላት ጀመርኩ።
ግን ምን ያክል ሆድ ቢብሳት ይሆን ይህን ያክል ዘመን ሌት ተቀን ብቻዋን የምትጠብቅ? ፍቅሯን ወይስ ጓደኛዋን?
ልጅነት ብዕር ነው፤ሁሉን ከትቦ ማስቀመጥ ይችላል። ልጅነት መፅሃፍ ነው፤ ትውስታወቹ ተነበው አያልቁም። ልጅነት ቅርስ ነው፤ ትዝታው አብሮህ ዘመን ይሻገራል።

የዛሬው ድምጿ ደግሞ ያምራል። ገናን ተከትሎ የመቅደስ በገና መስሎላታል። የሚገርመው ግን ወዳጇን የምትፈልገው ሌት ብቻ መሆኑ ነው። ይሄ ልዩ ዝማሬ ለኔ አንዳች መልዕክት ይኖረው ይሆን? " መጣሽ ቀረሽ?" አሁንም በጆሮየ ትጮሃለች። ምን አግኝቷት ይሆን ግን ወፍየን።
በቃ…ድምፄ ድምጿን ባይሆንም ዜማዋን ልከተላት በእኩለ ሌሊት ቃል ገብቻለው። ላመኑበት ነገር ፅናትን አስተምራኛለች።
" መጣሽ ቀረሽ" ቀድሞውንም በእኩለ ሌሊት ቃል ገብቻለዋ። በቃ እምነት፡ እውነት፡ ፅናት… እንደ ወፏ ሌት ተነስቼ መብረር ባልችልም ሌት ተነስቼ መጮህ እችላለው።
" መጣሽ ቀረሽ?" መጣሽ ቀረሽ?" መጣሽ ቀረሽ?"…


ወፍየን ጠይቋት ~ ምን አለ ከሆዷ
በሌሊት የሆነ ~ ምንጊዜም መንገዷ።
እስኪ ንገሩልኝ ~ ታበድረኝ ክንፍ
ልቤ ካሰበው ላይ ~ ተሻግሬ እንዳርፍ።


" መጣሽ ቀረሽ……" ከዚህ በሗላ ሙዚቃ ለምኔ…በቃ ይሄው ብቻ ነው እንጉርጉሮየ…" መጣሽ ቀረሽ…"

ሀሳብ አስተያየት ካልልችሁ👇👇
@ABUNE05
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ውድ የኤፍ ማን ቻናል ቤተሰቦች በቀን 5-04-15 አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ የምንለቅ ሲሆን ከተመቻችሁ በላይክ 👍 እና ካልተመቻችሁ 👎 ሀሳባችሁን ግለፁልን ሼር አድርጉ🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
+++"የመጨረሻው ደብዳቤ"+++

ይድረስልኝ ላንተ በቁምህ ለሞትከው
በደም ተጨማልቀህ ገምተህ ለሸተትከው
          ክቡር አልልህም ክብር የት ታውቅና
          ዶክተር አልልህም ምኑን ተማርክና
          ሃገር ሞተች እንጂ ባንተ ድድብና
እስኪ ልጠይቅህ ማነው ያለህ በርታ
እንደዚህ አርክሶ ያጣላህ ከጌታ
  እንዳሻህ ገደልከን እንደጉድ ሞትንልህ
   ቤተ እምነት አቃጠልክ አልቅሰን ዝም አልንህ
       በርሃም ቀጣኸን ላንተም ጸለይንልህ
          ማን አይዞህ ብሎህ ነው አሁን የለየልህ
ባንተ ዘመን እኮ
አባቱን ያልሰዋ ወንድም ያልቀበረ
እህቱ ተደፍራ ቅስሙ ያልተሰበረ
እናቱ ታርዳበት በደም ያልሰከረ
በጦቢያዬ ምድር ሰው የለም ነበረ
           ግን...
            ሁሉንም አልፈናል አዝነን ብናለቅስም
            ያሁኑ ድፍረት ግን አያለሳልስም
ቤተ እምነቷ ሲነድ ይሁን ያልፋል ባለች
ሃገር ሲተራመስ ምህላ በያዘች
ካንተ ክፉ እንዲርቅ ጾማ በጸለየች
ልጆቿን ሰብስባ ይቅር በሉ ባለች
ፍቅር ባስተማረች
ምኗ ቀሎህ ይሆን ባንተ የተደፈረች
            አላወክም እንጂ
            ኦርቶዶክስ መሆን የሃይማኖት ጥጉ
            ለእምነቱ መሞት ነው ወግ እና ማረጉ
የአቡነ ጴጥሮስ የእየሱስ ልጆች ነን
በሞት ውስጥ ነው ትንሳኤን ያገኘን
           ስለዚህ አንፈራም እመነን አንተ ሰው
           ረጋ በል ሰከን ሞትክን አታርክሰው።

ሀሳብ መስጫ
👇👇👇👇
👉@ABUNE05👈
👆👆👆👆
#ሼር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
❤️https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
❤️https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
❤️https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👇👇👇👆👆
♻️#ሼር ማረግ እንዳረሱ join
🖊
ዙሪያዬን ቆሻሻ ~ ተከምሯል መሰል
ጭራሽ ዝንቦች በዙ ~ እሽ ስል እሽ ስል

በቃ እሽታው ይቅር ~ ለእጄ ጭራ ልግዛ
እሽ ማለቴ ነው ~ ስቃዬን ያበዛ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
( አምላክ ተፈሪ )
" ወይ ዘንድሮ" አለ ኤፍሬም!
(ርዕሱ ነው)
🖊
ያ ነገረኛ ወንዝ ~ ወደ ላይ ፈሰሰ
ያምናውን ስንወቅስ ~ የዘንድሮው ባሰ።

እንደ ልውስ ተልባ ~ መላጋ የሆነ ቀን
ፍርዱን ሳይጀመር ~ ምህረቱ ናፈቀን።

ወዴት ነው ችሎቱ ~ ኧረ የት ነው ዳኛው?
እረፍት አለው ቤቱ ~ ከዚህ እስከወዲያኛው።

https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat

( አምላክ ተፈሪ)
kale😘😘 ድኮር
ቤታችሁን ድምቅ ፍክት የሚያደርግ የበአልን አዲስነት ስሜት የሚፈጥር ዉብ መጋረጃ የኮንፈርት ማስገቢያ ያለዉ  ቆንጆ እቃ አለን
ለማየት ዝግጁ ሁኑ በርግጠኝነት ትወዱታላችሁ ቤትወን ማስዋብ ይፈልጋሉ እንግዳውስ ከእናንተ የሚጠበቀው በዚህ ስልክ መደወል ብቻ ነው
ሀሳብ ካላችሁ 👉 @ABUNE05
👇👇👇👇👇
👉 ቃል ድኮር 👈
👉0919989498👈
👉0972340806👈
👆👆👆👆👆
ቤተሰብ ለመሆን👇👇👇👇👇 https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
💙​​የድሀ ፍቅር💙


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በኤፍ ማን የ ቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛

             🖤 ክፍል 1🖤


      ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግሁት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ  ነው አባቴን አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም እንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል,ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች ,
   
        እናቴ ያገኝችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ  መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች ,
  
         በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው  ከትምህርት ቤት እምደተመለስክ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ,.
  
     በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ,
   
       እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሀብታሞች,የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር  ክንፍ ብለናል,
       
       የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት  በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን,ሁለት ወር ክረምትን ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው .
 
        ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዬ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈልግም  እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር  ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ,.......


✎ ክፍል ሁለት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
♻️#ሼር ማረግ እንዳረሱ join
💙​​የድሀ ፍቅር💙


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በኤፍ ማን የ ቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛

             🖤 ክፍል 2🖤

    ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት ተጀመረ የማትሪክም ውጤት መጣ .በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ነበር ያለፍኩት .ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን ስትስማ የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ .,ሜላትም አልፋለች በከፈተኛ ውጤት ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ በልቤ!!

   ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት እናቴ ጋ ሄድን እናቴ ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አለች!!የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው ወረዱ እኔም ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን ,"እናቴ ገና አኮራሻለው"አልኳት በጆሮዋ የደስታ እንባ እየተናነቀኝ,.

    ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ እንባዋ ይወርድ ነበር ,እኔና እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን ሰምቷል ብላ ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች ,ናቲ ,"አይገርምህም እኔም እንዳንተ ጅግና ነው የምሆነው"ብሎ መጥቶ ተጠመጠመብኝ .,ጎበዝ እንደዚህ አስብ እሽ ብዬው መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ,.

   ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን አላውቅም.ወደ ኪሷ ገብታ 20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ አለችኝ እሽ አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት.,

   ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል አለችኝ መሬት መሬት እያየች .እኔ አሁን እቤት ስገባ ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን ይሄን ያክል ፍቅር ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች,.እኛ ቤት ንፁህ ፍቅር እንዳለ አውቃለው የሷን ስትነግረኝ ግን ግራ ገባኝ.,ብቻ በፍረሀት ለምን?አልኳት .እ!አለች,.እኛ ቤት ማንም ስለምይንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት የአባቴ ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት,.

    አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ ለማንኛውም እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣ እሷን ታክሲ አስይዜ ቻው ተባብለን ተለያየን,.

     ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ ፍቅር የለውም ,ለነገሩ ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የነሱ ቤተሰብ በሆንኩ.,!አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ ነው ::እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ .,እቤት ስደርስ እናቴ ብና አቀራርባ ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ አለኝ ,"እናቴ እወድሻለው"ብዬ ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ.,
 
    እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል,በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም ሰነገጥኩ እኔ ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት,ሜላት ግን በቃ እሽ ብላ ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች.እናቴ ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት  ፈዝዤ ቀረሁ..........



✎ ክፍል ሶስት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

ሐሳብ መስጫ👉
@ABUNE05

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


♻️#ሼር ማረግ እንዳረሱ join
💙​​የድሀ ፍቅር💙


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በኤፍ ማን የቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛

             🖤 ክፍል 3🖤

እናቴ በክረምት ወራት ሰርታ ያጠራቀመችውን ብር
ሰብስባ
ዩኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ
.ሜላት ቀድማ ዩኒፎርም አሰፍታ አመጣችልኝ
ደነገጥሁ ለምን
ገዛሽ ?እኔ እንድትረጂኝ አልፈልግም::አልኳት
ተቆጥቼ .ሜላትም ፊቷን አዙራ ከቤት
ወጣች .ስቆጣ ሰምታኝ
የማታውቀው እናቴ ደነገጠች.እኔም ሜላትን
ከመከተል ይልቅ
ፈዝዤ ቀረሁ,....
ድንገት ታናሽ ወንድሜ ገፍትሮኝ ወደ ውጪ ሲሮጥ
ብንን
እንደማለት አልኩ .እንደዛው
እንደቆምኩ ብዙም ሳልቆይ ታናሼ ምን እንዳላት
ባላውቅም
ሜላትን ይዟት መጣ .እስኪ ዞር
በል እንግባበት,ብሎኝ ይዟት ገብቶ ያለችው
መቀመጫ የኔ
የበሰበሰች ፈራሽ ላይ ተቀመጭ
አላት,.
እኔ አሁንም ፈዝዣለው እማዬ ቡና አፍይ እስኪ
አላት እናቴ እሽ
ብላ ተፍ ተፍ ማለት
ጀመረች.አቦ አትቁምብና ና ተቀመጥ!!አለኝ እሽ
ብዬ ሜላት ስር
ቁጭ አልኩ ለማየት
ፈራኃት .እንዳቀረቀርኩ ይቅርታ አድርጊልኝ ሜላት
አጥፍቻለው
አልኳት ,!አይ ችግር
የለውም !!አለችኝ ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ አየኃት
.እውነትሽን
ነው አልኳት አዎ
አልችኝ,.እጆቿን ያዝ አድርጌ ሜላትዬ እውድሻለው
አፈቅርሻለው
ግን በገንዘብ እንድትረጂኝ
ሳይሆን ንፁህ ፍቅርሽን ነው የምፈልገው አልኳት
አይናይኗን
እያየሁ.
እየውልህ የኔ ውብ እኔ እየረዳሁህ አይደለም
ማደርግ
ስለፈለግሁ እንጂ ደግሞ ካንተና
ከእናንተ ቤተሰብ የማገኘው ፍቅር ከሺ ሚልዮን
ብር በላይ
ደስታን ይሰጣል .አትበሳጭብኝ
ይቅርታ እሽ አለችኝ .,ታናሽ ወንድሜ ጣልቃ
በመግባት እድሜ
ለኔ መለስኩልህ ፈዛዛ ይኸኔ
እቤቷ ደርሳ ነበር አለኝ ተሳሳቅን ቡና ተፈላ ቤት
ያፈራውን
ቀማመስን በቃ ደስተኛ ሆነን
አመሽን በጣም ማምሽት ሰለማይፈቀድ ሜላቴንም
ወደ ቤቷ
ሸኘኃት.....
እኔም እሷን ሽኝቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ወደ ቤቴ
ተመለስኩ..እናቴም ዩኒፎርም
ስለተገዛላት ያለው ብር ለደብተርና እስክርቢቶ
ይሆናል ተመስገን
አለች.ዞር ብላ አንተ ከዚህ
በኃላ እንደዚህ ጮኸህ ስትቆጣ መስማት
አልፈልግም
አለችኝ.እሽ አልኳት,.
ቀናቶች ሄደው የትምህርት መሳሪያዎቼን አሟልቼ
ትምህርቴን
ጀመርኩ ሜላቴም እኩል
ጅመርን አንድ ክፍል መሆን ፈልገን ነበር ግን
አልተሳካም
መምህሮቹ አልፈቅድ አሉ ይሁን
ብለን በክፍል ተለያየን ግን እርፍት ሲሆን እኔ
ቀድሜ ቀወጣሁ
እነሱ ክፍል በር ላይ
እጠብቃታለው እሷም ከቀደመች እንደዛው .ደስ
የሚለው
ሁላችንም ዩኒፎርም ስለምንለብስ
የድሀ የሀብታም ልጅ ብሎ ነገር የለም .የሚበላ
ስንፈልግ ሜላት
ብር ሰጥታኝ እኔ
እከፍላለው .,
እኔና ሜላት ተለያይተን አናውቅም እኔም ከእሷ
ውጪ እሷም
ከእኔ ውጪ ትምህርት ቤት
ውስጥ ጏደኛ የለንም.ተማሪዎች ሁሉ ይቀኑብናል
.እሷ ቆንጆ
ነገር ስለሆነች ሌሎች
ይመኟታል እሷ ግን ከኔ ውጪ ማንንም
አትፈልግም.,እኔም
እንደዛው.
ከትምህርት ቤት ውጪ እኔ እናቴን ለማገዝ ስራ
ስለምሰራ
ብዙም አንገናኝም ጥናት
ካለብን ግን አብረን እናጠናለን ጥናት ስንጨርስ
ወክ አድርገን
እንለያያለን እናቴም
አብሮነታችን በጣም አስደስቷታል ደስተኛ ነች
እኔም እንደዛው
.አንድ ቀን ፈተና ስለደረሰ
ስናጠና ቆይተን ልሸኛት ወጥቼ ሻይ ቡና እንበል
ብላኝ ካፌ
ውስጥ ተቀምጠን ያላሰብነው
ሰው ድንገት መጣብን..........................
ይቀጥላል ...


✎ ክፍል አራት ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

ሐሳብ አስተያየት ላላችሁ 👉 @ABUNE05

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
 https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

♻️#ሼር ማረግ እንዳረሱ join
💙​​የድሀ ፍቅር💙


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በኤፍ ማን የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛

             🖤 ክፍል 4🖤

እኔና ሜላት ፈተና ስለደረሰ ሰናጠና አምሽተን
ልሸኛት
እንደወጣሁ ካፌ ሻይ ብና እንበል
ብላኝ ገብተን ቁጭ እንዳልን ድንገት የሜላት አባት
ከፊት
ለፊታችን ድቅን አሉብን ... እኔ ሰለማላውቃቸው
ዝም አልኩ
ሜላት ተርበተበተች ማ..ማነዉ አልኳት ? በጣቶቿ
አፏን
ተመተመች ዝም በል ለማለት ነበር...
ሜላት ከመቀመጫዋ ተነስታ አ...አባቢ አለች
እየተርበተበተች
... አባቢ ስትል ቀልቤ ግፍፍ አለ ..
ደግነቱ ዩኒፎርሜን ከላይ ያለውን አላወለቅሁትም
ነበር። የየየክፍሌ ተማሪ ነው ስናጠና ቆይተን ሻይ
ብና
እንበል ብለን ነው አለች እየተርበተበተች...
አባቷም ሰላምታ አይቀድምም ልጄ አሉ ...
ይቅርታ አባቢ ብላ አቅፋ ሳመቻቸው .እኔም
ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላም አልኳቸው.
የሜላት አባት ሰላም ብለውን በጊዜ ግቢ ቻው
ብለውን ሌላ
ወንበር ወደ አለው ጏደኛቸው
ሄዱ .,እኔና ሜላት ደንግጠናል ያዘዝነው
መጥቶልን ቶሎ ቶሎ
ጠጣን አባቷ ቀድመው ሂሳብ
ከፍለውልን ስለነበር ቻው ብለናቸው ተያይዘን
ወጣን.,.
ሜላት ፊቷ ላይ የፍረሀት ስሜት ይነበባል ሜላቴ
ምን ሆንሽ ምን
እያሰብሽ ነው አልኳት።
አባቢ... አለች አባትሽ ምን? ኡሁን እቤት ስገባ
ጭቅጭቁ
አይጣል ነው አለች በፍረሀት። አይቆጡሽም
አስጠኒዬ ነው
በያቸው ባይሆን ሁለተኛ አብረን
እንዳያዬን እንጠነቀቃለን
አልኳት እሽ አልችኝና ግንባሯን ለመጀመርያ ጊዜ
ስሜ ተለየኃት.,
ሜላትን በታክሲ ሽኝቼ እኔ ወክ እያደርግሁ ወደ
ቤት ተመለስኩ
ግን የሜላትዬ ፍርሀት እኔን
አሳሰበኝ አባቷ ይቆጡ ይሆን ብዙ ነገሮችን
አሰብኩ .ምክንያቱም
የሜላት ቤተሰቦች
ሀብታም ስለሆኑ ልጃቸው ደግሞ ከእንደኔ አይነት
መናጢ ድሀ
ጋር የፍቅር ግንኝነት
እንዳላት ቢያውቁ ከባድ ነው የሚሆነው...
አምላኬ አደራህን
ብዬ እቤቴ ገባሁ መንጋት አይቀር ነጋ...
ጠዋት ትምህርት ቤት ቶሎ ሄድኩ በሩ ላይ
ጠበቅኃት እሷም
እንደምጨነቅ ስለገባት
በጠዋት መጣችልኝ ደስ አለኝ ቶሎ ብዬ ምን
ተፈጠረ አልኳት
.,ሰላም በለኝ እንጂ ቅድሚያ
አለችኝ አቅፌ ሳምኳት .ምንም አልተፈጠረም
አባቢ ምንም
አላልኝም አለችኝ በጣም
ተደሰትኩ ለሚቀጥለው እንጠነቀቃለን አልኳትና
ተያይዘን ወደ
ትምህርት ቤቱ ግቢ ገባን,.
እኔና ሜላቴ ፍቅራችንን በድብቅ አድርገን
መዝናናትም ስንፊልግ
ደበቅ ያለ ቦታ እየሄድን
እንዝናናለን .አብዛኛውን ጊዜ ግን እኛ ቤት ነው
የምናሳልፈው.አመቱ አልቆ ተፈትነን ውጤት
መጣ ሁለታችንም አልፈናል ደስ የሚል ነገር
ተመስገን
አልተነጣጠልንም.,
ሁለት ወር ክረምትን ያው እንደተለመደው እኔ
እናቴን በማገዝ
አሳለፍኩ ከሜላትም ጋ አልፎ
አልፎ እቤት እየመጣች ካልሆነም ማታ ማታ እነሱ
ሰፈር
ቤተክርስቲያን ውስጥ
እንገናኛለን..በቃ ደስ በሚል መዋደድና መፈቃቀር
አብረን
ቀጠልን .,
አዲሱ አመት ገብቶ ትምህርት ጀመርን 12ኛ
ክፍልን በጣም
መጠናት እንዳለበት
ስለማምን ብዙ ጊዜያችንን በጥናት ነው
የምናሳልፈው .ሜላትም
ከኔ ጋር ታጠናለች
በርትተን መማር እንዳለብን ሁለታችንም
እናምናለንና .,ስለዚህ
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል
እናጠናለን.
እኔ ስናጠና ስለ ትምህርት ወክ ስናደርግ ስለ ነገ
ተስፋ ነው
የማስበው ወደፊት ምን
ማድርግ እንዳለብኝና ምን መሆን እንደምችል ብዙ
ነገር ሜላትን
እንደማገባት ነው
የማምነው ,.ሁሌም ስለያት ወይ ግንባሯን ወይ
አንገቷ ስር ስሜ
እለያታለው....
አንድ ቀን ማታ ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ሜላት
ፊቷን ሳይ
አኩርፋለች ምነው
ሜላትዬ ምን ሆነሽ ነው አልኳት.,ሳመኝ አለችኝ
አይናይኔን
እያየች ,.እ!! አልኳት ሳመኝኝኝኝ!
አልቸኝ ግንባሯን ሳምኳት ,ኡፍ ብላ ተበሳጨች
,ትዝ ሲለኝ እእ....እ
....... ይቀጥላል...

✎ ክፍል አምስት ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄

ሐሳብ አስተያየት 👉 @ABUNE05

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/fikirnbewubekalat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

♻️#ሼር ማረግ እንዳረሱ join
2024/05/02 19:36:48
Back to Top
HTML Embed Code: