Telegram Web Link
ኢላሂ!
ወንጀል የሚያስምር፤
አዲስ ሕይወት የሚያስጀምር፤
ጠባይ የሚያሳምር፤
የነፍስያና የሸይጣንን ተንኮል መና የሚያስቀር፤
ከመልካሞችና ከተወዳጆችህ ጋር የሚያስተሳስር፤
ከክፉዎች እና ካንተ ጠላቶች የሚያቃቅር፤
ተውበት ለግሰን!
አሚን!
151👍28😍1
ኢላሂ!
የአካል ጥማችንን በውሃ እንዳራስከው የቀልባችንን ድርቀት ደግሞ በኢማን ዝናብ አርጥብልን!
118👍20😢1
የተራዊሕ ህግጋት
(ክፍል አራት)
————————
ተራዊሕ ለሴቶች
ተራዊሕ በጀመዐ መስገድ የተደነገገ መሆኑን ከላይ አስቀድመናል። በጀመዓ የሚሰገድ ሶላት በግል ከሚሰገደው በሃያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል። የጀመዓ ትሩፋት ደግሞ ጾታ ሳይለይ ለወንድም ሆነ ለሴት የተሰጠ ፀጋ ነው።

ነገርግን አሳሳች ፈተናዎች በሚበዙበት ዘመን ሴት መስጂድ ሄዳ ከምትሰግደው ሶላት በቤቷ የምትሰግደው ይበልጣል። ነገርግን ከፈተና በተጠበቀ ሁኔታ ሴትየዋም ለዓመፅ በሚገፋፉ ነገሮች የማትታለል እንደሆነ በታመነበት መልኩ መመላለስ ከቻለች ከመስጂድ ጀመዓ ጋር ሶላት መስገድ ትችላለች።

ይህ በጨዋ ሴት ደንብ ጥብቅ ሆና በሐፍረት በተሞላ ጠባይ እስከሄደች ድረስ ነው። አለባበሷ ሸሪዓን የጠበቀ መሆኑም የግድ ነው። ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ልትፈተን የምትችልበት ስጋት ከሌለ ደግሞ ባል ወይም ወልይዋ (የቤተሰብ ኃላፊዋ) መስጂድ ከመሄድ ባይከለክላት መልካም ነው። መስጂድ በመሄዷ የምታገኛቸው በርካታ ጥቅሞች ስላሉ ይፍቀድላት። በዚያ ላይ የመስጂድ ሶላት ከቤት በተሻለ ቀልብን ይሰበስባል። ስለ ዲኗ የምትማርበት አጋጣሚም ታገኛለች። ከሙስሊሞች ጋር አላህን ትዘክራለች፤ ዱዓም ታደርጋለች። የስብስቡን በረካ ትካፈላለች።

ከዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እንደተዘገበው: ‐ «ሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] የሱብሒን እና የዒሻእ ሶላትን መስጂድ እየሄደች የምትሰግድ [ሚስት] ነበራቸው። እናም «ዑመር እንደማይወዱና ቀናተኛ እንደሆኑ እያወቅሽ ለምን ትወጫለሽ?» በማለት ሰዎች ጠይቋት።
እርሷም: ‐ «እሱ እኔን ከመከልከል ምን ያቅበዋል? [ለምን ራሱ አይከለክለኝም?]» በማለት መለሰች።
ጠያቂዎቹም: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ቃል ያቅበዋል። እርሳቸው እንዲህ ብለዋል: ‐ «የአላህ ሴት ባርያዎችን ከአላህ መስጂድ አትከልክሉ!»
[ሙስሊም ዘግበውታል]

ከኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁማ] እንደተዘገበው ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ለሴቶቻችሁ በሌሊትም [ቢሆን] ወደ መስጂድ መሄድ ፍቀዱላቸው።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ይሁንና ባል ወይም የቤተሰብ ኃላፊ (ወልይ) መስጂድ ከመሄድ የመከልከሉን ውሳኔ የግድ ነው ብሎ ከወሰደው ምእመኗ ሴት ለውሳኔው ራሷን ተገዥ ልታደርግ ይገባል። በዚህ ምክንያት በቤተሰብ መካከል ቅራኔ መፍጠር አይገባትም። የቤተሰብን ሰላም ማስጠበቅ የጀመዓን ትሩፋት ከማግኘት በላይ ተቀዳሚና አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

ኢማም ነወዊይ [ረዲያላሁ ዐንሁ] አል‐መጅሙዕ በተሰኘው እውቅ መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐

«ሚስት መስጂድ ለመሄድ ባሏን ካስፈቀደችው ቢፈቅድላት ይወደዳል። ነገርግን በመዝሀባችን (ሻፊዒያ) መሠረት ቢከለክላት ሐራም አይሆንበትም። ኢማም አል‐በይሀቂይ እንደሚሉት «ይህ የአብዝሃኞቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው።» ስለዚህ «የአላህ ሴት ባርያዎችን ከአላህ መስጂድ አትከልክሉ!» በማለት የተዘገበው የሐዲስ ክልከላ ቀለል ያለ መጠላት (ከራሃተ ተንዚህ) እንጂ እርምነትን አያስይዝም ተብሎ ይመለሳል። ምክንያቱም በማንኛውም መልኩ ባል ሚስቱን በቤት እንድትቆይ የማድረግ መብቱ ስላለው ግዴታ የሆነባትን መብት ትርፍ ለሆነ [የዒባዳ] ትሩፋት ብላ ልትተወው አይቻልም።»

በተለይም አሁን ባለንበት የፈተና ጊዜ በመስጂድ ሰበብ የሚሰሩ መጥፎ ነገሮች እንዳሉ እየሰማን ባለንበት ሴቶች መስጂድ እንዲሄዱ የፈቀደ ባል ወይም ወልይ ለአሳሳች ፊትናዎች እንዳይጋለጡ የመከታተል ግዴታ እንዳለበት ሊታወስ ይገባል!

ተራዊሕ መተው
የተራዊሕ ሶላት ሱና ነው። ፈርድ አይደለም። ስለዚህ አንድ ሰው ያለ ምክንያት ቢተወውም ወንጀለኛ አይባለም። የመስገድ ፍላጎት ኖሮት በአሳማኝ ምክንያት መስገድ የተሳነው ሰው ደግሞ እንደ ሰገደ ተደርጎ ይጻፍለታል፤ ምንዳውንም አያጣም።

ነገርግን መስጂድ ተገኝቶ በጀመዓ መስገድ ያልቻለ ሰው ባለበት ስፍራ ለብቻውም ቢሆን ሙሉ ተራዊሕ ወይም የቻለውን ያህል የሌሊት ሶላት መስገድ ይወደድለታል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የተናገሩትን ትሩፋትም ያገኛል ብለን እንከጅላለን: ‐
«ያመነ እና ምንዳውንም ከአላህ ብቻ ያሰበ ሲሆን ረመዳንን [በሌሊት ሶላት] የቆመ ሰው ያስቀደመውን ኃጢኣት ይማራል።» ቡኻሪ ዘግበውታል።

በማንኛውም ሁኔታ በሌሊት መስገድ ከተሳነው ደግሞ በማንኛውም ጊዜ ቀዷ ቢያወጣው ይወደድለታል። ነገርግን የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የሌሊት ቁርኣን እና ሶላታቸው ሲያመልጣቸው ያደርጉት እንደነበረው ከንጋት በኋላ ፀሀይ ከፍ ስትል ጀምሮ እስከ ዙሁር ሶላት አቅራቢያ ባለው ጊዜ ቀዷውን ቢያደርገው መልካም ነው። በሐዲስ እንደተረጋገጠውም «በሌሊት እንደሰራው ይቆጠርለታል።»

በተራዊሕ እና በተሀጁድ መሀል
ተራዊሕ ከቂያሙል‐ለይል ጋር ተመሳሳይነት አለው። ሁለቱም ሱናዎች ናቸው። ሁለቱም ከዒሻእ በኋላ እስከ ፈጅር ወቅት ባለው ጊዜ የሚሰገዱ ናቸው።

ነገርግን በሁለቱ መካከል የስፋት እና የጥበት ልዩነት አለ። ተራዊሕ የቂያሙል‐ለይል አንዱ አይነት ነው። ተራዊሕ በረመዳን በመጀመሪያው የሌሊት ክፍል የሚሰገድ ሲሆን በሌሊቱ በማንኛውም ክፍል የሚሰገድ ሶላት ደግሞ ቂያሙል‐ለይል ይባላል። በሌላ አባባል ተራዊሕ ቂያሙል‐ለይል ሲሆን በተቃራኒው ቂያም ሁሉ ተራዊሕ አይደለም።

በእርግጥም ተራዊሕ ከስድ የሌሊት ሶላት የሚለይባቸው ሌሎች ገደቦች አሉት። ተራዊሕ በረመዳን ወር በመጀመሪያው የሌሊት ጊዜ የሚሰገድ ነው። በረመዳን ብቻ የሚሰገድ ሶላት ነው። ቂያም‐ለይል ግን በማንኛውም የዓመቱ ወራት ይሰገዳል።

ተራዊሕን በጀመዐ መስገድ ሱና ነው። ስድ የሆነው ቂያም‐ለይልን ግን በጀመዓ መስገድ ይወደዳል አንልም።

ሙሉ ተራዊሕ ሃያ ረከዓ ነው። ኢብኑ አቢ ሸይባ ኢብኑ ዐባስን በመጥቀስ እንደዘገቡት: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በረመዳን ሃያ ረከዓ እና ዊትር ይሰግዱ ነበር።»

ተራዊሕን ከሁለት ረከዓ በላይ በአንድ ተስሊም መስገድ አይፈቀድም። አራቱን በአንድ ቢሰግድ ተራዊሑ ይበላሻል። የሌሊት ሶላትን (ቂያም‐ለይል) ግን ሁለት፣ አራት ወይም ሌላ እያደረገ መስገድ ይፈቀዳል።

ቂያም‐ለይልን በቤቱ ለብቻው መስገድ ይመረጣል። ተራዊሕ ግን በመስጂድ በጀመዐ መስገድ ይወደዳል።

ተሀጁድ የሚባለው ሶላት ደግሞ ተኝቶ ከተነሳ በኋላ የሚሰገድ የሌሊት ሶላት ማለት ነው። ከተራዊሕም ሆነ ከስድ የሌሊት ሶላት የሚለየው ከመኝታ በኋላ በመሰገዱ ብቻ ነው። ተሀጁድ ተራዊሕ እስካልሆነ ድረስ ለብቻ የሚሰገድ ሶላት ነው!
አላሁ አዕለም!
39👍14
«በረመዳን የሚከሰት ወንጀል ምንጩ የሰውየው ነፍስ ናት። ሸይጧን አይደለም። ረመዳን የሸይጧን ጉትጎታ ውጤት የሆነውን ወንጀላችንን የነፍሳችን ውጤት ከሆነው ወንጀል የምንለይበት አጋጣሚ ነው።

ረመዳን የወንጀሎቻችን ዓይነትና ባህሪም መለየት የምንችልበት እድል ነው። የምንወድቅባቸው ኃጢኣቶቻችን ተመሳሳይነት ያላቸው ከሆኑ ዋናው የኃጢኣቱ ቀስቃሽ ነፍስ ሆና ቨይጧን ተከታይ ነው። የወንጀሎቻችን በር የተለያየ እና ዘርፈ ብዙ ከሆነ ደግሞ ሸይጧን ዋናው ቆስቋሽ ሆኖ ነፍስ ተከታዩ ናት። ምክንያቱም ሰይጣን በማንኛውም በር ይሁን የሰውን ልጅ ለማጥፋት አቅዶ ይንቀሳቀሳል እንጂ ሰውየውን የሚጥልበት የኃጢኣት አይነት አያሳስበውም።

ነፍስ ግን ወንጀል ውስጥ የምትገባው ስሜቷን ለማርካት ነው። ስለዚህ በውዴታው የተፈተነችበትን እና እንደ ሱስ የወደቀችበትን ስሜት ለማሳካት ስትል በውስን ኃጢኣቶች ላይ ችክ ትላለች እንጂ ሁሉም ወንጀል ላይ አትዘባርቅም!»
ኢማም ሸዕራዊ [ረሒመሁላህ]
70👍5😢4🤔1
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ አሉ: ‐ «አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጠየቀ: ‐ «የአላህ ነብይ ሆይ! [ﷺ] ከሰዎች ሁሉ ከፍ ያለ ብልጥ ሰው ማን ነው?»

እርሳቸውም እንዲህ መለሱ: ‐ «አብዝተው ሞትን የሚያስታውሱ እና አብዝተው የሚዘጋጁለት። እነዚህ ብልጦች ናቸው። የዱንያን ክብር እና የአኺራን ሽልማት የወሰዱ ናቸው።»
ጦበራኒይ ዘግበውታል።
👍33😢166
የዘካ ፊቅህ በሻፊዒያ መዝሀብ
[ክፍል አንድ]
========
የዘካ ድንጋጌ መነሻ
[መንደርደሪያ]
:
ኢስላም ምሉዕ እና ሁለንተናዊ ስርዐት ነው። አላህ ለሰው ልጅ ክብርን ለማጎናፀፍ የደነገገው የህይወት መንገድ ነው። ሰው በህይወት ዘመኑ የሚያሳልፈው የምድር ህይወቱን በደስታ ያሳልፍ ዘንድ የሚያስፈልገው የመርህ ጥርቅም ነው።

የሰው ልጅ ደስታ የተሟላ የሚሆነው ደግሞ ከሁሉም አስቀድሞ ማንነቱን ሲያውቅ ነው። አንድና ብቸኛ የሆነ፣ የምሉእ ባህሪያት ባለቤት የሆነው ጌታ ባርያ መሆኑን ሲረዳ ነው። ከዚያ በመቀጠል የሰው ልጅን ደስታ ከሚያሟሉ፣ ለአላህ ብቻ ተገዥ እንዲሆን ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ የተከበረ ህይወት እንዲኖረው የሚያደርግ የኑሮ መመቻቸት ዋናው ነው።… 

ሰው የተከበረ ህይወት ይኖረው ዘንድ መረዳዳት እና መተጋገዝን የተላበሰ የህይወት ከባቢ ይፈልጋል። መከባበር የሰፈነበት መሰረት ላይ የተገነባ መኖሪያ ያሻዋል። በደልም ሆነ ብዝበዛ የሌለበት የህብረት እንቅስቃሴ ይፈልጋል። የሰው ልጅ ለማዳና ማህበራዊ ፍጡር ነው!…

ኢስላም ደግሞ ‐ከማናቸውም ሰው ሰራሽ ስርዐቶች በተለየ‐ ለሰው ልጅ ህይወት መሰረታዊ አስፈልጎቶችን የሚያረጋግጥ ብቸኛ ስርዐት ነው። ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር ይጣጣማል። የሰውን ልጅ ልዩ ባህሪያት ያከብራል። ዓቅሙንም ያሳድጋል።…

ምሉእ በሆነ ስርአት ማዕቀፍ ውስጥ የሰውን አስፈልጎት ለማሟላት ይተጋል። በሰው ልብ ውስጥ ያለውን እምነት [ዐቂዳ] ከማረቅ አንስቶ፣ ስለ ህይወት እና ስለሚኖርበት ከባቢ [ዩኒቨርስ] ያለውን ግንዛቤ ያስተካክላል። ከዚያም ስነምግባሩን ያሳምርለታል። ከሚኖርበት ከባቢ ጋር የሚያስተሳስረውን ግብረገብ የሚመሩ ደንቦችን ይደነግጋል። ጠባዩን የሚያስተዳድሩ ህጎችን ያረቅቃል። በሙሉ የመንፈስ ዝግጅትና ፈቃደኝነት በእነዚህ ህጎች ይተዳደር ዘንድ የመንፈስ ቅናቱን እና [ኢማኑን] የሚያጠናክሩ የስሜት ምግቦችንም ያደራጃል።…

ዘካ ከነዚህ በርካታ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች እና ደንቦች መካከል አንዱ ነው። የደስታን ትርጓሜና ጭብጥ የሚያሟሉ መስፈርቶችን በጠበቀ ሁኔታ፣ በህብረት የመኖር ጠባይ ላለው ሰብዐዊ ስብስብ የሚመጥን፣ የማህበረ‐ሰብዕን ጥቅም ታሳቢ አድርጎ፣ በህይወት ውስጥ የግል ማንነቱን እና ክብሩን ማስጠበቅ የሚሻውን ግለ‐ሰብን ሳይዘነጋ… ለሁሉም ሰው ደስታና ስኬት የሚበጁ  በርካታ ህግጋትን አርቅቋል። ዘካ ከነዚህ ህጎች አንዱ ነው!

የዘካ ዓላማ ‐በጥቅሉ‐ የግለሰብ ገቢና ብልፅግና በግለሰቦች መካከል ሊኖር የሚገባ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ላይ ድንበር በማይጥስበት መልኩ መቆጣጠር ማስቻል ነው። የግለሰብ ሀብት ለሁሉም ሰዎች መሰረታዊ መብት የሆነውን ራስን የመቻልና በራስ የመብቃቃት መብትን ባስከበረ መልኩ የተቃኘ እንዲሆን ዘካ ተደንግጓል።

ይህንን ከተከታዩ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ሐዲስ ማግኘት እንችላለን። ሰይዲና ሙዐዝን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ለየመን ሰዎች መልክተኛ አድርገው በላኳቸው ጊዜ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ ጥራቸው።… ይህንን ከታዘዙህ አላህ ከኃብታሞቻቸው ተወስዶ ወደ ድኾቻቸው የሚመለስ ምፅዋት ግዴታ አድርጎ እንደመደበባቸው አሳውቃቸው።» ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

ሸሪዐው እንዲህ ነው። ግለሠብ ራሱን ችሎ በነፍሱ ተብቃቅቶ ይኖር ዘንድ ለግል ልፋቱ፣ በእጁ ላይ ላለው ዓቅም እና በመንገዱ ለሚያገኛቸው እድሎች ብቻ አይተውም።…

በተቃራኒው የተቸገሩ ወንድሞቹን ለመርዳት እጁን ይዘረጋ ዘንድ ለህሊናው እና ለግል ተነሳሽነቱ ብቻ አይተውም።… 

ይልቁንስ ግለሰብ ከልፋቱና ከተነሳሽነቱ በተጨማሪ የተከበረ ህይወት ይኖረው ዘንድ የሚደግፈው ምርኩዝ፣ የወገኑን እገዛ እንዲያገኝ የሚያስችሉ ስርዐቶችን ያሰፍናል።

የሰው ልጅ ህሊና በራስ ወዳድነት በሽታ እንዳይጠቃ፣ ግፈኝነትን ተቀልቦ በበደል እንዳይደልብ፣ ለአውሬያዊ ስሜት እንዳይገዛ የሚያደርጉ መርሆዎችን ያነብራል።

ግለሰብ ከሌሎች ወንድሞቹ  ጋር የሚኖረውን ትስስር በፍትህ ገመድ የተጣመረ እንዲሆን ለማድረግ ይተጋል።

ስለዘካ ስንማር ይህ ጭብጥ ፍንትው ብሎ ይታየናል። ዘካ የሚሰበሰብበት መንገድ፣ የሚከፋፈልበት ሁኔታ ወዘተ. ከዘካ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎች ኢስላም በሦስተኛው ማዕዘኑ [ዘካ] የዘረጋው ስርዐት እጅግ የተለየና አምሳያ የሌለው እንደሆነ እንድንመሰክር ያደርጋል።
:
እንግዲህ ወዳጆች! ለመንደርደር ያክል ይህንን ካልን ዘካ ምንድን ነው? ከሚለው ጀምረን ዝርዝር ህግጋቱን ከዚህ በኋላ በተከታታይ እናቀርባለን።  በአፈፃፀሙ ላይ የሚኖሯችሁን የብዙዎቻችሁን ጥያቄዎች እየመለስን እንቀጥላለን፤ ኢንሻአላህ። አላህ ተውፊቁን ይስጠን!
👍142
እርሷን ማግኘት ከሻህ ቀድመህ አቅድ!
በጊዜ ተሰናዳ!
መታገያህን አዘጋጅ፣ ቀልብህንም ሆነ አካልህን አሰልጥን! በተንቀቅ ጠብቃት!
አላህ ሆይ ለይለቱል‐ቀድርን ግጠመን!
94👍4
Forwarded from Tofik Bahiru
የዘካ ፊቅህ በሻፊዒያ መዝሀብ
[ክፍል ሁለት]
=========
🔸 የ‌ቃ‌ል‌ ት‌ር‌ጓ‌ሜ‌:
"ዘካ(ት)" የሚለው ቃል በመነሻ ትርጉሙ ጨመረ፣ በለፀገ፣ በዛ ማለት ነው። አዝመራው በለፀገ፣ በዛ ይባላል። ንግዱ በረከተ፣ በለፀገ፣ አደገ [ዘካ] ይባላል።

"ዘካ" አሁንም በቋንቋ ውስጥ ንፅህናን በሚጠቁም ትርጉም ተጠቅሷል። ተከታዩ የአላህ ቃል ከዚህ መሀል አንዱ ነው: ‐
{قد أفلح من زكاها} 
«(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡»

ከቋንቋ ትርጉም በመነሳት በሸሪዓው አገባብ «ከተወሰኑ የገንዘብ ዓይነቶች የሚወሰድ፣ ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ፣ ወደፊት የምናብራራቸው መስፈርቶች በተሟሉበት ሁኔታ ግዴታ የሚሆን የተወሰነ የገንዘብ መጠን ነው።»

ይህ ገንዘብ ዘካ የተባለው የሰውየው መነሻ ገንዘብ በሚወጣው የዘካ ገንዘብ በረከት እና በዘካ ተቀባዩ ዱዓ ምክንያት ስለሚያድግ፣ ስለሚበለፅግ ነው። ዘካ አውጪው በእጁ የሚቀረው ገንዘቡ ከተለያዩ ፍቁድነታቸው የሚያደናግር [ሹቡሃ] ከሆኑ ነገሮች ስለሚፀዳለትና በገንዘቡ ላይ ከሚንጠለጠሉ ሐቆችን ስለሚያላቅቅበት ነው።

🔸 መ‌ች‌ ተ‌ደ‌ነ‌ገ‌ገ‌?
በትክክለኛው የዐሊሞች ሃሳብ መሰረት ዘካ በግዴታነት የተደነገገው ከነቢዩ [ﷺ] ሂጅራ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ላይ ነው።

🔸 ብ‌ይ‌ኑ‌ እ‌ና‌ መ‌ረ‌ጃ‌ዎ‌ቹ‌:

ዘካ ከአምስቱ የኢስላም ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው። ድንጉግነቱን የሚያመለክቱ፣ በአፅንዖት የተረጋገጡ እና ግልፅ መልእክት ያላቸው መረጃዎች አሉ። በመሆኑም የዘካ ድንጋጌ በግልፅ ከሚታወቁና ዓዋቂውም ሆነ ማይሙ በእኩል ከሚያውቃቸው "መዕሉም ሚነድ‐ዲን ቢድ‐ዶሩራ" ከሚሰኙት ህጎች መካከል አንዱ ሊሆን በቅቷል። ስለዚህ የዘካን ድንጉግነት የካደ ሰው ከኢስላም ይወጣል!

ይህንን እውነታ ከሚያስረዲ በርካታ የቁርኣን ማስረጃዎች መካከል አንዱ እንዲህ ይጠቀሳል: ‐
[وأقيموا الصلاة وآتوا الزكاة واركعوا مع الراكعين]
«ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም (ግዴታ ምጽዋትን) ስጡ፡፡ (ለጌታችሁ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ፡፡» አል‐በቀራ ፥ 43

በቁርኣን ውስጥ በዘካ የሚያዝዙ አንቀጾች በርካታ ናቸው። በቁርኣን ሰላሳ ሁለት ስፍራዎች ላይ ዘካ ተጠቅሷል።

የሐዲስ መረጃዎችም በርካታ ናቸው። ከእነርሱ መካከል: ‐
ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ኢስላም በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል: ‐ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አለመኖሩን በመመስከር፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ በመስገድ፤ ዘካ በመስጠት፤ ሐጅ በማድረግ እና ረመዳንን በመጾም።» ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ ላይ ሰይዲና ሙዐዝን ነቢዩ [ﷺ] ወደ የመን ሲልኩ የተናገሩት ቃል እንዲህ ተጠቅሷል: ‐ «…ለዚህም ከታዘዙህ ከኃብታሞቻቸው ተወስዶ ወደ ድኾቻቸው የሚመለስ ምፅዋት አላህ በግዴታነት እንደደነገገባቸው አሳውቃቸው።»

በዘካ ድንጋጌ ዙርያ የተዘገቡ የሐዲስ ጥቅሶች እጅግ በርካታ እና በቁጥር የማያልቁ ናቸው።

🔸ዘ‌ካ‌ የ‌ከ‌ለ‌ከ‌ለ‌ ሰ‌ው‌ ብ‌ይ‌ን‌:
⒈ የዘካን ግዴታነት በማስተባበል ዘካ የከለከለ: ‐
ዘካ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል አንዱ መሆኑን አሳውቀናል። እንደውም ከሁለቱ ሸሀዳዎች እና ከሶላት በመቀጠል ሶስተኛው የኢስላም ማዕዘን ዘካ ነው። ስለዚህ የዘካን ግዴታነት የሚክድ ሰው ከኢስላም እንደሚባረር ልሂቃን ይስማማሉ። ተውበት አድርጎ ወደ ኢስላም እስካልተመለሰ ደሙ የመከነ፣ በግድያ የሚቀጣ ከሀዲ ነው።

ምክንያቱም ዘካ ግዴታ መሆኑ በቀጥታ የሚታወቅ፣ ማስረጃ የማይሻ፣ የማያሻማ እና ከሊቅ እስከ ደቂቅ በእኩል የሚያውቀው ድንጋጌ ነው። "መዕሉም ሚነድ‐ዲን ቢድ‐ዶሩራ" ነው።

ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ኢማም አል‐ኸጧቢን ዋቢ በማድረግ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በዚህ ዘመን የዘካን ግዴታነት የካደ ሰው ከኢስላም የተባረረ ከሀዲ እንደሚሆን ሙስሊሞች ይስማማሉ።»… «ዘካ ግዴታ መሆኑ በሙስሊሞች መካከል በስፋት የተሰራጨ መረጃ ነው። ልሂቁም ተርታውም ይህ መረጃ ደርሶታል። ዓዋቂም ሆነ መሀይም አውቆታል። ማንም ሰው ግዳጅነቷን ለማስተባበል የሚያስችለው መነሻ ስለማያገኝ ግዴታነቱን ለማስተባበል የሚያበቃ ሰበብ አይኖረውም። ሙስሊሙ በአንድ ላይ የተስማማቸው ኃይማኖታዊ ድንጋጌዎችን ያስተባበለ ሁሉ ብይኑ ይህ ነው። እውቀቱ የተንሰራፋ ነገር ከሆነ ‐ለምሳሌ: ‐ እንደ አምስቱ ሶላቶች፣ የረመዳንን ወር መጾም፣ ከጀናባ መታጠብ፣ የዝሙት እርምነት፣ ለጋብቻ እርም የሆኑ ዘመዶችን መጋባት እና መሰል ድንጋጌዎችን‐ መካድ [ከኢስላም ያስወጣል።]» "ሸርሕ ሙስሊም"፥ ነወዊይ፥ ቅፅ 1፥ ገፅ 205

ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ዐስቀላኒይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ:‐ «የዘካን ድንጉግነት ከመሰረቱ መካድ ከኢስላም ያስወጣል።» ፈትሑል‐ባሪ፥ አል‐ዐስቀላኒይ፥ ቅፅ 3፥ ገፅ 262

⒉ ዘካን በስስት ተሸንፎ የከለከለ ሰው: ‐

ዘካ ድንጉግ መሆኑን፣ ግዴታ እና የዲን አካል መሆኑን ከማመኑ ጋር ዘካውን የከለከለ ሰው ደግሞ አመፀኛ፣ ኃጢኣተኛ ነው። በአኺራ ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል። አላህ እንዲህ ይላል:‐

[والذين يكنزون الذهب والفضة ولا ينفقونها في سبيل الله فبشرهم بعذاب أليم. يوم يحمى عليها في نار جهنم فتكوى بها جباههم وجنوبهم وظهورهم هذا ما كنزتم لأنفسكم فذوقوا ما كنتم تكنزون.]

«እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው፡፡
በርሷ ላይ በገሀነም እሳት ውስጥ በሚጋልባትና ግንባሮቻቸውም፣ ጎኖቻቸውም፣ ጀርባዎቻቸውም በርሷ በሚተኮሱ ቀን (አሳማሚ በኾነ ቅጣት አብስራቸው)፡፡ ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው፡፡ ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡» አል‐ተውባ: 34 እና 35

በሰይዲና ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ሐዲስ ላይ ‐ከራሳቸው ወይም ከፍ አድርገው ወደ አላህ መልክተኛ [ﷺ] አስጠግተው‐ ተከታዩ ቃል ተገኝቷል: ‐
«ዘካውን የሰጠህለት [ገንዘብ] ሁሉ ድልብ አይደለም። ዘካውን ያልከፈልክበት ሁሉ [ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ መሰረት] ድልብ ነው።»

ቡኻሪይ ሰይዲና አቡሁረይራን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አላህ ገንዘብ ሰጥቶት ዘካውን ያልሰጠ ሰው በቂያማ ቀን ገንዘቡ [ከአፉ የሚወጡ] ሁለት ጥርሶች ያሉት [ወይም ከዐይኑ በላይ ሁለት ጥቁር ነጥብ ያለው] መላጣ እባብ ይደረግበታል። በቂያማ ቀን በሰውየው አንገት ላይ ይጥጠለቃል። ከዚያም ሁለቱን ጉንጮቹን ይዞ «እኔ ገንዘብህ ነኝ። እኔ ድልብህ ነኝ።» ይለዋል። ከዚያም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ተከታዩን አንቀፅ አነበቡ: ‐
[لا تحسبن الذي يبخلون بما آتاهم الله من فضله هو خيرًا لهم بل هو شر لهم سيطوقون ما بخلوا به يوم القيامة]
«እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ፡፡» አል‐ዒምራን ፥ 180

ዘካ የከለከለ ሰው በዱንያም ቢሆን ከንብረቱ ላይ ዘካው በግድ መወሰዱ አይቀርም። ሞገደኛ ሆኖ ዘካውን ሊወስዱ የሚመጡ ሀላፊዎችን በጉልበት ለመመለስ ከሞከረ በሙስሊሙ መንግስት ወይም ሸሪዓን በሚያስከብር አካል አፀፋዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድበታል!
👍12
በችግር እና በመከራ ውስጥ የሚኖሩ የእምነት ወንድሞቻችን በኛ ላይ ያላቸው አነስተኛው ሐቅ [መብት] እነርሱን በዱዓ ማሰብ ነው።

አላህ ችግራቸውን ያንሳላቸው። ጭንቀታቸውን ይገላግላቸው። ቀልባቸውን ይጠግንላቸው። ጉዳያቸውን ያሳካለቸው!
76👍10😢7
Forwarded from Tofik Bahiru
የዘካ ፊቅህ በሻፊዒያ መዝሀብ
[ክፍል ሦስት]

ዘካ ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?
========================
🔸 ዘካ ግዴታ በሚሆንበት ሰው ላይ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
በአንድ ሰው ላይ ዘካ መስጠት ግዴታ እንዲሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ተከታዮቹ ናቸው: ‐

1. ሙስሊም መሆን: ‐ ካፊር [ሙስሊም ያልሆነ ሰው] በዱንያ ውስጥ ዘካ እንዲያወጣ አይጠየቅም።

ከዚህ ቀደም የተጠቀሰው የሰይዲና ሙዐዝ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ሐዲስ ለዚህ ማስረጃ ነው። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ነበር ያሉት: ‐ 
«ከአላህ መስተቀር በእውነት የሚመለክ ሌላ ጌታ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ ጥራቸው።… እሱንም ከታዘዙህ አላህ ከሀብታሞቻቸው ተወስዶ ለድኾቻቸው የሚሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው።»…

ሐዲሱ ዘካ መጠየቃቸውን ቀድሞ የተገለፀውን ‐ወደ እስልምና ለመግባት ፈቃደኛ መሆናቸውን‐ መስፈርት አድርጎ አቅርቦታል።

ቡኻሪይ በዘገቡት ሰይዲና አቡበክር ሐዲስ ላይም ተጨማሪ መረጃ አለ: ‐ «…ይህ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በሙስሊሞች ላይ ግዳጅ ያደረጉት ምፅዋት [ዝርዝር] ነው።»

ሐዲሱ ላይ እንደተመለከተው: ‐ «በሙስሊሞች ላይ» ይላል። ይህ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በዱንያ ውስጥ ዘካ እንዲያወጡ እንደማይጠየቁ ግልፅ ያደርጋል።

እነዚህ መረጃዎች የመጡት የገንዘብ ዘካን በተመለከተ ነው። ዘካቱል‐ፊጥር [የጾም ፍቺ ዘካ] ግን ካፊር ሙስሊም ለሆኑ፣ ወጪያቸውን የመሸፈን ግዴታ ላለበት የቅርብ ዘመዶቹ እንዲያወጣ ይገደዳል።

2. "ኒሷብ" የደረሰ የገንዘብ መጠን ባለቤት መሆን: ‐ "ኒሷብ" አነስተኛ የሀብት መጠን ማለት ነው። ዝርዝሩን ወደፊት በተደጋጋሚ ከእያንዳንዱ የዘካ ገንዘብ ዓይነት ጋር እያብራራን እንቀጥላለን።

3. "ኒሷብ" የሞላ ሀብት ከያዘ በኋላ በጨረቃ አቆጣጠር የሚሰላ አንድ አመት መዞር [ሐውል መሙላት]: ‐

ሀብት ምንም ያህል መጠን ቢደርስ እንኳን አመት እስካልሞላው ድረስ ዘካ አይኖርበትም። ይኸውም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በአቡዳዉድ በተዘገበ ሐዲስ ላይ የጠቆሙት ነው: ‐
«አመት እስካልሞላው ድረስ በገንዘብ ላይ ዘካ የለም።»

ነገርግን የአዝርእት እና የፍራፍሬ ዘካ ከዚህ መስፈርት ውጪ ነው። በእርሻ፣ የግብርና፣ የማዕድን እና ከተቀበሩ ስፍራዎች የሚገኝ ሀብት [ሪካዝ] ላይ የሚኖር ዘካ አመት መሙላትን መስፈርት አያደርግም። ይልቁንስ ወዲያው እንደተገኙ ዘካውን መክፈል ግዴታ ይሆናል። ዝርዝሩን ስለያንዳንዱ የገንዘብ ዓይነት ስናብራራ እናነሳዋለን። ኢንሻአላህ!
:
🔸 በህፃን ልጅ እና በአይምሮ ታማሚ [እብድ] ገንዘብ ላይ ዘካ: ‐
የላይኞቹን የዘካ መስፈርቶች ብቻ ስንጠቅስ ዘካ ዋጂብ [ግዴታ] ይሆን ዘንድ የገንዘቡ ባለቤት ለዓቅመ‐አዳም መድረሱ፣ የአእምሮ ጤናው የተጠበቀ መሆኑም ሆነ ገንዘቡን ለማስተዳደር የሚያበቃ የስነምግባር ሁኔታ ላይ ["ሰፊህ" ወይም ገንዘብ አባካኝ ሞኝ አለመሆኑ] መስፈርት እንዳልሆኑ መረዳት እንችላለን።

ስለዚህ የዘካ ግዳጅ በቀጥታ በራሱ ‐በገንዘቡ ላይ‐ እንጂ በባለገንዘቡ ጫንቃ ላይ የማያርፍ ግዳጅ በመሆኑ እንደአብዝሃኞቹ የአምልኮ ትእዛዛት የባለሀብቱ ምልእነትን መስፈርት አያደርግም። በመሆኑም በህፃን ልጅ እና በእብድ ገንዘብ ላይ ዘካ አለ።

🔹 በህፃን እና በእብድ ላይ ዘካ አለ ሲባል?…
ህፃን ልጅ እና እብድ የገንዘባቸውን ዘካ የማውጣት ግዴታ አለባቸው ማለት አይደለም። ዘካቸው ወጪ ካልሆነም እነሱ ይጠየቃሉ ማለትም አይሆንም። ነገርግን የዘካ መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ የዘካ ሐቅ በገንዘባቸው ላይ አርፏል። ስለዚህ የነርሱ ኃላፊ ወይም ሞግዚት የሆነ አካል ዘካቸውን እያሰበ የዘካውን ሐቅ ከገንዘባቸው ላይ ወጪ የማድረግ ግዴታ አለበት ማለት ነው። ሞግዚታቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ከተዘናጋ ኃጢኣተኛ እና ተጠያቂ ይሆናል ማለትም ነው።

ይሁንና ሞግዚት ካልነበራቸው ወይም ዘካቸውን ካልከፈለ ህፃኑ ለአቅመ አዳም ሲደርስ እብዱም ጤናው ሲመለስለት ያለፈውን ዘመን የዘካ ሐቅ ለይተው መክፈል አለባቸው። ለአምልኮ ግዳጅ በሚበቁ ጊዜ ሌሎቹ የዘካ መስፈርቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ ከዚህ በኋላ የዘካው ግዳጅ ወደ ጫንቃቸው ይሸጋገራል። ተጠያቂነትን በሚላበሱበት በማንኛውም ጊዜ ዘካው ጫንቃቸው ላይ ይኖራል!

🔻ማስረጃዎቻችን: ‐

በቅድሚያ: አላህ እንዲህ ይላል: ‐

(خذ من أموالهم صدقة تطهرهم وتزكيهم بها)
«ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡» አል‐ተውባ ፥ 103

( والذين في أموالهم حق معلوم للسائل والمحروم ) 
«እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡»

እነዚህ እና ሌሎችም አንቀጾች በአንድ ላይ አላህ ለባሮቹ ገንዘብ እንደሰጠ፣ ለባሮቹ ከሰጠው ገንዘብ ላይ የገንዘብን ፀጋ ለተነፈጉ ሰዎች መብትን እንደመደበ ያስረዳሉ።

ነቢዩ ﷺ ይህንን መብት እንዲያስጠብቁ፣ ዘካን ወቅቱን ጠብቀው እንዲሰበስቡ ያሳስቧቸዋል። ዘካ ለባለሀብቱ ንፅህና እና ከክፉ መጠበቂያ ጋሻ እንደሆኑ ያስረዳሉ። ነገርግን ሁሉም ጥቅሶች የባለቤቶቹን ማንነት ለይተው አላብራሩም። አንድን ገንዘብን ከሌላው አልለዩም።

ሁለተኛ: ከተጠቀሱት አንቀጾች በተጨማሪ ከላይ ያሰፈርነው የሰይዲና አቡበክር [ረዲየላሁዐንሁ] ሐዲስ መረጃ ነው: ‐

«…ይህ የአላህ መልክተኛ ﷺ በሙስሊሞች ላይ ግዳጅ ያደረጉት ምፅዋት [ዝርዝር] ነው።»
"ሙስሊሞች" በሚለው ጥቅል ቃል ውስጥ ሁሉም አለ። ህፃናትም ሆኑ አዋቂዎች፣ ጤነኞችም ሆኑ እብዶች ተካተዋል። ምክንያቱም በሸሪዓ መርሆች ውስጥ እንደሚታወቀው  «ከሸሪዓ መረጃ መልእክታቸውን የሚገድብ ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ በጥቅል የተጠቀሱ ነገሮች በጥቅልነታቸው ይዘልቃሉ።»

ዳረቁጥኒይ በዘገቡት የዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁዐንሁ] ሐዲስ ላይ እንደተገለፀው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ገንዘብ ያለው የቲም ህፃን ላይ የተሾመ [ሞግዚት] ለህፃኑ ይነግድለት። ገንዘቡን ዘካ እስከሚበላው ድረስ አያስቀምጠው።»

ኢማማችን ሻፊዒይ አል‐ኡም በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ዘካ እንዳይጨርሰው ለማድረግ በየቲሞች ገንዘብ ነግዱ።»

ከላይ የተጠቀሱት ሐዲሶች ላይ የተላለፈው መልእክት: ‐ ገንዘብ ያለ እንቅስቃሴ ከተተወ ዘካ ይበላዋል፤ ይጨርሰዋል። ዘካው ገንዘቡን የሚጨርሰው ደግሞ አመት በዞረ ቁጥር ከገንዘቡ ላይ የዘካው ሐቅ እንዲወጣ ስለሚደረግ ነው።

እንደሚታወቀው ግዴታ ከሆነው ዘካ ውጪ ከህፃን ልጅ ገንዘብ ላይ መመፅወት አይፈቀድም። ሞግዚት በህፃን ልጅ ገንዘብ ትርፍ ሶደቃዎችን ማድረግ አይፈቀድለትም። ስለዚህ ይህ መነሻ ከህፃን ልጅ ገንዘብ ላይ ዘካ መስጠት ግዴታ እንደሚሆን ያረጋግጥልናል።

እብድም በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ ህፃን ይታያል። ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ የእብድ እና የህፃን ልጅ ሁኔታ አንድ ዓይነት ነው።
:
በጉዳዩ ላይ የልሂቃን ልዩነት እንዳለ ሆኖ የሻፊዒይ [ረሒመሁላህ] እና የአብዝሃኞቹ መዝሀብ የሆነው ሃሳብ ከላይ ያብራራነውን ይመስላል። በእብድ እና በህፃን ልጅ ገንዘብ ላይ ዘካ ግዴታ እንደሚሆን የሚያስረዱ ሌሎች በርካታ መረጃዎችም አሉ። ለማሳጠር ትተናቸዋል!
አላሁ አዕለም!
👍224
ሙስሐፍን ማክበር አላህን የማክበር ምልክት ነው!
(በድጋሚ የተለጠፈ)
:
በ‌‌ሱ‌‌ጁ‌‌ድ‌‌ ወ‌‌ቅ‌‌ት‌‌ ቁ‌‌ር‌‌ኣ‌‌ን‌‌ን‌‌ በ‌‌መ‌‌ሬ‌‌ት‌‌ ላ‌‌ይ‌‌ ማ‌‌ኖ‌‌ር‌‌

መስሐፍን (የታተመ የቅዱስ ቁርኣን ቅፅ) ማክበር ግዴታ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐

{ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ}

«(ነገሩ) ይህ ነው፡፡ የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦች የኾነች ጥንቃቄ ናት፡፡»

ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይተሚይ "አልፈታዋ አል‐ፊቅሂያ" በተሰኘው መፅሐፋቸው ቅፅ 2፥ ገፅ 6 ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐
«ቁርኣንም ሆነ ማንኛውም የተከበረ ስም ‐ለምሳሌ: ‐ የአላህ ስም፣ የነቢይ ስም‐ ያለበት ፅሁፍን ማክበር፣ ማላቅ እና ማክበድ ግዴታ ነው።»
:
ሱጁድ ስናደርግ ወይም በሌላ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን በመሬት ላይ አለማስቀመጥ መስሐፍን ከማክበር መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው። በተለይም በተሀጁድ ወይም በሌላ ጊዜ ቁርኣን ይዞ የሚሰግድ ሰው፣ ለሱጁድ በሚወርድ ጊዜ ከመሬት ከፍ ያለ ማስቀመጫ ፈልጎ ከላይ ያድርገው፤ ወይም አጠገቡ ላለ ሰው ያቀብለው።

መስሐፍን መሬት ላይ ማስቀመጥ ከሻፊዒዮች ኢማም አል‐መይዳኒይ፣ ከማሊኪዮች ደግሞ ኢማም ዒለይሽ ሐራም ነው በማለት ፈትዋ ሰጥተውበታል።

ኢማም አል‐ቁርጡቢይ በሰነዳቸው በተፍሲራቸው ላይ ከዑመር ኢብኑ ዐብዱል‐ዐዚዝ እንደዘገቡት: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] መፅሐፍ በመሬት ላይ ተጥሎ ባለበት ስፍራ አለፉ። ከዚያም ከሁዘይል ጎሳ የሆነ አንድ ወጣት «ይህ ምንድን ነው?» አሉት። እርሱም: ‐ «አንድ አይሁድ የጻፈው ከአላህ መፅሀፍት መካከል ነው።» አላቸው። እርሳቸውም: ‐ «ይህንን ያደረገ ሰው ከአላህ እዝነት ይራቅ። የአላህን መፅሀፍ በቦታው እንጂ አታስቀምጡ።» አሉ።» ይህንን ዘገባ ኢማም አል‐ሐኪም አት‐ቲርሚዚም "ነዋዲሩል‐ኡሱል" በተሰኘው ደርሳናቸው ላይ አስፍረውታል።

አቡዳዉድ አል‐ሷሒፍ በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ ከዑመር ኢብኑ ዐብዱል‐ዐዚዝ እንደዘገቡት: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አላህ የተጠቀሰበትን መፅሐፍ መሬት ላይ ተጥሎ አገኙ። ከዚያም «ይህንን እንዲህ ያደረገ ማን ነው?» አሉ። «ሂሻም ነው።» አሏቸው። እርሳቸውም «ይህንን ባደረገ ሰው ላይ የአላህ ርግማን ይሁን። አላህ የሚወሳበትን ፅሁፍ ያለ ቦታው አታድርጉ።» አሉ።»

በእርግጥ  ታቢዒይ የሆኑት ዑመር ኢብኑ ዐብዲል‐ዐዚዝ ሶሐባ ሳይጠቅሱ በቀጥታ ነቢዩን [ﷺ] ዋቢ አድርገው በመዘገባቸው ሐዲሱ "ሙርሰል" ነው። ስለዚህ ድክመት አለበት። ነገርግን መግቢያችን ላይ የጠቀስነው አንቀፅን የመሰሉ ጥቅል መልእክት ካዘሉ መረጃዎች ጋር አጣምረን ጥንቃቄ እንድናደርግ ይገፋፋናል።

አንዳንድ ሰዎች በተለይም በተራዊሕ ወይም በተሀጁድ ጊዜ ሱጁድ ማድረግ ሲሹ በአንድ እጃቸው መስሐፉን ይዘው መሬት ላይ እያስቀመጡ ሲሰግዱ ይስተዋላል። ይህ አይነት ተግባር በአንድ በኩል ከሰባቱ የሱጁድ አካላት መካከል አንዱ የሆነው እጅ መሬት ላይ በትክክል እንዳያርፍ ስለሚያግድ ሱጁዱን ውድቅ ሊያደርግ ይችላል። በዚያ ላይ ሙስሐፍን ማዋረድና በመሬት ላይ መጎተት ሊንፀባረቅበት ይችላል።

ከፈትሑል‐ዐሊይ አል‐ማሊክ ፊል‐ፈትዋ ዐላ መዝሀቢል‐ኢማም ማሊክ" በተሰኘው የኢማም ዒለይሽ ኪታብ ላይ እንዲህ የሚል ሰፍሯል: ‐
«የፊቅህ ልሂቃን [ፉቀሃእ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሙስሐፍን (ቁርኣንን) በንፁህ መሬት ላይ በንቀት ማስቀመጥ ከኢስላም ያስወጣል።» ስለዚህ ሙስሐፍን ንቀት በሌለበት ስሜት መሬት ላይ ማስቀመጥ ደግሞ እርም መሆኑን ከዚህ ውስጥ መረዳት ይቻላል።»

"ሓሺየቱል‐ቡጀይሪሚ ዐለል‐ኸጢብ" በተሰኘው ታዋቂ የሻፊዒያ መዝሀብ መፅሀፍ ላይም እንዲህ ተብሏል: ‐ «ሙስሐፍን መሬት ላይ ማኖር ሐራም ነው። ይልቁንስ በተለምዶ [ክብሩን በሚያሳይ] ያክል ከፍ አድርጎ ማስቀመጥ የግድ ነው።»
:
ወ‌ሲ‌ያ‌
ወዳጆቼ በየተራዊሑና በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ እያየን ያለነው እየተለመደ ያለ ክፉ ተግባር አለ። ቁርኣንን በመሬት ላይ ማስቀመጥ ዋጂብ ነው የተባለ እስከሚመስል ድረስ በአንድ ሰልፍ ሰላሳ‐አርባ ሙስሐፎች እየቆጠርን እንገኛለን። አንዳንዴ በእግር መርገጥ፣ በእግር ገጾቹን ማጫወት፣ በላዩ ላይ ሌሎች ኮተቶችን መጫን ወዘተ. እጅግ አስከፊ የንቀት ተግባራትን ያለከልካይ በየመስጂዱ እያየን እንገኛለን።

ወዳጆቼ! ቁርኣንን ማክበር በቁርኣን መስራት ብቻ ነው በሚል ግልብ ንግግር ታጅቦም ነው ድርጊቱ የሚፈፀመው። በቁርኣን መስራት በገሀድ ለቁርኣን አክብሮት እንዳለን በሚያሳይ ሁኔታ ቁርኣንን ከመንከባከብ ይጀምራል። አካሉን ያላከበርከውን ቁርኣን ምጡቅ መልእክቱን አግኝተህ ልታከብረው የምትታደልበትን በረከት ልትቸር አይቻልህም!

ለልቅናው በሚመጥን ሁኔታ በማስቀመጥ ያላከበርነው ቁርኣን አያከብረንም! ቁርኣን ያዋረደው ደግሞ ምንም ነገር አያከብረውም! በአካላዊ ገፅታችን ክብር ላልሰጠነው ቁርኣን በቀልባችን እንሰጠዋለን ማለት ውሸት ነው! ስለዚህ ወዳጆች ጥንቃቄ አይለየን!
በጉዳዩ ላይም በህብረት የማንቃት ኃላፊነት አለብንና ድርጊቱ ሲፈፀም እያየን ዝም አንበል!
35👍12
በሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በተውበቱ ላይ ቋሚ ያልነበረ፣ ሁሌም እየቶበተ ተመልሶ እዚያው የሚነከር የኔ ቢጤ ነበር። ሃያ አመት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። እኔስ ብሆን ስንት ዓመቴ በዚህ መልኩ ስኖር?!…
:
አላህ ሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ላይ ራእዩን አወረደ። "እገሌ ለሚባለው ባርያዬ ንገረው። እኔ ተቆጥቼበታለሁ!" አላቸው።…
ሰይዲና ሙሳ መልእክቱን አደረሱ። ሰውየውም እጅግ አዘነ። ደነገጠ። እንዲህ እያለ ወደ ሜዳ ወጣ: ‐
«ኢላሂ! እዝነትህ አልቆ ነው?! ወይስ ኃጢኣቴ ጎድቶህ?! የይቅርታ ካዝናህ ነጠፈ?! ወይስ በባሮችህ ላይ ሰሰትክ?! የቱ ወንጀል ነው ከይቅርታህ የሚገዝፈው?!…
ቸርነት ቀዳሚ ጠባይህ ነው።…
መናጢነት፣ ኃጢኣት የመጤው "እኔ" ተከሳች ጠባይ ነው።…
ታዲያ የኔ ጠባይ ካንተ ጠባይ ሊያይል ይችላል?!…
ባሮችህን ከረሕመትህ ከጋረድክ ማንን ይከጅላሉ?!…
አንተ ካባረርካቸው ወደ ማን ይሸሻሉ?!…
ኢላሂ! እዝነትህ ካለቀና ቅጣትህን መቅመሴ የግድ ከሆነ የባሮችህን ኃጢኣት በሙሉ እኔ ላይ አድርግ። በነፍሴ በዥቻቸዋለሁ!… »
:
አዛኙ አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ሙሳ ሆይ! ሰውየው ዘንድ ሂድና እንዲህ በለው: ‐ «ኃጢኣትህ ሰማይና ምድርን ቢሞላ እንኳን እምርሃለሁ። በሙሉ ኃያልነቴ፣ በሰፊው ይቅርታዬ፣ በማይነጥፍ እዝነቴ እና በማያልቀው ምህረቴ እስካወቅከኝ ድረስ ምሬሃለሁ!»
:
ታሪኩን ኢማም አል‐ገዛሊይ "ሙካሺፈቱል‐ቁሉብ" ላይ አውርተውታል።

ረመዳን እንደ ቀልድ አስራ ስምንት ቀን እያሳለፈ ነው።
የእስካሁኑ ጉድለታችንን መጪውን የረመዳን ጊዜ ሳያበላሽ ባማረ ሁኔታ ማለፍ እንዲችል ማድረግ እንችላለን።
እስካሁኑን ያማሩ ቀናት አሳልፈን ከሆነም መጪውን ጊዜ በማበላሸት የቀደመውን ጊዜም ማበላሸት እንችላለን።
ምክንያቱም ስራዎች የሚለኩት በፍፃሜያቸው ነው!
51👍13😢5😍1
"اللهم استر، واجعل تحت الستر ما تحب".

«አላህ ሆይ! ሸፍን። ከመሸፈንህ ስር ደግሞ የምትወደውን ነገር አኑር።»
ኢማም ቢሽር ኢብኑል‐ሓሪስ አልሓፊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ]
23👍3
በባህር ላይ እየሰመጠ ያለ ሰው ዱዓ ሲያደርግ አይተህ ታውቃለህ?!
ከአላህ ውጪ ሌላ ተስፋ ቀልቡ ውስጥ ይኖራል?!
በእንዲህ አይነት ዱዓ ብቻ ለችግራችን መፍትሄ ለበሽታችን ፈውስ እናገኛለን!
:
ሑዘይፋ ኢብኑል‐የማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ወደፊት እንደሰጠመ ሰው ዱዓ ከሚያደርግ ሰው በስተቀር ማንም የማይድንበት ዘመን በሰዎች ይመጣል!»
😢388👍7
ITIKAF RAMADAN 1446 MINBER TV.pdf
13.2 MB
የኢዕቲካፍ ህግን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የጻፍኳቸው ልጥፎች በዚህ መልኩ አምረውና ተውበው ቀርበዋል። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን!
12👍2
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል አርባ ሦስት ኪታቡል‐ኢዕቲካፍ
📆 መጋቢት 10/ 2017 ዓ. ል.
👍5
ከነገ ወዲያ ፈጅር ጀምሮ ሱና የሆነው የዐሽሩል አዋኺር የኢዕቲካፍ ጊዜ ነው። ታላቁ ረመዳን ጥሎን እየሄደ ነው። መጪውን ጊዜ አላህ በረካ ያድርግልን!
👍37😢159
ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«የመጨረሻዎቹ የረመዳን ሌሊቶች በሙሉ ለይለቱል‐ቀድር ሊሆኑ ይችላል። ነገርግን ነጠላ ቁጥሮቹ የበለጠ ይከጀላሉ። ሻፊዒዮቹ ዘንድ ደግሞ #ሃያ #አንደኛው ሌሊት በይበልጥ #ለይለቱል‐ቀድር ሊሆን ይከጀላል ተብሎ ይታመናል።»
የረመዳን 21 ሌሊት #ዛሬ ነው!
46👍12
Forwarded from Tofik Bahiru
«ለይለቱል‐ጁሙዐ ከዐሽሩል‐አዋኺር ነጠላ ቀናት ጋር ከተጋጠመች ለይለቱል‐ቀድር መሆኑ እጅግ የተገመተ ነው!»
ታላቁ የሐንበሊዎች ልሂቅ ኢብኑ ሁበይራ (ረሒመሁላህ)
:
ዛሬ ለይሉ ለይለቱል‐ጁሙዐ ነው። 21ኛው ለይልም ነው። ስለዚህ ገጥሟልና እንታገልበት!
ትግል ጥሩ ነው!
በዱዓችሁ አስቡኝ!
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
31👍11
2025/10/27 15:27:41
Back to Top
HTML Embed Code: