ረመዳን ❹
የሚሰመርባቸው ነጥቦች: ‐
⚀ «ተውበት አድርጎ የተመለሰ ሰው ወንጀል እንዳልፈፀመ ሰው ነው።» ተወዳጃችን [ﷺ]…
በአግባቡ የታጠበ ልብስ ከመጀመሪያው እንዳልቆሸሸ ነው!…
⚁ ተውበተኛ የአላህ ወዳጅ ነው: ‐
{إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ التَّوّابينَ وَيُحِبُّ المُتَطَهِّرينَ }[ البقرة: ٢٢٢ ]
«አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡»
⚂ ተውበተኛ አላህ የሚደሰትበት ሰው ነው: ‐
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አላህ አንዳችሁ በጉዞ ላይ ሆኖ ከባድ አደጋ ባለበት ስፍራ ላይ አርፎ መጓጓዣ ግመሉን፣ ስንቁን እና መጠጡን ከራሱ ጋር አድርጎ ለጥቂት አፍታ ጋደም ብሎ ተኛ። ከዚያም ሲነቃ ግመሉ [ስንቁን እንደጫነች] ጠፍታለች። ሙቀት እና ጥም ሲጠናበት ሰውየው [ከፍለጋው ተስፋ ቆርጦ] ወደ ቦታዬ ልመለስ በማለት ወደነበረበት ተመልሶ ተኛ። ከዚያም ከእንቅልፉ ሲነቃ ግመሉ ተመልሳ አገኛት። አላህ ከዚህ ሰውዬ የበለጠ በባርያው ተውበት ይደሰታል።»
⚃ ተውበተኛ ምስጉን ነው: ‐ ዐውን ኢብኑ ዐብዲላህ ኢብኑ ዑትባ እንዲህ ይላሉ: ‐
«የአላህ ባርያ በወንጀሉ መጨነቁ እንዲተወው ይገፋፋዋል። መፀፀቱ ደግሞ የተውበት ቁልፍ ይሆንለታል። ሰውየው ወንጀሎቹ ከአንዳንድ በጎ ስራዎቹ በላይ እስከሚጠቅሙት ድረስ በወንጀሉ ከመጨነቅ አያቆምም!»

❤52👍8
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል አርባ፣ አርባ አንድ እና አርባ ሁለት ኪታቡስ‐ሲያም (የጾም መጽሐፍ)
📆 የካቲት 25/ 2017 ዓ. ል.

❤5👍1
የተራዊሕ ህግጋት
(ክፍል አንድ)
—————————
ተራዊሕ የረመዳን መለዮ፣ የድምቀቱ ማሳያ፣ ዒባዳነቱን ተሻግሮ የትውፊት ቀመር እና የባህል አሻራም ያኖረ ድንቅ ትእይንት ነው። የብዙዎቻችንን የልጅነት ጣዕም የቀመመ፣ የረመዳን ትዝታዎቻችንን ያዋቀረ፣ የመሰብሰብና የመዋሃድን ብርቅታ ያሳየ ልዩ ክስተት ነው። ረመዳን ሲባል እዝነ ህሊናችን ደግሞ ተራዊሕ ይላል። ሁለቱም በአንድነት የተቆራኙ የመንፈስ ምግቦች ናቸውና!…
ነገርግን በርካቶቻችን ስለተራዊሕ ህግጋት የምናውቀው ጥቂት ነው። ስለሆነም በመስጊዶቻችን ውስጥ በርካታ ስህተቶችና የግንዛቤ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። በበርካቶች አዕምሮ ውስጥ የሚመላለሱ በሚገባ ያልተብራሩ ብዙ ጥያቄዎችም ይኖራሉ። ስለዚህ የፊቅህ ድርሳናትን ‐በተለይም የሻፊዒዮቹን‐ አገላብጬ በአላህ ፍቃድ በዚህ ጉዳይ ላይ የተወሰኑ ሃሳቦችን ማንሸራሸር ወደድኩኝ!
[አላህ ለርሱ ተብሎ የተሰራ አበርክትዎ ያድርግልኝ፣ ለወንጀሌ ማስሰረያ፣ በመልካም ስራ ሚዛኔ ላይም ተደማሪ እንዲያደርግልኝ እለምናለሁ!]
⚀ ተራዊሕ ማለት
«ተራዊሕ» የሚለው ቃል "ተርዊሐ" የሚለው ቃል የብዜት ገላጭ ነው። "ተርዊሐ" ማለት ደግሞ አንድ ጊዜ ማረፍ ማለት ነው። ስለዚህ ተራዊሕ በተደጋጋሚ ማረፍ ማለት ይሆናል። ቃሉ ለምናውቀው የረመዳን የሶላት ክንዋኔ ስም ሆኖ የመጣው በሶሐቦቹ ዘመን ነው። ያኔ ሶላቱን ሲጀምሩት በየሁለት ተስሊማ (በየአራት ረከዐው) እረፍት ያደርጉ ስለነበር ሶላቱም ተራዊሕ (እረፍቶች ያሉበት ሶላት) ተብሏል።
ይህ ገለፃ ኢማም ኢብኑ ሐጀር ፈትሑል‐ባሪ ላይ እና ሌሎችም ልሂቃን የጠቀሱት ማብራሪያ ነው።
⚁ ብይኑ
ሶላቱት‐ተራዊሕ ጥብቅ ሱና ነው። ከሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተገኘው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«[በአላህ] ያመነ እና [ከአላህ ጋር ብቻ] የተሳሰበ ሲሆን ረመዳንን [በሌሊት በሶላት] የቆመ ሰው። ያስቀደመውን ኃጢኣት ይምረዋል።» ቡኻሪ ዘግበውታል።
ኢማም አን‐ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዳብራሩት የረመዳን የሌሊት ሶላት ማለት በዋናነት የተራዊሕ ሶላት ነው።
[ሸርሕ ሙስሊም ቅጽ 6፥ ገፅ 39 መመልከት ይቻላል።]
በእርግጥ በአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘመን የረመዳን የሌሊት ሶላት ለብቻ ይሰገድ ነበር። ከእለታት ጥቂት ቀናት ብቻ ያለርሳቸው ትእዛዝ ሶሓቦች ተከትለዋቸው በጀመዓ ሰግደው ነበር። ዳሩ አዛኙ ነቢይ [ﷺ] «ፈርድ እንዳይደረግባችሁ ሰጋሁ።» በሚል በህብረት መስገድ እንዲቆም አድርገዋል።
ኢብኑ ሺሃብ እንዲህ ይላሉ:‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ነገሩ እንዲህ ባለበት አረፉ። ከዚያም [የሰይዲና] አቡበክር የኸሊፋነት ዘመን እና [የሰይዲና] ዑመር የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት እንደዚሁ አለፉ።»
በመጨረሻም በይፋ በሚታወቀው ክስተት ሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] በመስጂድ ውስጥ በሰይዲና ኡበይ ኢብኑ ከዕብ ኢማምነት አሁን በሚታወቀው የሶላት አሰጋገድ በህብረት እንዲሰገድ አደረጉ። የሶሓቦቹ ስምምነትም ይህንን ውሳኔ የድንጋጌ ምንጭ አደረገው።
⚂ የረከዓዎቹ ቁጥር
አብዝሃኞቹ ልሂቃን ተራዊሕ ሃያ ረከዓ መሆኑን ይስማማሉ። ነገርግን ማሊኪዮች ሰላሳ ስድስት ረከዓ እንደሆነ ያምናሉ። በዚህ መሰረት በአብዝሃኞቹ ልሂቃን እና በማሊኪዮቹ መዝሀብ መሰረት ስምንት ረከዓ የሰገደ ከተራዊሕ ላይ የተወሰነ ረከዓ ሰገደ ይባላል እንጂ ተራዊሕን ሞልቶ ሰገደ አይባልም። በእርግጥም ያለጥርጥር ሰውየው የሰገደውን ያህል ምንዳ ያገኛል። ሌላ ችግርም አይገጥመውም።…
ይህ ኢማም በይሀቂይ [ረሒመሁላህ] [ሱነን] በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ሳኢብ ኢብኑ የዚድን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ዋቢ በማድረግ ከዘገቡት ሐዲስ ጋር የሚጣጣም ሐሳብ ነው: ‐ «[ሶሐቦቹ] በዑመር ኢብኑል‐ኸጧብ ዘመን በረመዳን ወር በሃያ ረከዐ ይቆሙ ነበር። [በየረከዐው] መቶ የቁርኣን አንቀፅ ያነቡ ነበር።»
ይህ ከዘመነ‐ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ጀምሮ በየዘመኑ ሁሉ በሁለቱ ሐረሞች ሳይቀር ሲሰራበት የቆየ እድሜ ጠገብ ተግባር ነው። በሙስሊሙ ዓለም በየትኛውም አቅጣጫ ላይ [የኡማው] አይነተኛ ተግባር ሆኖ የተመዘገበውም ይኸው ነው። እናም ይህንን በተግባር ያስገኘ ሁሉ ሱናውን አሟልቶ ሰርቷል። በከፊል የፈፀመውም ሱናውን በከፊል አስገኝቷል። አጅሩ ለሁለቱም የተመደበ የአላህ ችሮታ ነው። ከዚህ ውጪ ጎዶሎ የሚሰግደው ወገን ሞልቶ የሚሰግደውን ሊቃወምም ሆነ ሊከለክል አይችልም። ሞልቶ የሚሰግደውም በስምንት የሚያቆመውን ሊያነውርና ሊያወግዝ አይችልም።
ሶላት ምርጡ የሙእሚኖች ሥራ ነው። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ነገሮች ሁሉ ምርጡ ነው። ማብዛት የፈለገ ሰው ያብዛው።» ጦበራኒይ ዘግበውታል።
⚃ አሰጋገዱ
ኒያውን ለተራዊሕ ሶላት ለይቶ ማድረግ ግዴታ ነው። ሰውየው ወደ ሶላት የሚገባበትን ተክቢራ ሲያደርግ ከተክቢራው ጋር አቆራኝቶ "የተራዊሕ ሶላት ልሰግድ" በሚል ኒያ (ልበ‐ውሳኔ) ሊያደርግ ይገባል። ከፈለገም "የረመዳን የሌሊት ሶላት ልሰግድ" በሚል ኒያውን ሊያደርግ ይችላል። ነገርግን "ሱና ሶላት ልሰግድ" የሚል ስድ ኒያ አድርጎ ተራዊሕ ሊሰግድ አይችልም።
በየሁለት ረከዓው አንድ ጊዜ ማሰላመት አለበት። አራት ረከዓዎችን በአንድ ላይ መስገድ አይቻልም። ምክንያቱም የድንጋጌ መነሻ የሆነው ከሶሓቦቹ የተገኘው የተራዊሕ ሶላት አሰጋገድ እንዲህ ስለነበር በምንም መልኩ ከተዘገበበት ሁኔታ መለወጥ አይፈቀድም።
በተጨማሪም ተራዊሕ በህብረት ከሚሰገዱ ሱና ሶላቶች መካከል አንዱ ነው። በዚህ ፈርድ ሶላትን የመምሰል ጠባይም አለው። ስለዚህ ከተደነገገበት አሰጋገድ ውጪ የሆነን ለውጥ የማይቀበል ጥብቅነትንም ከዚሁ ጠባዩ ይወርሳል። በመሆኑም ከተገበበት ሁኔታ ለውጦ መስራት አይፈቀድም።
ስለዚህ ሰውየው ይህ መሆኑን እያወቀ እና ሆነ ብሎ (ረስቶ ሳይሆን) ለሦስተኛ ረከዓ ከተነሳ ሶላቱ ይበላሻል። ረስቶ ከሆነ ግን ባስታወሰ ጊዜ ወደነበረበት መመለስና በሁለት ረከዓው ላይ አብቅቶ ማሰላመት አለበት።
⚄ ጊዜው
የተራዊሕ ጊዜ ከዒሻ ሶላት በኋላ እስከ ፈጅር ሶላት ወቅት ድረስ ነው። ሰውየው በጉዞ ምክንያት የዒሻን ሰላት አስቀድሞ ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት ቢሰበስብ (ጀምዕ ቢያደርግ) ወዲያው ተራዊሑን አስከትሎ መስገድ ይችላል።
⚅ የሶላት ጥሪ
ለሶላቱ አት‐ተራዊሕ "አስ‐ሶላቱ ጃሚዐህ" ወይም "አስ‐ሶላት! አስ‐ሶላት!" የሚል ጥሪ ቢደረግ ችግር የለም። ከፈለገ «አት‐ተራዊሕ ረሒመኩሙላህ»፣ «አስ‐ሶላት አሣበኩሙላህ!» ወይም በራሱ ቋንቋ «ወደ ሶላት ኑ!» ወይም ተመሳሳይ ጥሪ ማድረግ ይፈቀዳል። ይህንን ጥሪ የሰማ ሰው ደግሞ ልክ አዛን ላይ "ሐያ ዐለሶላህ" ሲባል እንደሚመልሰው "ላሐውለ ወላ ቁው‐ወተ ኢላ ቢላህ" በሚል ምላሽ ቢሰጥ ተወዳጅ ነው።
[የኢማም ሺርቢኒይ [ረሒመሁላህ] የሻፊዒዮቹ አንጋፋ መጽሐፍ ‐"ሙጝኒል‐ሙሕታጅ" የዚህ ማብራሪያ ማጣቀሻችን ነው!]
:

👍72❤20😢1😍1
Tofik Bahiru pinned «የተራዊሕ ህግጋት (ክፍል አንድ) ————————— ተራዊሕ የረመዳን መለዮ፣ የድምቀቱ ማሳያ፣ ዒባዳነቱን ተሻግሮ የትውፊት ቀመር እና የባህል አሻራም ያኖረ ድንቅ ትእይንት ነው። የብዙዎቻችንን የልጅነት ጣዕም የቀመመ፣ የረመዳን ትዝታዎቻችንን ያዋቀረ፣ የመሰብሰብና የመዋሃድን ብርቅታ ያሳየ ልዩ ክስተት ነው። ረመዳን ሲባል እዝነ ህሊናችን ደግሞ ተራዊሕ ይላል። ሁለቱም በአንድነት የተቆራኙ…»
የተራዊሕ ህግጋት
(ክፍል ሁለት)
————————
⚆ ተራዊሕ በጀመዓ
ተራዊሕንም ሆነ ከበስተኋላው የሚሰገደውን ዊትር በጀመዓ መስገድ ሱና ነው። ለብቻ ከመስገድም ይበልጣል። ኢማም ነወዊይ "አል‐መጅሙዕ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«ተራዊሕን ለብቻም ሆነ በህብረት መስገድ ይፈቀዳል። የትኛው ይበልጣል? ሁለት የሻፊዒ ተማሪዎች/አስሓብ/ የታወቁ ሃሳቦች [አውጁህ] አሉ። በእርግጥ አንዳንድ የሻፊዒያ መዝሃብ ልሂቃን ሁለቱንም የኢማም ሻፊዒይ ‐የራሳቸው‐ ሃሳቦች (አቅዋል) አድርገው ይገልጿቸዋል። በእርግጥም በሁሉም የልሂቃን ስምምነት መሠረት ከሁለቱ ሃሳቦች ጀመዓ ይበልጣል የሚለው ሃሳብ ተመራጭ ነው። [ኢማም] አል‐ቡወይጢይ በግልፅ ያሰፈሩትም ይኸው ነው። አብዝሃኞቹ [ሻፊዒያ] ባልደረቦቻችንም የመረጡትም ይህንኑ ነው። ሁለተኛው ሃሳብ ግን ለብቻ መስገድ ይበልጣል ይላል።»
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ተራዊሕን ለሦስት ቀናት ያህል በህብረት ሰግደውታል። ከዚያም በቤታቸው ተወስነው ጀመዓ ሳይሰበስቡ ሰግደዋል። በአቡበክር እና በዑመር የመጀመሪያዎቹ ዓመታትም በዚሁ መልክ ቀጥሎ ቆይቷል። ተራዊሕ በጀመዓ አልተሰገደም። ከጊዜ በኋላ ግን ሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] በህብረት መስጂድ ውስጥ እንዲሰገድ አድርገዋል። የሶሓቦቹን ሙሉ ስምምነትም አግኝቷል። ታሪኩም የታወቀ ነው።
⚇ ተቀምጦ መስገድ
በተራዊሕ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሱና ሶላት ላይ ቆሞ መስገድ ሱና ነው። ሰውየው መቆም ቢችልም እንኳን በመሬት ላይም ሆነ በወንበር ላይ መስገድ ይፈቀዳል። ነገርግን ቆሞ መስገድ እየቻለ ያለምክንያት ተቀምጦ የሰገደ ሰው ቆሞ ከሚሰግደው ሰው ግማሽ ምንዳ ብቻ ይኖረዋል።
ቡረይዳ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት: ‐
«ዒምራን ኢብኑ ሑሶይን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ቡጉንጅ ነበረባቸው። እናም ተቀምጠው ስለመስገድ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ጠየቁና እንዲህ መለሱላቸው: ‐ «ቆሞ ቢሰግድ ተመራጭ ነው። ተቀምጦ የሰገደ ቆሞ ከሚሰግደው ሰው ምንዳው ግማሽ ይሆንበታል። ተጋድሞ ከሰገደ ደግሞ ተቀምጦ ከሚሰግደው ሰው ግማሽ ይሆንበታል።» ቡኻሪ ዘግበውታል።
ተቀምጦ የሚሰግድ ሰው ሩኩዕ እና ሱጁዱን አሟልቶ ማድረግ ከቻለ እንደዚያው ማድረግ አለበት። በተቀመጠበት ሩኩዑን ያደርጋል፤ ከቻለ በሩኩዑ ላይ በሱጁዱ ግንባር ማረፊያ ልክ ማጎንበስ ይወደዳል። ካልሆነ ቢያንስ ከጉልበቱ ቀጥሎ ያለውን መሬት ይቅጣጫል። ሱጁዱን ደግሞ እንደማንኛውም ሰው አሟልቶ ያደርጋል።
ችሎታው ከሌለውና አቅም ካጣ ግን ባለበት ሩኩዕና ሱጁዱን በምልክት ይሰራል፤ ለሁለቱ ምልክት እንዲሆንለት በመጠኑ ያጎነብሳል። ሁለቱን ለመለየት ደግሞ የሱጁዱን ከሩኩዑ "ጉንበሳ" ይበልጥ ዝቅ እንዲል ያደርጋል።
⚈ የዊትር ቁኑት
በሻፊዒያ መዝሀብ መሠረት አመቱን በሙሉ በሚሰገዱት ዊትሮች ላይ ቁኑት የለም። ነገርግን በረመዳን ወር ከአስራ አምስተኛው ሌሊት በኋላ በሚሰገዱት ዊትሮች ላይ ቁኑት ማድረግ ሱና ነው። ረስቶ ቢተወው ችግር አይኖርም። ነገርግን ከተስሊም በፊት የመርሳት ሱጁድ (ሱጁድ ሰህው) ማድረግ ይወደድለታል።
በሀገር ላይ ችግር ሲፈጠር ግን በማንኛውም ሶላት ላይ ቁኑት መቅራት ሱና ነው።
እንደማንኛውም ዱዓ በቁኑት ወቅት እጆችን ከፍ ማድረግ ሱና ነው። ነገርግን ዱዓው ሲያበቃ ፊትንም ሆነ ደረትን መዳበስ አይወደድም። ከሶላት ውጪ ባሉት ሁኔታዎች ግን ከዱዓ በኋላ ፊትን ማበስ ይወደዳል።
ቁኑት ላይ ኢማም ድምፁን ከፍ ማድረግ ይወደድለታል። ተከታዩ ደግሞ ለኢማሙ ዱዓዎች አሚን ይላል። ኢማሙ ውዳሴ ሲያደርግ ደግሞ ተከታዩም ለራሱ በሚሰማው ልክ ብቻ የግሉን ውዳሴዎች ያደርጋል።
❿ ቁኑትን ማርዘም
የቁኑትን ዱዓ አለማርዘም ይወደዳል። ከአላህ ነቢይ [ﷺ] በተገኙ ዱዓዎች መብቃቃትና ማሳጠር ይመረጣል። ዱዓ ሰብሳቢ በሆኑ ቃላት፣ ለአላህ መዋረድ እና በልመና መዋደቅ የሚንፀባረቅበት ከልሳን በፊት በቀልብ የሚከወን ዒባዳ ነው። ከመቼው ባለቀ በሚል የደከመው እና የተሰላቸ መእሙምና የሀፈዘውን በደረቅ መንፈስ በሚያነበንብ ኢማም መካከል የዱዓ ስሜት ይቀጭጫል። የሷሊሖቹ ዱዓ በተለይም በቁርኣኑ ውስጥ በተጠቀሰበት ስፍራዎች ላይ ከሰባት አረፍተ ነገር አይበልጥም። የነቢዩ ዱዓዎች ጥቅል ይዘትና ግሩም ውበት ያላቸው ነበሩ። ኢስቲጃባ ያለው ቃላት በማርዘምና ብዙ በመቆም ሳይሆን በተዶሩዕና በኹዱዕ ነው! በየተራዊሕ ቦታዎች የሚስተዋለው የተከታይን ዓቅም ያላስተዋለ ከሆነ አካባቢ በቀጥታ ተቀድቶ የሚደረገው የወገብ ፈተና (ወይም የዱዓ ማራቶን) ግን ሱናን የተከተለ ባለመሆኑ ሊታረም ይገባል ባይ ነኝ።
ነገርግን ቁኑቱን በዱዓ ቢያስረዝመው ሶላቱ ይበላሻል አንልም። ቢሆንም ቅሉ ልሂቃን የተለያዩበት አጀንዳ በመሆኑ፣ [ድክመት ቢኖረውም] በሻፊዒያዎች ዘንድ ቁኑትን ከተለመደው በላይ ማስረዘም ሶላትን ያበላሻል የሚል ሃሳብ በመኖሩ ብንጠነቀቅ መልካም ነው።
ሶላትን የሚያክል ዒባዳ ለልሂቃን ውዝግብ ክፍት ማድረግ ሞኝነት ስለሆነ መጠንቀቅ ተገቢ ነው!

❤36👍20
🌙
ሰባተኛው ሌሊት መሆኑ ነው?!…
ኢላሂ! ረመዷናችንን የዓፊያ ረመዳን አድርገው። ካንተ ከሚቆርጠን ነገር ሁሉ ዳግም ላንገናኝ ቁረጠን። ኃጢኣት ካንተ የሚጋርደን ሒጃብ ነው። በምህረትህ ሒጃባችንን ግለጠው።…
* * *
ኢላሂ! ከኃጢኣት እስር፣ ከነፍሱ ምርኮ የዳነ ያንተን ከራማ፣ የፍቅርህን ስጦታ ያገኛል።… ከፍቅርህ በኋላና በፊት ደግሞ ከጀነት በቀር ምን አለ?!…
ኢላሂ! ይህንኑ ፃፍልን!
* * *
ረመዳን የተሸከመውን የችሮታ ክምር በእኛ ላይ አኑረው። የዘልዓለም አዝመራችንን የምናጭድበት፣ የእድሜ ልክ ትርፋችንን የምናካብትበት ፀደይ አድርግልን።…
አሚን!

❤93👍15
የተራዊሕ ህግጋት
ክፍል ሦስት
————————
⑪ በተራዊሕ ማኽተም
በተራዊሕ ሶላት ላይ በየረከዓው መቀራት ያለበትን መጠን በአስገዳጅ መልኩ የሚደነግግ ምንም አይነት ሸሪዓዊ መረጃ አልተገኘም። ኢማም የተከታዮቹን ዓቅም እና ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የመቅራት ኃላፊነት አለበት። ሶሓቦቹ በየረከዓው መቶ አንቀጾችን ይቀሩ እንደነበር ተዘግቧል። እንደውም በሰይዲና ዑስማን ጊዜ በረዥሙ ከመቀራቱ ብዛት ዱላቸውን ተደግፈው ሶላታቸውን ይሰግዱ ነበር።
ቁርኣን ለማኽተም በየቀኑ አንድ ጁዝእ ቢቀራ መልካም ነው። የጀመዓው ዓቅም እና ሁኔታ ታይቶ ግማሽ ጁዝእ ወይም ከዚያ ያነሰ ቢቀራም መልካም ነው። የሰጋጅ ቁጥር ያበረክታል፤ ተነሳሽነት ይጨምራል። ጀመዓው ዓቅምና ዝግጁነት ስላለው ሁለት ጁዝእ ወይም ከዚያ በላይ የሚቀሩ ጎበዞች እንዳሉም እናውቃለን።
ኢማሞች ለተከታዮቻቸው ገራገር ይሁኑ። ተከታዮችም በዚህ ምክንያት ችግር ከመፍጠር ይቆጠቡ። በረዥም መስገድ ያልቻለ ተቀምጦም ቢሆን ሶላቱን ይስገድ እንጂ በዚህ ሰበብ ሶላት እንዳይተዉ። የሙስሊም መሪዎች እና የመስጂድ አስተዳዳሪዎችም በተለይም ተቀራራቢ በሆኑ መስጂዶች ላይ ለሁሉም በሚሆን መልኩ የአንዱን ረዥም የሌላውን አጭር አድርገው ቢመድቡ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ።
⑫ ቁርኣን እያዩ መስገድ
ከመስሐፍ (ከታተመ የቅዱስ ቁርኣን ቅፅ) ወይም ከስልክ ላይ እየቀሩ መስገድ ይፈቀዳል። ይህ ብቻውል ለሚሰግድ ሰው፣ ለኢማም ወይም ኢማሙ ከተሳሳተ ለማረም ለተመደበ ሰው ነው። ምክንያቱም እነዚህ ቁርኣን ሊያስይዝ የሚችል በቂ ምክንያት አላቸው። ቁርኣን ይዘው እያዩ መስገድ የሚከለክል ሸሪዓዊ እገዳ ደግሞ የለም።
ነገርግን በዚህ ጊዜ በብዛት የሚስተዋለው ተከታዮች ሁሉ ቁርኣን ይዘው ወይም በስልካቸው እያዩ የሚሰግዱበት ሁኔታ መልካም አይደለም። ምክንያቱም በቂ ወይም አስገዳጅ ምክንያት ካለመኖሩ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችንም ያመጣል። ሰጋጆቹ በጥሞና እያዳመጡ በቁርኣኑ ቀልባቸውን ለመንካት ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ቁርኣኑን በመሸከም፣ በማገላበጥ፣ በስልኮቻቸው ላይ በሚመጡ ምስሎችና ተያያዥ ነገሮች እንዲዘናጉ ያደርጋቸዋል። በዚህም ከራሳቸው አልፈው ከጎናቸው የሚሰግድን ሰው እስከመረበሽ ድረስ ሲደርሱ ይስተዋላል። በተጨማሪም የቁርኣኑን በማይጠብቅ መልኩ ሲያንገላቱት ይስተዋላል። በመሆኑም ይህ አይነቱ ተግባር ቢቀር መልካም ነው።
⑬ በየእረፍቱ ዚክር ማድረግ
በየአራት ረከዓው እረፍት ማድረግ ከሶሐቦቹ ዘመን ጀምሮ የመጣ ልማድ ነው። በእረፍቱ ንቃትን ለመጨመር፣ ወኔ ለመፍጠር፣ ለመበረታታት ይጠቀሙበታል። እናም በዚህ የእረፍት ጊዜ ዚክር፣ ተስቢሕ፣ ቁርኣን፣ ምክር (ወዕዝ) ወይም ሶለዋት ቢደረግበት መልካም ነው። ዚክሩን በግልም ሆነ በጋራ ማድረግ ይቻላል። ይህንን የሚከለክል ምንም ዓይነት መረጃም የለም። ይሁንና ዚክሩ ግዴታ ነውም አንልም። የወደደው ይሰራዋል። የጠላውንም የሚያስገድደው መሰረት የለም።
ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ቦታዎች በሰጋጆች መካከል የሚፈጠረው የተካረረ ቁርሾና ፀብ ሸሪዓዊ መሰረት የሌለው ቅድሚያ የሚሰጠውን ኢስላማዊ አንድነትን እና ህብረትን የሚንድ ውጉዝ ተግባር ነው!
⑭ ተራዊሕን ለሌሊቱ ማካፈል
ተራዊሕን በሌሊቱ የተለያዩ ክፍለ ጊዜዎች ማከፋፈል ይፈቀዳል። ተራዊሕ በአንድ የጊዜ ገደብ ተከታትሎ መፈፀሙን የሚያስገድድ መሠረት የለም። ከዒሻእ በኋላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ከፋፍሎ መስገድ ይቻላል።
⑮ በስምንት በሚሰግድ ኢማም የተከተለ
ከዚህ በፊት እንደጠቀስነው አብዝሃኞቹ ልሂቃን በግልፅ እንዳሰፈሩት ተራዊሕ ሃያ ረከዓ ነው። ይሁንና ኢማሙ በስምንት ካበቃ ተከታዩ ለብቻው ሶላቱን ሃያ ረከዓ ቢሞላ መልካም ነው። ነገርግን ኢማሙ ከስምንት ረከዓ በኋላ ዊትር ከሰገደ ተከትሎት ይስገድ እንጂ ትቶት አይሂድ፤ ዊትሩንም ጥንድ (ሸፍዕ) አያድርግ።
አላሁ አዕለም!

❤44👍22