Telegram Web Link
ደርሳችን በጉዞ እና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ከረመዳን በኋላ ሳይቀጥል በመቆየቱ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በውስጥም ሆነ በአስተያየት መስጫ በኩል ውትወታ ስታደርጉ የነበራችሁ ወዳጆቼንም አመሰግናለሁ። እነሆ ዛሬ ካቆምንበት ኪታቡል‐ሐጅ ቀጥለናል። ወቅቱ የሐጅ እንደመሆኑም መልካም አጋጣሚ ነውና እየተከታተላችሁ። ሐጅ የተነሳችሁ ወዳጆች ካላችሁም ደርሱን እውቀት ለማግኘት እንደ አማራጭ ብትይዙትና ብታሰራጩት ደስተኛ መሆኔን እገልፃለሁ። አላህ በኸይር ስራ ተጠቃሚ ያድርገን!
30👍9
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል አርባ አምስት ፥ ኪታቡል‐ሐጅ 2
📆 ግንቦት 10/ 2017 ዓ. ል.
👍91
Forwarded from Tofik Bahiru
የ͟ተ͟ከ͟በ͟ሩ͟ ወ͟ራ͟ት͟
(አ͟ሽ͟ሁ͟ሩ͟ል͟‐ሑ͟ሩ͟ም͟)

አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
"إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ"
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
:
የተከበሩ ወራት አራት ናቸው:
⚀ ዙል‐ቀዕዳ (ቂዕዳ አትበሉ😊)
⚁ ዙል‐ሒጃ
⚂ ሙሐር‐ረም
⚃ ረጀብ
ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው። አንዱ ብቸኛ ነው። እርሱም ረጀብ ነው። በሂጅራ አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው።
:
ኢማም አል‐ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
[ከላይ የጠቀስነው አያ ውስጥ] ኃጢኣት በመፈፀም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ማለት ነው። ምክንያቱም የመልካም ሥራዎች ምንዳ እንደሚነባበረው ሁሉ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ኃጢኣትም ቅጣቱ ይነባበራል።
ቀታዳ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በተከበሩት ወራት የሚፈፀም በደል በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው እጅግ የከፋ ኃጢኣት ነው።»
:
ለነፍሳችን መዳን የምንመርጠው ጊዜ ላይ አለንና እናስብበት!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
👍105
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል አርባ አምስት ፥ ኪታቡል‐ሐጅ 3
📆 ግንቦት 11/ 2017 ዓ. ል.
1
የተወዳጁን ነቢይ [ﷺ] ታላቅነት ከሚያስረዱ የአላህ ስጦታዎች መካከል መሬት ውስጥ የርሳቸው ዝክር ያልተወሳበት ምንም ዘመን አለመኖሩ ተጠቃሽ ነው። ምድር ከተፈጠረች ጀምሮ እስከ ፍፃሜዋ ድረስ ያልተቋረጠ መታወስ ተከትቦላቸዋል። ምክንያቱም ከዘመን በቀደመው የሩሕ ዓለም ውስጥ ነቢያት ከሰይዲና አደም [ﷺ] ጀምሮ እስከ ቂያማ ያሉትን ሰብስቦ አላህ [ሱብሐነሁ] ቃልኪዳን አስገብቷቸዋል።

ነቢይ ሙሐመድ [ﷺ] በእነርሱ ዘመን ከመጡ ሊያምኑባቸው፣ ሊያግዟቸው እና ሊከተሏቸው፣ ለህዝባቸውም የርሳቸውን መምጣት እንዲያበስሩ አደራ ተጥሎባቸዋል። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐

«አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡»
:
አንጀት አረስርሱ ኢማም አል‐ቡሶይሪይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የሀምዚያ መድብላቸው ላይ አሳምረው ገልፀውታል: ‐

ما مضت فترةٌ من الرُّسْلِ إِلّا
بَشَّرَت قومَها بك الأنبياءُ

تتباهَى بك العصورُ وتَسمو
بِك علياءٌ بعدها علياءُ

«ከቶ አላለፈም የነቢያት ዘመን
አንቱ ሳያወሳ ሳያውጅ ጀብድሁን
መልክተኛው ነግሯል አለቅነትሁን
የሁሉ መላቂያው አንቱ መሆንሁን።
የቀን መፎከሪያ ከፍ ብሎ የሚታይ
ደምቆ የሚያፈካው አልቆ እንደ ሰማይ
የዘመናት ዝክር የዝንቱ ዳንኪራ
ተሰቅሎ የሚኖር የማይወርድ ባንዲራ
አንቱ መሆንሁን ይኖራል ሲያወራ
ሁሉም በየተራ!…
52👍8😍1
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል አርባ ስድስት ፥ ኪታቡል‐ሐጅ 4
📆 ግንቦት 13/ 2017 ዓ. ል.
👍8
የሙቀዲመቱ ባፈድል ኪታቡል‐ሐጅ እዚህ ድረስ ነበር። አላህ ካለ በሐጅ እና በዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት ዙርያ ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማከታተል እሞክራለሁ። እየተከታተላችሁ፣ ለሌሎችም እያጋራችሁ ቆዩኝ። ቻናሉ አሁን ካለው ተከታይ በላይ በሰፊው እንዲሰራጭና እንዲያድግ እንድታግዙኝም እጠይቃለሁ!
👍169
2025/10/27 13:46:43
Back to Top
HTML Embed Code: