❸ ጥቂት ተጨማሪ ሐሳብ
ሸሪዓ ሁሉንም ነገር የሚመዝንበት በነገሩ ላይ የተወሰነ ሚዛን አለው። ሁሉንም ጉዳይ የሚተነትንበት ልዩ የመረጃ ምንጭ አለው።
አንደኣንድ ክንውኖች ከነዝርዝራቸው ተብራርተው የተደነገጉ ዒባዳዎች የሚመዘኑት የቁርኣንና የሐዲስ አናቅጽ በመጥቀስ ብቻ ይሆናል። ስላስደሰተን ጭማሪ ማከልም ሆነ ስላልተመቸን መቀነስ ክልክል ነው። እነዚህን ዒባዳዎች በወሕይ በተብራራው መልኩ ከመፈፀም ውጪ ቅርጹን መለወጥ አልተፈቀደልንም። ማሻሻያ ለማድረግም እንዲሁ መብት አልተሰጠንም።
ዝርዝር አፈፃፀም እና ጥብቅ ገደብ ባልተቀመጠላቸው የዒባዳ አይነቶች ላይ አብዝሃኞቹ የእስልምና የዘርፉ ልሂቃን የተለየ ምልከታ አላቸው። ለሰዎች አስተንትኖትና የግል የአፈፃፀም አቅም ሰፊ ስፍራን ትተዋል። ዝርዝር የአፈፃፀም ሁኔታ ያልተደነገገላቸው ዒባዳዎችን ሰዎች ከራሳቸው አቅም እና አመቺ ሁኔታ በተከተለ መልኩ መተግበር እንዲችሉ ክፍተት እንደሚኖረው መክረዋል። ይህንን ሁኔታ ሊቃውንት ''ቢድዐ‐ኢዷፊያ'' ሲሉ ይገልጹታል። አብዝሃኞቹ ዐሊሞች ይፈቅዷቸዋል። [ወደፊት በሰፊው ለማብራራት እንሞክራለን ኢንሻአላህ።]
በሌላ በኩል ሸሪዐው ባህል እና ልማድን የሚመዝንበት የራሱ መለኪያም አለው። ሙሉ ለሙሉ ዒባዳ (አምልኮ) ሊሰኙ የማይችሉ ልማዶች (ዓደቶች) የሚመዘኑት በአንድ መሠረታዊ መርህ ነው: ‐
''الأصل في العادات الإباحة إلا إذا دل دليل صحيح صريح على حرمتها''
«ባህል (ልማዶች) መነሻ ታሳቢያቸው ፍቁድነት ነው። ይኸውም እርም የሚያደርጋቸው ትክክለኛ እና ግልፅ መረጃ እስካልመጣባቸው ድረስ ነው።»
ሸዋል ስምንት ላይ የሚደረገው የመዘያየርና ዘመድ አዝማድ የመጠያየቁ ድርጊት ከላይ እንዳስቀደምነው ሸሪዓዊ ዒድ ነው በሚል እምነት የሚከናወን ባለመሆኑ ልማድ፣ ወግ፣ ትውፊትና ባህል ያሰኘዋል። ተርታው ሰው በስም ደረጃ ዒድ ማለቱ የዒልም መድረክ ላይ የውይይት አጀንዳ የሚሆን ጭብጥ ሐሳብ የለውም። ዋናው የብይን መዘውር በእለቱ የሚከናወኑ ድርጊቶች ምንነት እና የፈፃሚዎቹ ግንዛቤና እምነት ነው። ስለዚህ ከላይ እንዳብራራነው ተመሳሳይ ተለምዶዎችን ስንዳስስ የምንነሳበት ታሳቢ ፍቁድነታቸው ሲሆን እርም የሚያደርጋቸው ትክክለኛ እና ግልፅ ምክንያት እስካልተገኘባቸው ድረስ የተፈቀዱ ሆነው ይቀጥላሉ።
አላሁ አዕለም!

👍35❤11
የረጋ ወተት
ማንኛውም መስአላ ላይ አስተያየት ከመሰጠቱ በፊት አራት ሂደቶች መታለፍ አለበት:‐
⏸ ተክዪፉል መስአላ/ጥያቄውን መግለፅ
ጥያቄን ከመመለስ በፊት የጥያቄውን ሁለገብ የሚያሳይ ፍኖተ‐ካርታ ማውጣት ያስፈልጋል። ጥያቄው ከየት መጣ? ምን ዓይነት ዐውድ አለው? በየትኛው የኢስላም ክፍል ውስጥ የሚካተት ነው? የጥያቄው ዳራና ድንበሩ ምንድን ነው?… ወዘተ
ከዚህ በኋላ ምርምር፣ ጥናት፣ ክርክር ይደረጋል። የጥያቄው ካርታ ሳይወጣ የሚደረግ ጥናት፣ ውይይትና ክርክር ፋይዳ ቢስ ነው፤ ወይም ስህተት ላይ ይጥላል።
⏺ ተእሲሉል መስአላ/ከትክክለኛ የመረጃ ምንጮች ጋር ማጣመር
ይህ ሁለተኛው ሂደት ነው። በጥያቄው ላይ ወይም በተመሳሳይ ወይም በተቀራራቢ ርዕሶች ላይ የተጠቀሱ ቅዱሳን ጥቅሶችን መሰብሰብ ቀዳሚ ስራ ነው። ሁለገብ የመረጃ ሜኑ ማቅረብ ተገቢ ነው። ከዚያም መረጃዎቹ እንደየደረጃቸው ይዘረዘራሉ። ደካማ ነው ተብሎ ሳይጠቀስ የሚቀር መረጃ አይኖርም። ሁሉም ይጠቀሳል።
🈁 ተሕሊሉል መስኣላ/ትንታኔ መስጠት
የቀረቡት መረጃዎችን በማጤን የመስኣላውን ዐውድ የጠበቀ፣ ዳር ድንበሩን ያልዘነጋ ትንታኔ መስጠት። በዚህ እርከን ላይ አንድ ሺህ ዓይነት እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ምላሾች ሳይቀሩ ይቀርባሉ። ይደረደራሉ።
🔶 ኢስቲኽራጁ ነታኢጅ/ውጤት ወይም አቋምን ማውጣት
በዚህ እርከን መረጃዎች ከጥያቄዎቹ ዐውድ ጋር በተነፃፃሪ ይተቻሉ። በምርመራው መሰረት የወደቁና ያለፉ ሃሳቦች ወይም ምላሾች ተለይተው ይቀርባሉ። አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለሐቅ የቀረቡ ሃሳቦች በአጥኚው ግምገማ መሠረት በቅደም ተከተላቸው እንደ ጥንካሬያቸው ይፋ ይሆናሉ።
:
🔴 ሐቅን መመርመርና እውነትን ለማግኘት ይህ ሁሉ ድካም አለው። ካርታ ሳታወጡ ምላሹን ለመመለስ አትሞክሩ ለማለት ነው። ሂደቶቹን ዘሎ ብይን መስጠት ያለ ጊዜው መውለድ ነው! ያለ ጊዜ መውለድ መጨንገፍ ነው! አደጋ ነው! መክሸፍ ነው!…

❤44👍22😍1
ማስታወሻ
ያለ ሸሪዓዊ ምክንያት ዘካቱል‐ፊጥርን ከዒድ ቀን መግሪብ ወቅት በኋላ ማቆየት ሐራም ነው። ኃጢኣት አለበት፤ በተጨማሪም ቀዷውን በአስቸኳይ ማውጣት አለበት። ቀዷውን ማቆየትም ተጨማሪ ኃጢኣት ሆኖ ይመዘግብበታል።
አሳማኝ ምክንያት ካለው ‐ለምሳሌ: ‐ ሊከፍልበት የሚችልበት ገንዘቡ በእጁ ከሌለና ዘካ የሚከፍልበት ገንዘብ ማግኘት ካልቻለ (ልሂቃን እንደሚሉት: ‐ ከሁለት ቀን ጉዞ ርቀት በላይ ገንዘቡ ከራቀ) ኃጢኣት አይኖርበትም። ነገርግን ገንዘቡ በእጁ ሲገባ ቀዷውን ማውጣት አለበት። ተበድሮ ዘካውን መስጠት ግዴታ አይሆንበትም።

👍21
ነገ ሰኞ ነው!
የሰዎች ስራ አላህ ዘንድ የሚቀርብበት ቀን ነው። «ጾመኛ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብ እሻለሁ!» የተባለበት ነው!
በዚያ ላይ ሸዋል እንደመሆኑ ሁላችንም ለመጾም እንነይት! ስድስቱን ያልሞላን ሰዎችም ጾማችንን እናሟላበት!
ሰዎችንም እንቀስቅስ!

👍84❤10
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
እርግጥ ነው የተወዳጁን የአላህ ነቢይ [ﷺ] ደረጃ የሚመጥን ምንም አይነት መልካም ነገር አይኖረኝም!… ይህንን የምለው ለትህትና አይደለም!…
እንደውም ከኔ ትንሽነት ከፍ ብለን የዓለም የሁሉ ዘመን ታላላቆች ተሰብስበው በኡመታቸው ላይ ለዋሉት ውለታ የሚስተካከል ምስጋና ሊያደርሱ ቢሹ እንኳን ከርሳቸው ልቅና አንፃር ልፋታቸው ሁሉ ኢምንት ነው!…
ነገርግን ስለርሳቸው ስናገርም ሆነ ሶለዋት ሳወርድ የሚሰማኝ ስሜት ወይም እንዳገኝ የምመኘው ትልቁ ነገር አንድ ነው። ሸፈዐቸውን ማግኘት!…
ምናልባት የቂያም ቀን ስንሰበሰብ ስለርሳቸው ስናገር የሰማ፣ የፃፍኩትን ያነበበ፣ ሶለዋቴን የሰማ ወይም ያየ አንድ ሰው እንኳን አገኝ ይሆናል ብዬ ነው። ያኔ እጄን ይዞ ከፊታቸው አቁሞኝ: ‐ «ያረሱለላህ! ይህ ሰው ስለርሶ ነግሮኝ እንድወዶት አድርጎኛል። ቅስቀሳው በርስዎ ላይ ሶለዋት እንዳበዛ አድርጎኛል።»… ብሎ መስክሮልኝ ቀልባቸውን ያራራልኝ ይሆናል፤ በቅርባቸው እንድቀመጥ ምክንያት ይፈጥርልኝ ይሆናል ብዬ ነው።
ከዚያ ውጪ እርሳቸውም እርሳቸው ትልቁ፣ እኔም እኔው በጣም ትንሹ ነኝ። ከኔ ወደርሳቸው ልገሳ የማደርገው ነገር የለኝም!
#ቢአቢ #ወኡሚ #ሰይዲ #ረሱለላህ

❤68👍9😢3
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
የተከበረው እጃቸው በምንም ነገር ላይ ሲያርፍ የዚያ ነገር ምንነት ይቀየራል። በሽተኛ ላይ ካረፈ ይድናል። ተክል ላይ ካረፈ ይፀድቃል፤ ይፋፋል፤ ያፈራል። ምግብ ላይ ካረፈ ይባረካል፤ ይበዛል። ውሃ ላይ ካረፈ ይንቧቧል፤ ይጎርፋል። ቀልብ ላይ ካረፈ ይረጋል፤ ይሰክናል። ጭንቅላት ላይ ካረፈ ይፀናል፤ ይነቃል። እጅ ላይ ካረፈ የትም ባልተገኘ ሽታ ይታወዳል። ለበርካታ ቀናት በማይጠፋ መዓዛ ይታጠናል።
የነቢያችን [ﷺ] እጅ እንዲህ ነበር!
#ሶሉ ዐለይሂ
የነቢያችን [ﷺ] እጅ እንዲህ ነበር!
#ሶሉ ዐለይሂ
❤106😍3👍2
Audio
ጁሙዐ ቀን ከዐስር በኋላ
================
ኢማም አድ‐ዳረቁጥኒ፣ አልሐፊዝ አስ‐ሰኻዊ፣ ኢማም አል‐ገዛሊ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በጁሙዐ ቀን ሰማንያ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያደረገ ሰው የሰማንያ ዓመት ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል።»
ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዴት ብለን ሶለዋት እናድርግቦት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «እንደዚህ በል አሉ: ‐
" اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ"
«አላሁም‐መ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ዐብዲከ ወነቢይ‐ዪከ ወረሱሊከ አን‐ነቢይ‐ዪል ኡም‐ሚይ‐ይ»
ይህንን አንድ ብለህ ቁጠር።»
:
ሰማንያ ስትሞላ በአላህ መልክተኛ ላይ ሰላምታን በማድረግ ጨርስ። «ሶለ‐ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም» በል።»
:
ያያያዝኩላችሁ የድምፅ ፋይል በዘመናችን ከነበሩ ታላላቅ የተሰዉፍ ሰዎች መካከል የነበሩት ሸይኽ ረጀብ ዲብ ከሙሪዶቻቸው ጋር ሶለዋት ሲያደርጉ የተቀረፀ ነው። ትንፋሻቸው ወኔያችንን ከቀሰቀሰ በማለት የተለጠፈ ነው!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1198

❤26👍8
አንድ ሰው እንዲህ አለ: ‐
«ወላሂ! አላህ እገሌን አይምረውም።»
አላህ ደግሞ በምካሹ እንዲህ አለ: ‐
«ማነው እኔ እገሌን እንደማልምር በእኔ እየማለ የሚናገረው?!…
በእርግጥ እኔ እገሌን ምሬዋለሁ። ያንተን ስራ ግን አበላሽቻለሁ!»
📜ኢማም ሙስሊም ጁንዱብ ኢብኑ ጁናዳን ዋቢ አድርገው ዘግበውታል።

❤28😢10👍4
🔶 ለቀልብ ባለቤቶች!
ጀላሉዲን አር‐ሩሚ [ቁዲሰ ሲሩሁ] በመንገድ ላይ ሲሄዱ መንገዳቸውን የሚያቋርጥ የተኛ ውሻ ገጠማቸው። ውሻውን ለመቀስቀስ ተሳቀው ተቀምጠው መንቃቱን መጠባበቅ ጀመሩ። መቸገራቸውን ያየ ልቅናቸውንና ሐያኣቸውን የሚያውቅ ሰው ግን ውሻውን ቀሰቅሶ ከመንገድ አስነሳው።
መውላና: ‐ «ለምን ቀሰቀስከው?! አዛ አደረግከው!» በማለት ተቆጡ።
በሌላ ጊዜ በመንገድ ላይ ሳሉ ሁለት ሰዎች ሲጣሉ፣ ሲዘላለፉ ደረሱ። አንዱ በሌላው ላይ ሲዝት እንዲህ አለ: ‐
«አንድ ጊዜ ብትሰድበኝ ዐስር አድርጌ እመልስልሃለሁ!»
ሩሚም: ‐ «በእናንተ ፈንታ እኔ አለሁላችሁ፤ ዝለፉኝ። ሺህ ብትሰድቡኝ አንድ አልመልስላችሁም።» በማለት እንዲታረቁ ገሰጿቸው። ሰዎቹም በድንጋጤ እግራቸው ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቅ እርቅ አደረጉ።»
:
🌟 እኛ እርስ በእርሳችን አዛ መደራረግን ሱስ አድርገን እንደያዝነው ትልልቆቹ ዝቅተኛ ተብሎ የተገመተች ነፍስን መንከባከብን እንኳን ወደ አላህ መድረሻ መንገድ አድርገው ይዘውታል!…
አላህ ያግራልን!

❤84👍20
«የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ሥራውን የሚሰራ ህላዌ [ዛት] ነው። ህይወት ሲያበቃ ደግሞ ስራው እርሱን ዘልዐለማዊ የሚያደርግ ህላዌ ይሆናል። መልካም ከሰራ መልካም ሆኖ ለዝንተዐለም ይዘልቃል። ክፉ ከሰራም በክፋቱ ዝንተዐለም ይዘወትራል። ሞት ማለት ሩሕ ከሥራዋ የምትወለድበት ክስተት ይመስላል። ሩሕ ሁለቴ ትወለዳለች። አንዴ ወዲህ ስትመጣ፤ ሌላም ወደመጣችበት ስትሄድ።»
ሙስጠፋ ሳዲቅ አር‐ራፊዒይ፥ ወሕዩል‐ቀለም
ሙስጠፋ ሳዲቅ አር‐ራፊዒይ፥ ወሕዩል‐ቀለም
❤43😢14👍12😍1
Forwarded from Tofik Bahiru
ታላቁ ታቢዒይ አቡ ዐብዲር‐ረሕማን አስ‐ሱለሚይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከጁሙዐ በፊት አራት ከበስተኋላዋ አራት እንድንሰግድ ያዙን ነበር።»
ዐብዱረዛቅ "አል‐ሙሶነፍ" በተሰኘው ኪታባቸው ዘግበውታል። አል‐ሀይተሚይ "ዘጋቢዎቹ ታማኞች ናቸው።" ብለዋል።…
ይህ የሱፍያን ሰውሪይ፣ የዐብዱላህ ኢብኑል‐ሙባረክ እና የሌሎቹም የሰለፍ ልሂቃን መዝሀብ ነው። ጁሙዐ እንደ ዙህር ከበስተፊቷ አራት ከበስተኋላዋ አራት ረከዐ ሱና አላት። «ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ዒባዳዎች ሁሉ ምርጧ ናት!»
ባረከላሁ ፊኩም!

❤41👍16😢2