Zakat Al fitr 2023.pdf
3.5 MB
ታላቁ የዒራቅ ዓሊም የኢማማችን ሻፊዒይ ሸይኽ ኢማም ወኪዕ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ለወርሀ ረመዳን ዘካቱል‐ፊጥር ማለት ለሶላት የመርሳት ሱጁድ ማለት ነው። የመርሳት ሱጁድ የሶላቱን ጉድለት እንደሚጠግነው ዘካቱል‐ፊጥርም የጾሙን ጉድለት ይጠግነዋል።»
:
ይህንን ፅሁፋችንን በማንኛውም መንገድ አሰራጩ። በግልም ሆነ በጀመዓ ተማማሩበት። ዒባዳችሁን በእውቀት አድርጉት። አላህ ስራዎቻችንን ይቀበለን!

👍31
ዘካን በውክልና ማከፋፈል
ለዘካቱል‐ፊጥር የሚደረግን እህል በመግዛትም ሆነ፣ የዘካን ገንዘብ ለሚገባቸው ሰዎች በማከፋፈል ሥራ ላይ ዘካ ሰጪው ሌላን ሰው መወከል ይችላል።
ኢማም ነወዊይ "አል‐መጅሙዕ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለፁት ይህ የልሂቃን ልዩነት የሌለበት ሙሉ የመዝሀባችን ሰዎች የተስማሙበት ሃሳብ ነው።
«ዒባዳ (የአምልኮ ተግባር) ከመሆኑ ጋር ውክልና የተፈቀደው በባህሪው [ዘካ] እዳን ከመክፈል ጋር ይመሳሰላል። በተጨማሪም ገንዘቡ ዘካ አውጪው ካለበት አካባቢ ሩቅ መሆኑ እና ሌሎችም ምክንያቶች አሉ።»
ማወከል ቢፈቀድም ቅሉ ሰውየው ራሱ ዘካውን ማከፋፈሉ በላጭ ወይም ተመራጭ ነው። ይህ ቤተሰብ ስለ ዘካ እንዲያውቅ፣ በረከቱን አንዲቋደስ፣ በማከፋፈል ስራው ላይ እንዲሳተፍ በር ይከፍታል። ድምቀቱንም በቤት ውስጥ ያስተጋባል። ምናልባት ከጊዜ በኋላ ስለ ዘካ የማያውቅ እና አተገባበሩን ያልተረዳ ትውልድ አንዳይፈጠርም ይታደጋል።
ኢማም ነወዊይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ባልደረቦቻችን (ሻፊዒዮች) እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሌላን ሰው ከመወከል ዘካቱል‐ፊጥርን በራስ ማከፋፈል ይበልጣል። በዚህ ላይ ልዩነትም የለም። ምክንያቱም ሰውየው በትክክል መከፋፈሉን ማረጋገጥ ይችላል። ወኪል ሲሆን ግን በትክክል መከፋፈሉ ላይ እርግጠኛ መሆን ሊቸግረው ይችላል። ተወካዩ አደራውን ክዶ ሳይሰጥ ቢቀር ከባለ ዘካው ላይ ግዳጁ አይወድቅም። ምክንያቱም የወኪሉ እጅ እንደ ባለ ዘካው እጅ ነው። ለባለ ሐቆቹ ዘካው እስካልደረሰ የባለ ዘካው ጫንቃም ከእዳው አይጠራም።»
በዚህ መሰረት ሰውየው ዘካውን ለግለሰብ ወይም ለድርጅት ቢሰጥ ለተወካዩ አካል በመስጠቱ ብቻ ጫንቃው ከግዳጁ አይጠራም። ወኪሎቹ በተገቢው ጊዜ ለባለ ሐቆች መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ ወኪሉ ዘካውን ተቀብሎ በእጁ ላይ ቢያቆይ እና ለተገቢዎቹ ሰዎች በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ ቢቀር ክልክል የሆነ ነገር ተከስቷል። ዘካው የወጀበበት ሰው ጫንቃም ከግዳጁ አይጠራም።
ዘካው መዘግየቱን ዘካ አውጪው የሚያውቅ ከሆነ ደግሞ ወንጀል አለበት። ካላወቀ ግን ወንጀል አይኖርበትም። በወኪሉ እጅ እንዳለ ዘካው ቢወድም በእሱ እጅ እያለ ቢወድም እንደሚያደርገው በቦታው የድሆቹን ሐቅ መተካትና ለሚገባቸው አካላት ማድረስ ይጠበቅበታል።
አላሁ አዕለም!

👍15❤5
ታላቁ ታቢዒይ አቡ ዐብዲር‐ረሕማን አስ‐ሱለሚይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከጁሙዐ በፊት አራት ከበስተኋላዋ አራት እንድንሰግድ ያዙን ነበር።»
ዐብዱረዛቅ "አል‐ሙሶነፍ" በተሰኘው ኪታባቸው ዘግበውታል። አል‐ሀይተሚይ "ዘጋቢዎቹ ታማኞች ናቸው።" ብለዋል።…
ይህ የሱፍያን ሰውሪይ፣ የዐብዱላህ ኢብኑል‐ሙባረክ እና የሌሎቹም የሰለፍ ልሂቃን መዝሀብ ነው። ጁሙዐ እንደ ዙህር ከበስተፊቷ አራት ከበስተኋላዋ አራት ረከዐ ሱና አላት። «ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ዒባዳዎች ሁሉ ምርጧ ናት!»
ባረከላሁ ፊኩም!

❤11👍11
አሁን የመስጂዳችን ኢማም ታላቁ ዓሊም ሸይኽ መኑል‐ከሪም [አላህ ያቆያቸው] ሲናገሩ እንደሰማሁት (ስለ ዘካቱል‐ፊጥር ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ): ‐
— ዘካቱል‐ፊጥርን በገንዘብ መስጠት የኢማም አቡ ሐኒፋና የተወሰኑ ልሂቃን መዝሀብ ነው።
— አብዝሃኞቹ ልሂቃን ዘካቱል‐ፊጥር በእህል እንደሚሰጥ ያምናሉ።
— ከዚህ ቀደም በገንዘብ ምን ያህል እንደሚደርስ እናገር ነበር። አሁን ግን የተለያዩ ዋጋዎች ስለደረሱኝ መወሰን አልቻልኩምና በራሳችሁ ዋና አጣርታችሁ የሁለት ኪሎ ተኩል ስንዴ ዋጋ ስጡ።
🔴 ወንድማችሁ (ተውፊቅ ባህሩ) የገበያውን ዋጋ አጣርቶ አማካዩን በመያዝ የሁለት ኪሎ ተኩል ስንዴ ዋጋ በአማካይ 237.5 ሳንቲም እንደሚመጣ ገምቷል።
—ለነገሩ ሸይኻችንም ለመጠንቀቅ 250 ብር አውጡ ብለዋል።

❤58👍18
«እኔ ስሜ ዐመር አል‐ጀማሲይ ይባላል። ስሙ ዐብዱል‐ከሪም አን‐ነይረብ የሚባል ልጅ አንድ ሼክል እዳ አለብኝ። ዐብዱል‐ከሪም አቡ ናፊዝ ጎዳና አካባቢ የሚኖር ልጅ ነው።…
እኔ እወዳችኋለው። ሶላት እንዳትተዉ አደራ እላለሁ። ቁርኣን መቅራት እና ኢስቲጝፋር ማድረግ እንዳትተዉ!»
ይህ በቅርብ ከነቤተሰቡ የተሰዋ የጛዛ ህፃን ወሲያ ነው።…
አላህ ከመከራው ያውጣቸው። ቁስለኞቻቸውን ያሽር። ታጋዮቻቸውን ይርዳ። ትግላቸውን ፍሬያማ ያድርገው።
በዱዓ አትርሷቸው!

❤54😢24👍4
የመጨረሻው የረመዳን ሌሊት:
የኢማም አሕመድ [ሙስነድ] የተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ አሉ: ‐
«[በረመዳን] በመጨረሻው ሌሊት [ለህዝቦቼ] ሁሉ ምህረት ይደረግላቸዋል።»
ሰዎችም: ‐ «ለይለቱል‐ቀድር እርሷ ናት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «በፍፁም! ነገርግን [ተቀጣሪ] ሠራተኛ ሥራውን ሲጨርስ ደመወዙ ይሰጠው የለ?!» በማለት መለሱ።»
:
አላህ ሆይ! ሥራዎቻችንን ውደድልን። በእዝነትህ ሸፍነህ ካለብን ክፍተት ጋር ተቀበለን!

❤86👍15😢9
Forwarded from Tofik Bahiru
የአባዬ_ሾንኬ_ተክቢራ_ኪታብ_Shonke_Nessim_Almuhaba.pdf
13.6 MB
የተዋበውና በብዙ መልክቶች የታጀበው የአባዬ ሾንኬ የተክቢራ ኪታብ ነው። ከላይኛው የአባቶቻችን ድምፅ ጋር ቤተሰብ ሰብስባችሁ ዒዳችሁን አድምቁ።
እንኳን አደረሳችሁ!
እንኳን አደረሳችሁ!
👍19❤6
እንኳን ለዒድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አመት ለአመት ያድርሰን!
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
❤56👍12
ከዓኢሻ [ረዲየላሁ ዐንሃ] እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ያገቡኝ በሸዋል ወር ነው። ጫጉላ ይዘውኝ የወጡት በሸዋል ወር ነው። እርሳቸው ዘንድ ከነበሩት ሚስቶቻቸው እንደኔ የታደለች ማን አለች!» ሙስሊም ዘግበውታል።
ይህንን ሐዲስ ከጠቀሱ በኋላ ኢማም ነወዊይ ሸርሕ ሙስሊም ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሸዋል ከገባ በኋላ ማግባት፣ መዳር እና ጫጉላ ማድረግ ይወደዳል።»
:
…ያው ለማስታወስ ነው!
ያገባችሁ ሸዋል ሳይወጣ የስድስቱን ቀን ጾማችሁን ጨርሱ!…
ላጤዎችም ሸዋል ሳይወጣ እንደምንም ብላችሁ አግቡ!…😊
… በመጨረሻም የሚያስደነግጥ ማስታወሻም አለኝ። ከስር ያለውን አንብቡ። ስድብ አይደለም!😊
:
«…ያለ ሴት (ያለ ሚስት) የሚኖር ወንድነት ያለ እውቀት ከሚኖር ዓቅል ጋር በጣም ይመሳሰላል። ይህኛው የደነዘዘ ዐቅል ሲሆን ያኛው ደግሞ የደነዘዘ ወንድነት ነው!
ሴት የህይወትን ትርጉም በብዙ መጠን ታበዛለች። ስለዚህ ያለጥርጥር ያለ ሴት የሚገፋ እድሜ ደግሞ የሞትን ትርጉም በብዙ እጥፍ ያበዛዋል። ይህንን እውነታ የሚያውቅ ያውቀዋል፤ የማያውቅ አያውቀውም!…»
🥀ወሕዩል‐ቀለም፥ ሙስጦፋ ሷዲቅ አር‐ራፊዒይ🥀

👍31❤8🤔4😢1😍1
Forwarded from Tofik Bahiru
የሸዋል የሸዋል ጾም
============
ከአቡ አዩብ አል‐አንሷሪይ [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን ጾሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው ይህ ዓመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል።
ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን የጾመ ከዚያም ከፊጥር በኋላ ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠራል። አንድን መልካም ስራ የሰራ ሰው በዐስር አምሳያዎቹ ይባዛለታል።» ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
:
የመልካም ስራ ምንዳው በዐስር ይባዛል። ስለዚህ የረመዳን ጾም በዐስር ሲባዛ ዐስር ወራት ይሞላል። የሸዋል ስድስት ቀናት በዐስር ሲባዙ ስድሳ ቀናት ይሆናሉ። ሁለት ወር ማለት ነው። ስለዚህ ሰውየው ሙሉ አመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።
:
የዒድ ማግስትን ማስከተል
=================
በሁለቱ ሐዲሶች መሰረት ስድስቱን ቀን ከዒዱ ቀን ማግስት ጀምሮ በመሀል ምንም ክፍተት ሳይኖር መጾም እንደሚወደድ ያመለክታሉ። ሻፊዒዮቹ ይህንን ሃሳብ ይመርጣሉ። ምክንያቱም በዚህ መንገድ መልካም ስራን በማከታተሉ ጾሙን እንዳይተወው ያግዘዋል። በሰፊው የሀገራችን ክፍል ከአባቶቻችን ጀምሮ የለመድነው አካሄድም ይህንን መሰረት ያደረገ ነው።
:
በእርግጥ ሐዲሶቹ ቀናቶቹን አከታትሎ መደርደር መልካም መሆኑን በይበልጥ የሚያመለክት ስሜት ቢኖራቸውም ቀናቶቹን አለያይቶ እያረፉ መጾም ችግር እንደሌለውም ይጠቁማሉ።
ስለዚህ ከዒዱ ዋዜማ አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ የጾመ ሰውም ሆነ አዘግይቶ ሰብስቦ በማከታተል ወይም እያረፈ ነጣጥሎ የጾመ ሰው ሱናውን አግኝቷል። ይህ ሻፊዒዮቹ፣ አሕመድ እና አብዝሀኞቹ ዑለሞች ዘንድ የተረጋገጠ ሃሳብ ነው።
:
ሐነፊዮቹ ተመራጭ ያደረጉት ሃሳብ ስድስቱን የሸዋል ቀናት መጾም ችግር የለውም [ይወደዳል ሳይሆን] የሚለውን ሃሳብ ነው። በእርግጥ ከሐነፊዮች ከፊሎቹ አከታትሎ መጾም ይጠላል ያሉበት ሁኔታም ነበር። ለዚህ ድምዳሜ ምክንያት ያደረጉት ከሸዋል ስድስት ቀን መጾም ከረመዳን ጋር እንዳይመሳሰል ወይም ተጨማሪ ግዳጅ እና ድንጋጌ እንዳይመስል መስጋታቸውን ብቻ ነው። ከኢማም ማሊክም ተመሳሳይ ሃሳብ ተሰንዝሯል። ነገርግን የዒድን ቀንን በማፍጠር ከረመዳን ጋር የመመሳሰል ስሜቱ ስለሚጠፋ ሸዋልን መጾሙ ችግር የለውም የሚለውን ሀሳብ ብዙዎቹ ሐነፊዎች መርጠውታል። "አልሂዳያ" "አልጋያ" የተሰኙ መፅሀፍቶቻቸው ይህንን አብራርተዋል።
:
በርግጥም ከላይ የጠቀስናቸው ሐዲሶች የስድስቱ የሸዋል ቀናት ጾም ተወዳጅ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ሐዲሶቹ መከራከሪያ ለመሆን ብቁ የሆኑ ግልፅ መረጃዎች ናቸው። ስለዚህ ሳንጠራጠር በዚሁ መንገድ መጓዝ እንችላለን።
:
ከሌላ ኒያ ጋር ማቆራኘት
===============
የስድስቱ ቀን ጾም ላይ ቀዳእን ጨምሮ በመነየት መጾም ይፈቀዳል። ሰውየው የሁለቱንም ምንዳ ያገኛል። ኢማም ሲዩጢይ [ረዐ] 'አል‐አሽባህ ወን‐ነዟኢር' በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐ "ለምሳሌ በዐረፋ ቀን ከዐረፋ ጾም ጋር ቀዷእን፣ የስለት ጾምን፣ ከፋራን… በአንድ ላይ ነይቶ መጾም አስመልክቶ እንደሚፈቀድና ምንዳውም እንደሚገኝ አል‐ባሪዚይ ፈትዋ ሰጥተዋል። እንደውም እለቶቹን ልቅ በሆነ የጾም ኒያ ቢያሳልፈውም የስድስቱን የሸዋል ጾም ምንዳ ያገኛል ብለዋል። እርሳቸው የሸዋልን ጾም በተሒይ‐የቱል‐መስጂድ ሶላት መስለውታል።"
ማንኛውም ሰው መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዐና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሶላት ቢሰግድ ተሒያን ቢነይትም ባይነይትም የተሒያውን ምንዳ እንደማያጣው፣ ፈርድ ወይም ሱና ሲሰግድ አብሮ ተሒያን መነየት እንደሚፈቀድለት ሁሉ የሸዋል ጾምም በዚሁ አኳያ መታየት አለበት እያሉ ነው።
ምክንያቱም ተሒይ‐የቱል መስጂድ ያስፈለገው ሰውየው መስጂድ ሲገባ ከመቀመጡ በፊት ሶላት እንዲሰግድ ማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ በማንኛውም ሶላት ይህንን ማሳካት ስለሚችል ተሒያውን ያገኘዋል።
የተሒይ‐የቱል መስጂድ ድንጋጌን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "እያንዳንዳችሁ መስጂድ ስትገቡ ሁለት ረከዐ ሳትሰግዱ አትቀመጡ።"
በሸዋል ወር ያሉት የስድስት ቀናት ጾምንም አል‐ባሪዚይ እና በርካታ መሰሎቻቸው እንደዚሁ ተመልክተውታል።
በዚህ መሰረት ሱና ጾም በፈርድ ውስጥ መካተት እንደሚችል ዐሊሞች [በተለይ ሻፊዒዮች] ጠቁመዋል። ነገርግን ፈርድ ጾም በሱና ጾም ኒያ ውስጥ መካተት አይችልም።
:
ስለዚህ ሴቶች በረመዳን በወር አበባ ምክንያት ያመለጣቸውን ከሸዋል ጾም ጋር በአንድ ላይ በመነየት ቀዳቸውን መክፈል ይችላሉ ማለት ነው።
ነገርግን በቅድሚያ ቀዷቸውን ቢከፍሉ ከዚያም ሸዋል ሳይወጣባቸው የሸዋልን ጾም ቢጾሙ፤ ወይም በተቃራኒው መጀመሪያ የሸዋል ስድስቱን ጾም አስቀድመው ቢጾሙ ከዚያም ቀዳቸውን አስከትለው ቢከፍሉ የተሻለ ነው። ምክንያቱም ደርቦ በመጾም ምንዳ ያገኛል ማለት ነጣጥሎ በመጾም የሚገኘውን የተሟላ ምንዳ ያገኛል ማለት አይደለም። ነጣጥሎ በተለያዩ ጊዜያት ኒያውን ሳያደራርብ የጾመ ሰው ኒያዎችን አደራርቦ ከጾመ ሰው የበለጠ ምንዳ አለው።
:
ኢማም ረምሊይ [ረዐ] እንዲህ ይላሉ: — "በሸዋል ወር ቀዳእን፣ ስለትን እና ሌሎች ጾሞችን የጾመ ሰው የሸዋል ሱና ጾምን ምንዳ ያገኛል። ይህ አባቴ [ረሒ] አል‐ባሪዚን፣ አል‐አስፈዊን፣ አን‐ናሺሪን፣ አል‐ፈቂህ ቢን ሷሊሕ አል‐ሐድረሚን እና ሌሎችንም ዋቢ በማድረግ የሰጡት ፈትዋ ነው። ነገርግን ረመዳንን በስድስት የሸዋል ቀናት ጾም አስከትሉት የተባለበትን የተሟላ ምንዳ አያገኝም።"
:
የስድስቱ ቀናት የሸዋል ጾም በፈርዱ ላይ የተከሰተን ጉድለት ይሞላል። የረመዳን ጾም ተቀባይነት ማግኘቱን ይጠቁማል። ምክንያቱም መልካም ስራ ተቀባይነት ማግኘቱን ከሚጠቁሙ ምልክቶች መሀል አንዱ ወዲያው መልካም ስራን ማስከተል ነው። ሰውየው አላህን ማምለክ እንደማይሰላች ማረጋገጫም ይሆናል።
የሸዋል ጾምም ሆነ የማንኛውም ሱና ጾምን ኒያ በሌሊት ብቻም ሳይሆን እስከ ዙህር ባለው ሰዓት ማስገኘት ይቻላል።
:
በመልካም ነገር ላይ እንተጋገዝ። እንዘያየር። በሸዋል ጾም አደራ እንባባል።
መልካም ዒድ!
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

👍15❤9
Forwarded from Tofik Bahiru
ስለ ሸዋል ጾም ተጨማሪ ሃሳቦች
=================
عَنْ أَبي أَيوبِ رضي الله عنه، أَنَّ رسولَ اللَّهِ [ﷺ] قَالَ: مَنْ صَامَ رَمَضانَ ثُمَّ أَتَبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كانَ كصِيَامِ الدَّهْرِ رواهُ مُسْلِمٌ.
وفي رواية "فكأنما صام السنة كلها"
«ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው እድሜውን (ደህር) ሁሉ እንደጾመ ይሆንለታል።»
ሙስሊም አቡ አዩብ አል‐አንሷሪን በመጥቀስ ዘግበውታል።
በአሕመድ ዘገባ: ‐ «አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል።»
:
⚀ ትርጉም: ‐ «ሁሌም ከረመዳን በኋላ ስድስት የሸዋል ቀናት የጾመ ሰው እድሜውን በሙሉ ፈርድ ጾም እንደጾመ ይቆጠርለታል ማለት ነው።»
ኢብኑ ቃሲም ዐለት‐ቱሕፋ፥ ቅፅ 3፥ ገፅ 457
«የስድስቱን ቀን ጾም እያለፈ ከጾመ ደግሞ የጾመበት አመት ላይ ዓመቱን በሙሉ [ፈርድ] እንደጾመ ይቆጠርለታል። ካልጾመ ግን ዐስሩን ወር ብቻ እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ቡጀይሪሚ ዐለል‐ኸጢብ፥ ገጽ 2682
ወይም የመጀመሪያውን ዘገባ ከሁለተኛው ጋር በማመሳከር "ደህር" ማለት "ዓመት" ማለት ነው ልንል እንችላለን።
:
⚁ በዚህ መሰረት ከረመዳን በኋላ ስድስቱን በመጾም ሰውየው የሚያገኘው ጥቅም ዓመቱን በሙሉ ፈርድ እንደጾመ መቆጠሩን ነው። አለበለዚያ አመቱን በሙሉ ሱና እንደጾመ ይቆጠርለታል ማለት ነው ካልንማ በሌላው ወር ከሚገኘው ትሩፋት የተለየ ነገር በሸዋል አይገኝም ማለት ይሆንብናል።
ለምሳሌ: ‐ ረመዳንን ጾሞ ከዙል‐ቀዕዳ ወር ስድስት የጨመረ ሰውም አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል። በቀላሉ የረመዳንን ጾም በዐስር አባዝተን የ10 ወር ጾም ስድስቱን እንዲሁ በ10 አባዝተን የሁለት ወር ጾም በማድረግ የዓመት ሱና ጾም ጾመናል ማለት ይቻላል። ነገርግን የሸዋል ጾም ከሌላው ይለያል። ዓመቱን ሙሉ ፈርድ እንደጾምን እንዲታሰብልን ያደርጋል። በዚህ ምክንያት ነው ሸዋል ተለይቶ የተነገረን።
:
⚂ ረመዳን በሃያ ዘጠኝ ቀን ቢያልቅም እንኳን ሰውየው የተጠቀሰውን ምንዳ ማግኘቱ አይቀርም።
ኢማም ኢብኑ ሙለቅ‐ቂን ቱሕፈቱል‐ሙሕታጅ፥ ቅፅ 5፥ ገፅ 229 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «የሰውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሐዲስ በነሳኢይ 'ሐሰን' በሆነ ሰነድ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የረመዳን ወርን መጾም በዐስር ወር ይባዛል። የስድስቱ ቀን ጾም ሁለት ወር ይሆናል። ይኸውም ዓመት ሙሉ እንደመጾም ይቆጠራል።»
ይህ ሐዲስ እንደሚያመለክተው የረመዳን ወር ሙሉ [ሰላሳ ቀን] ቢሆንም ጎዶሎ [ሃያ ዘጠኝ ቀን] ቢሆንም ልዩነት እንደማይፈጠር ነው። የረመዳን ወር መነባበር የሚገኘው ቀኑን ታሳቢ በማድረግ ሳይሆን ወሩን በማሰብ መሆኑን ሐዲሱ ይጠቁመናል።»
የኢማም ኢብኑል‐ሙለቅ‐ቂን ቃል እዚህ ድረስ ነበር።
:
⚃ ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስቱን ያስከተለ ሰው ዓመቱን በሙሉ ፈርድ እንደጾመ ይቆጠራል። አመቱን ሳይጨርሰው ቢሞት እንኳን ያልደረሰበት የዓመቱ ክፍል ምንዳው ይከተለዋል።
«አካላዊ ዒባዳ ሰውየው ከሞተ በኋላ ሰው ተክቶት ሳይፈፅምለት ምንዳው በራሱ ተከትሎት መቀጠሉ የሚገርም [እንግዳ] ነገር ነው!»
ኢማም ኢብኑል‐ሙለ‐ቅ‐ቂን፥ ቅፅ 5፥ ገፅ 230
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

👍15
ረመዳን ሃያ ዘጠኝ መሆኑ እና የሸዋል ጾም ትሩፋት
የዓመቱ የረመዳን ወር ቀናት ሃያ ዘጠኝ ቢሆን የሸዋል ወር የስድስቱ ቀን ጾምን ትሩፋት ለማግኘት የሠላሳኛውን ቀን ማካካሻ አንድ ተጨማሪ ቀን መጾም አይጠበቅም።
ምክንያቱም የሸዋል ጾምን ትሩፋት የሚነግሩት ሐዲሶች በሙሉ ረመዳን ወርን የጾመ ይላሉ እንጂ ሠላሳ ወይም ሃያ ዘጠኝ የረመዳን ቀናትን የጾመ በሚል አልለዩትም። ስለዚህ ረመዳን ወርን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን በመጾም ያስከተለ ሰው ሁሉ ምንዳውን በተሟላ ሁኔታ ያገኛል።
በጨረቃ አቆጣጠር ወር ሃያ ዘጠኝ ቀናት ወይም ሠላሳ ቀናት ሆኖ ሊያበቃ ይችላል። ስለዚህ በሃያ ዘጠኝም ይለቅ በሠላሳ ወሩ የተሟላ ነው።
አቡ አዩብ አል‐አንሷሪይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው ዓመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠራል።» ሙስሊም ዘግበውታል።

❤23👍15
▪️ረመዳን በፍጥነት በማብቃቱ በጣም አዝኜ ነበር። ከዚያም ይች መልእክት ደረሰችኝ። መፅናኛና ብርታት ሆነችኝ: ‐
«መሰናበቱ አያሳዝናችሁ። ይልቁንስ አላህ ስላደረሳችሁ አመስግኑ። ተደሰቱ። ስንብቱን በተክቢራ አድምቁት። አላህ ለጾም እና ለሶላት ስላበቃችሁ አወድሱት።
ባይሆን በቀሪው ዓመት ይዛችሁት ተጓዙ።
ረመዳን አንድ ወር አይደለም። ይልቁንስ የህይወት ዘዬ ነው። የለውጥ ጅምር ነው።
አታሰናብቱት! ከናንተ ጋር አብሮ ይኖር ዘንድ እድሉን ስጡት። እናንተም በርሱ መንገድ ህያው ሁኑ።
▪ጾም አያልቅም፤
▪ከቁርኣን ጋር መኮራረፍ አይበጅም፤
▪መስጂድም አይሸሽም።»
:
{وَاعبُد رَبَّكَ حَتّى يَأتِيَكَ اليَقينُ}
«እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡»
[الحجر - آية ٩٩]
:
አላህ ሆይ! ረመዳናችንን ተቀበለን። መርጠኸን እንዳስረከብከን የወደድክልን ሆኖ ተረከበን!
አላህ ሆይ! ከረመዳን በኋላም በዒባዳህ ላይ አዘውትረን!

❤77👍16😍4
Forwarded from Tofik Bahiru
ታላቁ ዓሊም አል‐ሐቢብ ዑመር ቢን ሙሐመድ ቢን ሐፊዝ [ሐፊዘሁላህ] «ከረመዳን በኋላ ለመፈፀም የምንነይታቸው ኒያዎች ምንድን ናቸው?» በማለት ተጠይቀው እንዲህ አሉ:‐
❶ መላው እድሜያቸው ረመዳን እንደሆኑ ሰዎች ለመሆን፤
❷ በቀንም ሆነ በማታ የምናከናውናቸው ተግባራት ከረሕማን ጋር ያለንን ቁርኝት የሚገልፁ እንዲሆኑ፤
❸ በሦስቱ ዐበይት ጉዳዮች [በዒልም፣ በመልካም ትድድር እና ሰዎችን ወደ አላህ በመጣራት (በዳዕዋ)] በመልካም ሁኔታ ኡመቱን ማገልገል፤
❹ የአላህን ውዴታ መፈለግ፤ የመልክተኛውን [ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም] ደስታ መሻት።
❺ ሁሌም ከአላህ ጋር ቀልባችንን በመሰብሰብ ላይ እንድንበረታ፤ በተለይም ቁርኣን በማንበብ እና በዚክር ላይ እንድንጠነክር፤
❻ ለአላህ ከተወዳጀናቸው ወንድሞቻችን ጋር መልካም የትውውስ መድረኮችን መፍጠር፤
❼ ስድስቱን የሸዋል ጾም መጾም፤
❽ በዓመት የሚገኙትን የዓረፋ ቀን፣ የሙሐረም ወርን ዘጠኝ እና ዐስር ቀን እና መሰል ጊዜያትን በጾም ማሳለፍ፤
❾ በወር ከሦስት ቀናት ያላነሰ መጾም።
አላህ ይወፍቀን!

❤63👍11
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
ዛሬ ለይለቱል‐ጁሙዓ ነው። የሶለዋት ሌሊት።
ከበላእ፣ ከሃሳብ፣ ከጭንቀት፣ ከኃጢኣት አደጋ፣ ከድህነት፣ ከእዳ ውጥረት፣ ከሪዝቅ መጣበብ ወዘተ በሶለዋት ከለላ ውስጥ እንደበቅ!
#ሶሉ
💚 💚 💚
اللهم صلِّ على سيدنا محمد عبدك ونبيك ورسولك، صلاة تغيث بها الملهوف، وتقي من الحتوف، وتؤمن الخائف، وتزيل الكرب، وترفع البلاء، ما نسَمت نسمةُ رضًى تُبرد أكباد المبتلين، وتُؤنس بها وحشة المستوحش، وعلى آله وأصحابه وسلم.

❤37👍25😍2
ሸዋል ስምንት ምን አለ?
(የሸዋል ዒድ/ዒዱል‐አብራር)
ምንነት፣ ግንዛቤ እና ብይን
==================
የረመዳን ድምቀት እንዳለፈ ገና ከጾም ድባብ ባልወጣ አንደበታችን ምንዳ የሚያሳጡንን የክርክር እና የብሽሽቅ ቃላት ተጠቅመን የምንነታረክበት ርዕስ ነው፤ የሸዋል ወር ስምንተኛው ቀን ባህላዊ/ትውፊታዊ ዉሎ።
እንደ ዒድ አል‐ፊጥር እና ዒዱል‐አድሓ ሁሉ ዒድ ነው የሚሉ ''አሉ'' የሚሉ አሉባልታዎች ይደመጣሉ። (እንኳን ከዓሊሞች ከተርታው ማህበረሰብ እንኳን እንዲህ የሚል ሰው መኖሩ በቀጥታ ባይገጥመኝም)።
በሌላ ፅንፍ ደግሞ በእለቱ መዘያየርን፣ ደስታ መጋራትን እና መሰል ማንኛውንም የደስታ ምልክቶች ማንፀባረቅን "ቢድዓ" በሚል የተበደለ መፈክር ያነወረ፣ የእርሞች እርም፣ የወላእ እና የበራእ አጀንዳ፣ የአለሌ ሙናፊቅና የአመፀኛ መገለጫ ያደረገ ሰበካም አለ። በሁለቱ መካከል በማህበረሰባችን መካከል የሚዘዋወሩ ሌሎች ሃሳቦችም ይኖራሉ።
🗯 ተገቢ የሆኑ ጥያቄዎች
የጉዳዩ ትክክለኛ ስፍራ ምንድን ነው? ሸሪዓችን ስለ ''ዒድ'' ፅንሰ ሃሳብ ምን ይላል? በዚህ ጉዳይ ላይ መያዝ ያለብን ነጥብ ምንድን ነው?
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን እና ማስታወሻዎችን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ቃላት እና ፊደላቴን ሁሉ ለአላህ ያድርግልኝ! እውነቱን እንድገልጥ ተውፊቁ ይግጠመኝ! መልካም መንገድ ማመልከቻ ያድርግልኝ! አሚን!
** *
አንዳንድ ተከባሪ የውጭ ሀገር (በተለይም ይህ ልማድ የሌለባቸው ሀገራት ቀደምት እና የዘመናችን) የእርምነት ብይን የሰጡ ዓሊሞች ከመኖራቸው እና በርካታ ልሂቃን ደግሞ በተቃራኒው በፍቁድነት አይተውት ወይም ሲተገበር ተመልክተው አልፈውት የኖሩበት ተግባር በመሆኑ ጉዳዩን ከጥቅል የፊቅህ መርሆች (ቀዋዒድ) አንፃር ለማብራራትና የተሻለ ነው ብዬ የማምንበትን፣ ከደካማዋ ነፍሴ የቀዳሁትን ሐሳብ ሳይሆን ከአሳዳጊ አባቶቼ (ሙረቢ ሸይኾቼ) የተማርኩትን ፍርድ ለመግለጥ እሞክራለሁ።
:
❶ ሸዋል ስምንት ዒድ ነውን?
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ''ዒድ" ከዐረቢኛ ቋንቋ እና ከሸሪዓ መደበኛ ፍቺ አንፃር መቃኘት ያስፈልጋል። ከዚያም የሸዋል ዒድ (ሸዋል ስምንት) ዒድ መሆኑን እና አለመሆኑን ከድምዳሜ እንደርሳለን። በቀጣይም እለቱን በመዘያየር የሚያሳልፉ ሰዎችስ ሸሪዓዊ ዒድ ነው ብለው ያምናሉ ወይ? ወይንስ ግንዛቤያቸው ሌላ ነው? ወደሚለው ጥያቄ እንሄዳለን።…
⚀ ዒድ: ‐ በዐረቢኛ ቋንቋ ''ዓደ፣ የዑዱ፣ ዐውደን'' ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን "ተመለሰ፣ ይመለሳል፣ መመለስ" እንደማለት ነው። ሐሳብ ተመለሰ፣ ህመም ተመለሰ፣ ናፍቆት ተመለሰ ይባላል። ታላላቅ የደስታ፣ ተወዳጅ፣ ተከባሪ ጊዜዎች ዞረው የሚመለሱበትን ቀን በዐረብ አፍ ''ዒድ'' የሚል ስያሜ አገኙ።
ኢብኑል‐አዕራቢይ እንዲህ ይላሉ: ‐
" سمي العيد عيداً، لأنه يعود كل سنة لفرح مجدد"
«ዒድ የተባለው በየአመቱ ደስታን እንደ አዲስ ይዞ ተመልሶ ስለሚመጣ ነው።»
በእርግጥ ትክክለኛ በሆነው የቋንቋ አረዳድ ''ዒድ'' በዓመት የሚመለስ ቀንን በመግለፅ ብቻ አይወሰንም። ይልቁንስ በወርሃዊነትም ሆነ በሳምንት ውስጥ የሚመላለስ ቀንም በዐረብኛ ዒድ ይባላል። ከዚህ አኳያ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የጁሙዓ ቀንን "ዒድ" ብለው መጥራታቸውን መጥቀስ ይቻላል። ኢብኑ ማጀህ እና ሌሎችም ያሰፈሯቸው ሐዲሶች አሉ።…
በጥቅሉ በዐረቢኛ ቋንቋ ዒድ በሸሪዓ የተደነገጉም ሆኑ ያልተደነገጉ፣ የተፈቀዱም ሆኑ ያልተፈቀዱ የቀን አጋጣሚዎችን የሚገልፅ ትርጉም ይዟል። ስለዚህ በዐረቢኛ ቋንቋ ስድ ትርጉም ያዘለ፣ ሰፊ ጭብጥ ያለው ቃል ነው።
⚁ በሸሪዓው መደበኛ ትርጉም (ኢስጢላሕ): ‐
ዒድ የተለያዩ አምልኮዎች እንዲከወኑ የተደነገገበት ልዩ ቀን ነው። የሸሪዓ ምልክት የተደረገ፣ ደስታችንን ይፋ እንድናደርግበት የታዘዝንበት ክቡር ቀን ነው። በሸሪዓው እይታ "ዒድ" የሚያካትታቸው መሠረታዊ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው: ‐
✦ በሌላ ቀን የማይከናወኑ ልዩ ዒባዳዎች (አምልኮዎች) አሉት። ለምሳሌ: ‐ በሐጅ ስነስርዐት ፍፃሜ ላይ የሚመጣው ዒዱል‐አድሓን ብንወስድ በውስጡ እርድ (ኡድሒያ)፣ የዒድ ሶላት፣ ተክቢራ እና እለቱን [እስከ አያሙ‐ተሽሪቅ መባቻ ድረስ] መጾም እርም መሆንን የሚያካትቱ ልዩ ድንጋጌዎችን አዝሏል።
ከረመዳን ጾም በኋላ የተደነገገው ዒዱል‐ፊጥርም ቢሆን ተክቢራ፣ ዒዱል‐ፊጥርን፣ ሶላትን እና መጾም እርም መሆኑን የሚያካትት ይዘት ያላቸው ድንጋጌዎችን በመሠረታዊነት ይዟል።
✦ ዒድ በወሕይ የተመረጠ፣ ለእለቱ ከተመደቡለት አምልኮዎች አንፃር ከሌላው ቀን ልዩ ተደርጎ በአላህ የተደነገገ፣ የተከበረ ቀን ነው። ስለዚህ በዒዱል‐ፊጥር ቀን ዘካቱል‐ፊጥር ማውጣት ቀኑ ካለፈ በኋላ እንደሚሰጠው ሶደቃ አይደለም። ኡድሒያም እስከ አያሙ‐ተሽሪቅ ሦስተኛው ቀን የመግሪብ ወቅት ድረስ ተገድቦ የተደነገገ አምልኮ ነው። ከተመደበው ገደብ ከኋላ ሰዎች በዘልማድ የሚያርዱት እርድ ኡድሒያ አይሆንም። ሌሎቹንም የአምልኮ ድንጋጌዎች በሙሉ በዚሁ መልኩ እናያቸዋለን።
🔸ከሁለቱ ነጥቦች አንፃር የሸዋል ስምንትን (ወይም በተለምዶ ሸዋል ዒድን) ከተመለከትን ማንም ሙስሊም የዒድ መለዮ የሆኑ መገለጫና ድንጋጌዎችን ለእለቱ ሰጥቶ ሲከራከር ሰምተን አናውቅም። እለቱን ለመጠያየቅና ለመዘያየር ከመጠቀም ባሻገር ከሸዋል ሰባት ወይም ከሸዋል ዘጠኝ የተለየ ክብር የተገባው ነው ብሎ የሚያምን ሙስሊም ገጥሞንም አናውቅም። ተክቢራ ወይም ሶላት የፈጠረለት ዐሊም አናውቅም። እለቱን መጾም እርም ነው ያለ ሰውም እናገኝም። እንደው ለክርክር አለ ቢባል እንኳን የዒልም መድረክ ላይ ሃሳቡ የሚንሸራሸርለት ዓዋቂ ዐሊም ሳይሆን ቃሉ የማይደመጥ ጃሂል (ማይም) ብቻ ነው። ይህ ተጨባጩ ላይ ያለን መነሻ ነው። ልሂቃን እንዲህ ይላሉ: ‐
"الحكم على الشيئ فرع عن تصوره."
«ስለ አንድ ነገር የሚሰጠው ብይን መነሻ ላይ ያለው ግንዛቤው ቅርንጫፍ (ውጤት) ነው!»
:
ይቀጥላል!

👍58❤16😍1
❷ አከራካሪው ምንድን ነው?
በርካታ ሙስሊሞች (በተለይም የሻፊዒያን መዝሀብ እና የአንዳንድ ልሂቃንን ሃሳብ የሚከተሉ ከፊል የሙስሊም አካላት) ስድስቱን የሸዋል ጾም አከታትለው እንደሚጾሙ ይታወቃል። ይህንን የሚያደርጉትም የረመዳን ጾምን እንዳጠናቀቁ ወዲያውኑ ነው። ከፈርዱ በኋላ ሱናውን ስላስጾማቸው አላህን በማመስገን ደስታቸውን ይለዋወጣሉ። ከአንድ ወር በላይ የዘለቀውን በጾምና በዒባዳ ያሳለፉትን ጊዜ ለማካካስ የተራራቋቸውን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን የሚጠይቁበትን የሸዋል ስምንት [የዚያራ ፕሮግራም] ልምድ “ሐራም ነው።” የሚሉ ፈትዋዎች መበራከታቸውን እየተመለከትን ነው። እንደከባድ ነውር እና አሳፋሪ ድርጊት በዘለፋም ጭምር ሲወገዝ ይስተዋላል።
በሌላ በኩል እለቱን የሀገራችን በርካታው የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ደግሞ ''ሸዋል ዒድ/ ሸዋሊድ'' በሚል ስያሜ ዐረቦች ዘንድ ደግሞ ''ዒዱል‐አብራር'' በሚል ስያሜ እየተጠራ ይፈፀማል። በእርግጥ እለቱን በደስታና በመዘያየር የሚያሳልፈው ተርታው የህብረተሰባችን ክፍል [ዓመተናስ] ዘንድ ዒድ የሚል ስያሜ ቢሰጠውም ከላይ ለማብራራት የሞከርንውን የዒድ ትርጉም ወይም ጭብጥ እንደማያሟላ እና ዒድ ተብሎ እንደማይታመን ግልጽ ነው። እናም ጭብጡ ላይ እንከን እስካልተገኘበት ድረስ ሰዎች ''ዒድ'' በሚል ስም መጥራታቸው በእለቱ የሚፈፀመውን ክንውን ሁሉ እርም አያደርገውም። የፊቅህ ልሂቃን መርህ እንዲህ ይላል: ‐
"لا مشاحة في الإصطلاح"
«[ጭብጥ ላይ እንጂ] የሰዎች ተግባቦት ላይ ክርክር የለም።»
ሲጾሙ ከርመው የነበሩ ሰዎች ወዳጆቻቸውን መዘየራቸው እና ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ ሸዋል ስምንትን መጠቀማቸው ጥፋት የለውም። ስድስቱን ቀን እንዲጾሙ አላህ ስለፈቀደላቸው ደስታቸውን መግለጻቸው፤ ለአምላካቸው ምስጋና ማቅረባቸው ''ዒድ'' የሚል ስያሜ ስለሰጡት ብቻ ሙሉ ለሙሉ ሐራም ይሆናል አይባልም። የመርህና ትርጉም ክፍተት እስካልታየበት ድረስ ችግር የለውም።
ሰዎች ሸዋል ስምንት ላይ የዒድን መሠረታዊ ክንዋኔዎች ለመፈጸም የሚያሰችል ህግ አልደነገጉም። የዒድ ሶላት አልመደቡም። ዘካቱል‐ፊጥር የሚባል ነገር የለም። ኡድሒያ ለመፈጸም ሲሞክሩ ተመልክተን አናውቅም። የዒድ ተክቢራ ሲያደርጉ አላየንም። እንደዒዶቻችን እለቱን መጾም እርም ነው አላሉም። ስለዚህ ስያሜውን በልማድ ዒድ ብለው እንደጠሩት ግልጽ ነው። በጥቅሉ ምንም አይነት የዒድ መለዮዎችን አልሰጡትም። እለቱን የተመለከተ የተለየ ድንጋጌ አይስተዋልም። ስለዚህ ይህንን ልማድ ወይም ባህል ወይም (እንደ ቁርኣን ውድድር፣ እንደ የጎዳና ኢፍጣር፣ እንደ መደበኛ የመድረክ ፕሮግራሞች) ዓመታዊ ክንውን አድርጎ ማሰብ ይገባል። ከዚያ የሚለይበት አንዳች ምክንያታዊ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። ለራስ ልማድ ምክንያት እየተሰጠ የሌላውን ለመንቀፍ ወይም ለማጣጣል መሞከር ትክክል አይደለም። በየአመቱ ኮንፈረንስ እየተሰበሰቡ መማማርም ሆነ ሸዋሊድ የተለያዩ አይደሉም። ሐራም ወይንም ያልተፈቀዱ ተግባራት እስካልተስተዋለ ድረስ ሊቀጥሉ ይገባል።
በተረፈው በእለቱ የደስታ መግለጫ ክንውኖች መኖራቸውን እንከን አድርጎ የሚያይ ሰው ካለ ተሳስቷል። ምክንያቱም ሸሪዐዊው የዒድ ድንጋጌ ላይ ደስታን መግለፅ አንኳር እና መሠረታዊ የአምልኮ ክንውን አይደለም። ይልቁንስ ተወዳጅና ተፈላጊ ተግባር ብቻ ነው።
በተጨማሪም ደስታን መግለፅ እና ማመስገን ለዒድ ቀን ብቻ የተወሰነ ልዩ የዒድ አምልኮ አይደለም። ሁሌም ቢሆን ሰዎች በአላህ ችሮታ እና በእዝነቱ መደሰት እና ምስጋና ማድረስ እንደሚገባቸው በቁርኣን ተገልጿል። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
{قُل بِفَضلِ اللَّهِ وَبِرَحمَتِهِ فَبِذلِكَ فَليَفرَحوا هُوَ خَيرٌ مِمّا يَجمَعونَ}
«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡»
[يونس - آية ٥٨/ሱረቱ ዩኑስ፥ 58]
ይህ አንቀጽ በቋሚነት በአላህ ፀጋዎች እና በትሩፋቱ መደሰት እንደሚገባ የሚያስረዳ መልእክት አለው።
ታዲያ ታላቁን ወር አግኝቶ ከመጾም በኋላ የአንድ አመት ጾም ምንዳ የሚያስገኘውን ስድስቱን የሸዋል ጾም አሟልቶ እንደመጾም የሚያስደስት ምን ዓይነት ነገር አለ?!…
ከአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንደተዘገበው: ‐ «ጾመኛ ሁለት ደስታ አለው። አንደኛው ደስታ ሲያፈጥር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ጌታውን [በቂያማ ቀን] ሲያገኘው ነው።»
እኔ እስከማውቀው ድረስ (ከዚህ ውጪ ሌላ ተጨባጭም የለም) ሸዋል ስምንትን ሸሪዓዊ ዒድ ነው ብሎ የሚያምን አንድ ሰው የለም። በተጨባጭ ያለው እውነታ ሰዎች ከረመዳን በኋላ በዒዱል‐ፊጥር ማግስት ስድስቱን የሸዋል ጾም አከታትሎ መጾም መልካም ነው ብለው የሚያምኑ መዝሀቦችን ተከትለው ስለሚጾሙ ከፈርዱ በኋላ ሱናውንም ጨምሮ እንዲጾሙ እድል የሰጣቸውን ጌታ ያመሰግናሉ፤ ደስ ይላቸዋል። ረመዳን ሰውን አያገናኝምና ከሰላሳ ቀናት በላይ የተጠፋፏቸውን ዘመዶቻቸውን ይዘይራሉ፤ ይጠያየቃሉ። አለቀ!
''ዒድ'' በሸሪዓ ሚዛን መሠረታዊ እና ልዩ የዒባዳ ክንውኖች ያሉበት ድንጋጌ ነው። ስለዚህ ሸሪዓው ዒድ ያላደረገውን ዒድ አንልም። ተርታው ሰው ዒድ ብሎ በተለምዶ የጠራውን ቃል ይዘንም በጭብጥ የሚያስከለክል እንከን የሌለውን የስብስብ፣ የዝክር፣ የምስጋና እና የደስታ ክንውንን ሁሉም ሐራም ወይም ቢድዓ አንልም።
[በአመቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሚከናወኑ እንደ ዚክረል‐መውሊድ፣ ዚክረል‐ኢስራእ ወል‐ሚዕራጅ፣ ዚክረል‐ሂጅራ አሽ‐ሸሪፋ ያሉ የዝክር ቀናትን ሁሉ በዚህ መልኩ ማየት ይቻላል።]
ዒድ ሁለት ነው። በየሳምንቱ ከሚመላለሰው የጁሙዐ ቀን ጋር ሦስት። እነዚህ ግን የታሪክ አጋጣሚዎች እና የአላህ ፀጋ የሚታወስባቸው የአላህ ቀናቶች (አያሙላህ) ናቸው። የአላህን ፀጋዎች አንስቶ ደስታን መግለጽ ተገቢ ነው። አያመላህን እያወሱ መማማርን የሚከለክል ምንም ዓይነት ሸሪዓዊ መነሻ የለም። ጉዳዩን ከስሜት በራቀ እና ከውግዘት በጸዳ መነጽር መመልከት ይገባል። በዚህና በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ እውቀት ላይ የተመሰረተ ሙግቱ ከባለቤቶቹ እንጠብቃለን። ጠንከር ያለ ሙያዊ ብይን ይጠይቃል።
ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ያስተላለፉት ሐዲስ እንዲህ ይላል: ‐
«የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አንድ ቀን ባልደረቦቻቸው ክብ ሰርተው የተቀመጡበት [ስብስብ] ላይ ወጡ። ከዚያም «ለምን ተሰባስባችሁ ተቀመጣችሁ?» በማለት ጠየቋቸው።
ባልደረቦቻቸውም: ‐ «አላህን [በዱዐ] ልንለምነው፣ ለኢስላም ስለመራን እና እርስዎን በመላክ ስለለገሰን ልናመሰግነው ተቀምጠናል።» በማለት መለሱ።
እርሳቸውም: ‐ «በአላህ ማሉ! ከዚህ ውጪ ሌላ ነገር አሰባስቦ አላስቀመጣችሁምን?» በማለት ጠየቁ።
ሶሓቦቹም: ‐ «ወላሂ! ከዚህ ውጪ ሌላ ነገር ሰብስቦ አላስቀመጠንም።» በማለት መለሱ። በመጨረሻም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ: ‐ «በአላህ እምላለሁ! እኔኮ ተጠራጥሬያችሁ አላስማልኳችሁም። ይልቁንስ ጂብሪል [ዐለይሂ ሰላም] እኔ ዘንድ መጥቶ አላህ እናንተን [በማድነቅ] መላኢካዎች ላይ እየፎከረ መሆኑን ስለነገረኝ ነው።»
ነሳኢይ ዘግበውታል።

❤63👍17😍4🤔1