Telegram Web Link
ከረዥም አመታት ጀምሮ በሀገራችን ከተለመደው በተለየ ሁኔታ ለተማሪዎቼ ሙቀዲመቱ ባፈድልን ከአቡሹጃዕ አስቀድሜ አስተምራለሁ። በ እርግጥ ከጊዜያት በኋላ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ ይህንኑ ሃሳብ በዓለም ላይ ታዋቂ የሆኑ ሻፊዒዮች ያሉባቸው የዒልም ስፍራዎችም እየሰሩበት ይገኛል። የነርሱን ምክንያት ባላውቅም የእኔ ምክንያት በዋናነት አንድ ነው። እርሱም አቡሹጃዕ ከዒባዳ በዘለል ሌሎች የፊቅህ ክፍሎችን የግብይት ህጎችን፣ የኒካሕ እና ተያያዥ ህጎችን፣ ውርስ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግጋትን [ጂናያት] እና ሌሎችንም በሰፋፊ መፅሐፍት ላይ የሚሰፍሩ ትምህርቶችን በመያዟ ነው። በተጨማሪም አቀራረቧ ከመብራራት የራቀ በጣም አጭር በመሆኗ ሃሳቧ አይያዝም። ስትተነተን ትንቦረቀቃለች፣ ለአብዝሃኛው ሙስሊም የነፍስ ወከፍ እውቀቶች ያልሆኑ ነጥቦችንም አካታለች ብዬ ስለማስብ ነው።

በአንጻሩ ባፈድል መጠኗ ሚዛናዊ ከመሆኑ ጋር ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የነፍስ ወከፍ እውቀቶችን ብቻ የያዘች በመሆኗ አንገብጋቢና ለሁሉም ሙስሊም አማካይ ናት ብዬ አስባለሁ። ባፈድል አርካኑል‐ኢስላምን ብቻ በበቂ ስፋት የምትዳስስ መጽሐፍ ናት።

እግረመንገዴን ኢስላማዊ እውቀት ሚሹ ታናናሾቼ እውቀትን ካሪኩለም ተከትለው ቀደምቶቻችን ባስቀመጡት መልኩ፣ ሸይኽ ስር፣ እርከናቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ እመክራለሁ። ጉራማይሌ የሆነ የእውቀት ፍለጋ የጊዜ ብክነት ከማስከተሉ ጋር የማይጨበጥ ጉም ውስጥ ይከታል። አዋቂ የሚመስሉ ጥራዝ ነጠቆችን እንጂ የእውነት የእውቀት ባለቤቶችን አያፈራም።

በመጨረሻም የአዝካር  ነወዊ ደርሳችንን በመጪው ሳምንት በሳምንት ሁለት ቀን መለቀቅ እንደሚቀጥል ከመግለፅ ጋር በርካቶቻችሁ ስትወተውቱ የነበረው የአቡሹጃዕ ደርስን በቀጥታ [ላይቭ] ለማስተማር ከራሴ ጋር እየተማከርኩ መሆኑን አሳውቃለሁ። ኢንሻአላህ!

ሙኽተሶር አቡ ሹጃዕ [አል‐ጛየቱ ወት‐ተቅሪብ] እኔ ዘንድ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ ልቤ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላት መጽሐፍ ናት! ትርጉምና ማብራሪያዋንም ከዚህ ቀደም ''ሰፊናን'' በሰራሁበት መንገድ ማዘጋጀቴንና በቅርቡ በመጽሐፍ ጥራዝ በእጃችሁ እንደምትገባ አበስራለሁ!
በዱዓችሁ!
👍4024
👍13🤔1
================
የዐስሩ የዙል‐ሒጅ‐ጃ ቀናት
ትሩፋት
================
⚀ አላህ የማለባቸው ቀናት: ‐
አላህ የማለባቸው ነገሮች ልቅና ያላቸው ነገሮች ናቸው። ምክንያቱም የልቅና ባለቤት ልቅና ባለው ነገር እንጂ በሌላ አይምልም። አላህ እንዲህ አለ: ‐
«በጎህ እምላለሁ፡፡ በዐሥር ሌሊቶችም፡፡»
በርካታ የተፍሲር ልሂቃን እንደሚሉት ዐስር ሌሊቶች በማለት የተጠቀሱት ዐስሩ የዙልሒጃ የመጀመሪያ ቀናት ናቸው።
ኢብኑ ከሲር «ይህ ትክክለኛው ተፍሲር ነው።» ብለውታል።
:
⚁ ዚክር ማብዛት የታዘዘባቸው "የታወቁ ቀናት": ‐
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐

[لِّيَشْهَدُوا۟ مَنَٰفِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ فِىٓ أَيَّامٍ مَّعْلُومَٰتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْبَآئِسَ ٱلْفَقِيرَ]

«ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡»
:
⚂ ምርጦቹ የአላህ ቀናት: ‐
ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምርጦቹ የዱንያ ቀናት ዐስሩ የወርሀ ዙልሒጃ ቀናት ናቸው።
ሰዎችም «በሌሎች ወራት በጂሃድ ላይ ከማሳለፍም ይበልጣሉ?» በማለት ጠየቁ።
የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «አዎን! በሌሎች ወራት በአላህ መንገድ ላይ (ጂሃድ) ላይ ከመሆንም ይበልጣሉ። ፊቱን በአፈር ላይ ያደረገ (ሰማእት የሆነ) ሰው ሲቀር!» በማለት መለሱ።» በዝ‐ዛር እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።
:
⚃ የዐረፋ ቀንን የያዙ ቀናት: ‐
የዐረፋ ቀን ዘጠነኛው የዙልሒጃ ቀን ነው። ታላቁ የሐጅ ስራ የሚከናወንበት ቀን ነው። ኃጢኣት የሚማርበት ቀን ነው። ሰዎች ከእሳት ነፃ የሚሆኑበት ቀን ነው። በዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት ውስጥ ከዐረፋ ቀን በቀር ምንም ባይኖር እንኳን የዐስሩን ቀናት ትሩፋት የገዘፈ ያደርገዋል።
:
⚄ የእርዱ ቀንን (የዒዱል‐አድሓ ቀን) በውስጣቸው የያዙ ቀናት: ‐
አንዳንድ ዐሊሞች ዘንድ የዓመቱ ምርጥ ቀን ይህ ቀን ነው። ታላቁ የሐጅ ቀን (የውሙል‐ሐጂል‐አክበር) ይኸው ቀን ነው። ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አላህ ዘንድ ታላቅ የሆነው ቀን የእርዱ ቀን ነው።» አቡ ዳዉድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል።
:
⚅ ዋናዎቹ የዒባዳ ዘርፎችን ያካተቱ ቀናት: ‐
አል‐ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር "ፈትሑል‐ባሪ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐ «የዙል‐ሒጃ ዐስሩ ቀናት ከሌሎች ቀናት የተለዩት ዋናዎቹ የዒባዳ ዘርፎችን አካተው በመያዛቸው ነው። እነሱም ሶላት፣ ጾም፣ ሶደቃ እና ሐጅ ናቸው። በሌሎች ጊዜያት ይህ ሊሳካ የሚችል አይደለም።»
:
❦ ዛሬ እነዚህ የተከበሩ ቀናት አንድ ብለው ጀምረዋል። ራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ቀስቅሰን በዒባዳ እንበርታ!
አላህ ተውፊቁን ይለግሰን!
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
21👍14
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል አንድ)
=============
አላህ አዛኝ ነው። ለባሮቹ ካለው እዝነት እና ችሮታ የተነሳ የመልካም ሥራዎች ገበያ የሚደራባቸው ልዩ ቀናትን መደበ። የሰዎች ስሜት ለመልካም እንዲነሳሳ በሚያደርጉ ምንዳዎች አጅቦ ባሮቹ ለኸይር የሚሽቀዳደሙባቸውን ቀናት አሰናዳ። የገፈለው እንዲነቃ እና ወደ አላህ ሐድራ እንዲቀርብ የሚያደርግ አካሄድ ዘረጋ። ይህ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ያበሰሩት የመልካም ችሮታው ድግስ ነው። በአንዳንድ ልዩ ቀናት የመልካም ሥራዎች ምንዳ ከሌሎቹ እንደሚለይ ተናግረዋል። መልካሞች ሲሰሙት ያለ መታከት እንዲነቃነቁ የሚያደርጉ ምንዳዎች የተዘጋጁባቸውን ቀናት ጠቁመዋል። እነዚህ ልዩ ቀናት በርካታ ናቸው። ሁሉም በጊዜያቸው ተዘክረዋል። ልንቀበለው የተቃረብነው ግን ልዩ ነው!…
:
ጌታችን አዛኝ ነው!…
ቤቱን ለማየት ያለንን ጉጉት፣ የሐረሙን ንፋስ ለመማግ ያለንን ሸውቅ ተመልክቶ እዚያው ለመገኘት ያልታደልነውን ሊክሰን በፍትህ ዓይኑ ቃኘን። በተሰጠን ዓቅም መከወን የምንችላቸውን በርካታ ነገሮች ደነገገልን። እዚሁ ሆነን ከሐጀኞች ጋር የምንወዳደርባቸው ትሩፋቶችን አነባበረልን።

ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ: ‐
«አላህ በሙእሚኖች ቀልብ ውስጥ የሐረምን ትእይንቶች የመታደም ስሜት ፈጠረ። ነገርግን ሁሉም በየአመቱ እዚያ የመገኘት ዓቅም አያገኝም። ስለዚህ ችሎታው ያላቸው በእድሜ አንድ ጊዜ ሐጅ እንዲያደርጉ ፈርድ አድርጎ ደነገገ። ብሎም የሐጅ ክንውን የሚፈፀምባቸውን ዐስሩን ቀናት ተጓዦቹም ሆነ ተቀማጮቹ የሚጋሯቸው የመልካም ሥራ ዐውዶች አደረገ። በአንድኛው ዓመት ሐጅ ለማድረግ ያልታደለ እቤቱ ሆኖ መፈፀም የሚችላቸውን መልካም ተግባራት አዘጋጀ። ሰውየው በእነዚህ ቀናት የሚያከናውናቸውን ማናቸውንም ተግባራት ከጂሃድ በላይ ዋጋ እንዳለው ‐እንደ ጂሃድ‐ እንዲታዩ አደረገ።»
:
ይህ የአላህ ችሮታ ነው። ሐጅ ባንሄድም የአላህ እዝነት እና ትሩፋት በሐጅ ሥራ ብቻ አልታጠረምና ከተጓዦቹ ጋር ለመወዳደር እንሰናዳ!
አላህ ይወፍቀን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
30😍9👍3
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል ሁለት)
================
የዐስሩ የዙል‐ሒጅ‐ጃ ቀናት
ትሩፋት
================
⚀ አላህ የማለባቸው ቀናት
↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽
አላህ የማለባቸው ነገሮች ልቅና ያላቸው ነገሮች ናቸው። ምክንያቱም የልቅና ባለቤት ልቅና ባለው ነገር እንጂ በሌላ አይምልም። በነገሮች የሚምለው ደግሞ የማለባቸው ነገሮች ላይ ሰዎች እንዲየተኩሩ ለማድረግ ነው።
አላህ እንዲህ አለ: ‐

{وَالْفَجْرِ وَلَيَالٍ عَشْرٍ}
«በጎህ እምላለሁ፡፡ በዐሥር ሌሊቶችም፡፡»

በርካታ የተፍሲር ልሂቃን እንደሚሉት ዐስር ሌሊቶች በማለት የተጠቀሱት ዐስሩ የዙልሒጃ የመጀመሪያ ቀናት ናቸው።
ኢብኑ ከሲር «ይህ ትክክለኛው ተፍሲር ነው።» ብለውታል።
:
⚁ "የታወቁ ቀናት"
↽↽↽↽↽↽
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐

[لِّيَشْهَدُوا۟ مَنَٰفِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ فِىٓ أَيَّامٍ مَّعْلُومَٰتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْبَآئِسَ ٱلْفَقِيرَ]

«ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ለሐጅ ይመጡሃል)፡፡»
:
⚂ ምርጦቹ የአላህ ቀናት
↽↽↽↽↽↽↽↽
ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው ተወዳጁ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምርጦቹ የዱንያ ቀናት ዐስሩ የወርሀ ዙልሒጃ ቀናት ናቸው።»
⚃ በተራ ሥራ የጂሃድ ምንዳ
↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽
ተወዳጁ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«መልካም ሥራ እጅግ የሚወደድባቸው እንደነዚህ ቀናት አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ቀናት የሉም።»

ከዚያም ሰዎች እንዲህ በማለት ጠየቁ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! [በሌሎች ወራት] በጂሃድ ላይ ከማሳለፍም ይበልጣሉ?»
የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «አዎን! በሌሎች ወራት በአላህ መንገድ ላይ (በጂሃድ ላይ) ከመሆንም ይበልጣሉ። ፊቱን በአፈር ላይ ያደረገ (ሰማእት የሆነ) ሰው ሲቀር!» በማለት መለሱ።» አል‐በዝ‐ዛር እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።
:
ይህ የሚያመለክተው በእነዚህ ቀናት የሚሠሩ ዒባዳዎች በነፍስ፣ በገንዘብም ሆነ በሌሎች መንገዶች ጂሃድ ወጥቶ ተመልሶ ከመምጣት በላይ መሆኑን ነው። ነገርግን በማንኛውም ጊዜ በገንዘቡም ሆነ በነፍሱ ለጂሃድ ወጥቶ ተመልሶ ያልመጣ ሰው ከየትኛውም ሥራ የበለጠ ሰርቷል።
ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ: ‐
«የዙል‐ሒጃን የመጀመሪያ ዐስር ቀናት ከነሌሊታቸው በዒባዳ ማሳለፍ ነፍሱን እና ገንዘቡን ይዞ ለጂሃድ ወጥቶ ሳይመለስ ከመቅረት ውጪ ከሁሉም ሥራዎች ይበልጣል።»
:
እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ነጥብ አለ። አላህ በእነዚህ ቀናት የሚፈፀሙ ዒባዳዎችን አልለየም። የትሩፋቱን ብዛት በአምልኮው ዘርፍ ሳይሆን በቀናቱ በረከት እንዲገዝፍ አድርጓል። ቀናቱ ብሩክ ናቸው። የተላቁ ናቸው። የተከበሩ ናቸው። ነገርግን ለሁሉም ዓይነት ዒባዳ ክፍት ናቸው። በፈለግከው ዒባዳ አላህን መቅረብ ያንተ ፋንታ ነው!
:
በነዚህ ቀናት መቶ ብር መለገስ በሸዕባን፣ በረመዳን፣ በሸዋል ተመሳሳዩን ከመለገስ ይበልጣል። በእነዚህ ቀናት የሚሰገድ ሁለት ረከዓ በሌሎች ቀናት ከሚሰገደው እጅግ የበለጠ ምንዳ ያስገኛል።…
:
ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ: — «በዐስሩ ቀናት የሚፈፀም መልካም ሥራ በሌሎች ጊዜያት ከሚፈፀመው የሚበልጥ ከሆነ፣ በዚህ ጊዜ የተሰራ አነስተኛ የሚባል ሥራ በሌላ ጊዜ ከሚሰራው በላጭ ከሆነ ሥራ የላቀ ምንዳ ያስገኛል ማለት ነው።»
:
በእነዚህ ቀናት ላይ በዒባዳና በመልካም ሥራዎች መጠመድን ጥብቅ የሚያደርገውም ይኸው ነው። በእነዚህ ቀናት የሚሰራ ዒባዳ በሌላ ጊዜ ከመፈፀም ጂሃድ ጋር የሚነፃፀር፣ እንደውም የሚበልጥ እንደሆነ በሐዲሶቹ ተመልክቷል።
:
⚃ የዐረፋ ቀንን የያዙ ቀናት
↽↽↽↽↽↽↽↽↽
የዐረፋ ቀን ዘጠነኛው የዙልሒጃ ቀን ነው። ታላቁ የሐጅ ስራ የሚከናወንበት፣ ኃጢኣት የሚማርበት ቀን ነው። ሰዎች ከእሳት ነፃ የሚሆኑበት ቀን ነው። በዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት ውስጥ ከዐረፋ ቀን በቀር ምንም ባይኖር እንኳን የዐስሩን ቀናት ትሩፋት የገዘፈ ያደርገዋል።
:
⚄ የእርዱ ቀንን (የዒዱል‐አድሓ ቀን) የያዙ ቀናት
↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽
አንዳንድ ዐሊሞች ዘንድ የምንጊዜም የዓመቱ ምርጥ ቀን ይህ ቀን ነው። እለቱ ታላቁ የሐጅ ቀን ‐የውሙል‐ሐጂል‐አክበር‐ በማለት ተወድሷል።

ተወዳጃችን [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አላህ ዘንድ ታላቅ የሆነው ቀን የእርዱ ቀን ነው።» አቡ ዳዉድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል።
:
⚅ ዋናዎቹ የዒባዳ ዘርፎችን ያካተቱ ቀናት
↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽↽
አል‐ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር "ፈትሑል‐ባሪ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐
«የዙል‐ሒጃ ዐስሩ ቀናት ከሌሎች ቀናት የተለዩት ዋናዎቹ የዒባዳ ዘርፎችን አካተው በመያዛቸው ነው። እነሱም ሶላት፣ ጾም፣ ሶደቃ እና ሐጅ ናቸው። በሌሎች ጊዜያት ይህ ሊሳካ የሚችል አይደለም።»
:
❦ ሷሊሖቹ፣ ምርጦቹ፣ ዓቢዶቹ ለእነዚህ ቀናት ልዩ ክብር አላቸው። ለጧኢፉል‐መዓሪፍ በተሰኘው መፅሀፍ ላይ አቡ ዑስማን አን‐ነህዲይ የሚከተለውን እንደተናገሩ ተዘግቧል: ‐
«ሰለፎች ሦስት ዐስርቶችን ያከብሩ ነበር: ‐ የመጨረሻዎቹ ዐስሩ የረመዷን ቀናት፣ የመጀመሪያዎቹ ዐስር የዙል‐ሒጃ ቀናት እና የመጀመሪያዎቹን የሙሐረም ዐስር ቀናት።»
ከአነስ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ «[በሶሐቦቹ ዘመን] እያንዳንዱ የዐስሩ ቀናት ቀን ከአንድ ሺህ ቀናት ጋር ይወዳደራሉ፤ የዐረፋ ቀን ደግሞ በአስር ሺህ ቀናት ይመነዘራል ይባል ነበር።»
:
እንዳይረዝም በሌላ ክፍል እቀጥላለው!
ሼር ይደረግ ባረከላሁ ፊኩም
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
29👍8
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል ሦስት)
====================
ዐሽሩ ዚል‐ሒጅ‐ጃ እና ሷሊሖቹ
====================
ኢማም ኢብኑል‐ጀውዚይ እንዲህ ይመክራሉ: ‐
«የቀደምቶቹን፣ "የሰለፎቹን" ጠባይ አጥኑ። ድርሰቶቻቸውን አንብቡ። ታሪካቸውን መርምሩ። መጽሀፍቶቻቸውን ማጥናት እነርሱን እንደማየት ነው።»
ደጋጎችን መሆን እንኳን ቢጠና መምሰሉ የግድ ነውና ዐስሩ ቀናትን እንዴት ያሳልፉ እንደነበር በጥቂቱ እንቃኝ።
:
እርግጥ ነው! ከዚህ ቀደም ያነሳኋቸው የእነዚህ ቀናት ትሩፋት እንኳን ባለ ንቁ ልቦናዎቹን ቀርቶ ድንዙዛንን እንኳን መቀስቀሳቸው አይጠረጠርም። በሰለፎች የዒባዳ ጉጉት፣ ለአላህ ቅርብ ሆኖ ለመገኘት ባላቸው ተነሳሽነት እና ለመልካም ስራ የተገራ መንፈስና አካል ባለቤት መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ትጋታቸውን ማሰብ በቂ ነው።
ነገርግን ፈለጋቸውን ለሚሹ ነፍሶች ይሆን ዘንድ ጥቂት ምሳሌዎችን ይዣለሁ!
:
⚀ ትምህርት መዝጋት

እነዚህ የተባረኩ ቀናትን በአግባቡ ለመጠቀም እና የሚገባቸውን ትኩረት ለመስጠት ሲሉ የትምህርት ማእዳቸውን የሚያቆሙ ነበሩ። በፈንታው ጊዜያቸውን በዒባዳ በመታተር እና በኸይር ስራዎች ላይ በመሳተፍ ይጠመዱ ነበር።
የኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ደረሳ "አል‐አስረም"  እንዲህ ብለዋል: ‐
«በዐስሩ ቀናት ኢማም አሕመድ ዘንድ መጣን። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: ‐ «እኛም ሰዒድ አል‐ጀሪሪይ ዘንድ በዐስሩ ቀናት እንመጣ ነበር። እርሱ ግን: ‐ «ይህ የሥራ ጊዜ ነው። ሰዎችም ብዙ ጉዳዮች አሏቸው።» አለን።»
:
⚁ ከወንጀል መታቀብ

ሰለፎች ዐስሩን ቀን ከሚያከብሩባቸው መንገዶች አንዱ ከምንጊዜም በላይ ከኃጢኣት መጠንቀቅ ነው። ከጥንቃቄያቸው ብዛት ሐራምን ከመራቅ ተሻግረው ዶዒፍ እና የተሳሳተ ዘገባ ያለው ሐዲስን ማውራትን እስከመሸሽ ይደርሱ ነበር።

አል‐በርዘዒይ ለሸይኻቸው ‐አቡዙርዓ‐ የጠየቋቸው ጥያቄዎችን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ: ‐
«አቡዙርዓን ነቢዩ [ﷺ] ዐስሩ የዙልሒጃ ቀናትን ስለሚያሳልፉበት ሁኔታ የተዘገበውን የሂንድ ቢንት ሃላ ሐዲስ ጠየኳቸው። እርሳቸው ግን ሐዲሱን ከማንበብ ተቆጠቡ። አጥብቄ ስጠይቃቸው "ትክክል አይሆንም ብዬ የምገምተው ቃል አለበት።" አሉኝ። ከዚያም ችክ ብዬ ጥያቄዬን ስደግምላቸው "እሺ ዐስሩ ቀን ይለፍ። እንዲህ ዓይነቱን ወሬ በዐስሩ ቀን ማውራት አልወድም።" አሉ። ከማውራት የተቆጠቡት ሐዲስ አቢ ገስ‐ሳን ከጀሚዕ ኢብኑ ዑመር የዘገቡት ደካማ [ዶዒፍ] ዘገባ በመሆኑ ነው።»
:
ከጥንቃቄያቸው ብዛት ዶዒፍ ሐዲስን ከማውራት እንኳን ይጠነቀቁ ነበር። ዶዒፍ ሐዲስን ‐በተለይም የመልካም ሥራ ትሩፋትን የተመለከቱ ሲሆን‐ ደካማነቱን ከመጥቀስ ጋር ማውራት የሚከለክል ምንም እገዳ ባይኖርም የታላላቆችን ጥንቃቄ የሚያሳይ ታላቅ ምሳሌ የሚሆን አርዓያ ነው!
:
⚅ በተክቢራ ማድመቅ

ሙጃሂድ እንዲህ ይላሉ: ‐ «አቡሁረይራ እና ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁማ] በዐስሩ ቀን የገበያ ቦታ በመሄድ ተክቢራ ያደርጋሉ። ሰዎችም ተከትለዋቸው ተክቢራ ያደርጋሉ። ገበያ የሚሄዱት ለዚሁ ጉዳይ ብቻ ነበር።»
ሶሐቦቹም ሆኑ ከነርሱ በኋላ የመጡ ሰለፎች በእነዚህ ቀናት ተክቢራ ያበዙ ነበር። ቀልባቸውም ልሳናቸውም በተክቢራ ይደምቅ ነበር። በግል ስፍራዎችም ሆነ በህዝብ ቦታዎች ላይ ቀናቱን በተክቢራ ወጀብ ያናውጡት ነበር።
ሳቢት አል‐ቡናኒ እንደሚሉት: ‐ «ሰዎች [ሰለፎች] በዐስሩ ቀናት ተክቢራ ያደርጉ ነበር። በመጨረሻ ግን ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ ከለከላቸው። እስካለንበት ዘመን ድረስ መካ ውስጥ ያለው ሁኔታ ይኸው ነው። ሰዎች በዐስሩ ቀናት በየገበያ ስፍራው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።»
መይሙን ኢብኑ ሚህራን እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሰዎች [ሰለፎች] በዐስሩ ቀናት ተክቢራ ሲያደርጉ ደርሼባቸዋለሁ። እንደውም [ተክቢራ አድራጊው] ከመብዛቱ የተነሳ ከወጀብ ድምፅ ጋር አመሳስለዋለሁ።»
ሙጃሂድ በዐስሩ ቀናት አንድ ሰው ተክቢራ ሲያደርግ ሰሙና እንዲህ አሉ: ‐ «ድምፁን ከፍ አያደርግም! እኔ ሰዎቹን [ሶሐቦቹን] አግኝቻቸዋለሁ፤ አንዱ በመስጂድ ውስጥ ሆኖ ተክቢራ ሲያደርግ የመስጂዱ ሰዎች በድምፅ ይናወጡ ነበር። ከዚያም ድምፁ የሸለቆው ሰዎች ዘንድ ይደርሳል። ከዚያም አብጦሕ [የሚባለው ስፍራ] ይደርሳል። አብጦሕም በሰዎቿ ተክቢራ ትናወጣለች። መነሻው ግን አንድ ሰው ነው።»
:
⚄ ሐጀኞችን መምሰል

አንዳንድ ሰለፎች ሐጀኞችን መምሰል ይሻሉ።
ኢብኑ ጁረይጅ እንዲህ ይላሉ: ‐
«የመካው አሚር አቡ ጂራብ [የመካውን ፈቂህ] ዐጧእን ዙልሒጃ ከገባ ጀምሮ ኢሕራም እንዲያደርጉ አዘዘ። እርሱም በመካከላችን ሆኖ ኢሕራም ሳያደርግ "ለበይክ" ይል ነበር። ተልቢያውንም ከፍ ባለ ድምፅ ያሰማ ነበር። የመካ ሰዎች እና ልሂቃኖቻቸው በቀደመው ዘመን እንዲህ ነበሩ። በዐስሩ ቀናት ሰዎች እንደ ሐጀኞች ከተሰፋ ልብስ ተላቀው ሐጀኞችን መምሰል ይወዱ ነበር።»
📚 አኽባሩ መካ፥ ኢማም አል‐ፋኪሃኒይ
:
⚇ ኢዕቲካፍ ማድረግ

አል‐ሓፊዝ ኢብኑ ዐሳኪር [ረሒመሁላህ] «በዐስሩ ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር።»
:
ከብዙው በጥቂቱ ፈለጎቻችን ለእነዚህ ቀናት የነበራቸውን አክብሮት፣ ጉጉት እና አጠቃቀም አመልክተናል።
ፊታችን የተደቀኑት ቀናት አላህ ያከበራቸው ታላቅ ቀናት ናቸው።
የሻም ሀገሩ ልሂቅ ኢማም አል‐አውዛዒ እንዲህ ይላሉ: ‐ «ሸሂድ በመሆን ከተመረጠ ሰው በስተቀር በእነዚህ ቀናት መልካም ሥራን መስራት ቀኑ እየተጾመ ሌሊቱም በጥበቃ [ሒራሳ] ከታደረበት ጂሃድም እንደሚበልጥ ዘገባዎች ደርሰውኛል።»
:
እንዴት እንቀበላቸው?!
==============
⚀ ዱዓ ማድረግ: ‐ አላህ አድርሶን ከሚጠቀሙባቸው እንዲያደርገን፣ የእነዚህን ቀናት ክብር በልባችን እንዲያሳድር፣ ዓቅሙን ሰጥቶን በመልካም ሥራዎች ከሚሯሯጡት እንዲያደርገን… አላህን መለመን ይገባናል። አስቀድሞ ሩሓችንን እንዳይወስድና የቀናቱን ቱሩፋት እንዳይነፍገን መማፀን አስፈላጊ ነው። የትኛው ሰዓታችን የሞት ቀጠሯችን የተወሰነበት እንደሆነ አናውቅም። አምሽተን ከሆነ ለማደር፣ አንግተን ከሆነ ለማርፈዳችን ዋስትና የለንም!
:
⚁ ተውበት ማድረግ

ለዚህ ቀን ዝግጅት ቀልባችን ይወለወል ዘንድ፣ ካደፈው የኃጢኣት ጥቀርሻ ተላቀን በንፁህ ቀልብ ወደ አላህ እንዞር ዘንድ በተውበት ልባችንን በማጠብ እንዘጋጅ። ተውበት ደግሞ የየቀኑ ዒባዳ ነው። ኃጢኣት መጥፎ ገድ አለው። ከመልካም ሥራዎች ያግዳል። በድንገት መልካም ከሰራንም ለዛውን ያሳጣናል።
ኃጢኣታቸው ሁሉ የተማረላቸው ተወዳጃችን [ﷺ] በቀን መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር በማድረግ ወደ አላህ ይመለሱ ነበር!
:
⚂ ዕቅድ ማዘጋጀት

«በእቅድ ላይ የወደቀ ለውድቀቱ ያቀደ ሰው ነው።» አስቀድሞ ያልተሰናዳ ከቀናቱ የሚገኘውን ቱሩፋት ማግኘት አይችልም። ሳይዘጋጅ የተቀበላቸው በትጋት ሊጠቀምባቸው አይችልም።
:
⚀ እናስተውል!

አቡ ሓሚድ አል‐ገዛሊ እንዲህ ይላሉ: ‐
«አላህ ባርያውን ሲወድ በምርጥ ጊዜያት ምርጥ ሥራዎች ላይ እንዲገኝ ያደርገዋል። ሲጠላው ደግሞ በምርጥ ጊዜያት በክፉ ሥራዎች ይጠምደዋል። ይህም አሳማሚ ቅጣቱ እና እጅግ የከበደ ጥላቻው ማሳያ እንዲሆን ያደርጋል። ሰውየው የጊዜያቱን በረከት ከመነፈጉ በተጨማሪ  የጊዜውን ክብር በመዳፈሩ የተነሳ የሚገጥመው ዝቅጠት ከባድ ነውና!»
:
አላህ በሰላምና በጤና ያድርሰን! ከተጠቃሚዎች ያድርገን!
ሼር ማድረግ አትርሱ! ባረከላሁ ፊኩም!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
19👍3😢1
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ባቡን‐ነጃሳት
🔴 ከዚህ ቀደም ተዘሏል እያላችሁ ስትጠይቁን ነበር። አልሀምዱሊላህ እዚህ አግኝተነዋል!
👍53
11👍2
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል አራት)
================
በዐስሩ ቀናት ምን እንስራ?
================
የሰው ልጅ በነፍስ እና በሩሕ ወይም በስጋ እና በመንፈስ መሀል የሚዋልል ፍጡር ነው። አንዴ መንፈሱ በሌላ ጊዜ ስጋው እየተሸናነፉ ይኖራል። እንደ መላኢካ የመንፈስ ህይወት ብቻ እንዲኖር፣ በአላህ ዒባዳ ላይ በቋሚነት ያለማቋረጥ እንዲሰነብት አልተደረገም። መንፈሳዊነቱ ሁሌም ቋሚ አይደለም። በእርግጥ ሁሌም ወደ ከፍተኛው የመንፈሳዊነት ልዕልና የሚያድጉ ነቢያትን የመሰሉ ሰዎች በሰው ዘር ውስጥ ቢኖሩም አብዝሃኛው ግን ከፍታና ዝቅታ ያለበት የመንፈስ ህይወት የሰው ልጅ መደበኛ ጠባይ መሆኑን ያሳብቃል። ሰው አንዴ ከመላኢካ በላይ በሌላ "አዕላ ዒሊዪን" ላይ በኬላ ጊዜ ከሰይጣናት ጋር "አስፈለ ሳፊሊን" የሚኖር ህዝብ ነው!
:
ነገርግን የአላህ ችሮታ ሆኖ ይህ ድክመታችንን ይሸፍንልን ዘንድ፣ ሰነፎች ወደ ታታሪዎቹ የአላህ ወልዮች ከፍታ ያስጠጋን ዘንድ ልዩ የአምልኮ ጊዜያት ተሰጥተውናል። በስንፍና ወራታችን ያሳለፍነውን እንድናካክስ ድጋፍ ተደርጎልናል።
ደጋጎች በእነዚህ ጊዜያት መልካም ስራን በማብዛት ከጌታቸው ለሚወርደው እዝነት ራሳቸውን ያቀርባሉ። ጌታቸው ዘንድ ቅርብ በሚያደርጓቸው ስራዎች ላይ ይሻማሉ። ምርጥ የአላህ ባርያ ሆኖ ለመታየት ይሽቀዳደማሉ። በጥቂት ጊዜያት ትእግስት ትልልቅ ደረጃዎችን ይጎናፀፋሉ። እነዚህ የታደሉ ሰዎች ናቸው!
:
አንዳንዶች ደግሞ እነዚህን ልዩ ጊዜያትም እንደሌላው ተራ ጊዜያት በዋል ፈዘዝ ያሳልፋሉ። የአላህ እዝነት ከምን ጊዜውም በላይ በሚቀርባቸው ቀን እንኳን እነርሱ ከአላህ ይሸሻሉ። ማትረፍ እየቻሉ ይከስራሉ። መዳን እየቻሉ ይጠፋሉ። ከፍ ማለት እየቻሉ ይወድቃሉ። አላህ ይጠብቀን!
:
የዐሽሩ ዚል‐ሒጅ‐ጃ (ዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት) ትሩፋት ከእነዚህ የአላህ ስጦታዎች አንዱ ነው። ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦች፣ መልካም ስራ ከምንም ጊዜ በላይ ታላቅ ምንዳ የሚያስገኝባቸው እና አላህ የማለባቸው ታላቅ ቀናት ናቸው።
ይህን የአላህ ስጦታ ለማግኘት መጓጓት፣ የተሰጠንን ታላቅ እድል ለመቋደስ መኳተን፣ ዓቅም በፈቀደው ሁሉ ታግለን ለአኺራችን ለመሰነቅ እና ለአላህ ያለንን ፍቅር ለማሳየት መንጎዳጎድ የኛ ፋንታ ነው!
አቀባበሉን ማሳመር፣ አጠቃቀሙን ማወቅ እና በታላቅ ወኔ ማሳለፍ የኛ ሚና ነው!
አላህ ተውፊቅ ይስጠን!
:
⚀ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ምን እናድርግ?
❶ ተውበት: ‐
በማንኛውም ጊዜ‐ ለኔ ቢጤ ኃጢኣተኛ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአላህ ባሪያ ምርጡ ተግባር ተውበት ነው። በተለይ እንዲህ ዓይነት ጊዜያትን በተውበት ስሜት ማሳለፍ ወሳኝ ነው። እውነተኛ ተውበት፣ በሙሉ ወኔ ወደ አላህ መመለስ፣ ርቀነው ወደሄድነው የጌታችን እቅፍ መጠጋት የመጀመሪያም የመጨረሻም ስራችን መሆን አለበት።
በዱንያም ሆነ በአኺራ የሰው ልጅ መድህን እና ስኬት ያለው በዚህ ውስጥ ነው። ያፈረስነውን መገንባት፣ ያቆሸሽነውን ማፅዳት፣ ያበላሸነውን ማደስ… ተውበት ነው።
ማን አለ ከእኛ መሀል ያላመፀ? ማናችን አለ ያላጠፋ? ማን አለ ንፁህ? ማን አለ ግፍ ያልሰራ?
ማንም!
ማጥፋቱን እንደተካንበት ሁሉ ያሳለፍነውን ደግሞ እንድንክስ ዘንድ የተሰጠን እድል ነው፤ ተውበት።
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
[وَتُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ ٱلْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ]
«ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡»
:
❷ ጊዜውን ለመጠቀም መጓጓት: ‐
እነዚህን ጊዜያት ለመጠቀም እና በመልካም ስራዎች ለማሸብረቅ መጓጓት አለብን። አላህ በሚፈልገው መልኩ በአግባቡ ጊዜውን ለመጠቀም መወሰን አለብን። አንድን ነገር ከልቡ ወስኖ የነየተን ሰው አላህ ያግዘዋል።
[وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلْمُحْسِنِينَ]
«እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡»
:
❸ ከኃጢኣት መራቅ: ‐
በእነዚህ ወቅቶች የሚሰራ መልካም ስራ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ወደ አላህ እንደሚያቃርቡ ሁሉ በእነዚህ ጊዜያት የሚፈፀሙ ኃጢኣቶችም ከሌላው ጊዜ በበለጠ ከአላህ የሚያርቁ መሆናቸው መታወቅ አለበት። ምናልባት ከምንም ጊዜ በበለጠ ከአላህ እዝነት ሊያባርሩን ይችላሉ።
አንዳንዴ በአንድ ኃጢኣት ምክንያት ከአላህ የምንርቅበትን መጠን መገመት ልንቸገር እንችላለን።
«ጀነት ከአንዳችሁ የነጠላ ጫማ ዘለበት በላይ የቀረበች ናት። እሳትም እንደዚያው።» ብለዋል ተወዳጃችን [ﷺ]
ስለዚህ ኃጢኣትህ እንዲማር፣ ከእሳት ነፃ እንድትደረግ፣ የአላህ ቅርብ ባሪያ መሆን ከሻህ በማንኛውም ጊዜ ከኃጢኣት ራቅ። በተለይም በእንዲህ ባሉ ወቅቶች የተለየየ ጥንቃቄ አድርግ!
:
የሚያገኘውን ነገር ትልቅነት ያወቀ የሚከፍለው ዋጋ ያንስበታል!
ጥቂት መታገስ ለመገመት የሚያዳግት ፍሬ ያፈራል!
ከሞት በኋላ ሁሉም ነገር ይገለጣል!
:
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
19
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል አምስት)
================
በዐስሩ ቀናት ምን እንስራ?
(…ካለፈው የቀጠለ)
================
❹ ዚክሩላህ: ‐
ቀላሉ ዒባዳ ነው። ወጪ አይጠይቅም፤ ጉልበት አይፈልግም፤ አያደክምም፤ ቦታም ሆነ ጊዜን አይመርጥም፤ ብዙ መስፈርቶች የሉትም!… ነገርግን ዚክር ታላቅ ዒባዳ ነው። ታላቅ ምንዳን ያስገኛል።

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ: ‐ «ከስራዎቻችሁ መሀል ምርጥ የሆነውን፣ ጌታችሁ ዘንድ ንፁህ የሆነውን፣ ደረጃችሁን የሚያደርግላችሁን፣ ወርቅና ብርን ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን፣ ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱና እነርሱም አንገታችሁን ከሚመቱ የሚበልጥ የሆነውን ትልቅ ስራ ልንገራችሁ?»
ሰዎችም: ‐ «አዎን! ይንገሩን።» አሉ።
ነቢዩ [ﷺ] «አላህን መዘከር!» አሉ።» ቲርሚዚ ዘግበውታል።
:
ሰይዲና ሙዐዝ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አላህን ከመዝከር የበለጠ ከአላህ ቅጣት የሚያድን ምንም ስራ የለም።»
:
❺ ሶላቱል‐ጀማዓ: ‐
ሶላትን በጀመዐ መስገድ ነቢዩ [ﷺ] ቅስቀሳ ያደረጉበት፣ ሰዎች ያለ በቂ ምክንያት እንዳይዘናጉ ያስጠነቀቁበት እና ታላቅ ምንዳ ያለው ተግባር ነው።

አቡዳዉድ አቡ ኡማማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] በመጥቀስ እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ከቤቱ ዉዱእ አድርጎ ግዴታ የሆነን ሶላት ለመስገድ የወጣ ሰው ሐጅን ኢሕራም ያደረገ ሰውን ምንዳ ያገኛል። የዱሓን ሶላት ለመስገድ የወጣ ሰው ደግሞ ‐ከሶላት ውጪ ሌላ ምክንያት ከሌለው‐ ዑምራ ያደረገ ሰውን የሚያህል ምንዳ ያገኛል። በመካከል ቧልትን ሳይቀላቅሉ ከሶላት አስከትሎ ሌላ ሶላትን መስገድ ሰውየውን አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ካሉት "ዒሊይ‐ዪን" ጋር ያስመዘግበዋል።»
:
❻ ጾም: ‐
ዘጠኙን ቀናት መጾም እንደሚወደድ የሚጠቁሙ በርካታ ሐዲሶች ተገኝተዋል።

አቡ ኡማማ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ እዘዙኝ!» አልኳቸው። እርሳቸውም: ‐ «ጾምን አብዛ፤ እርሱን የሚስተካከል የለም።» አሉኝ።» ነሳኢይ ግበውታል።
:
«ነቢዩ [ﷺ] ዓሹራን፣ የዙልሒጃን ዘጠኝ ቀናት እና ከየወሩ ሦስት ቀናት ይጾሙ ነበር።» ነሳኢይ ዘግበውታል።
:
❼ ሶደቃ: ‐
ሶደቃ ታላቅ ምንዳ አለው። ሲሳይን ይባርካል። በዱንያ መልካም ስም፣ በአኺራ ደግሞ ታላቅ ደረጃን ያስገኛል።
:
በቲርሚዚይ ዘገባ እንደተገለፀው የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ማንም ሰው አንድን መልካም ነገር ከመፀወተ ‐አላህ መልካምን እንጂ አይቀበልም‐ አዛኙ ጌታ በቀኙ (በጥሩ ሁኔታ) ይቀበለዋል። አንዲት ተምር ብትሆን እንኳን በርሱ እጅ ላይ (እንክብካቤ) ትፋፋለች። አንዳችሁ ግልገላችሁን እንደምትንከባከቡት ከተራራ እስከምትበልጥ ድረስ ተንከባክቦ ያሳድጋታል።»
:
❽ ቁርኣን: ‐
ዐስሩን ቀናት በረመዳን እና በዙልሒጃ መሀል ለሁለት ወራት ያህል አብዝሃኞቻችን ከተውነው ቁርኣን ጋር ለመታረቅ እንጠቀምባቸው። ቁርኣንን ቢያንስ አንድ ጊዜ እናኽትም። ከመልክቱ ጋርም ቅርርብ እንፍጠር።…

ቁርኣንን ማንበብ ከሌሎች ዚክሮች የበለጠ ትልቅ ምንዳ አለው።

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከአላህ መፅሀፍ ውስጥ አንድን ፊደል ያነበበ ሰው አንድ ሐሰና አለው። እያንዳንዱ ሐሰና ደግሞ በዐስር አምሳያው ይባዛል። الم (አሊፍ ላም ሚም) አንድ ፊደል ናት አልልም። ነገርግን አሊፍ አንድ ፊደል፣ ላም አንድ ፊደል እና ሚምም አንድ ፊደል ናቸው።» ቲርሚዚይ ዘግበውታል።
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
23👍1
ሐጅ ባይሳካልኝም…
(ክፍል ስድስት)
===========
ንፁህ ተውበት = 0 ኃጢኣት
====
ሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁዐንሁ] እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ]: ‐ «ሐጅ ያደረገ፣ የወሲብ ወሬን ያላወራ፣ የዓመፅ ተግባር ያልፈፀመ ሰው እናቱ እንደወለደችው ቀን ሆኖ ይመለሳል።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
:
…እናቱ የወለደችው ቀን ምንም አያውቅም። ሩሑ የሥጋውን ጠባይ አልወረሰችም። ከአላህ እንደመጣች ሁሉ አላህን ባላመፀችበት ንፅህናዋ ኩልል ብላ እንደፀዳች ናት። ልሳኑ ክፉን ከመናገር ዲዳ ነው። ጆሮው ክፉን ከማድመጥ ደንቁሯል። እጁ ክፉን ከመስራት ደካማ ነው። አእምሮው ክፉን አያስብም። ዐይኑም በሐራም ላይ አይቀላውጥም። የሰው ልጅ ከእናቱ ማህፀን በወጣ ቀን ፅዱ ነው።
ሐጀኛም ሐጁን እንደ ህፃን ልጅ ''ተቆጥቦ'' ካሳለፈው ያለፈው ህይወቱ ሳያስተጓጉለው የህፃንን ንፅህና ይላበሳል።…
:
ነገርግን ንፁህ ለመሆን ሐጅ መሄድ የግድ ነው?!…
በፍፁም!
እዚሁ ተቀምጠህ፣ ያለ ቲኬት፣ አካልህ ሳይደክም፣ ሳትንገላታ መፅዳት ትችላለህ።
አዲስ ነገር ልነግርህ አይደለም!
ተውበት አድርግ። «ከኃጢኣቱ ንሰሓ ያደረገ ኃጢኣት እንደሌለበት ነው!» ብለዋል ተወዳጁ [ﷺ]።
:
በእርግጥ ተውበትም ቀላል ነው አልልህም። እጅግ ጥኑ ዒባዳ ነው!
ነፍስን የስሜቷን ጡጦ መንጠቅ፣ ከምትወደው ነገር እንድትርቅ ማድረግ፣ ዝንባሌዋን እንድትቆጣጠር ማረቅ፣ እንደውም ባሳለፈችው "የደስታ" ዳንኪራዋ እንድትፀፀት ማድረግ ቀላል አይደለም!
"ተውበት ፀፀት ነው።" ብለዋል ተፈቃሪያችን [ﷺ]።
:
በልብህ ውስጥ የኃጢኣትህ ደስታ እያለ ተውበት የለም! ያሳለፍከውን ስታስብ በፀፀት እስካልተንገበገብክ ተውበት የለም!
የተውበት አስኳሉ ፀፀት ነው። የተውበት ድርና ማጉ፣ ዋልታና ማገሩ፣ አልፋና ኦሜጋው…
ከአላህ ያሸሸህን ወንጀልህን ስታስብ ቢያንስ ልታጣቸው ከማትሻቸው ወዳጆችህ በነጠለህ ጥፋትህ ልክ መፀፀት አለብህ። ካፈቀርካትና ከምታፈቅራት ሚስትህ የነጠለህ ወንጀልን ስታስብ፣ ከምትወዳት እናትህ ወይም አባትህ ጋር ያጣላህ ጥፋት ትዝ ሲልህ፣ ጋሻና ደጀንህ ከነበረ ወንድምህ የነጠለህን ክፋት ስታስተውል የሚሰማህን ስሜት ታውቀዋለህ?!
ያ… ስሜት በአላህ ላይ ያመፅክበትን ወንጀል ስታስብ ካልተሰማህ ተውበት የለህም!
:
በሰይጣን ባህር ስትዋኝ አምሽተህ ፈጅር አምልጦህ ሳትቆጭ ቀርተህ በቀዷ ልትክስ ብትሞክር አልቶበትክም!
ከዱርዬ ጓደኞችህ ጋር እየቦረቅክ፣ ራስህን በኃጢኣት አጥር አካበህ እየኖርክ ተውበት የለም!
:
በኃጢኣት ዐውድ እየዞርክ፣ ዛሬ ያለፍከውን ነገም እየደገምክ፣ ሳትሳቀቅ፣ ሳትፈራ፣ ሳትጨነቅ፣ ምንም እንዳልሆነ እየኖርክ ተውበት የለም!
:
ወንጀል ሙያ መስሎህ እያፈቀርከው፣ በሚያሸማቅቀው ዓመፅህ እየደነፋህ፣ መደበቅ ሲገባህ ደረትህን ነፍተህ፣ አደባባይ ላይ እየተሰጣህ፣ ከፈጣሪም ከተፈጣሪም ሳታፍር ተውበት የለም!
:
«ተውበት ''ከባኢር'' ላይ የወደቁ ሰዎች ሥራ ነው፤… አደጋ ውስጥ ያሉት እነርሱ ብቻ ናቸው፤…» አንተና እኔ ''አነስተኛ'' ብለን በምናስባቸው ኃጢኣት እንደማይመረመሩ እያሰብን ተውበት የለም!…
በኛ ግምት ''ከባኢር'' የሚባለው ኃጢኣት ዚናና ኸምርን መድፈር ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው ሁሉ ሳይሰራም የተማረ፣ ተሰርቶም የተሰረዘ ይመስለናል። ''በሶጋኢር" ላይ ችክ ማለት ትንሹንም ትልቅ እንደሚያደርገው አናውቅም። ዓመፅን ''ትንሽ'' ብሎ ማሰብ በራሱ ያለውን ክብደት አንገነዘብም። ዓመፁን ሳይሆን ያመፅነውን አካል ትልቅነት አንመለከትም። አደጋ ውስጥ እንዳለን ስለማንረዳ በሞኝነት ባህር ሰምጠን በደህነኝነት አዞ ተውጠናል። አንነቃም። አንደነግጥም። አንመለስም።
:
የሰው ሐቅ እየነጠቁ ለድኻ እየሶደቁ ተውበት አለ?!… አንዱን ሙስሊም ወዶ ሌላውን ወንድም እየናቁ ተውበት አለ?!…
:
ኃጢኣተኛን የሚወድ፣ ለግፈኞች የሚያጨበጭብ፣ የኃጢኣተኛን ኃጢኣት በአድናቆት እየተመለከተ፣ ከአፈንጋጮች ጋር ወዳጅነት የመሰረተ፣ የአላህን ሰዎች እየጠላ ተውበተኛ ይባላል?!
:
ተውበት ቀልድ አይደለም። በእርግጥም ጥኑ ነው። እግር ሳይሆን ቀልብ የሚጓዝበት ከባድ ዐቀበት ነው።
ከዚህ ሁሉ ቀልድ ጋር ተውበት የለም!…
ከመነሻዬ ሳልርቅ ነፍሴንም ሆነ ወዳጆቼን ልምከር። እንደ ሐጀኛው ሁሉ ተውበት ያደረገም "እናቱ እንደወለደችው ቀን" ንፁህ ይሆናል!
ሐጅ ባይሳካልንም ከተውበት የሚያግደን የለም!…
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
27😢1
Rules of Uduhiya.pdf
1.6 MB
ኡድሒያን ከልማድ አውጥተን እንደ ዒባዳ ካየነው እንዲህ ዓይነት ትምህርቶችን መውሰድ አለብን። ጥያቄ ካላችሁ አስተያየት መስጫው ውስጥ ጣሉልን ለሁሉም እንዲጠቅም አድርገን በዚሁ ቻናል ውስጥ መልስ እንሰጥበታለን። ባረከላሁ ፊኩም!
9
🔸ኢማም አውዛዒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«አላህን ለመለመን ጉዳዮቻቸውን ለዐረፋ ቀን የሚያስቀምጡ ሰዎችን [ሰለፎችን] አግኝቻለሁ።»
:
የዐረፋ ቀንን ጥቅም የሚያገኘው የእለቱን ታላቅነት ያወቀ ሰው ብቻ ነው።
«አላህ የወደደው ሰው በምርጦቹ ጊዜያት አላህ በወደዳቸው ምርጥ ስራዎች ይጠመዳል። አላህ የጠላው ምርጥ ጊዜያትን ሳይቀር በከንቱ ነገሮች ያሳልፋል። ይኸውም ቅጣቱን ድርብ ሊያደርግበት እና ውድቀቱን ከፍተኛ ሊያደርግበት የመሻቱ ምልክት ነው። የጊዜን በረከት ነስቶት የተሰጠውን ወቅት ያባክናል።» ኢማም አል‐ገዛሊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ]
:
ወዳጆቻችን ሆይ!
የዐረፋ ቀን እንደሌላው ቀን አይደለም። ከየትኛውም የዓመቱ ቀናት የላቀ ክቡር ቀን ነው። ስለዚህ በአግባቡ ለመጠቀም የተለየ ትኩረት ያሻናል። ለምሳሌ እነዚህን ስራዎች በእለቱ ለማከናወን እንነይት: ‐

❶ የዐረፋን ቀን ክብር ማሰብ፣ ከዐሊሞች ማድመጥና በቀልብ ውስጥ ተገቢውን የክብር ስሜት ለመፍጠር መጣር።

❷ ሌሊት ሰሑር መብላት።

❸ እለቱን መጾም። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለሁ።»

❹ ከእለቱ ፈጅር ሶላት በኋላ ከሶላት ጋር የተያያዘውን ተክቢራ [ተክቢራ ሙቀይ‐የድ] መጀመር።

❺ የጠዋት ውዳሴና ዚክር ማድረግ።

❻ የዱሓ ሶላት መስገድ።

❼ ዱዓ ማብዛት። የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔም ሆንኩኝ ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ከተናገሩት ሁሉ ምርጡ ተከታዩ ነው: ‐ «ላኢላሀ ኢል‐ለላህ። ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል‐ሙልኩ ወለሁል‐ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።»

❽ ተውበት እና ኢስቲግፋር ማብዛት።

❾ ለሙእሚኖች ዱዓ እና ኢስቲግፋር ማድረግ።

❿ እለቱን በጥንቃቄ ማሳለፍ። ሁላችንም የአላህን ምህረትን ከሚከለክሉ ጠባዮች ራሳችንን እንጠብቅ። በእለቱ አላህ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ እጅግ ብዛት ያለውን ምእመን ይምራል። ይቅርታውን ይቸራል።
አላህ ተውፊቁን ይስጠን!
45
ዛሬ የዙልሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን ነው
ሐጀኞች በሙሉ ለነገው ዋናው የሐጅ ስራ— ለዐረፋው ዉቁፍ— እየተዘጋጁ ነው። ሁሉም ሚና ላይ ከትመዋል።
ዕለቱ የውሙት–ተርዊያ (ውሃን የማጠራቀም ቀን) ይባላል። ስያሜውን ያገኘው ሐጀኞች በዚህ ቀን የውሃ ማጠራቀሚያ "ቀርበታዎቻቸውን"— ለነገው የዐረፋ ቀን ጥም— ብለው የሚሞሉበት ቀን ስለሆነ ነው። ምክንያቱም ዐረፋ ሜዳ ላይ ውሃ አይገኝም።…
                          
በዚህ አጋጣሚ ለኛ የሚሆን መልእክት ላንሳ…
ለአኺራ ስለመሰነቅ አስበባችኋል!?…
የኢማን፣ የተቅዋ እና የበጎ ስራ ጥም ነው ያን ቀን የሚኖረው። የዚክርና የአምልኮ ዝናብ ነው ከድርቁ የሚያተርፈው። ረዥም መንገድ አለ ውዶቼ። ስንቃችን ግን ምን ያህል ያስኬዳል!?… ቀልብህን ዛሬ በጎርፍ ሙላው። በተቅዋና በመልካም ስራ ጎርፍ።…
                          
ነገ የዐረፋ ቀን ነው። ሐጀኞች ዐረፋ ላይ ይውላሉ። እኛ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ለማበር እንፆማለን። የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመት ኃጢኣት ያስምራል" ብለዋል።
እና ምን ወሰናችሁ!?… እነሆ የሚምር ጌታ ኑ ልማራችሁ እያላችሁ ነው!…
ዱዐ የእለቱ ምርጥ ዒባዳ ነው። "ምርጡ ዱዐ የዐረፋ ቀን ዱዐ ነው" ብለዋል ነብያችን [ﷺ]።
የዱዐን ጉድ በኋላ አወራችኋለሁ!
53😍5👍1
Tofik Bahiru pinned «🔸ኢማም አውዛዒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «አላህን ለመለመን ጉዳዮቻቸውን ለዐረፋ ቀን የሚያስቀምጡ ሰዎችን [ሰለፎችን] አግኝቻለሁ።» : የዐረፋ ቀንን ጥቅም የሚያገኘው የእለቱን ታላቅነት ያወቀ ሰው ብቻ ነው። «አላህ የወደደው ሰው በምርጦቹ ጊዜያት አላህ በወደዳቸው ምርጥ ስራዎች ይጠመዳል። አላህ የጠላው ምርጥ ጊዜያትን ሳይቀር በከንቱ ነገሮች ያሳልፋል። ይኸውም ቅጣቱን ድርብ ሊያደርግበት…»
ዓረፋ‐ትልቁ የአላህ ቀን
==============
ነገ ጠዋት ፀሀይ ስትፈነጥቅ አላህ የፈቀደላቸውና በምርጫው ከሌሎች የለያቸው ጥቂት ሑጃጅ የአላህ ባሮች ወደ ዐረፋ ሜዳ ያመራሉ። ዋነኛውን የሐጅ ስነስርዐት አካል "ዉቁፍን" ሊፈፅሙ።…
በእርግጥ የተርዊያ ቀን የሚሰኘውን የዛሬውን ቀን ሚና ውስጥ በዒባዳና በዚክር አሳልፈዋል።
:
የዐረፋ ቀን ታላቁ የአላህ ቀን ነው። ኃጢኣት ይሰረዝበታል። በእለቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል። ከምንም ጊዜ በበለጠ የአላህ እዝነት ለባሮቹ ቅርብ ይሆናል።
:
የዐረፋ ቀን ዲን የተሟላበት ቀን ነው። በሙስሊሞች ላይ የአላህ ፀጋ የተፈፀመበት እለት ነው።
የተውበት ቀን ነው። ምህረት የሚታደልበት ቀን ነው። ለአላህ የሚዋደቁበት የዱዓ ቀን ነው። የለቅሶና የተስፋ ቀን ነው። በርካታ ትሩፋቶቹ በሐዲስ ላይ ተጠቅሰዋል። በእለቱ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት ተጠቁመዋል: ‐
:
⚀ የአመቱ ምርጥ ቀን
ጃቢር [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከቀናት ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ነው።» ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።
በሌላ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከዐረፋ ቀን በላይ አላህ ዘንድ በላጭ የሆነ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ቅርቡ ሰማይ ወርዳል። በሰማይ ፍጡራን ላይም በምድር ሰዎች [ልቅና] ይፎክራል።»
:
⚁ መላኢካ የሚሰበሰብበት ቀን:
የዐረፋ ቀንን ክብር ለማወቅ አላህ የማለበት ቀን መሆኑ ብቻ ይበቃል። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ]
«በተጣጅና በሚጣዱበትም፤ (እምላለሁ)፡፡»
ከአቡሁረይራ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «[ሱረቱል ቡሩጅ ላይ] 'ወልየውሚል‐መውዑድ/በተቀጠረው ቀን' የተባለው የቂያማን ቀን ነው። አልየውሙል‐መሽሁድ/የሚጣዱበት ቀን ደግሞ የዐረፋ ቀን ነው። አልየውሙሽ‐ሻሂድ/የሚጣደው ቀን ደግሞ ጁሙዐ ቀን ነው።» ቲርሚዚ ዘግበውታል።
ሱረቱል‐ፈጅር ላይም በድጋሚ አላህ የማለበት ቀን ነው። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَٱلشَّفْعِ وَٱلْوَتر]
«በጥንዱም በነጠላውም።»
በዚህ አንቀፅ አል‐ወትር/ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጥንድ የተባለው [ዙልሒጃ 10 ወይም] የአድሓ ቀንን ነው። ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን [ዙልሒጃ 9] ነው።»
:
⚂ ዲን የተሟላበት ቀን:
ቡኻሪና ሙስሊም ዑመር ኢብኑል ኸጣብን [ረዐ] ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት «አንድ አይሁድ ዑመርን እንዲህ አላቸው: «የሙእሚኖች አሚር ሆይ! በመፅሀፋችሁ ውስጥ ያለች አንዲት አንቀፅ አለች። በእኛ በአይሁዶች ላይ ወርዳ ቢሆን የወረደችበትን ቀን ዒድ አድርገን እንይዘው ነበር።» አለ። ዑመርም «የቷ አንቀፅ?» አሉ። ተከታይዋን አንቀፅ ጠቀሰላቸው: ‐
[اليوم أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا]
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡»
ዑመርም [ረዐ] እንዲህ አሉ: ‐ «ይህ የወረደበትን ቀን እና በነቢዩ [ﷺ] ላይ የወረደበትን ስፍራም አውቀነዋል። በጁሙዐ ቀን የዐረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ሳለ የወረደ ነው።»
:
ዲን በዚያን ቀን ተሟላ የተባለው ሙስሊሞች ከዚያ በፊት ሐጅ አድርገው ስለማያውቁ ነው። ሐጅ ሲያደርጉ ዲኑ ያኔ ተሟላ። ምክንያቱም ሐጅ የኢስላም አንዱ መዐዘን ነው። በዚያን ዓመት ከሺርክ የፀዳው በኢብራሂም መንገድ ላይ የተመሰረተው የሐጅ ስነስርዐት ከነሙሉ ክብሩ ዳግም ተግባራዊ ተደርጓል። ዲኑም ሙሉ ማእዘናቱ ተሟልቷል።
:
⚃ ምርጡ ዱዓ:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ምርጥ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔና ሌሎች ነቢያት ከተናገርነው ሁሉ ምርጡ ንግግር "ላኢላሀ ኢልለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ቃል ነው።»
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
በዐረፋ ቀን የአላህን እዝነት እና ምህረት ለማግኘት ዚክርና ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል። በተለይም «ላኢላሀ ኢልለላህ» የእለቱ ምርጥ ዚክር ነው።
:
⚄ ጾም:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ አምናለሁ።» ሙስሊም ዘግበውታል
:
⚅ የዒድ ቀን ነው:
የዐረፋ ቀን የዒድ ቀን ነው። ሙስሊሞች ከሚኮሩባቸው የበዓል ቀናቶቻቸው መሀል ይመደባል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«የዐረፋ ቀን፣ የአድሐ ቀን እና የተሽሪቅ ቀናት ለሙስሊሞች የዒድ ቀናችን ናቸው። የመብልና የመጠጥ ቀናት ናቸው።» ቲርሚዚ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል።
:
⚆ የምህረት እና ከእሳት ነፃ የሚደረግበት:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «አላህ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ከዐረፋ ቀን የበለጠ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ምድር ይቀርባል። በመላኢካዎች ላይም ይፎክራል። 'እነዚህ ባሮቼ ከእኔ ውጪ ሌላን አይፈልጉም!' ይላል።» ሙስሊም ዘግበውታል።
:
በዚህ እለት ከእሳት ነፃ መሆንና የአላህን ምህረት ማግኘት የሚሻ ሰው በአላህ እዝነት ለመታየት የሚያበቁትን ተግባራት ይፈፅም። ከሁሉም የመጀመሪያው ስራ ደግሞ ከኃጢኣት ነፍሱን መጠበቅ ነው።
ሌሎች ተግባራት ተከታዮቹ ናቸው:
① ጾም
ከሐጀኛ በስተቀር ሌላው ሰው ይጾማል። የዚህ ቀን ጾም የሁለት ዓመታት ኃጢኣት ያስምራል።ተክ
② ተክቢራ
ተክቢራ የእለቱ ዓርማ ነው። በተለይም ከሱብሒ ሶላት ጀምሮ ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይደረጋል።
③ ማንኛውም ዚክርና ዱዓእ
ቁርኣን መቅራት፣ ሶለዋት ማድረግ፣ ተክቢራ፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ ኢስቲግፋር ማድረግ። አንዳንዴ ለብቻ ቆይቶም በጀመዐ ዱዓና ዚክር ማድረግ የእለቱ ድምቀት ነው።
እለቱ ጥቂት ተሰርቶ ብዙ የሚገኝበት በመሆኑ እንጠቀምበት! ቤተሰቦቻችንን እናንቃ! የምናውቀውን ሁሉ እናነሳሳ!
አላህ ተውፊቅ ይስጠን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
32
ኢላሂ!
የሰጠኸን አሟላልን።
የለገስከንን አትግፈፈን።
የሸፈንክልንን አትግለጥብን።
የምታውቀውን ኃጢኣታችንን በሙሉ ማረን።
36👍5
ኢላሂ!
በየሀገሩ ያሉ ተበዳይ ደካሞችን ሁሉ እርዳ። ጨካኝ ግፈኞች ላይም ትእግስትህን እንዳሳየኸን ቁጣና በቀልህንም አሳየን።
42👍4
2025/10/26 09:49:41
Back to Top
HTML Embed Code: