Telegram Web Link
Rules of Uduhiya.pdf
1.6 MB
ኡድሒያን ከልማድ አውጥተን እንደ ዒባዳ ካየነው እንዲህ ዓይነት ትምህርቶችን መውሰድ አለብን። ጥያቄ ካላችሁ አስተያየት መስጫው ውስጥ ጣሉልን ለሁሉም እንዲጠቅም አድርገን በዚሁ ቻናል ውስጥ መልስ እንሰጥበታለን። ባረከላሁ ፊኩም!
9
🔸ኢማም አውዛዒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«አላህን ለመለመን ጉዳዮቻቸውን ለዐረፋ ቀን የሚያስቀምጡ ሰዎችን [ሰለፎችን] አግኝቻለሁ።»
:
የዐረፋ ቀንን ጥቅም የሚያገኘው የእለቱን ታላቅነት ያወቀ ሰው ብቻ ነው።
«አላህ የወደደው ሰው በምርጦቹ ጊዜያት አላህ በወደዳቸው ምርጥ ስራዎች ይጠመዳል። አላህ የጠላው ምርጥ ጊዜያትን ሳይቀር በከንቱ ነገሮች ያሳልፋል። ይኸውም ቅጣቱን ድርብ ሊያደርግበት እና ውድቀቱን ከፍተኛ ሊያደርግበት የመሻቱ ምልክት ነው። የጊዜን በረከት ነስቶት የተሰጠውን ወቅት ያባክናል።» ኢማም አል‐ገዛሊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ]
:
ወዳጆቻችን ሆይ!
የዐረፋ ቀን እንደሌላው ቀን አይደለም። ከየትኛውም የዓመቱ ቀናት የላቀ ክቡር ቀን ነው። ስለዚህ በአግባቡ ለመጠቀም የተለየ ትኩረት ያሻናል። ለምሳሌ እነዚህን ስራዎች በእለቱ ለማከናወን እንነይት: ‐

❶ የዐረፋን ቀን ክብር ማሰብ፣ ከዐሊሞች ማድመጥና በቀልብ ውስጥ ተገቢውን የክብር ስሜት ለመፍጠር መጣር።

❷ ሌሊት ሰሑር መብላት።

❸ እለቱን መጾም። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለሁ።»

❹ ከእለቱ ፈጅር ሶላት በኋላ ከሶላት ጋር የተያያዘውን ተክቢራ [ተክቢራ ሙቀይ‐የድ] መጀመር።

❺ የጠዋት ውዳሴና ዚክር ማድረግ።

❻ የዱሓ ሶላት መስገድ።

❼ ዱዓ ማብዛት። የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔም ሆንኩኝ ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ከተናገሩት ሁሉ ምርጡ ተከታዩ ነው: ‐ «ላኢላሀ ኢል‐ለላህ። ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል‐ሙልኩ ወለሁል‐ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።»

❽ ተውበት እና ኢስቲግፋር ማብዛት።

❾ ለሙእሚኖች ዱዓ እና ኢስቲግፋር ማድረግ።

❿ እለቱን በጥንቃቄ ማሳለፍ። ሁላችንም የአላህን ምህረትን ከሚከለክሉ ጠባዮች ራሳችንን እንጠብቅ። በእለቱ አላህ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ እጅግ ብዛት ያለውን ምእመን ይምራል። ይቅርታውን ይቸራል።
አላህ ተውፊቁን ይስጠን!
45
ዛሬ የዙልሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን ነው
ሐጀኞች በሙሉ ለነገው ዋናው የሐጅ ስራ— ለዐረፋው ዉቁፍ— እየተዘጋጁ ነው። ሁሉም ሚና ላይ ከትመዋል።
ዕለቱ የውሙት–ተርዊያ (ውሃን የማጠራቀም ቀን) ይባላል። ስያሜውን ያገኘው ሐጀኞች በዚህ ቀን የውሃ ማጠራቀሚያ "ቀርበታዎቻቸውን"— ለነገው የዐረፋ ቀን ጥም— ብለው የሚሞሉበት ቀን ስለሆነ ነው። ምክንያቱም ዐረፋ ሜዳ ላይ ውሃ አይገኝም።…
                          
በዚህ አጋጣሚ ለኛ የሚሆን መልእክት ላንሳ…
ለአኺራ ስለመሰነቅ አስበባችኋል!?…
የኢማን፣ የተቅዋ እና የበጎ ስራ ጥም ነው ያን ቀን የሚኖረው። የዚክርና የአምልኮ ዝናብ ነው ከድርቁ የሚያተርፈው። ረዥም መንገድ አለ ውዶቼ። ስንቃችን ግን ምን ያህል ያስኬዳል!?… ቀልብህን ዛሬ በጎርፍ ሙላው። በተቅዋና በመልካም ስራ ጎርፍ።…
                          
ነገ የዐረፋ ቀን ነው። ሐጀኞች ዐረፋ ላይ ይውላሉ። እኛ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ለማበር እንፆማለን። የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመት ኃጢኣት ያስምራል" ብለዋል።
እና ምን ወሰናችሁ!?… እነሆ የሚምር ጌታ ኑ ልማራችሁ እያላችሁ ነው!…
ዱዐ የእለቱ ምርጥ ዒባዳ ነው። "ምርጡ ዱዐ የዐረፋ ቀን ዱዐ ነው" ብለዋል ነብያችን [ﷺ]።
የዱዐን ጉድ በኋላ አወራችኋለሁ!
53😍5👍1
Tofik Bahiru pinned «🔸ኢማም አውዛዒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «አላህን ለመለመን ጉዳዮቻቸውን ለዐረፋ ቀን የሚያስቀምጡ ሰዎችን [ሰለፎችን] አግኝቻለሁ።» : የዐረፋ ቀንን ጥቅም የሚያገኘው የእለቱን ታላቅነት ያወቀ ሰው ብቻ ነው። «አላህ የወደደው ሰው በምርጦቹ ጊዜያት አላህ በወደዳቸው ምርጥ ስራዎች ይጠመዳል። አላህ የጠላው ምርጥ ጊዜያትን ሳይቀር በከንቱ ነገሮች ያሳልፋል። ይኸውም ቅጣቱን ድርብ ሊያደርግበት…»
ዓረፋ‐ትልቁ የአላህ ቀን
==============
ነገ ጠዋት ፀሀይ ስትፈነጥቅ አላህ የፈቀደላቸውና በምርጫው ከሌሎች የለያቸው ጥቂት ሑጃጅ የአላህ ባሮች ወደ ዐረፋ ሜዳ ያመራሉ። ዋነኛውን የሐጅ ስነስርዐት አካል "ዉቁፍን" ሊፈፅሙ።…
በእርግጥ የተርዊያ ቀን የሚሰኘውን የዛሬውን ቀን ሚና ውስጥ በዒባዳና በዚክር አሳልፈዋል።
:
የዐረፋ ቀን ታላቁ የአላህ ቀን ነው። ኃጢኣት ይሰረዝበታል። በእለቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል። ከምንም ጊዜ በበለጠ የአላህ እዝነት ለባሮቹ ቅርብ ይሆናል።
:
የዐረፋ ቀን ዲን የተሟላበት ቀን ነው። በሙስሊሞች ላይ የአላህ ፀጋ የተፈፀመበት እለት ነው።
የተውበት ቀን ነው። ምህረት የሚታደልበት ቀን ነው። ለአላህ የሚዋደቁበት የዱዓ ቀን ነው። የለቅሶና የተስፋ ቀን ነው። በርካታ ትሩፋቶቹ በሐዲስ ላይ ተጠቅሰዋል። በእለቱ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት ተጠቁመዋል: ‐
:
⚀ የአመቱ ምርጥ ቀን
ጃቢር [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከቀናት ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ነው።» ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።
በሌላ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከዐረፋ ቀን በላይ አላህ ዘንድ በላጭ የሆነ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ቅርቡ ሰማይ ወርዳል። በሰማይ ፍጡራን ላይም በምድር ሰዎች [ልቅና] ይፎክራል።»
:
⚁ መላኢካ የሚሰበሰብበት ቀን:
የዐረፋ ቀንን ክብር ለማወቅ አላህ የማለበት ቀን መሆኑ ብቻ ይበቃል። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ]
«በተጣጅና በሚጣዱበትም፤ (እምላለሁ)፡፡»
ከአቡሁረይራ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «[ሱረቱል ቡሩጅ ላይ] 'ወልየውሚል‐መውዑድ/በተቀጠረው ቀን' የተባለው የቂያማን ቀን ነው። አልየውሙል‐መሽሁድ/የሚጣዱበት ቀን ደግሞ የዐረፋ ቀን ነው። አልየውሙሽ‐ሻሂድ/የሚጣደው ቀን ደግሞ ጁሙዐ ቀን ነው።» ቲርሚዚ ዘግበውታል።
ሱረቱል‐ፈጅር ላይም በድጋሚ አላህ የማለበት ቀን ነው። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَٱلشَّفْعِ وَٱلْوَتر]
«በጥንዱም በነጠላውም።»
በዚህ አንቀፅ አል‐ወትር/ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጥንድ የተባለው [ዙልሒጃ 10 ወይም] የአድሓ ቀንን ነው። ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን [ዙልሒጃ 9] ነው።»
:
⚂ ዲን የተሟላበት ቀን:
ቡኻሪና ሙስሊም ዑመር ኢብኑል ኸጣብን [ረዐ] ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት «አንድ አይሁድ ዑመርን እንዲህ አላቸው: «የሙእሚኖች አሚር ሆይ! በመፅሀፋችሁ ውስጥ ያለች አንዲት አንቀፅ አለች። በእኛ በአይሁዶች ላይ ወርዳ ቢሆን የወረደችበትን ቀን ዒድ አድርገን እንይዘው ነበር።» አለ። ዑመርም «የቷ አንቀፅ?» አሉ። ተከታይዋን አንቀፅ ጠቀሰላቸው: ‐
[اليوم أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا]
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡»
ዑመርም [ረዐ] እንዲህ አሉ: ‐ «ይህ የወረደበትን ቀን እና በነቢዩ [ﷺ] ላይ የወረደበትን ስፍራም አውቀነዋል። በጁሙዐ ቀን የዐረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ሳለ የወረደ ነው።»
:
ዲን በዚያን ቀን ተሟላ የተባለው ሙስሊሞች ከዚያ በፊት ሐጅ አድርገው ስለማያውቁ ነው። ሐጅ ሲያደርጉ ዲኑ ያኔ ተሟላ። ምክንያቱም ሐጅ የኢስላም አንዱ መዐዘን ነው። በዚያን ዓመት ከሺርክ የፀዳው በኢብራሂም መንገድ ላይ የተመሰረተው የሐጅ ስነስርዐት ከነሙሉ ክብሩ ዳግም ተግባራዊ ተደርጓል። ዲኑም ሙሉ ማእዘናቱ ተሟልቷል።
:
⚃ ምርጡ ዱዓ:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ምርጥ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔና ሌሎች ነቢያት ከተናገርነው ሁሉ ምርጡ ንግግር "ላኢላሀ ኢልለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ቃል ነው።»
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
በዐረፋ ቀን የአላህን እዝነት እና ምህረት ለማግኘት ዚክርና ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል። በተለይም «ላኢላሀ ኢልለላህ» የእለቱ ምርጥ ዚክር ነው።
:
⚄ ጾም:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ አምናለሁ።» ሙስሊም ዘግበውታል
:
⚅ የዒድ ቀን ነው:
የዐረፋ ቀን የዒድ ቀን ነው። ሙስሊሞች ከሚኮሩባቸው የበዓል ቀናቶቻቸው መሀል ይመደባል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«የዐረፋ ቀን፣ የአድሐ ቀን እና የተሽሪቅ ቀናት ለሙስሊሞች የዒድ ቀናችን ናቸው። የመብልና የመጠጥ ቀናት ናቸው።» ቲርሚዚ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል።
:
⚆ የምህረት እና ከእሳት ነፃ የሚደረግበት:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «አላህ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ከዐረፋ ቀን የበለጠ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ምድር ይቀርባል። በመላኢካዎች ላይም ይፎክራል። 'እነዚህ ባሮቼ ከእኔ ውጪ ሌላን አይፈልጉም!' ይላል።» ሙስሊም ዘግበውታል።
:
በዚህ እለት ከእሳት ነፃ መሆንና የአላህን ምህረት ማግኘት የሚሻ ሰው በአላህ እዝነት ለመታየት የሚያበቁትን ተግባራት ይፈፅም። ከሁሉም የመጀመሪያው ስራ ደግሞ ከኃጢኣት ነፍሱን መጠበቅ ነው።
ሌሎች ተግባራት ተከታዮቹ ናቸው:
① ጾም
ከሐጀኛ በስተቀር ሌላው ሰው ይጾማል። የዚህ ቀን ጾም የሁለት ዓመታት ኃጢኣት ያስምራል።ተክ
② ተክቢራ
ተክቢራ የእለቱ ዓርማ ነው። በተለይም ከሱብሒ ሶላት ጀምሮ ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይደረጋል።
③ ማንኛውም ዚክርና ዱዓእ
ቁርኣን መቅራት፣ ሶለዋት ማድረግ፣ ተክቢራ፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ ኢስቲግፋር ማድረግ። አንዳንዴ ለብቻ ቆይቶም በጀመዐ ዱዓና ዚክር ማድረግ የእለቱ ድምቀት ነው።
እለቱ ጥቂት ተሰርቶ ብዙ የሚገኝበት በመሆኑ እንጠቀምበት! ቤተሰቦቻችንን እናንቃ! የምናውቀውን ሁሉ እናነሳሳ!
አላህ ተውፊቅ ይስጠን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
32
ኢላሂ!
የሰጠኸን አሟላልን።
የለገስከንን አትግፈፈን።
የሸፈንክልንን አትግለጥብን።
የምታውቀውን ኃጢኣታችንን በሙሉ ማረን።
36👍5
ኢላሂ!
በየሀገሩ ያሉ ተበዳይ ደካሞችን ሁሉ እርዳ። ጨካኝ ግፈኞች ላይም ትእግስትህን እንዳሳየኸን ቁጣና በቀልህንም አሳየን።
42👍4
የሐጀኞችን ሐጅ አላህ ይቀበላቸው። እኛንም አላህ ተውፊቅ ይስጠን።
እንኳን ለዒዱል‐አድሓ በዓል አደረሳችሁ!
42👍1
ጁሙዐ እና ዒድ
ዒድ በጁሙዓ ቀን ከዋለ ጁሙዓዎች መደበኛውን ቀጠሮ ተከትለው በየመስጂዱ ይሰገዳሉ።
ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ዒዱን በጀመዐ ከሰገደ በኋላ ጁሙዓውንም እንደተለመደው ቢያስከትል እጅግ የተመረጠ ነው። ነገርግን ሁለቱንም ሶላቶች ማስገኘት የማያስችል ምክንያት ካለው ጁሙዓን ማስበለጥ አለበት። ምክንያቱም ጁሙዐ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው። ጁሙዓን ግዴታ የሚያደርጉ መስፈርቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ ዒድ ስለሆነ ተብሎ አይተውም።

• የጁሙዐ ሶላት ብይን
የጁሙዐ ሶላት ግዴታ [ፈርድ] መሆኑ የልሂቃን ስምምነት ያለበት ነጥብ መሆኑ ይታወቃል። በሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር ጁሙዐን መተው ወንጀል ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐

{  يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا إِذا نودِيَ لِلصَّلاةِ مِن يَومِ الجُمُعَةِ فَاسعَوا إِلى ذِكرِ اللَّهِ وَذَرُوا البَيعَ ذلِكُم خَيرٌ لَكُم إِن كُنتُم تَعلَمونَ }[ الجمعة:  ٩ ]

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው።»

ከሰይዲና ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን በጁሙዐ እለት ጁሙዐ ሶላትን የመስገድ ግዴታ አለበት። ህመምተኛ፣ በጉዞ ላይ ያለ፣ ሴት፣ ህፃን እና ባርያ ሲቀር። ከዚህ ውጪ በጨዋታ እና በንግድ የተብቃቃን ሰው አላህም ከርሱ ይብቃቃል። አላህን እጅግ የተብቃቃ [ሀብታም] እና ምስጉን ነው።» በይሀቂይ፣ ዳረቁጥኒይ እና ኢብኑ አቢ ሸይባ ዘግበውታል።

ጁሙዐ በኢስላም ውስጥ ያለው ስፍራ ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አጥብቀን እንድንይዛት አደራ ብለዋል። ጁሙዐን ከመተውም በጥኑ አስጠንቅቀዋል። ጁሙዐን የተወ ሰው አላህ ቀልቡን ያሽግበታል። ከዝንጉዎችም ይሆናል በማለት አስፈራርተዋል።

ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሰዎች ጁሙዐን ከመተው ይታቀቡ። ወይም አላህ ቀልባቸውን ያሽገዋል። ከዝንጉዎችም ይሆናሉ።»

ይህ ሐዲስ ጁሙዐ ግዴታ መሆኑን ከማስረዳቱ በተጨማሪ ያለ ምክንያት ጁሙዐን ማሳለፍ የሚያስከትለውን አደጋም ይበይናል።

• የዒድ ሶላት ብይን
የዒድ ሶላት ጥብቅ ሱና ነው። ግዴታ [ፈርድ] አይደለም። ይህ የማሊኪዮች፣ የሻፊዒዮች እና የአብዝሃኞቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው። ሐነፊዮች እና ኢማም አሕመድ ዘንድ አንዱ ዘገባም ይኸው ነው። ሐነፊዮች ዘንድ በተገኙ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የዒድ ሶላት ዋጂብ ነው ተብሎ ይታመናል።

• ሁለቱ ዒዶች ሲጋጠሙ
የጁሙዐ ቀን ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከሁለቱ ዒዶች አድሓ እና ፊጥር ጋር የሚጋጠምበት ሁኔታ ይፈጠራል። እናም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ እንላለን።…
ጁሙዓ ሶላት ፈርድ ነው። የዒድ ሶላት ደግሞ ሱና ነው። ሱና ፈርድን አያስቀርም። የፈርድን ቦታም አይተካም።
በአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘመን በጁሙዓ ቀን ዒድ ውሎ ያውቃል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ሁለቱንም ሶላቶች ሰገዱ እንጂ አንዱን ለአንዱ ብለው አልተዉትም። ሁለቱም ሶላቶች ላይ ያሉትን ኹጥባዎችም አልተዉም። ዒድንም ሆነ ጁሙዐን አልተዉም።

ይህ በሐዲስ መዛግብት ላይ በግልፅ የታወቀ እና አብዝሃኞቹ ልሂቃን የተጓዙበት መዝሀብ ነው። ከአራቱ መዝሀቦች ሐነፊዮች፣ ማሊኪዮች እና ሻፊዒዮች የሚያምኑበት መንገድ ነው።  ሐንበሊዮች ዘንድም በከፊል የተዘገበ ሃሳብ ነው።

በእርግጥ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዒድና ጁሙዐ በተጋጠሙ ጊዜ ጁሙዐን መተው መፍቀዳቸውን የሚያመለክት ዘገባ አለ። የፈቀዱት ግን በልቅ ሳይሆን "ዓዋሊ" የሚሰኘው የመዲና ዳርቻ ላይ ከነቢያዊው መስጂድ ርቆ ለሰፈረው መንደር ነዋሪዎች ብቻ ነው። ለነርሱ የፈቀዱትም የዒድ ሶላት ከአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጋር ሰግደው ወደ ቤት ከተመለሱ በኋላ በድጋሚ ለጁሙዓ መመለስ እጅግ ከባድ ስለሆነባቸው ነበር። ስለዚህ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ለዓዋሊ ነዋሪዎች በመንደራቸው ባሉበት በጁሙዐ ፈንታ ዙህር እንዲሰግዱ ፈቀዱላቸው። ንግግራቸው እንዲህ ተዘግቧል: ‐

«በዚህ ቀናችሁ ላይ ሁለት ዒዶች ተሰብስበዋል። የፈለገ ሰው ከጁሙዐ ሶላት [የዒድ ሶላት] ያብቃቃዋል። እኛ ግን ጁሙዐ እንሰግዳለን።»  አቡዳዉድ ዘግበውታል።

ይህንን ሐዲስ አብዝሃኞቹ ልሂቃን ‐ሐነፊዮች፣ ማሊኪዮች እና ሻፊዒዮች‐ ለዒድ ሶላት ከመዲና ውጪ ካሉ ስፍራዎች ለመጡ ሰዎች የተነገረ መሆኑን ያምናሉ። እነዚህ በመዲና ዙርያ ከመዲና ውጪ የሚኖሩት ሰዎች ቀድሞውንም ጁሙዓ መስገድ ግዴታ አይሆንባቸውም ነበር። ምክንያቱም የተገነባ ከተማ ውስጥ የማይኖሩ ሰዎች በመሆናቸው ለጁሙዐ ግዳጅ የሚያበቁ መስፈርቶችን መጀመሪያም አላሟሉም ነበር። ስለዚህ ዒድን ከአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጋር ከሰገዱ በኋላ እስለ ጁሙዓ ሶላት ድረስ መጠበቅ በጣም ያስቸግራቸዋል። ወደ ቤት ተመልሰው ጁሙዐ ሲደርስ ይመለሱ ቢባልም በጣም ከባድ ይሆናል። በመሆኑም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጁሙዓን መተው ፈቀዱላቸው።

የማሊኪዮች እውቅ ልሂቅ አል‐ቃዲ ዐብዱል‐ወሃብ አል‐ማሊኪይ "አልመዑና ዐላ መዝሀቢ ዓሊሚል‐መዲና" በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 311 ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐
«ጁሙዐ እና ዒድ ከተጋጠመ አንዱ በሌላው አይወድቅም። ይኸውም የዒድ ሶላት ላይ የተገኘ ሰው ጁሙዓን መተው ይችላል ከሚሉ ሰዎች የተለየ ሃሳብ ነው። አላህ በቁርኣን እንዲህ ብሏል: ‐
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው።»

የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «ጁሙዐ [መስገድ] በሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ ነው።» ብለዋል።
በተጨማሪም የጁሙዐ መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ ጁሙዐን መስገድ ግዴታ ነው።»

የሻፊዒዮቹ እውቅ መጽሐፍ "ሙጝኒል‐ሙሕታጅ" ቅፅ 1፥ ገጽ 539 ላይ እንዲህ ይላል: ‐
«ዒድ በጁሙዐ ቀን ከዋለ [ከከተማ ዳር የከተማው] አዛን የሚሰማቸው ሰዎች ዒድ ሊሰግዱ ወደ [ጁሙዐው] ከተማ ከመጡ ከዚያም ወደ ቤታቸው ተመልሰው በድጋሚ ወደ ጁሙዐ ሶላት ለመምጣት ቢሞክሩ ጁሙዓ ሊያመልጣቸው የሚችልበት ያህል ችግር ከወደቁ ለዚያ ቀን ጁሙዓውን ትተው ወደ ቤት መመለስ ይችላሉ።  ይህ እጅግ የተመረጠው የሻፊዒይ ቃል ነው። ስለዚህ ከደራሲው ልቅ ቃል ይህኛው ጥያቄ ፍልቅታ ይወጣል። አዎን! ወደ ቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት የጁሙዓ ወቅት ቢገባ ‐ለምሳሌ: ‐ ከዒድ ሶላት እንዳሰላመቱ የጁሙዓ ወቅት ቢገባ‐ በግልፅ እንደተመለከተው ሸይኻችን እንዳሉት ጁሙዐን የመተው መብት አይኖራቸውም።»

የሐነፊዮቹ ታዋቂ መጽሐፍ "አል‐ቢናያ ሸርሑል‐ሂዳያ" ቅጽ 3፥ ገጽ 97 ላይ እንዲህ ሰፍሯል: ‐
«እዚህ ላይ ሁለት ዒዶች ተጋጠሙ ማለት ዒድ አል‐ፊጥር ወይም ዒዱል‐አድሓ በጁሙዐ ቀን ዋለ ማለታችን ነው።… አንዱ ሶላት ለሌላው ተብሎ አይቀርም። ጁሙዐ የማይተወው ፈርድ ስለሆነ ነው። ዒድን መተው ደግሞ ጥሜት እና አዲስ ፈጠራ [ቢድዐ] በመሆኑ ነው።… የአላህ መልክተኛ [ﷺ] "እኛ ጁሙዐ እንሰግዳለን።" ማለታቸው ጁሙዐን መተው እንደማይፈቀድ ያስረዳል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በስድ የፈቀዱላቸው እና ዑስማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ምርጫ የሰጧቸው ቤታቸው በመዲና  ዳር ላይ ሩቅ ስለሆነ ነበር። ስለዚህ ከጁሙዐ በፊት ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ጁሙዓን መተዋቸው ችግር አይኖረውም።»
26😢1
ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] "አል‐መጅሙዕ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 4 ገጽ 491 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «የጁሙዐ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ተጋጥሞ የጁሙዐ አዛን ስለሚሰማቸው ጁሙዐን መስገድ ግዴታ የሚሆንባቸው መንደሮች ዒድ ሶላት ላይ ተገኝተው ቢሰገዱ ጁሙዐን መስገድ አይቀርላቸውም። [በጁሙዐው] ከተማ ነዋሪዎች ላይ ይህ ብይን የልሂቃን ልዩነት የለበትም። [ከጁሙዐው] ከተማ ውጪ የሚገኙ መንደሮች ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች ጁሙዐ ይቀርላቸዋል ወይ በሚለው ዙርያ ግን ሁለት ዓይነት የሻፊዒይ ተማሪዎች ሃሳብ አለ። ትክክለኛውና ራሳቸው ኢማም ሻፊዒይ "አል‐ኡም" በተሰኘው መጽሐፋቸው በግልጽ ያስቀመጡት እና ቀዳሚው ሃሳባቸው ለነዚህ ብቻ ጁሙዐ ይቀርላቸዋል የሚለው ሲሆን ሌላኛው ግን የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ አይቀርላቸውም ይላል።»

በኢማም ማሊክ አንዱ ዘገባ እና በሻፊዒዮቹ ተቀባይነት ባለው ሃሳብ መሰረት የዒድ ሶላት ላይ ለመገኘት ጁሙዐ ከማይሰገድባቸው ሩቅ ስፍራዎች ‐ለምሳሌ: ‐ ከከተማ የራቀ ገጠር‐ የመጣ ሰው ዒድ ከሰገደ ጁሙዐ መስገድ ግዴታ አይሆንበትም። ነገርግን በጁሙዐ ፈንታ ዙህር መስገድ አለበት። ይህ የዑስማን ኢብኑ ዐፋንም መንገድ ነው።»

ኢማም አል‐ቀራፊይ አል‐ማሊኪይ "አዝ‐ዘኺራ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 2፥ ገጽ 355 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«ከከተማ ርቀው የሚኖሩ ሰዎችን በተመለከተ "አል‐ኪታብ" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ እንደሰፈረው ጁሙዐን መተው አይችሉም። የለም! ጁሙዐን መተው ይችላሉ የሚል ዘገባም ተገኝቷል።  ይኸውም ዑስማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] አል‐ዐዋሊ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች መፍቀዳቸውን እንደማስረጃ በመጠቀም የተባለ ነው። ምክንያቱም ዒድ ሰግደው ጁሙዐን መጠበቅም ሆነ ከዒድ በኋላ ቤታቸው ደርሰው መመለስ እጅግ ከባድ እንደሚሆንባቸው ታሳቢ በማድረግ ነው።»

በእርግጥ የሐንበሊ መዝሀብ ፉቀሃዎች በብዛት የዒድ ሶላትን የሰገደ ሰው የጁሙዐ ሶላት መስገድ አይጠበቅበትም ባይ ናቸው። ይልቁንስ ባለበት በጁሙዐ ፈንታ ዙህርን መስገድ ይበቃዋል። እንደነርሱ ከሆነ ኢማም ግን የጁሙዐ ሶላትን የማሰገድ ግዴታ አለበት። ''አል‐ሙብዲዕ'' የተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 2፥ ገጽ 180 እንዲህ ይላል: ‐
«ዒድ በጁሙዐ ቀን ካረፈ በዒድ ሶላት ከጁሙዐ መብቃቃት እና በጁሙዐ ምትክ ዙህርን መስገድ ይቻላል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የዒድ ሶላት ከሰገዱ በኋላ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጁሙዐን መስገድ የፈለገ ይስገድ።» አሕመድ ዘይድ ኢብኑ አርቀም ጠቅሰው ዘግበውታል።
በዚህ መሰረት ሰውየው ላይ የመስገድ ግዴታ ሳይሆን ጁሙዐ ሶላት ላይ የመገኘት ግዳጅ ይወድቅለታል። በመሆኑም ሰውየው እንደ መንገደኛ ሳይሆን እንደ ህመምተኛ ይታያል።  [ህመምተኛ የጁሙዐ ግዳጅ ሳይሆን ጁሙዐ የሚሰገድበት ስፍራ የመገኘት ግዳጅ እንደሚነሳለት ይህኛውም ሰው ጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ስፍራ ላይ የመገኘት ግዳጁ ይነሳለታል። በአንፃሩ መንገደኛ [ሙሳፊር] ግን ጁሙዐ ቦታ ላይ የመገኘት ግዳጅ ብቻ ሳይሆን የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ ይወድቅለታል።]
የዒድ ቀን ከጁሙዐ ቀን ጋር በሚጋጠምበት ጊዜ የዒድ ሶላትን በጀመዐ የሰገደ ሰው የዙህርን ሶላት እንደ ''ዑዝረኛ'' [ሸሪዓዊ ምክንያት እንዳለው ሰው] ይሰግዳል። በሌላ በኩል ጥቅል መረጃዎችን በመንተራስ የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ በዒድ ሶላት ምክንያት አይወድቅም የሚል ሌላ ዘገባም ተገኝቷል።»

ነገርግን ሁሉም ሙስሊም በዒባዳ ጉዳይ ጫንቃውን ከተጠያቂነት የሚያድነውን ጥንቃቄ ያለበትን መንገድ መያዝ ይገባዋል።
በእርግጥ ካለፈው የተለየ የዒድ ቀን ከጁሙዐ ቀን ጋር ከገጠመ የዙህር ሶላት ራሱ በዒድ ሶላት ምክንያት ይወድቃል የሚል ሃሳብ መኖሩም ይነገራል። ነገርግን ፊታችንን ዞር አድርገን የምንመለከተው ፍሬ ያለው ሃሳብ አይደለም። ተቀባይነት ካላቸው የአህሉስ‐ሱና መዝሀቦች ውጪ የሆነ ውድቅ መላምት ነው። እርሱን መከተል፣ በርሱ መስራት፣ ፈትዋ መስጠት አይፈቀድም። በቀን እና በሌሊት አምስት ሶላት እንዲሰገድ ከሚያዙት በርካታ መረጃዎች ጋር ይቃረናል። ከአንዳንድ ሶሓቦች ዒድ በጁሙዐ ቀን ሲውል ዙህርን መተው እንደሚፈቀድ በወል ምልከታቸው የሚጠቁሙ ዘገባዎች ተገኝተዋል። ነገርግን የትኛውም ዘገባ የተረጋገጠ ሰነድ የለውም። ትንታኔው በጥሞና ሲቃኝም ለተባለው መሰረት የለሽ ሃሳብ መረጃ መሆን የሚችል ትርጉም የለውም። ሰነዱ ጠንካራ ቢሆን እንኳን የሙስሊሞች ስምምነት በሚደግፋቸው አምስቱ ሶላቶች ግዴታ መሆኑን በሚያመለክቱ መረጃዎች የተነሳ ውድቅ ይሆናል። እንግዳ ከሆነው ይህ ዘገባ ይልቅ አምስቱ ሶላት ግዴታ መሆኑን የሚያመለክቱትን መረጃዎችን እናስቀድማለን። ልሂቃን ዘንድ ተቀባይነት ያለው አካሄድም ይኸው ነው።

ኢማም ኢብኑ ሩሽድ "ቢዳየቱል‐ሙጅተሂድ" የተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 1፥ ገጽ 230 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«የዙህር እና ምትኩን የጁሙዐን ግዳጅ ለዒድ ሶላት ብሎ ማስቀረት ግን እጅግ በጣም ከመሰረት የወጣ ውድቅ ሃሳብ ነው።»

እንደማጠቃለያ ሰዎች በለመዱት መዝሀብ እንዲሰሩና አፈንጋጭ እስካልሆነ ድረስ በተግባቡበት አፈፃፀም ጌታቸውን እንዲያመልኩ መተው እንደሚገባ አምናለሁ። ህዝብ ያልለመደውን መዝሀብ ከኪታብ እየመዘዙ ተርታውን ህዝብ ማወዛገብ እና የንትርክ አጀንዳዎችን ማብዛት ሰውየው አዋቂ ነኝ ብሎ ራሱን ለማሳየት የሚያደርገውን ጥረት እንጂ ሌላን አያመለክትም። በሙስሊሞች መካከል ልዩነትን የሚያሰፉ፣ ጭቅጭቅን የሚያነግሱ፣ ክፍፍልን የሚያጠናክሩ ሃሳቦችን ማራገብ ተገቢ አይደለም። አጠራጣሪ ያልሆኑ ግልፅ መረጃዎችን መከተል፣ ታላላቅ ሊቃውንት የተጓዙበትን ዱካ ተከትሎ መሄድ አማራጭ የማይገኝለት መስመር ነው።
አላህ የበለጠ ያውቃል!
21
Tofik Bahiru pinned «ጁሙዐ እና ዒድ ዒድ በጁሙዓ ቀን ከዋለ ጁሙዓዎች መደበኛውን ቀጠሮ ተከትለው በየመስጂዱ ይሰገዳሉ። ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ዒዱን በጀመዐ ከሰገደ በኋላ ጁሙዓውንም እንደተለመደው ቢያስከትል እጅግ የተመረጠ ነው። ነገርግን ሁለቱንም ሶላቶች ማስገኘት የማያስችል ምክንያት ካለው ጁሙዓን ማስበለጥ አለበት። ምክንያቱም ጁሙዐ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው። ጁሙዓን ግዴታ የሚያደርጉ መስፈርቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ…»
በዒድ አል‐አድሓ ቀን መስራት ያለብንን ❿ ነገሮች እናስታውስ: ‐
❶ የቀኑን ትልቅነት ማሰብ፤ የውሙል‐ሐጂል‐አክበር ነው።
❷ ድምፅን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረግ፤
❸ ገላ መታጠብ፤ አዲስ ወይም ምርጥ ልብሳችንን መልበስ፤ ሽቶ መቀባት፤ ጥርስን መፋቅ፤
❹ ሶላት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ምንም ሳንቀምስ እንደጾመኛ "ኢምሳክ" ማድረግ።
❺ ወደ ዒድ ሶላት ሜዳ ተሰብስበን በህብረት ተክቢራ ደምቀን መሄድ፤
❻ ሶላታችንን መስገድ፤ ኹጥባ ማዳመጥ፤
❼ በዜማ እና በሌላ ጨዋታ ዒዱን ማድመቅ፤
❽ የሄዱበትን መንገድ ቀይሮ መመለስ፤
❾ በዒዱ ቀን ዓቅመ ደካማዎችን መዘየር፤ በደስታ እንዲያሳልፉት ማገዝ፤
❿ በነዚህ የደስታ ሰዓት እንኳን በግፍ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በተለይም ፊሊስጢኖችን በዱዓ ማሰብ።
:
በድል ጨረቃ ታጅበን፣ በኢስላም ልዕልና ደምቀን፣ በሀገራችን ሰላም ተውበን፣ በአንድነት እና በፍቅር ከአመት አመት ያድርሰን!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
45
ተክቢራ በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ
===================
«በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት (ከዒዱል‐አድሓ እለት ቀጥለው ባሉት ሦስት ቀናት) የሚደረገው ተክቢራ የግድ ከፈርድ ሶላት በኋላ መሆን አይጠበቅበትም። [በመርሳት ወይም በሌላ ምክንያት] ቢተወውም በተመቸው ጊዜ ሊያደርገው ይችላል።»

ኢማም ነወዊይ "ሚንሃጅ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት ሶላት ቀዷእ ሲያወጣ፣ መደበኛ ሱና ሶላቶችን ሲጨርስ፣ ማንኛውም ዓይነት ሱና ሲሰግድ አስከትሎ ተክቢራ ማድረግ ይወደዳል የሚለው [የኢማም ሻፊዒይ] ሀሳብ እጅግ የተሻለ (አዝሀር) የሆነው ሃሳብ ነው።»

ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይሰሚይ "ቱሕፋ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዳሰፈሩት: ‐ «ለምሳሌ: ‐ ከዱሓ ሶላት፣ ከዒድ ሶላት እና ከመሳሰሉት ሶላቶች በኋላ፣ ልቅ ከሆኑ ሱና ሶላቶች በኋላ፣ እንደውም ከጀናዛ ሶላት በኋላ ሳይቀር ተክቢራ ይደረጋል። ምክንያቱም ተክቢራ የጊዜው ዓርማ ነው።»

"ሙኽተሶሩ ባፈድል" በበኩሏ እንዲህ ትላለች: ‐
«ከሐጀኛ ውጪ ያለ ሰው ሁሉ ከፈርድም ሆነ ከሱና ሶላት በኋላ ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱ ትኩስም ይሁን ቀዷእ ወይም የጀናዛ ሶላት ምንም ልዩነት የለም። ተክቢራውን ከረሳ ሲያስታውስ ያድርገው።»

የዒድ ተክቢራ በህብረት ብቻ የሚደረግ የሚመስላቸውም ሰዎች ይኖራሉ። ነገርግን ስህተት ነው። ተክቢራው በግልም በጀመዓም እንደሚደረግ ይታወስ።
:
ዒድ ይደጋግመን። በጤናና በሰላም አመት ከአመት ያድርሰን ያድርሳችሁ።
ዒድ ሙባረክ!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
32👍6
ኡድሒያ ማረድ አንዳንድ ዐሊሞች ዘንድ ዋጂብ ቢሆንም አብዝሃኞቹ ዘንድ ጥብቅ ሱና ነው። ጎረቤትን በከብት ፈርስ፣ በተጣሉ የከብት ቆሻሻዎች ማስቸገር እና በማንኛውም መልኩ አዛ ማድረግ ደግሞ ሐራም ነው።
እባካችሁ ወዳጆች የእርዳችን ፋና የሆኑ የደም፣ የፈርስ ተረፈ ቆሻሻ እያስወገድን የዲናችንን ግዴታ እንወጣ። መልካም ስራችንን አናበላሽ!
👍459
ዛሬ አያም ተሽሪቅ ሦስተኛ ቀን ነው። እርዳችንን ያልፈፀምን እስከ መጪው መግሪብ ድረስ እድሉ አለን። ኡድሒያ አስቤዛ አይደለም። ዒባዳ ነው። ስጋውን ለመብላት ሳይሆን መስዋዒት በማድረግ ወደ አላህ ለመቅረብ እንነይት።
:
«ሱና ዐለል ዐይን» — የነፍስ ወከፍ ሱና ነው የሚሉ ዐሊሞች አሉ። በአንድ ቤት ውስጥ ከአንድ በላይ ዓቅም ያላቸው ሰዎች ካሉ እያንዳንዳቸው በተናጠል ማረድ አለባቸው ማለታቸው ነው። ስለዚህ ድሆችን ማገዝ ያስችለን ዘንድ በርከት አድርገን እንረድ። «ኡድሒያ ደሙ መሬት ከመውደቁ በፊት አላህ ዘንድ ነው የሚያርፈው።»…
:
በዒድ መደሰት የዲን ዓርማ ነው። ተደሰቱ! በመንዙማው ተፅናኑ። በነሺዳው ድምፅ ተዛናኑ። ልጆቻችሁን አጫውቱ። ቤታችሁን በልዩ ድባብ አድምቁት።…
:
ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይቀጥላል። እስከ ነገ ዐስር ድረስ። ከነገው ዐስር በኋላም ተክቢራው ተደርጎ ይጠናቀቃል።…
ዒዱኩም ሙባረክ!
64👍10
«ጀግንነት እና ተገንነት ምርጥ ጠባይ ነው። ጀግንነት ማለት የቁጣ አቅምን ለአዕምሮ ፍርድ ተገዥ እንዲሆን ማድረግ ነው። ተገንነት ማለት ለመልካም ነገር ስኬት ሲባል ነፍስን ያለ ፍርሃት ሞት ወዳለበት ስፍራ መላክ ነው።

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በጀግንነትና በተገንነት ይታወቁ ነበር። እጅግ የከበዱ አደገኛ ሁኔታዎች ላይ ተገኝተው ተፈትነዋል። በርካታ ጀግኖችና ጀብደኞች በተደጋጋሚ ከዙርያቸው ሸሽተዋል። እርሳቸው ግን ቦታቸው ላይ ፀንተው ተጋፍጠዋል። ሳያፈገፍጉ ፊትለፊት ፍልሚያቸውን ቀጥለዋል። አልተርበተበቱም።

ማንኛውም ጀግና ጥቂትም ቢሆን የሽሽት አጋጣሚም ይኖረዋል። ያፈገፈገበት ቀንም አያጣውም። ይህ ግን እርሳቸውን አይጨምርም!»

📚 አሽ‐ሺፋእ ቢተዕሪፊ ሑቁቂል‐ሙስጦፋ፥ ኢማም ቃዲ ዒያድ
43
ከዚክር ማህደር
ኑሮ የተወሳሰበ ሰው ምን ይበል?
ከሰይዲና ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እንደተዘገበው የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አንዳችሁ የኑሮው ጉዳይ ከተወሳሰበበት ከቤቱ ሲወጣ እንዲህ ከማለት ምን ያግደዋል?!: ‐
«በአላህ ስም ነፍሴን፣ ገንዘቤን እና ዲኔን [በማስተካከል ላይ እታገዛለሁ]።
አላህ ሆይ! በፍርድህ አስደስተኝ። ያዘገየኸውን ማስቸኮል፣ ያስቀደምከውን ማዘግየት እስከማልወድ ድረስ በተወሰነልኝ ነገር ላይ በረከት አድርግልኝ።»

ኢብኑ ሱኒይ ዘግበውታል። አዝካር ላይ ኢማም ነወዊይ ጠቅሰውታል።
54👍9
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ሰውየው በቂያማ ቀን በመጀመሪያ [አላህ ዘንድ] የሚተሳሰበው ነገር ሶላቱን ነው!
እርሷ ከተስተካከለች በእርግጥ [ትልሙ] ተሳካለት [ፍላጎቱን] አገኘ!
እርሷ ከተበላሸች ደግሞ በእርግጥ ከሰረ ጠፋ!»
ቲርሚዚይ ዘግበውታል።
:
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
49😢6
ከተፈቃሪያችን [ﷺ] ጋር የተሰጠን ትልቁ የአላህ ፀጋ ከርሳቸው ጋር የተፈቀደልን ቅርበት ነው። ሶለዋት እና ሰላምታ ስናቀርብላቸው ይደርሳቸዋል። እርሳቸው ናፍቀናቸው አንብተዋል። እኛ የርሳቸው እጣ እርሳቸውም የኛ እድል እንደሆኑ ነግረውናል። የህይወት ውሏቸው፣ የአካል ገፅታቸው እና የቤተሰብ ግንኙነታቸው ሳይቀር ተሰንዶ ተዘግቦልናል። ከህይወታቸው ገፅታ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ተዳፍኖ የቀረ የለም!

ስለዚህ ፍቅር ያለው ወዳጃቸው ከእቅፋቸው ሳይወጣ፣ ተዝካራቸው ከህይወት ማእዱ ሳይርቅ ይመላለስበታል። እነሆ ዛሬ ዝክረ ሂጅራቸው ድምቀታችን ይሆን ዘንድ አላህ አድርሶናል!
አልሐምዱሊላህ!

እናም አደራ የምላችሁ!…
ስለ ሂጅራቸው ለልጆቻቸን እንንገር። እለቱን ከታሪክ ዐውዱ ጋር አቆራኝተን ደማቅ ወጋችን እናድርገው። የመድረሳ ባለቤቶች፣ የመስጂድ አስተዳዳሪዎች፣ ዳዒዎች፣ የረሱልን ፍቅር በትውልድ ልብ ውስጥ መዝራት የሚሻ ሁሉ ዓመቱን ሁሉ ከህይወታቸው ክስተት እየቀዳ ይጠጣ። ለሌላውም ያጋራ። ከህይወት ቅኝታቸው የሚገኘውን አስተምህሮና ለዛ ይቋደስ!
እንኳን ለ1447 ኛው ዓመተ ሂጅራ አደረሳችሁ! የከርሞ ሰው ይበለን!
62👍8😍2
የልጆቻችን ክረምት እንዴት እንዲያልፍ ወስነናል?
ከቁርኣን ጋር ወይስ ክረምትንም ለቁርኣን ሰስተናል?!…
27🤔2
2025/10/31 12:54:21
Back to Top
HTML Embed Code: