Telegram Web Link
ኢላሂ!
ስወድቅ እንዴት እንደምነሳ አሳውቀኝ።
ስነሳ ደግሞ ዝቅ ብዬ የወደቁትን እንዳነሳ አግዘኝ።
157👍22
«ከሙስሊም ላይ አንድን ጭንቀት ያስወገደ ሰው አላህ ከቂያማ ጭንቀቶች አንድን ጭንቀት ይገላግለዋል።»
የአላህ መልክተኛ [ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም]፥ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ጭንቅን ማስወገድ በገንዘብ ሊሆን ይችላል። በዝናና በክብሩ በመጠቀምም ሊሆን ይችላል፤ ወይም በአካላዊ እገዛም ሊሆን ይችላል። በሃሳብ፣ በምክር እና መላ በመስጠት ማገዝም ጭንቅን የማስወገጃ አካል መሆኑ ግልፅ ነው።»
ሸርሑ ሶሒሕ ሙስሊም፥ ቅጽ 16፥ ገጽ 135
:
መተጋገዝ የግድ የሀብታሞች ብቻ አይደለም። ባለን ነገር መተጋገዝ መልካም ነው!
አላህ ያግራልን!
82
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«አንዲት አንቀጽም ብትሆን ከኔ የሰማችሁትን ለሌላ አድርሱ!»
ቡኻሪይ ዘግበውታል።
57
ዝናብ ሲጥል የሚደረግ ዱዓ
==================
ዝናብ የአላህ እዝነትና ትሩፋት ምልክት ነው። ዝናብ የሚጥልበት ሰዓት ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ጊዜያት አንዱ ነው።
ተወዳጃችን [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሁለት ዱዓዎች አይመክኑም። በአዛን ጊዜ የሚደረገው ዱዓ እና ዝናብ ሲዘንብ የሚደረገው ዱዓ።» ሓኪም ዘግበውታል።
:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዝናብ ሲዘንብ የሚያዘወትሩት ዱዓ አለ: ‐
"اللهم صيبا نافعا"
ንባብ: ‐«አል‐ላሁም‐መ ሶይ‐ዪበን ናፊዓን»
ትርጉም: ‐ «አላህ ሆይ ጠቃሚ ዝናብ አድርገው።»
:
ክረምታችን ረሕመት የሚወርድበት ዘመን ይሁንልን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
49👍6
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«የዶሮ ጩኸት ስትሰሙ አላህን ከትሩፋቱ ለምኑት፤ እርሷ መላኢካ አይታ ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ኢማም ቃዲ ዒያድ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ሷሊሖች [ደጋግ ሰዎች] በተገኙበት ዱዓ ማድረግ እና በነርሱ ሰበብ በረካን መከጀል የተወደደ መሆኑ በሐዲሱ ተጠቁሟል።»
ይህንን ኢማም ነወዊይ [ረሒመሁላህ] "ሸርሑ ሙስሊም" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰውታል።
50👍2
«በማይመለከትህ ነገር ውስጥ ገባህ፤ የሚመለከትህን ነገር ከመመልከት አገደህ። የሚመለከትህ ነገር ላይ ብትጠመድ ኖሮ የማይመለከትህን ነገር ትተው ነበር።»
ኢማም ፉደይል ኢብኑ ዒያድ [ቀደሰላሁ ሲረሁ]
83😍7👍5
ሰይዲና አቡ በርዛ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ በማለት የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ጠየቁ:‐
«የአላህ ነቢይ ሆይ! የምጠቀምበትን አንድ ነገር አሳውቁኝ!»
የአላህ መልክተኛም [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐
«ሰዎችን የሚያስቸግሩ ነገሮችን ከመንገድ ላይ አስወግድ!»
:
በተለይ በክረምት ወራት በየመንደራችን ሰውን በጎርፍ የሚያሰቃዩ መንገዶችን አስቧቸው። የአንዳንዶቹ ሰበብ በጥቂት ስራ ቱቦዎቹን በመነካካት ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ናቸው።

"መልካም ነገሮች ሁሉ ምጽዋት ናቸው።" በሚለው የዲናችን ትምህርት መሠረት በቸላተኝነት የምናልፋቸው ምጽዋቶችን ለማስታወስ ያህል ነው።
አላህ ያበርታን!
76👍5
የአላህ ወልዮች የአላህን ፍጥረት ከአላህ ጋር የሚያስተሳስሩ ሰንሰለቶች ናቸው።
ከአቡየዚድ አል‐ቡስጧሚ [ቁዲሰ ሲሩሁ] እንደተዘገበው:‐
«መጅሊሳቸው ላይ ሰዎች ሲንጋጉ ተመለከቱ። መልካም የአላህ ባርያ መሆናቸውን አምነው በውዴታ ስሜት ወደርሳቸው ይጎርፉ ነበር።…

…እጃቸውን ለዱዓ አነሱ። አላህን እንዲህ አናገሩት:‐

«አላህ ሆይ! እነዚህ ሰዎች አንተን ፈልገው እኔ ዘንድ እንደሚመጡ ታውቃለህ። የሚወዱትም አንተን ነው። ነገርግን እኔን በደጃፍህ ጉበን ላይ ተንጠልጥዬ አግኝተውኝ ነው የከበቡኝ። አንተ እንድትቀበላቸው ይከጅላሉ። ወዳንተ መግባትም ይሻሉ።»
81👍5
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«አንድ ሰው ሌላ ሰውን ስለሰደበ በአጸፋው ሰውየው ደግሞ ሙሉ ጎሳን መሳደቡ ከቅጥፈት ሁሉ የከበደ ቅጥፈት ነው።»
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
:
🔴 የግለሰብን ጥፋት ስህተት በሌሎች ንጹሐን ላይ ማላከክ ራሱን የቻለ የኃጢኣት ዓይነት ነው! በዚህ ዘመን ደግሞ እየተንሰራፋ ነውና ተጠንቅቀን እናስጠንቅቅ!
63
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ልክ ልብስ እንደሚያረጀው ኢማንም በአንዳችሁ ሆድ ውስጥ ያረጃል። አላህ ኢማናችሁን እንዲያድስላችሁ ለምኑት።»
ጠበራኒይ እና ሓኪም ዘግበውታል።
62👍6
«አንቺ አላህ ዘንድ ተወዳጇ ሀገር ነሽ። እኔም ዘንድ ተወዳጅ ሀገር ነሽ። ሙሽሪክ [ከሀዲያን] ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ ትቼሽ አልሄድም ነበር።»
:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ለቀዋት የተሰደዱ ቀን መካን በእነዚህ የፍቅር ቃላት ባያባብሏት ኖሮ በቁጭት ስሜት ተወጥራ ትፈነዳ ይሆን ብዬ አስባለሁ።
ከተወዳጁ [ﷺ] ጋር አደብ ያጡ ነዋሪዎቿን አርገፍግፋ ታሽቀነጥር እንደነበር ይሰማኛል።
:
የርሳቸው ነገር ግን ይገርማል!
ሰው የተገፋበትን፣ የተሰቃየበትን፣ መከራ የበላበትን ምድር ሳይቀር እንዴት ያፈቅራል!? ሊወድ የተፈጠረ ስለሆነ እንጂ!…
100😍2
የሶለዋት ዊርድ አለህ?
Anonymous Poll
50%
አዎን፤ አልሐምዱሊላህ።
50%
ዛሬ እጀምራለሁ
11👍3😍1
Audio
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር
📗 ክፍል አንድ:‐ የኪታቡ ኹጥባ 2ኛ ክፍል [መግቢያ]
📆 ነሐሴ 06/ 2017 ዓ. ል.
4
እየፈራሁም ቢሆን ከነዐይቤ ይጠቅማችኋል ብዬ የአዝካር ደርሳችንን አስቀጥዬዋለሁ። እየተከታተላችሁ!
36
Forwarded from Tofik Bahiru
የረጋ ወተት

ማንኛውም መስአላ ላይ አስተያየት ከመሰጠቱ በፊት አራት ሂደቶች መታለፍ አለበት:‐

ተክዪፉል መስአላ/ጥያቄውን መግለፅ

ጥያቄን ከመመለስ በፊት የጥያቄውን ሁለገብ የሚያሳይ ፍኖተ‐ካርታ ማውጣት ያስፈልጋል። ጥያቄው ከየት መጣ? ምን ዓይነት ዐውድ አለው? በየትኛው የኢስላም ክፍል ውስጥ የሚካተት ነው? የጥያቄው ዳራና ድንበሩ ምንድን ነው?… ወዘተ

ከዚህ በኋላ ምርምር፣ ጥናት፣ ክርክር ይደረጋል። የጥያቄው ካርታ ሳይወጣ የሚደረግ ጥናት፣ ውይይትና ክርክር ፋይዳ ቢስ ነው፤ ወይም ስህተት ላይ ይጥላል።

ተእሲሉል መስአላ/ከትክክለኛ የመረጃ ምንጮች ጋር ማጣመር

ይህ ሁለተኛው ሂደት ነው። በጥያቄው ላይ ወይም በተመሳሳይ ወይም በተቀራራቢ ርዕሶች ላይ የተጠቀሱ ቅዱሳን ጥቅሶችን መሰብሰብ ቀዳሚ ስራ ነው። ሁለገብ የመረጃ ሜኑ ማቅረብ ተገቢ ነው። ከዚያም መረጃዎቹ እንደየደረጃቸው ይዘረዘራሉ። ደካማ ነው ተብሎ ሳይጠቀስ የሚቀር መረጃ አይኖርም። ሁሉም ይጠቀሳል።

🈁 ተሕሊሉል መስኣላ/ትንታኔ መስጠት

የቀረቡት መረጃዎችን በማጤን የመስኣላውን ዐውድ የጠበቀ፣ ዳር ድንበሩን ያልዘነጋ ትንታኔ መስጠት። በዚህ እርከን ላይ አንድ ሺህ ዓይነት እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ምላሾች ሳይቀሩ ይቀርባሉ። ይደረደራሉ።

🔶 ኢስቲኽራጁ ነታኢጅ/ውጤት ወይም አቋምን ማውጣት

በዚህ እርከን መረጃዎች ከጥያቄዎቹ ዐውድ ጋር በተነፃፃሪ ይተቻሉ። በምርመራው መሰረት የወደቁና ያለፉ ሃሳቦች ወይም ምላሾች ተለይተው ይቀርባሉ። አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለሐቅ የቀረቡ ሃሳቦች በአጥኚው ግምገማ መሠረት በቅደም ተከተላቸው እንደ ጥንካሬያቸው ይፋ ይሆናሉ።
:
🔴 ሐቅን መመርመርና እውነትን ለማግኘት ይህ ሁሉ ድካም አለው። ካርታ ሳታወጡ ምላሹን ለመመለስ አትሞክሩ ለማለት ነው። ሂደቶቹን ዘሎ ብይን መስጠት ያለ ጊዜው መውለድ ነው! ያለ ጊዜ መውለድ መጨንገፍ ነው! አደጋ ነው! መክሸፍ ነው!…
26👍9
እለተ ረቡዕ በዙህር እና በዐስር መካከል ዱዓ ተቀባይነት አለው። በዚያ ላይ በዝናብ የሚደረግ ዱዓም ኢስቲጃባ ይከጀላል። በዱዓችሁ አስቡን!
61
ስለትዳር ስናስብ ለብዙ ነገሮች ትኩረት እንሰጣለን፣ ሰርጉ፣ ጥሎሹ፣ ኒካሁ፣ የቤት እቃው፣ መጋረጃው ምንጣፉ፣ ማንኪያው ሳይቀር ያሳስቡናል 😊 ያው እንደባለቤቱ የሚያስጨንቀውና የሚያሳስበው ነገር ቢለያይም!

በሰርግ ሰሞን ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ዋነኞቹን ኒካህ፣ ወሊማና የጫጉላ ምሽትን ሸሪዓዊ እይታ  በዚህ ወር ውይይታችን ከኡስታዝ ቶፊቅ ባህሩ ጋር የምናደርግ ይሆናል።

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ  ነሀሴ 10 እና 11 ከምሽቱ 3:30 ጀምረን እንሰየማለን 😊

እስከዛ ኮመንት ላይ በሚገኘው የቴሌግራም ሊንካችን አባል እየሆኑ ይጠብቁን 😊
https://www.tg-me.com/+X0y-TUg1v11hZDI0
40👍12
2025/10/23 21:39:51
Back to Top
HTML Embed Code: