Forwarded from የረሕማን ስጦታ
የተከበረው እጃቸው በምንም ነገር ላይ ሲያርፍ የዚያ ነገር ምንነት ይቀየራል። በሽተኛ ላይ ካረፈ ይድናል። ተክል ላይ ካረፈ ይፀድቃል፤ ይፋፋል፤ ያፈራል። ምግብ ላይ ካረፈ ይባረካል፤ ይበዛል። ውሃ ላይ ካረፈ ይንቧቧል፤ ይጎርፋል። ቀልብ ላይ ካረፈ ይረጋል፤ ይሰክናል። ጭንቅላት ላይ ካረፈ ይፀናል፤ ይነቃል። እጅ ላይ ካረፈ የትም ባልተገኘ ሽታ ይታወዳል። ለበርካታ ቀናት በማይጠፋ መዓዛ ይታጠናል።
የነቢያችን [ﷺ] እጅ እንዲህ ነበር!
#ሶሉ ዐለይሂ
የነቢያችን [ﷺ] እጅ እንዲህ ነበር!
#ሶሉ ዐለይሂ
❤106😍3👍2
Audio
ጁሙዐ ቀን ከዐስር በኋላ
================
ኢማም አድ‐ዳረቁጥኒ፣ አልሐፊዝ አስ‐ሰኻዊ፣ ኢማም አል‐ገዛሊ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በጁሙዐ ቀን ሰማንያ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያደረገ ሰው የሰማንያ ዓመት ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል።»
ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዴት ብለን ሶለዋት እናድርግቦት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «እንደዚህ በል አሉ: ‐
" اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ"
«አላሁም‐መ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ዐብዲከ ወነቢይ‐ዪከ ወረሱሊከ አን‐ነቢይ‐ዪል ኡም‐ሚይ‐ይ»
ይህንን አንድ ብለህ ቁጠር።»
:
ሰማንያ ስትሞላ በአላህ መልክተኛ ላይ ሰላምታን በማድረግ ጨርስ። «ሶለ‐ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም» በል።»
:
ያያያዝኩላችሁ የድምፅ ፋይል በዘመናችን ከነበሩ ታላላቅ የተሰዉፍ ሰዎች መካከል የነበሩት ሸይኽ ረጀብ ዲብ ከሙሪዶቻቸው ጋር ሶለዋት ሲያደርጉ የተቀረፀ ነው። ትንፋሻቸው ወኔያችንን ከቀሰቀሰ በማለት የተለጠፈ ነው!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1198

❤26👍8
አንድ ሰው እንዲህ አለ: ‐
«ወላሂ! አላህ እገሌን አይምረውም።»
አላህ ደግሞ በምካሹ እንዲህ አለ: ‐
«ማነው እኔ እገሌን እንደማልምር በእኔ እየማለ የሚናገረው?!…
በእርግጥ እኔ እገሌን ምሬዋለሁ። ያንተን ስራ ግን አበላሽቻለሁ!»
📜ኢማም ሙስሊም ጁንዱብ ኢብኑ ጁናዳን ዋቢ አድርገው ዘግበውታል።

❤28😢10👍4
🔶 ለቀልብ ባለቤቶች!
ጀላሉዲን አር‐ሩሚ [ቁዲሰ ሲሩሁ] በመንገድ ላይ ሲሄዱ መንገዳቸውን የሚያቋርጥ የተኛ ውሻ ገጠማቸው። ውሻውን ለመቀስቀስ ተሳቀው ተቀምጠው መንቃቱን መጠባበቅ ጀመሩ። መቸገራቸውን ያየ ልቅናቸውንና ሐያኣቸውን የሚያውቅ ሰው ግን ውሻውን ቀሰቅሶ ከመንገድ አስነሳው።
መውላና: ‐ «ለምን ቀሰቀስከው?! አዛ አደረግከው!» በማለት ተቆጡ።
በሌላ ጊዜ በመንገድ ላይ ሳሉ ሁለት ሰዎች ሲጣሉ፣ ሲዘላለፉ ደረሱ። አንዱ በሌላው ላይ ሲዝት እንዲህ አለ: ‐
«አንድ ጊዜ ብትሰድበኝ ዐስር አድርጌ እመልስልሃለሁ!»
ሩሚም: ‐ «በእናንተ ፈንታ እኔ አለሁላችሁ፤ ዝለፉኝ። ሺህ ብትሰድቡኝ አንድ አልመልስላችሁም።» በማለት እንዲታረቁ ገሰጿቸው። ሰዎቹም በድንጋጤ እግራቸው ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቅ እርቅ አደረጉ።»
:
🌟 እኛ እርስ በእርሳችን አዛ መደራረግን ሱስ አድርገን እንደያዝነው ትልልቆቹ ዝቅተኛ ተብሎ የተገመተች ነፍስን መንከባከብን እንኳን ወደ አላህ መድረሻ መንገድ አድርገው ይዘውታል!…
አላህ ያግራልን!

❤84👍20
«የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ሥራውን የሚሰራ ህላዌ [ዛት] ነው። ህይወት ሲያበቃ ደግሞ ስራው እርሱን ዘልዐለማዊ የሚያደርግ ህላዌ ይሆናል። መልካም ከሰራ መልካም ሆኖ ለዝንተዐለም ይዘልቃል። ክፉ ከሰራም በክፋቱ ዝንተዐለም ይዘወትራል። ሞት ማለት ሩሕ ከሥራዋ የምትወለድበት ክስተት ይመስላል። ሩሕ ሁለቴ ትወለዳለች። አንዴ ወዲህ ስትመጣ፤ ሌላም ወደመጣችበት ስትሄድ።»
ሙስጠፋ ሳዲቅ አር‐ራፊዒይ፥ ወሕዩል‐ቀለም
ሙስጠፋ ሳዲቅ አር‐ራፊዒይ፥ ወሕዩል‐ቀለም
❤43😢14👍12😍1
Forwarded from Tofik Bahiru
ታላቁ ታቢዒይ አቡ ዐብዲር‐ረሕማን አስ‐ሱለሚይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከጁሙዐ በፊት አራት ከበስተኋላዋ አራት እንድንሰግድ ያዙን ነበር።»
ዐብዱረዛቅ "አል‐ሙሶነፍ" በተሰኘው ኪታባቸው ዘግበውታል። አል‐ሀይተሚይ "ዘጋቢዎቹ ታማኞች ናቸው።" ብለዋል።…
ይህ የሱፍያን ሰውሪይ፣ የዐብዱላህ ኢብኑል‐ሙባረክ እና የሌሎቹም የሰለፍ ልሂቃን መዝሀብ ነው። ጁሙዐ እንደ ዙህር ከበስተፊቷ አራት ከበስተኋላዋ አራት ረከዐ ሱና አላት። «ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ዒባዳዎች ሁሉ ምርጧ ናት!»
ባረከላሁ ፊኩም!

❤41👍16😢2
ደርሳችን በጉዞ እና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ከረመዳን በኋላ ሳይቀጥል በመቆየቱ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በውስጥም ሆነ በአስተያየት መስጫ በኩል ውትወታ ስታደርጉ የነበራችሁ ወዳጆቼንም አመሰግናለሁ። እነሆ ዛሬ ካቆምንበት ኪታቡል‐ሐጅ ቀጥለናል። ወቅቱ የሐጅ እንደመሆኑም መልካም አጋጣሚ ነውና እየተከታተላችሁ። ሐጅ የተነሳችሁ ወዳጆች ካላችሁም ደርሱን እውቀት ለማግኘት እንደ አማራጭ ብትይዙትና ብታሰራጩት ደስተኛ መሆኔን እገልፃለሁ። አላህ በኸይር ስራ ተጠቃሚ ያድርገን!
❤30👍9
Forwarded from Tofik Bahiru
የ͟ተ͟ከ͟በ͟ሩ͟ ወ͟ራ͟ት͟
(አ͟ሽ͟ሁ͟ሩ͟ል͟‐ሑ͟ሩ͟ም͟)
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
"إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ"
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
:
የተከበሩ ወራት አራት ናቸው:
⚀ ዙል‐ቀዕዳ (ቂዕዳ አትበሉ😊)
⚁ ዙል‐ሒጃ
⚂ ሙሐር‐ረም
⚃ ረጀብ
ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው። አንዱ ብቸኛ ነው። እርሱም ረጀብ ነው። በሂጅራ አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው።
:
ኢማም አል‐ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
[ከላይ የጠቀስነው አያ ውስጥ] ኃጢኣት በመፈፀም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ማለት ነው። ምክንያቱም የመልካም ሥራዎች ምንዳ እንደሚነባበረው ሁሉ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ኃጢኣትም ቅጣቱ ይነባበራል።
ቀታዳ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በተከበሩት ወራት የሚፈፀም በደል በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው እጅግ የከፋ ኃጢኣት ነው።»
:
ለነፍሳችን መዳን የምንመርጠው ጊዜ ላይ አለንና እናስብበት!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

👍10❤5