Forwarded from የረሕማን ስጦታ
የተወዳጁን ነቢይ [ﷺ] ታላቅነት ከሚያስረዱ የአላህ ስጦታዎች መካከል መሬት ውስጥ የርሳቸው ዝክር ያልተወሳበት ምንም ዘመን አለመኖሩ ተጠቃሽ ነው። ምድር ከተፈጠረች ጀምሮ እስከ ፍፃሜዋ ድረስ ያልተቋረጠ መታወስ ተከትቦላቸዋል። ምክንያቱም ከዘመን በቀደመው የሩሕ ዓለም ውስጥ ነቢያት ከሰይዲና አደም [ﷺ] ጀምሮ እስከ ቂያማ ያሉትን ሰብስቦ አላህ [ሱብሐነሁ] ቃልኪዳን አስገብቷቸዋል።
ነቢይ ሙሐመድ [ﷺ] በእነርሱ ዘመን ከመጡ ሊያምኑባቸው፣ ሊያግዟቸው እና ሊከተሏቸው፣ ለህዝባቸውም የርሳቸውን መምጣት እንዲያበስሩ አደራ ተጥሎባቸዋል። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
«አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡»
:
አንጀት አረስርሱ ኢማም አል‐ቡሶይሪይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የሀምዚያ መድብላቸው ላይ አሳምረው ገልፀውታል: ‐
ما مضت فترةٌ من الرُّسْلِ إِلّا
بَشَّرَت قومَها بك الأنبياءُ
تتباهَى بك العصورُ وتَسمو
بِك علياءٌ بعدها علياءُ
«ከቶ አላለፈም የነቢያት ዘመን
አንቱ ሳያወሳ ሳያውጅ ጀብድሁን
መልክተኛው ነግሯል አለቅነትሁን
የሁሉ መላቂያው አንቱ መሆንሁን።
የቀን መፎከሪያ ከፍ ብሎ የሚታይ
ደምቆ የሚያፈካው አልቆ እንደ ሰማይ
የዘመናት ዝክር የዝንቱ ዳንኪራ
ተሰቅሎ የሚኖር የማይወርድ ባንዲራ
አንቱ መሆንሁን ይኖራል ሲያወራ
ሁሉም በየተራ!…

❤52👍8😍1
የሙቀዲመቱ ባፈድል ኪታቡል‐ሐጅ እዚህ ድረስ ነበር። አላህ ካለ በሐጅ እና በዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት ዙርያ ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማከታተል እሞክራለሁ። እየተከታተላችሁ፣ ለሌሎችም እያጋራችሁ ቆዩኝ። ቻናሉ አሁን ካለው ተከታይ በላይ በሰፊው እንዲሰራጭና እንዲያድግ እንድታግዙኝም እጠይቃለሁ!
👍16❤9
ከረጅም ገፍላችን ስንመለስ ዐስሩ የምድር ልዩ እና ድንቅ ቀናት (ዐሽሩ ዚልሒጃ) እየቀረቡ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት በተለያየ መልኩ ስለነርሱ አንስተን እንተዋወሳለን። እስከዚያው ይህንን ቻናል ለዘመድ ለጓደኛችሁ በማጋራት ያስተዋውቁልን። ተከታዩን ሊንክን በመጫን ቤተሰብ መሆን ይቻላል።
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
❤51👍4
በእጃችን የሚገኙ የሙቀዲመቱ ባፈድል ህትመቶች እዚህ ድረስ ናቸው። ስለዚህ በ48ኛው ክፍል ኪታባችንን አኽትመናል። አልሀምዱሊላህ!
❤9
المقدمة الحضرمية.pdf
2.9 MB
እኛ በእጃችን በስፋት በሚገኙት ህትመቶች መሰረት ኪታባችንን ብናኸትምም ደራሲው ሸይኽ ዐብዱላህ ባፈድል አል‐ሐድረሚይ [ረሒመሁላህ] ግን ከዚህ በኋላም ቀጥለውበታል። ባያያዝኩላችሁ ፒዲኤፍ ላይ እንደምታዩት ኪታቡል‐ቡዩዕን እስከ ባቡል‐ሂባ ድረስ አስሂደውታል። የማይቀረው ሞት መጥቶ ጠፊውን ዓለም ተሰናበቱ እንጂ!
ከርሳቸው በኋላም አል‐ሚንሃጁል ቀዊም ብለው ለዚህ ኪታብ ሸርሕ የሰሩት ታላቁ የሻፊዒያ ልሂቅ ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይተሚይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] በዋናው ደራሲ አጣጣልና እቅድ መሰረት እርሳቸው ካቆሙበት የቀጠሉ ቢሆንም እስከ ፈራኢድ ድረስ ከፃፉ በኋላ የሰማዩን ጥሪ እሺ ብለው ነጎዱ። እርሳቸውንም አላህ ይማራቸው። እኛንም በደጋጎቹ ዒልም እና በረካ ይጥቀመን!
አሚን!
ለሁለቱም ፋቲሓ እንቅራላቸው!

👍24❤4