Forwarded from የረሕማን ስጦታ
የላቀው ውልደታቸው በመላእክት፣ በጂንም ሆነ በሰዎች ዓለም ውስጥ ምልክቶች ተደርጎለት ነበር። ዘመን፣ ስፍራ፣ የዩኒቨርሱ ሁለንተና በከፍተኛ መሰናዶ ውልደታቸውን ይጠባበቅ ነበር። ሰማይ እና ምድር በውስጣቸው ካቀፉት ፍጥረት ጋር መገለጣቸውን በጉጉት ይጠብቁ ነበር።
በእርግጥም የዓለሙን አስኳል፣ የፍጥረቱን ዐይን ለመጠበቅ ይህ ሁሉ መሰናዶ መደረጉ ተገቢ ነበር። ውልደታቸው ዘመናትም ሆኑ ስፍራዎች አስተናግደውት የማያውቁት ልዩ ክስተት ነበር!
እናቴም አባቴም ቤዛ ይሰዉሎትና!
በእርግጥም የዓለሙን አስኳል፣ የፍጥረቱን ዐይን ለመጠበቅ ይህ ሁሉ መሰናዶ መደረጉ ተገቢ ነበር። ውልደታቸው ዘመናትም ሆኑ ስፍራዎች አስተናግደውት የማያውቁት ልዩ ክስተት ነበር!
እናቴም አባቴም ቤዛ ይሰዉሎትና!
❤44🤔2
Forwarded from Tofik Bahiru
ኑ ረሱላችንን እንወቅ-1.pdf
1019.2 KB
ምናልባት ከዚህ ቀደም ካላያችኋት ይችን አጭር መጽሐፍ አንብቡልኝ። ስለረሱል [ﷺ] ሲራ ማወቅ የሚገቡንን መሰረታዊ የህይወት ክፍሎቻቸውን እጅግ ባጠረ መልኩ የምታስቃኝ መጽሐፍ ናት። በአንድ ማኪያቶ የምታልቅ "አጤሪራ" ናት። በእርግጠኝነት በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ መሰል መጽሐፍ አታገኙም። በህትመት በፖኬት ሳይዝ ተዘጋጅታ ተሰራጭታለች። ለሰዎች ማከፋፈል ወይም ማሰራጨት የምትፈልጉ 0912055014 ላይ መደወል ትችላላችሁ!
❤27👍4
Forwarded from Tofik Bahiru
ቃዲ አቡ ጦዪብ አጥ‐ጦበሪይ [ረሒመሁላህ] ሰይዳችንን [ﷺ] በመናም አይዋቸው። የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «አንተ ፈቂህ ሆይ!» በማለት ጠሯቸው።…
ታዲያ አቡ ጦዪብ አጥ‐ጦበሪይ በዚህ መናም ይደሰቱ ነበር፤ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ፈቂህ ብለውኛል።» እያሉ!…
አቡ ጦዪብ ከ348 ‐ 450 ዓመተ ሂጅራ የኖሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው።
ታዲያ አቡ ጦዪብ አጥ‐ጦበሪይ በዚህ መናም ይደሰቱ ነበር፤ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ፈቂህ ብለውኛል።» እያሉ!…
አቡ ጦዪብ ከ348 ‐ 450 ዓመተ ሂጅራ የኖሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው።
😍20❤15
Forwarded from Tofik Bahiru
ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤73👍6
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
«[ዐረቦች ዘንድ] በተከበሩት ሌሎች ወራት ሳይሆን በወርሀ ረቢዐል‐አወል መወለዳቸው እርሳቸው በዘመናት ክብር የሚከበሩ ሳይሆኑ ዘመን በእርሳቸው እንደሚከበር ያመለክታል።»
ኢማም ኢብኑ ሐጀር [ረሒመሁላህ]
ኢማም ኢብኑ ሐጀር [ረሒመሁላህ]
❤39👍5
https://www.tg-me.com/mercy_to_the_worlds
👆ከላይ ያለው ሊንክ ስለ የዓለማቱ እዝነት ብቻ እያወራን ፍቅርና ናፍቆትን የምናብሰለስልበት ቻናል ነው። ተቀላቀሉን። ለሌሎችም ሼር አድርጉልን። ባረከላሁ ፊኩም!
👆ከላይ ያለው ሊንክ ስለ የዓለማቱ እዝነት ብቻ እያወራን ፍቅርና ናፍቆትን የምናብሰለስልበት ቻናል ነው። ተቀላቀሉን። ለሌሎችም ሼር አድርጉልን። ባረከላሁ ፊኩም!
Telegram
የረሕማን ስጦታ
{ وَما أَرسَلناكَ إِلّا رَحمَةً لِلعالَمينَ }[ الأنبياء: ١٠٧ ]
«(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም፡፡»
«(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም፡፡»
👍9
የተወዳጁ ነቢይ [ﷺ] ወሬ ሲነሳ የሙእሚኖች ልብ፣ የተቂዮች መንፈስ፣ የሙሒቦች ስሜት ይነቃል።
ሲራቸውን ሲሰሙ እዝነ ህሊናቸው በናፍቆት ይፈነድቃል። ስለ ግሩም ጠባያቸው ለማድመጥ ሁለመናቸው ይንጠራራል። የላቀው ስብእናቸውን ለማድነቅ ነፍሳቸው ይንገበገባል። የተከበረው አደባቸውን ለማሰብ አይምሯቸው ይተጋል። ሁሌም በየአመቱ የውልደታቸውን በረከት ለመዝከር ወዳጅ ሁሉ ይሰበሰባል!
ይህ መልካም ልማዳቸው ነው። የዝንተ ዓለም ደስታቸውን በተለየ ሁኔታ በውልደት ወራቸው ያስታውሳሉ። ወደ ምድር መምጣታቸውን እንደ አዲስ ያስቡና እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም እንደ አዲስ በድጋሚ ይፈነድቃሉ። በየሀገሩ ዚክራ ነቢይ [ﷺ] ይደራል። ህፃን አዋቂው ሁላ በስማቸውና በግብራቸው ትውስታ ይነቃነቃል። ይህ ዘመን ጠገብ የመልካሞቹ ውርስ ነው!
ከወርሀ ረቢዕ ሁሉም ድርሻውን ይወስዳል። በየፈርጁ እንደሚሰራው ስራ ይለያያል። ቀጥ ያለውን የመልካሞቹን ጎዳና ይዞ የሚሄድ አለ። ከጠፊዎች ጋር የሚጠፋ ሸህዋ አምላኩም ሞልቷል። በመካከልም ልብንና አዕምሮን ጠቅልሎ በሚወስደው የውልደታቸው ክስተት ሰሞን እንኳን ልቡን በሌላ ነገር፣ በሃሳብ ጅምናስቲክ እና በቡድን ግብግብ የሚጠመድም አለ። እኛ ግን መልካም እንነይት። ስለሳቸው ሲራ አብዝተን ለማጥናት፣ ስብዕናቸውን በተለየ ሁኔታ ለመሰልጠን፣ የሶለዋት ክምችታችንን ለማድለብና መልእክታቸውን ለሌላ ለማድረስ።…
{ قُل كُلٌّ يَعمَلُ عَلى شاكِلَتِهِ فَرَبُّكُم أَعلَمُ بِمَن هُوَ أَهدى سَبيلًا }[ الإسراء: ٨٤ ]
«ሁሉም በሚመስለው መንገዱ ላይ ይሠራል፡፡ ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የኾነውን ሰው ዐዋቂ ነው በላቸው፡፡»
ዛሬ ረቢዑል‐አወል ሰባት ብሏል!
እንኳን ለደማቁ ወር ለረቢዑን‐ነቢይ አደረሳችሁ!

❤31
Audio
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር
📗 ክፍል አምስት:‐ በፈዷኢሉል አዕማል መስራት፣ ሒለቁ ዚክር፣ የቀልብና የልሳን ዚክር፣ የዚክር ፈዳኢል፣ የዛኪር ሁኔታው
📆 ነሐሴ 24/ 2017 ዓ. ል.
📗 ክፍል አምስት:‐ በፈዷኢሉል አዕማል መስራት፣ ሒለቁ ዚክር፣ የቀልብና የልሳን ዚክር፣ የዚክር ፈዳኢል፣ የዛኪር ሁኔታው
📆 ነሐሴ 24/ 2017 ዓ. ል.
❤15