Telegram Web Link
{  لَقَد مَنَّ اللَّهُ عَلَى المُؤمِنينَ إِذ بَعَثَ فيهِم رَسولًا مِن أَنفُسِهِم يَتلو عَلَيهِم آياتِهِ وَيُزَكّيهِم وَيُعَلِّمُهُمُ الكِتابَ وَالحِكمَةَ وَإِن كانوا مِن قَبلُ لَفي ضَلالٍ مُبينٍ }[ آل عمران:  ١٦٤ ]

«አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡»
:
«የሚያጠራቸው» ሲል…
ማጥራት የርሳቸው ስልጣንና ስራ መስሎ ቀርቧል። በእርግጥ ቀጥተኛ ስራቸው ሰዎች የሚጠሩበትን እውቀት በማስተማር ሰዎች እንዲጠሩ ማገዝ ነው። በዚሁ አያ ላይ «መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን» ሲል ይህንኑ ያንፀባርቃል። የማጥራት ሂደቱ ሙእሚኖችን የሚለውጡት፣ ከሺርክ እና ከኃጢኣት ጠርተው በኢማን ከፍታ ላይ እንዲያርፉ የሚያደርጓቸው መጽሐፉን እና ጥበብን በመጠቀም ነው።…
ይህ አንድ አካሄድ ነው!…

በእርግጥ "ማጥራት" የርሳቸው ስራ ሆኖ የቀረበበት ሌላም መንገድ ይኖራል።…
ወጣቱ ልጅ ዝሙት እንዲፈቀድለት ፈልጎ እርሳቸው ዘንድ መጣና በተከበረው እጃቸው ዳብሰው ዱዓ አደረጉለት። ወዲያው በልቡ ውስጥ ተጎዝጉዞ የነበረው ቆሻሻ ቡንን አለ። ወስዋሱም ጠፋ። ቀልቡ ተረጋጋ።

ከሱማማ ኢብኑ ኡሳል ጋር የነበራቸው ረዥም ውይይት፣ ምርኮኛ ሆኖ በእጃቸው ገብቶ ሳለ በተደጋጋሚ የነበራቸው ግንኙነት ቀልቡን አጠራለት። በኢማን ላይ እንዲቆምም ብርታት ሆነው።

በርካታ ሰዎችን በእጃቸው ደረታቸውን በመዳበስ ብቻ በነፍሶቻቸው ውስጥ የነበረን ቆሻሻ ያፀዱላቸዋል። ለከፍታና ለፅናት ያበቋቸውም ነበር።

ከዚህ ውጪ እጅግ የታወቁ በርካታ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት በእጃቸው በመዳበስ ብቻ በሶሓቦቻቸው ላይ የሚከሰቱ አካላዊ በሽታዎችን ያክሙ እንደነበር ተዘግቧል።

እናም ከመጽሐፍ [ቁርኣን] መምህርነታቸው ባሻገር ሁለመናቸው ቀልብን የሚያፀዳ ምትሀት ባለቤትም ነበር። ስለዚህም "ማጥራት" የርሳቸው ቀጥተኛ ተግባር ተደርጎ በቁርኣን ተጠቅሷል ማለትም እንችላለን። አላሁ አዕለም!
:
وصلى الله وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه.
#ረቢዑን‐ነቢይ
20👍1😍1
«የአላህ መልክተኛ [ﷺ] መዲና የገቡ ጊዜ መዲና ውስጥ ሁሉም ነገር አበራ!»
ሰይዲና አነስ [ረዲየላሁ ዐንሁ]
#ረቢዑል‐አንዋር
50😍7
ለመውሊድ ቀን የሚሆን መልካም ሃሳብ ልንገራችሁ!
ቤተሰቦቻችንን ሰብስበን የላቀውን የውልደት ትርክታቸውን መንገር። በሰይዳችን [ﷺ] መምጣት የሰው ልጆች ያገኙትን ፀጋ ማብራራት። የተወሰኑ መድሖችን በጋራ ማንጎራጎር። የተለየና የሚወዱትን ምግብ ማብላት።…

ይህ በልጆቻችን ልብ ውስጥ የፍቅር ስሜት ያነብራል። ለታላቁ ነቢይ [ﷺ] ያላቸውን ክብር ይጨምራል። የአላህን ፀጋዎች አስታውሶ የማመስገን ዝንባሌ ያድጋል። እድሜ ልካቸውን በነቢይ [ﷺ] ፍቅር ላይ እንዲፀኑ ንቅናቄ ይፈጥራል!

እኛ በሙረቢ ሸይኾቻችን በዚህ መልኩ ታንፀን ጠቅሞናል። እናንተ ደግሞ ለልጆቻችሁ ሞክሩት!
እንኳን አደረሳችሁ!
133👍2
Forwarded from Tofik Bahiru
አቡ ሰዒድ አል‐ኹድሪይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ክብ ሰርተው የተቀመጡ ባልደረቦቻቸው ዘንድ ወጡና «ለምን ተቀመጣችሁ?» አሏቸው።

የተከበሩት ሶሐቦችም: ‐ «አላህን ልንዘክር፣ ለኢስላም ስለመራንና በርሱም ችሮታውን ስላኖረልን ልናመሰግነው ተቀምጠናል።» በማለት መለሱ።

እርሳቸውም: ‐ «በአላህ ማሉ! የተቀመጣችሁት ከዚህ ውጪ ሌላ ምክንያት አይደለም?» አሉ።

ሶሐቦቹም «ወላሂ! ከርሱ ውጪ በሌላ ምክንያት አልተቀመጥንም።» በማለት መለሱ።

የአላህ መልክተኛም [ﷺ] እንዲህ አሉ: ‐ «እኔም ተጠራጥሬያችሁ አላስማልኳችሁም። ነገርግን ጂብሪል እኔ ዘንድ መጣና አላህ እናንተን [በማወደስ] መላኢካዎች ላይ እየፎከረ እንደሆነ ነግሮኝ ነው!»
ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ለመላው ወዳጆቼና ተከታታዮቼ እንኳን ለታላቁ የነቢዩ [ﷺ] ዝክረ መውሊድ በሰላም አደረሳችሁ!
73
Audio
ጁሙዐ ቀን ከዐስር በኋላ
================
ኢማም አድ‐ዳረቁጥኒ፣ አልሐፊዝ አስ‐ሰኻዊ፣ ኢማም አል‐ገዛሊ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በጁሙዐ ቀን ሰማንያ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያደረገ ሰው የሰማንያ ዓመት ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል።»
ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዴት ብለን ሶለዋት እናድርግቦት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «እንደዚህ በል አሉ: ‐
" اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ"
«አላሁም‐መ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ዐብዲከ ወነቢይ‐ዪከ ወረሱሊከ አን‐ነቢይ‐ዪል ኡም‐ሚይ‐ይ»

ይህንን አንድ ብለህ ቁጠር።»
:
ሰማንያ ስትሞላ በአላህ መልክተኛ ላይ ሰላምታን በማድረግ ጨርስ። «ሶለ‐ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም» በል።»
:
ያያያዝኩላችሁ የድምፅ ፋይል በዘመናችን ከነበሩ ታላላቅ የተሰዉፍ ሰዎች መካከል የነበሩት ሸይኽ ረጀብ ዲብ ከሙሪዶቻቸው ጋር ሶለዋት ሲያደርጉ የተቀረፀ ነው። ትንፋሻቸው ወኔያችንን ከቀሰቀሰ በማለት የተለጠፈ ነው!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1198
14
Al_Majdooja_tul_hasana_fil_istighasa_be_Asma_Allah_al_Husna_by_imam.pdf
234.7 KB
ከሶለዋታችን በኋላ የጁሙዐ ዱዓችንን በሰይዲ አል‐ኢማም ዩሱፍ አን‐ነብሃኒ ታዋቂ የአላህ ስሞች ዱዓ መድብል "አል‐ሙዝደወጀቱል‐ሐስናእ" ለፊለስጢን (ጋዛ) ወንድሞቻችን ነስር እንዲያገኙ እና በጉዳያቸው ላይ የአላህ እገዛ እንዲገባበት ዱዓ እናድርግ!
18😍6👍2
ኑሩ ሙሐመድ
[ክፍል ስድስት]
ንጹሁ/አጥ‐ጧሂር [ﷺ]

አካላቸው፣ ልብሳቸው፣ ቤታቸው እና ማረፊያቸው ሁሉ ንፁህ ነበር። አካላቸው ንፁህና የፀዳ ነበር። የሂንድን ገለፃ ከዚህ ቀደም አሳልፈነዋል:‐
"الأنور المتجرد"
«[ከፀጉር] የተራቆተው የአካል ክፍላቸው እጅግ አንፀባራቂ ነው።» በማለት ገልፀዋቸዋል።
ይህ የንፅህናቸው ምልክት ነው።

በቲርሚዚይ ዘገባ ከአቡ ጡፈይል  እንደተገኘው:‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ቀይ የቀላቀለ ነጭ፣ ውብ፣ አንፀባራቂ እና ባለመካከለኛ ቁመት ናቸው።»

አሁንም ቲርሚዚይ ከኢብኑ አቢ ጁሕፋ አባታቸውን በመጥቀስ እንደዘገቡት እንዲህ ብለዋል:‐ «የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ቀይ ሙሉ ልብስ ለብሰው አይቻቸዋለሁ። የባታቸውን ንጣት አሁን ድረስ የማየው ይመስለኛል።»

ልብሳቸው ከጉልበታቸው በታች የባታቸው አጋማሽ ድረስ ስለነበረ የተከበረ ባታቸውን አይተውታል።

የጠረናቸው ማራኪነት የአካላቸውን ንፅህና ይመሰክራል።
ከሰይዲና አነስ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል:‐ «ቀጭንም ሆነ ወፍራም ሐርን ነክቻለሁ፤ እንደ ነቢዩ [ﷺ] መዳፍ የለሰለሰ ግን አላገኘሁም። ሁሉንም ዓይነት ሽቶ አሽትቻለሁ እንደ ነቢዩ [ﷺ] ጠረን ማራኪ ግን አላገኘሁም።» ቡኻሪ ዘግበውታል።

አቡ ቂርሷፋ እንዲህ ይላሉ:‐
«እኔ፣ እናቴ እና አክስቴ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ቃል ተጋብተናቸው ተመለስን። ከዚያም እናቴና አክስቴ እንዲህ አሉ:‐ «ልጄ ሆይ! እንደዚህ አይነት ሰው አይተን አናውቅም። መልኩ የሚያምር፣ ልብሱ የፀዳ፣ ንግግሩ የለዘበ እንደርሱ አይነት ሰው አላየንም። ብርሃን ከአፉ የሚወጣ ይመስላል።»

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አካላቸው ጽዱ ነበር። ልብሳቸውም የጠራ ነበሩ። ከቤት ሲወጡም ሆነ ወደ ቤት ሲመለሱ ጥርሳቸውን ይፍቁ ነበር።

ለንፅሕና ያላቸውን ቦታ በትእዛዞቻቸውና በአስተምህሯቸው ፋና መገምገም እንችላለን!…
[ይቀጥላል]
20
«በአላህ መልክተኛ [ﷺ] ማመንን ምሉእ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል:‐ በሰው ልጅ ገፅታ ላይ እንደርሳቸው ያለ ውበት የተሰበሰበበት ማንም አካል አለመኖሩን ማመን ይጠቀሳል። ምክንያቱም ውጫዊ ገፅታ የውስጥ ውበት እና የመልካም ጠባይም ምልክቶች ናቸው። በዚህ ረገድ ከርሳቸው በላይ ምልኣት ላይ የደረሰ፣ እንደውም የሚወዳደራቸው ሰው የለም። ስለዚህ የዚህ ምልኣት ምልክት የሆነው [ውብ ገጽታ] ላይም የሚደርስባቸው የለም።

ከዚህ በመነሳት ኢማም አል‐ቁርጡቢይ [ረሒመሁላህ] አንዳቸውን ዋቢ በማድረግ እንዲህ ብለዋል:‐ «ውበታቸው ሙሉ ለሙሉ አልተገለጠም። ውበታቸው ሙሉ በሙሉ ቢገለጥ ኖሮ ሶሐቦቹ እርሳቸውን መመልከት በተሳናቸው ነበር።»
ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይተሚይ [ረሒመሁላህ]
18😍2
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘውታሪው ብርሃን.pdf
1.7 MB
2004 በኢትዮጲያ አካባቢ የተከተበች ድርሰቴ ናት። ከ13 ዓመት በኋላ በዛሬው ተውፊቅ ባትታረምም አንብቡልኝ ብዬ ጀባ ብያለሁ። በብዛት አሳትማችሁ መሶደቅ የምትሹ ካላችሁ 0911473590 በመደወል አለቃዬን አናግሩ😊
31
Forwarded from Tofik Bahiru
የጨረቃ ግርዶች ይኖራል እየተባለ ነው። ከዚህ ቀደም የጻፍነውን አንብቡ። ይጠቅማችኋል!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/20
8
Audio
ይህችም የባፈድል ደርሳችን ላይ አንዲት ክፍል ናት። በከፊል ስለ ግርዶሽ ሶላት ታወራለች። ማንበብ ለማንወድ ሰዎች😊
7
የሶላቱል-ኩሱፍ ህግጋት
===============
❶ ትርጓሜ
በዐረብኛ ቋንቋ ኩሱፍ ወይም ኹሱፍ ተመሳሳይ ቃላቶች ናቸው፡፡ የፊቅህ ልሂቃን ዘንድ ‹‹ኩሱፍ››ን ለፀሀይ ‹‹ኹሱፍን›› ደግሞ ለጨረቃ ግርዶሽ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡
:
❷ ድንጉግነት
ሻፊዒይ (ረሒ) ከአቡ መስዑድ አል-በድሪይ እንደዘገቡት ‹‹የነቢዩ (ﷺ) ልጅ የሆኑት ኢብራሂም ሲያርፉ ሰዎች ‹‹እርሱ በመሞቱ ምክንያት ፀሀይ ተጋረደች፡፡›› ተባባሉ፡፡ ነቢዩ (ﷺ) ግን እንዲህ አሉ፡- ‹‹ፀሀይ እና ጨረቃ ሁለት የአላህ ተዓምራቶች ናቸው፡፡ ማንም ስለሞተ ወይም ስለተወለደ አይጋረዱም፡፡ ይህ መከሰቱን ስትመለከቱ አላህን ለማውሳት እና ለሶላት ተጣደፉ፡፡››
:
ሰዎች ተሰብስበው ቢሰግዱት መልካም ነው፡፡ ከሶላቱ በኋላ ኹጥባ ማድረግም ይወደዳል፡፡ ስለዚህ መሰብሰብ እንደተደነገገባቸው ሶላቶች ገላ መታጠብ ይወደዳል፡:፡
አዛን አይደረግም፡፡ ነገርግን ‹‹አስ-ሶላተ ጃሚዓህ›› የሚል ጥሪ ይደረጋል፡፡
ሶላቱል-ኩሱፍን በህብረትም ሆነ በግል መስገድ ይፈቀዳል፡፡ መንገደኛም ሆነ በሀገሩ ተቀማጭ የሆነ ሰው መስገድ ይችላል፡፡
❸ አፈጻጸም
አብዝሃኞቹ ዑለሞች ዘንድ ሶላቱል-ኩሱፍ ሁለት ረከዓ ነው፡፡: በእያንዳንዱ ረከዓ ላይ ደግሞ ሁለት ጊዜ መቆም አለ፡፡ ሁለት ጊዜ ቂርኣት አለ፡፡ ሁለት ጊዜ ሩኩዕ አለ፡፡ ሁለት ሱጁድም አለ፡፡
:
የተሟላ ነው የሚባለው አፈጻጸም ሰውየው መጀመሪያ በሚቆምበት ሰዓት ከፋቲሓ በኋላ ሱረቱል-በቀራን ወይም ከርሱ ጋር የሚቀራረብ ርዝመት ያለውን ምዕራፍ ያነባል፡፡ በሁለተኛው ቂያም ላይ ከፋቲሓ በኋላ ሱረቱል-ዒምራንን የሚያህል ርዝመት ያለውን ሱራ ያነባል፡፡ በሶስተኛው ቂያም ላይ መጠኑ ከዚህ ያነሰ ምዕራፍ ያነባል፤ ለምሳሌ ሱረቱ ኒሳእን፡፡ በኣራተኛው ቂያም ላይ አሁንም ከፋቲሓ በኋላ ከሱረቱ ኒሳእ ያነሰ ምዕራፍ ያነባል፤ ለምሳሌ፡- ሱረቱል-ማኢዳን፡፡
መጀመሪያ ይቆማል፡፡ የጠቀስነውን ያህል ቁርኣንን ያነባል፡፡ ከዚያም ይነሳል፡፡ በድጋሚ የጠቀስነውን ያህል ቁርአን ያነባል፡፡ ከዚያም ይነሳል፤ ወደ ሱጁድ ይወርዳል፤ ሁለቱን ሱጁዶች በተለመደው መልኩ ያሟላል፡፡ ከዚያም ይነሳል፡፡ ቁርኣንን ባሳለፍነው መልኩ ለሦስተኛ ጊዜ ያነባል፡፡ ከዚያም ሩኩዕ ይወርዳል፡፡ ተመልሶ ይቆማል፡፡ ቁርኣንን ለአራተኛ ጊዜ ያነባል፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሩኩዕ ያደርጋል፡፡ ከዚያም ወደ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ከዚህ በኋላ በተለመደው መልኩ ሶላቱን ይቀጥላል፡፡
የመጀመሪያው ሩኩዕ ላይ ከሱረቱል-በቀራ መቶ አንቀጾችን ለሚያህል ጊዜ ተስቢሕ ያደርጋል፡፡ በሁለተኛው ሩኩዕ ላይ ሰማንያ የሱረቱል-በቀራ አንቀጾችን ሊያስነብብ ለሚችል ለሚችል ጊዜ ተስቢሕ ያደርጋል፡፡ በሦስተኛው ሩኩዕ ላይ ሰባ፣ በአራተኛው ላይ ሃምሳ የሱረቱል-በቀራ አንቀጾችን የሚያህል ተስቢሕ ያደርጋል፡፡ የሱጁዶቹ ርዝመት ከሩኩዑ ርዝመት ጋር የሚጣጣም መሆኑ የተወደደ መሆኑ በመረጃ የተደገፈ ነው፡፡
በሶላቱል-ኩሱፍ ላይ የፈለገውን ሱራ ማንበብ ይችላል፡፡ በፋቲሓ ብቻ መብቃቃትም ይችላል። ቂርኣቱን ረዥም ማድረግም ሆነ ማሳጠር ይፈቀዳል፡፡
:
❹ ድምጽን ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ

ጨረቃ ሲጋረድ የሚሰገደው ሶላት ላይ ድምጽን ከፍ ማድረግ ይወደዳል፡፡ ፀሀይ ሲጋረድ የሚሰገደው ሶላት ላይ ግን በቀን እንደሚሰገዱት ፈርድ ሶላቶች ድምጹን ዝቅ አድርጎ ይሰግዳል፡፡
:
❺ የሚሰገድበት ወቅት

ሶላቱል-ኩሱፍ እና ሶላቱል-ኹሱፍ የፀሀይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ በሚፈጠርበት ወቅት የሚሰገዱ ሶላቶች ናቸው፡፡
ሶላት ከመጀመሩ በፊት ፀሀይ ግርዶዋ ተገፍፎ ከተገለጠች ወይም እንደተጋረደች የምትጠልቅበት ወቅት ደርሶ ከጠለቀች የፀሀይ ግርዶሽ ሶላት (ሶላቱል-ኩሱፍ) ያመልጣል፡፡
የጨረቃ ግርዶሽ ሶላት (ሶላቱል-ኹሱፍ) ደግሞ ሶላት ከመጀመሩ በፊት ግርዶሹ ተገፍፎ በመገለጧ ወይም ነግቶ ፀሀይ በመውጣቷ ያመልጣል፡፡
ሶላት ከጀመረ በኋላ መግገለጥ ከተከሰተ ግን ሶላቱን አቅልሎ በመደበኛው መልኩ ያገባድደዋል፡፡
:
❻ ኢማምን በሁለተኛው ሩኩዕ ላይ ማግኘት

ተከትሎ የሚሰግድ ሰው ኢማሙን በሁለተኛው ሩኩዕ ላይ ካገኘው ምን ያደርጋል?
ኢማም ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹በዚህ ሁኔታ የደረሰበትን ረከዓ አላገኘውም፡፡ ምክንያቱም የረከዓውን አብላጫ ክፍል አላገኘም፡፡››… ‹‹በዚህ መሰረት ተከታዩ የቀረውን የረከዓውን ክፍል ኢማሙን ለመከተል በሚል ይሰግደዋል፡፡ ከዚያም ኢማሙ ሶላቱን ሲያገባድድ ተከታዩ ይነሳል፡፡ ግርዶሹ አሁንም ካለ ሁለተኛውን ረከዓ በመደበኛው አፈጻጸሙ ያከናውነዋል፡፡ ግርዶሹ ገተገለጠ ደግሞ ሶላቱን በመደበኛው አፈጻጸም ነገርግን አሳጥሮ ይሰግደዋል፡፡››
:
❼ የሶላቱል-ኩሱፍ ኹጥባ

ሶላቱን ሲያገባድድ ሁለተ ኹጥባ ማድረግ ሱና ነው፡፡ ሁለቱን ኹጥባዎቸ በመካከል በመቀመጥ ይለያቸዋል፡፡ ‹‹ሐምድ›› የሚለው ስርወ-ቃል እና ከርሱ የተፈለቀቁ ቃላቶችን በመጠቀም አላህን ያመሰግናል፡፡ በነቢዩ (ﷺ) ላይ ሶለዋት ያወርዳል፡፡ አላህን በመታዘዝና እርሱን በመፍራት ላይ ምክር ያደርጋል፡፡ ቢያንስ አንድ አንቀጽ ያነባል፡፡ በአጭሩ ልክ እንደ ጁሙዓ ዓይነት ኹጥባ ያደርጋል፡፡
ኢማም ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ምጽዋት እንዲሰጡ ይምከራቸው፡፡ ተውበት እንዲያደርጉ ይዘዛቸው፡፡ አላህን ምህረት እንዲለምኑና ከኃጢኣት እንዲርቁ አደራ ይበላቸው፡፡››
:
❽ ዱዓና ዚክር
በግርዶሽ ወቅት ዚክር፣ ኢስቲግፋር፣ ዱዓ እና ሌሎች ወደ አላህ የሚያቃርቡ መልካም ተግባራትን ማብዛት ይወደዳል፡፡ ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ግርዶሽን ስትመለከቱ ዱዓ፣ ተክቢራ እና ሶደቃ አድርጉ፡፡››
በሌላ ዘገባ፡- ‹‹አላህን ወደ መዝከር፣ ወደ ዱዓ እና ወደ ኢስቲግፋር ፍጠኑ፡፡››
ግርዶሽ ሳይንሳዊ ትንታኔው ምንም ይሁን ምን የአላህ ማስፈራሪያ መሆኑ ይታመናል፡፡ ስለዚህ አላህ በመልካም እንዲያሳልፈው መለመን እና ደንግጦ ወደ አምልኮ መጣደፍ ይገባል፡፡ ከሶላት በኋላ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ዞሮ በፍርሃት ስሜት ዱዓ ማድረግ የተወደደ ተግባር ነው፡፡
አላህ የተሻለ ያውቃል!!
www.tg-me.com/fiqshafiyamh
10👍6
Forwarded from Tofik Bahiru
እግረ መንገድ
=========
በነቢዩ [ﷺ] ዘመን ፀሀይ ተጋረደች። ሰዎች ይህ የሆነው የርሳቸው ጨቅላ ህፃን ልጅ ኢብራሂም [ዐሰ] በመሞቱ እንደሆነ አወሩ።
:
ይህንን ያደረጉት የአላህን መልክት ቀን ከሌት የሚያስተላልፈው ነቢይ ቀላል ሰው አለመሆኑን ከማመናቸው የተነሳ ነው። ተፈጥሮን ያስገኘው ፈጣሪ መልክተኛነት ልዩ ደረጃን ስላገኙ ተፈጥሮ የርሳቸውን የህይወት አፅናፎች እየተከተለች እንድታዝንና እንድትደሰት ያደርግላቸዋል የሚል እምነት አድሮባቸው ነው። ለነቢያቸው የነበራቸው ክብር ከዚህም በላይ ቢባል እንዲቀበሉ የሚያደርግ ነበር። ደግሞም ሰዪዳችን በርካታ መለዮዎች አሏቸው፤ ይህ ከዚያ ውስጥ ቢካተት አይገርምም።…
:
ወሬው ከየት እንደመጣ አልታወቀም። እርሳቸው ልጄ ስለሞተ ፀሀይ ተጋረደ አላሉም። እንደማንኛውም ወፍ ዘራሽ ወሬ በቅጥፈት ጀመረ። አማኞች ለነቢያቸው ﷺ ባላቸው ፍቅር ተነሳስተው ሳያጣሩ አናፈሱት።
:
ነገርግን የአላህ ነቢይ ﷺ ምን አደረጉ?
የወሬውን እውነተኝነት የሚያጠናክር ፍንጭ ሰጡ?
እኔ ባልልም ሰዎች ይህንን ክብር ከሰጡኝ ዝም ልበላቸው እንዳሻቸው ያውሩ አሉ?…
በፍፁም!
ህዝቡን ሰበሰቡ። አላህን አመሰገኑ። አወደሱት። ከዚያም «ፀሀይና ጨረቃ የአላህ ተዐምራት ናቸው። ማንም ስለሞተም ሆነ ስለተወለደ አይጋረዱም።…» አሉ።
:
የሰዎች አዕምሮና ልብ የአማና እቃቸው ነው። በውስጣቸው እውነትን ብቻ የመሙላት ግዳጅ አለባቸው። ከጌታቸው በሆነው መልክት በሉ የተባሉትን ብቻ ይላሉ። ክብርና ዝናን፣ የሰዎችን አድናቆትና ፍቅር ለተሸከሙት እውነት ይሰዋሉ። ስለዚህ ከሰው መሀል ቆመው አእምሮን ይገርዛሉ! እምነትን ያፀዳሉ! ሀሰትን ይዋጋሉ!
ኃላፊነታቸው ይህ ነው!…
:
ታዲያ ሰዪዲ ሙሐመድ ﷺ ነቢይ ነኝ ሲሉ ዱንያዊ መሻት እንደሌላቸው ጥብቅ መረጃ አላገኘንም!?
አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ!
www.tg-me.com/fiqshafiyamh
18
ኢብኑ ኹዘይማ እና ሌሎችም እንደዘገቡት:‐
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የግርዶሽ ሶላት ሰገዱ።…

«ከዚያም ሱጁድ አደረጉ። ራሳቸውን ከመሬት ላይ ሳያነሱ ረዥም ጊዜ ቆዩ። [በጭንቀት] «ኡፍ! ኡፍ!» በማለት [እየተነፈሱ] እንዲህ ዱዓ አደረጉ:‐

«ጌታዬ ሆይ! እኔ በመካከላቸው እስካለሁ ድረስ እንደማትቀጣቸው ቃል ገብተህልኝ አልነበር?!… ጌታዬ ሆይ! እኛ ምህረት እስከለመንህ ድረስ እንደማትቀጣን ቃል ገብተህልኝ አልነበር?!…»
:
እዚህ ጋር ቁምና በቃላቶቻቸው መካከል ያለውን የአባት ጭንቀት፣ ለኡመታቸው ያላቸውን ርሕራሔ ተመልከት!

ለአላህ ያላቸውን ፍርሐት እና በማንኛውም ጊዜ የአላህ ቅጣት እንዳይመጣ ምን ያህል ይሳቀቁ እንደነበርም በጥልቀት ታዘብ!…

ይህ ሁሉ ፍርሃት ከታላቅ ማንነታቸው እና አላህ ከሰጣቸው በርካታ ስጦታዎች ጋር መሆኑን ስታይ ደግሞ "ከማናችሁም በላይ አላህን ፈሪው እኔ ነኝ።" ማለታቸው ለምን እንደሆነ ይገለጥልሃል።
20😢1😍1
ኑሩ ሙሐመድ
[ክፍል ሰባት]
የንጽሕና መንገድ
ንጽሕና ፅኑ ትእዛዛቸው ነው። ንጽሕና መጠበቅ ያለውን መልካም ውጤት እያስረዱ ሰዎችን ይቀሰቅሱም ነበር። ቆሻሻነትን ይዋጉ ነበር። ይህንን በተለያየ ረገድ እንመልከተው:‐

❶ ንጽሕና ከኢስላም መሰረታዊያን እንደሆነ አብራርተዋል:‐
ቲርሚዚይ ከሰዕድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «አላህ መልካም ነው። መልካምን ይወዳል። ንጹሕ ነው። ንጽሕናን ይወዳል። ቸር ነው። ቸርነትን ይወዳል። ለጋስ ነው። ልግስናን ይወዳል። ቀዬዎቻችሁን አጽዱ። ከአይሁዶች ጋር አትመሳሰሉ።»

ከሱለይማን ኢብኑ ሱረድ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «ጥርሳችሁን ፋቁ። ራሳችሁን አጽዱ። ዊትርም [ነጠላ ሶላት] ስገዱ። አላህ ነጠላ (ዊትር/አንድ) ነው። ዊትር [ነጠላን] ይወዳል።»

አል‐ኸጢብ እና ሌሎችም ከሰይዳ ዓኢሻ እንደዘገቡት የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «ኢስላም ጽዱ ነው። ራሳችሁን አጽዱ። ንጹሕ እንጂ ጀነት አይገባም።»

አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «በምትችሉት ነገር ሁሉ ራሳችሁን አጽዱ። አላህ ኢስላምን የገነባው በንጽሕና ነው። ንጹሕ እንጂ ጀነት አይገባም።»

❷ ቅስቀሳዎቻቸው:‐
በበርካታ ሐዲሶች ሰዎች እንዲታጠቡ ቀስቅሰዋል። ካለመታጠብ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ ውስጥ ጥቂቱን እናንሳ:‐
ኢማም አሕመድ ከጃቢር [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ በየሰባት ቀኑ አንዴ መታጠብ አለበት። እርሱም የጁሙዐ ቀን ነው።»

አንዳንድ የአካላት ጫፎችን ስለማጽዳት በተናጠል አብራርተው ተናግረዋል። ቆሻሻ የሚያጠራቅሙ እነዚህ አካላትን ማጽዳት ተፈጥሮኣዊ የኃይማኖት ድንጋጌ መሆኑን ገልጸዋል። የሁሉም የነቢያት መልክት ውስጥ የሰረጸ የአላህ ትእዛዝ እንደሆነም ተናግረዋል:‐

ሙስሊም ከዓኢሻ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
ዐስር ነገሮች ተፈጥሮኣዊ የኃይማኖት ድንጋጌዎች (ሱነን አል‐ፊጥራ) ናቸው:‐
⚀ ቀድሞ‐ቀመስን (የላይኛውን የከንፈር ጺም) ማሳጠር፤
⚁ የአገጭን ጺም ማጎፈር፤
⚂ ጥርስን መፋቅ፤
⚃ በአፍንጫ ውሃን መሳብ (ኢስቲንሻቅ)፤
⚄ ጥፍርን መቁረጥ፤
⚅ የጣት መገጣጠሚያዎችን ማጠብ፤
⚆ የብብትን ጸጉር መንጨት፤
⚇ የብልት ጸጉርን መላጨት፤
⚈ ኢስቲንጃእ ማድረግ።»

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እነዚህን የአካል ክፍሎች ለረዥም ጊዜ ችላ ማለት እንደማይገባ አሳስበዋል።
ሱነኑ አቢ ዳዉድ ላይ ከሐሰን [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል:‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ቀድሞ‐ቀመስን ለማሳጠር፣ ጥፍርን መመቁረጥ፣ የብብት ጸጉርን ለመንጨት እና የብልት ፀጉርን ለመላጨት የጊዜ ገደብ አድርገውልን ነበር። ከአርባ ቀን በላይ ቸላ ብለን እንዳንተው መድበዋል።»

ማለትም ችላ ብሎ መተው የግድ የሚሆንበት በየሳምንቱ ማጽዳት የማይመችበት ሁኔታ ቢፈጠር እንኳን ከዐርባ ቀን በላይ ማሳለፍ ግን ክልክል ነው። የክልክልነት ደረጃው ላይ ልሂቃን የተለያዩ አስተያየቶችን ቢሰጡም፣ መከልከሉ ግን ያስማማል።

❸ የምግብና የመጠጥ ተረፎችን ማጽዳት:‐
ሐኪም እና ቲርሚዚይ ከዐብዱላህ ኢብኑ ቡስር እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ጥፍሮቻችሁን ቁረጡ። የተቆረጡ ጥፍሮቻችሁን ቅበሩ። የጣቶቻችሁን መተጣጠፊያ አጽዱ። ላንቃዎቻችሁን ከምግብ ፋና አጽዱ። ጥርሳችሁን ፋቁ። ጥርሳችሁን ቢጫ አድርጋችሁ አፋችሁ እየገማ እኔ ዘንድ አትግቡ።»

ቲርሚዚይ ከሰልማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «የምግብ በረከቱ ከበስተፊቱ እና ከበስተኋላው እጅን መታጠብ ነው።»

❹ ልብስን ስለማጽዳት:‐
ጦበራኒይ እና አቡኑዐይም ከዑመር ኢብኑል‐ኸጧብ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «ሙእሚንን አላህ ዘንድ ክብር (ከራማ) ከሚያሰጡት ነገሮች መካከል የልብስ ጽዳት እና [ከዱንያ ነገሮች] በትንሽ ነገር መብቃቃት ይገኙበታል።»

አቡኑዐይም ከጃቢር እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አንድ ሰውዬን ልብሱ ቆሽሾ አዩት። ከዚያም እንዲህ በማለት ተቆጡ:‐ «ይህ ሰውዬ ልብሱን የሚያጸዳበት ነገር አላገኘምና ነው [እንዲህ የቆሸሸው]?!»

እርሳቸው ዘንድ ቆሻሻ ልብስ ያስወቅሳል። በእርግጥ ሰውየውን በቀጥታ አልተናገሩትም። ቀልቡን ለመጠበቅ ለሌላ ሰው ነው መልክት ያደረሱት። በዚያውም ሌሎች ሰዎች ሰምተው ይጠነቀቃሉ። በዚያውም ልብሳቸውን በንፅህና ለማይለብሱ ሁሉ ወቀሳቸውን ያደርሳሉ።

ነቢዩ [ﷺ] ልብስን ለቆሻሻ መዳረግንም ይቃወሙ ነበር። ከአሽዐስ ኢብኑ ሱለይም እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል:‐ አክስቴ አጎቷን ጠቅሳ እንደምትናገረው እንዲህ ብለዋል:‐
«በመዲና መንገድ ላይ እየሄድኩኝ ከጀርባዬ አንድ ሰው እንዲህ ሲል አገኘሁት:‐ «ሽርጥህን ከፍ አድርግ። ይህ ጽዱ፣ ፈሪሐ አላህ ያለበት እና ልብስህንም የሚበረክት እንዲሆን ያደርግልሃል።» ከዚያም [ዘወር ስል] የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ሆነው አገኘኋቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአዘቦት [የስራ] ልብስ ነውኮ።» አልኳቸው።
እርሳቸውም:‐ «እና የእኔን ፈለግ አትከተልም!» አሉኝ። አተኩሬ ሳያቸው ሽርጣቸው የባታቸው አጋማሽ ላይ ነው።»
ቲርሚዚይ "ሸማኢል" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ዘግበውታል።

[ይቀጥላል]…
27
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
نعم سرى طيف من أهوى فأرقني
31👍11
2025/10/21 23:14:51
Back to Top
HTML Embed Code: