Telegram Web Link
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 2 ወንድም እህቶቻችን የዚህን ቀን ሰደቃ እየተሽቀዳደሙ ነው እናንተም ተሽቀዳደሙ ለአላህ መልካም ብድር በማበደር ሀጃችሁ እንዲሳካ የጎደለባችሁ እንዲሞላ ነይታችሁ ሌሎችን አስደስቱ በትንሿ ዱንያ ትልቋን ጀነት እንሸምት

ገንዘቡን ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ @ifadasales ላይ አካውንት በመውሰድ ማስገባት ትችላላችሁ!  ያስገባችሁበትን ደረሰኝ ላኩልን!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
🔥7👏76
የጎደሉ አሉ 2! 20ሺህ!
ነፃ አውጥተን ነፃ እንወጣለን!
.
20 ሺህ ብር ደርሰናል! ተክቢር! ገና መጀመሩ ነው …. ብዙ ብር ያስፈልገናል፡፡ የቻላችሁትን ያህል ኒያችሁን አሳምራችሁ በዚህ ልዩ የሰደቃ ፕሮጀክት ላይ ተሳተፉ!

የቂያም ቀን በነቢ ምልጃ ነፃ መውጣትን ሽተን በየእስር ቤቱ የዋስ ገንዘብ አጥተው የሚማቅቁትን በአላህ ፈቃድ ነፃ እናወጣለን! ጠያቂ ያጡትን የምግብ ሽታ የናፈቃቸውን አብልተን ‹‹አላህ ምግብን ከመውደድ ጋር ለድሆች፣ ለየቲሞች እና ለእስረኞች ያበላሉ፡፡›› ካላቸው ውስጥ መግባትን እንከጅላለን!

የተሳተፋችሁትን በሙሉ አላህ ዱንያ አኼራችሁ ይመር! ሀጃችሁ ይውጣ! ከዱንያም ከአኼራም ውርደት ይጠብቃችሁ! ዘር ዘራችሁን ችግር አያግኘው!

መሳተፍ የምትፈልጉ @ifadasales ላይ አካውንት በመውሰድ የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ! በዚህ በረመዳን ወር አጅራችሁን እፈሱ!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@ifadasales
@ifadasales
26
ክቡራትና ክቡራን!

ውዶቹ የረመዳን ቀናት እስኪያልቁ ድረስ የኢፋዳ መፅሀፍ ሽያጭ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እናደርጋለን! አቅም ይዟችሁ ያልገዛችሁ እድሉን ተጠቀሙት! ሌሎችም ለኢድ ስጦታ ለመስጠት ጥሩ አጋጣሚ ይሆንላችኋል! ሽያጩ በሞባይል ባንኪንግ @ifadasales ላይ ብቻ በመግዛት የምታገኙት ነው፡፡ በካሽ ለሚገዙ ቅናሽ የለም፡፡

እስከ ረመዳን 26 ድረስ 50 ፐርሰንት! በ250ብር ብቻ! ያደረግነው ቅናሽ ሊያልቅ 1 ለሊት ከ1 ቀን ብቻ ቀርቶታል ከረመዳን 27እስከ ኢድ ድረስ 350 ብር ብቻ!

@ifadasales ላይ ሸምቱ!

መልካም ሸመታ!
.
@ifadasales
@ifadasales
6😍1
የጎደሉ አሉ  2 እንደቀጠለ ነው
ጀነት ለነፍስ በሚከብዱ ነገሮች የተከበበች ነች ለነፍስ ከሚከብዱ ነገሮች ዋናው ደግሞ ሰደቃ መስጠት ነው ሁሉም ያለፉ ሰዎች ወደ ምድር የመውረድ እድል ቢሰጣቸው ወርደው በመጀመሪያ ለማድረግ የሚያስቡት ሰደቃ መስጠትን ነው

وَأَنفِقُوا مِن مَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَا أَخَّرْتَنِي إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ الصَّالِحِينَ

አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡(ሱረቱል ሙናፊቁን 10)

ገንዘቡን ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ @ifadasales ላይ አካውንት በመውሰድ ማስገባት ትችላላችሁ!  ያስገባችሁበትን ደረሰኝ ላኩልን!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
🥰9👏3
የጎደሉ አሉ  2 እንደቀጠለ ነው
በእናንተ የተባበረ ጥረት ከ 50,000 ሀምሳ ሺ ተሻግረናል
ገና ነን አሁንም ይቀረናል በዚህ የተከበረ ወር ለአላህ መልካም ብድርን ማበደር የሚፈልግ ማነው ?

مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً ۚ وَاللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْسُطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡(ሱረቱል በቀራ 245)

ገንዘቡን ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ @ifadasales ላይ አካውንት በመውሰድ ማስገባት ትችላላችሁ!  ያስገባችሁበትን ደረሰኝ ላኩልን!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
1
😭😭😭
(ፉአድ ሙና)

ረመዳን መጥቶልን ነበር!

በወንጀል ትብታብ የተሳሰረች ነብሳችንን ከአመፃዋ ለአፍታ ገትቶልን!
ነብሳችንን የእንባ ቋንቋን አልምዶልን!
ጆሯችንን በቲላዋ አርክቶልን!
አይናችንን ከቁርዓን አለመሰልቸትን አግዞልን!

ረመዳን መጥቶልን ነበር!

በመምጣቱ የልብ ንጣት የቀድሞ መጥቆራችንን አየን!
በሰራነው ስራ አፍረን ወደ ጌታችን ተደፋን!
ማህርታን ስለመውደዱ ሲል እንዲምረን ለመንን!
በህብረትና በተናጠል ቀኑንም ሌቱንም አስዋብን!

ረመዳን መጥቶልን ነበር!

ከብዙ መጥፎ ልማዳችን በአላህ ፈቃድ ተገታን!
ከእሳት ነፃ መባልን ከጀልን!
በጀነት መበሸርን ወደድን!
አስበን የማናውቀውን ያህል ወደ ጌታችን ተዋደቅን!

ረመዳን ሰው አድርጎን ነበር!

ስለ አኼራው የሚያስብ …. ሰው!
ወንጀል የሚጠየፍ ….. ሰው!
አምልኮ የሚያበዛ …. ሰው!
ስለ ጥፋቱ የሚፀፀት …. ሰው!

ረመዳን ጓዙን ጠቀለለ!

ሰው ያደረገን ወር ሊሄድ ተነሳ!
የምንለምነው ብዙ ነበረን!
ብንጨምር ደስ የሚለን አምልኮ በርካታ ነበር!
ሰው ሆነን ብንቆይ በወደድን ነበር!

የተቆጠሩ ቀናት …. ነበሩና!
አንድ ሁለት ሶስት እያሉ 28 ደረሱ!
መማራችንን ሳናረጋግጥ! በብዙ አጉድለን!
ቀናቱ አለቁ!

يا شهر رمضان ترفق،
دموع المحبين تُدفق،
قلوبهم من ألم الفراق تشقق،
.
@fuadmu
57🥰8
የዛሬው ምሽት
የዚህ አመት ረመዳን
የመጨረሻ ተራውሒ ሰላት ሊሆን ይችላል
ምናልባት የህይወታችንም!
የመጨረሻ!!!!!!!!!
.
@fuadmu
71🥰7🔥5
ኢድ ሙባረክ!

የተቆጠሩት ቀናት ተጠናቀቁ!
መስፈሪያውም ወደነበረበት ተመለሰ!
የታሰሩት ሰይጣኖችም ከኢድ ሰላት መልስ ይፈታሉ!

ከፆማቸው ምንዳን ካተረፉት ያድርገን!
ከረመዳን በኋላም በመንገዱ ላይ ያፅናን!
በጤና በሰላም ከአመት አመት ረመዳኑን ይመላልስብን!
የሞከርነውን ይቀበለን!

ለሁላችሁም የተባረከ የኢድ አል ፊጥር በዓል እመኛለሁ፡፡

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
81🥰6
Fuad Muna (Fuya) pinned Deleted message
የጎደሉ አሉ 2!

በየእስር ቤት ዋስ ቢፈረድላቸውም በዋስ የሚወጡበት ገንዘብ አጥተው በእስር ጨለማ ላይ ያሉትን ብርሀን ለማሳየት ጉዞ ጀምረናል፡፡ ገንዘብ ማሰባሰብ በጀመርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ስድሳ ሺህ ተሻግረናል፡፡ አሁን ስራውን ለመጀመር በመንደርደር ላይ እንገኛለን፡፡ እናንተ የምትዛመዱት በዚህ መልኩ የታሰረ ሰው ካለ ለቻናላችን ቤተሰቦች ቅድሚያ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ @ifadasales ላይ ጠቁሙን!

ለዚህ ፕሮጀክት በርካታ ገንዘብ ያስፈልገናል፡፡ አላህ ቢሻና ገንዘብ በደንብ ብናገኝ ታሳሪ የማብላትም እቅድ አለን፡፡ ይህ ሁሉ ሀሳብ ያለእናንተ ድጋፍ ምንም ነው! @ifadasales ላይ አካውንት ወስዳችሁ የቻላችሁትን አስገቡ! አላህ ይቀበለን!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
@Fuadmu
35
Live stream started
2025/07/09 08:19:23
Back to Top
HTML Embed Code: