Telegram Web Link
Live stream finished (2 hours)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የልብ ነገር in mind 😘
.
@Fuadmu
🥰485👏4😘3😍1
ክቡራትና ክቡራን!

የረመዳንን ወርቃማ ለሊቶች እና የኢድ አል ፊጥር በዓልን አስመልክተን አድርገነው የነበረው ከፍተኛ ቅናሽ ተጠናቋል፡፡ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ መፅሀፉን በመደበኛ ዋጋው 500 ብር @ifadasales ላይ እንዲሁም በመሸጫ ቦታዎቻችን ማግኘት ትችላላችሁ!

ደህና እደሩ! መልካም ሸዋል!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
🥰19
የጎደሉ አሉ!
ፕሮጀክት ሁለት!

ባሳለፍነው ረመዳን የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ባካሄድነው ዘመቻ በአላህ ፈቃድ በጅማ ዞን ሳኮሩ ወረዳ 1 የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሀረማያ 2 የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት እና የበርካታዎችን ድካም ለማቅለል ችለናል፡፡ አሁን ደግሞ እስርቤት ውስጥ ሆነው የዋስ ብር መክፈል አቅቷቸው እየማቀቁ ያሉ ወንድም እህቶችን በማያውቁት እጅ ነፃ እናወጣቸው ዘንድ ፕሮጀክት 2 ጀምረን ስድሳ ሺህ ብር አልፈናል፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገን ገንዘብ ብዙ ነውና ሁላችሁም የራሳችሁን አሻራ እንድታሳርፉ እጠይቃለሁ፡፡

አካውንት @ifadasales ላይ በመውሰድ የአቅማችሁን አበርክቱ! አላህ ሀጃችሁን ያውጣ! ስራችንን ይውደድ!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
@fuadmu
25👏5😍1
የአድራሻ ለውጥ!

ጀሞ ሰይድ ያሲን ህንፃ አሊፍ መረዳጃ ውስጥ የነበረው የኢፋዳ ፒካፕ ሎኬሽናችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ፉሪ ሙዲን ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ አሊፍ መረዳጃ የተዘዋወረ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ሰሞኑን ወደ ሰይድ ያሲን ሄዳችሁ ለተጉላላችሁ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን!
.
@ifadasales
10👏2
‹‹ሰው ማለት ሰዎችን ወደ ራሱ የሚሰበስብ አይደለም! ሰው ማለት የሰዎችን ቀልብ ወደ አላህ የሚሰበስብ ነው፡፡››
ሸይኽ አዲል ሸሪፍ
.
@fuadmu
187🥰22👏15🔥5
Live stream started
Live stream finished (4 hours)
Live stream started
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት ተሳትፎ
👏1
Live stream finished (3 hours)
ቀኑ ቅዳሜ ነው!!!

ፈገግታ መጅሊስ!

ፈገግታ መጅሊሳችን ዛሬ ከምሽቱ 3፡00 ላይ እንደተለመደው ይካሄዳል!

ስነፅሁፍ

እኔ ቻሌንጅ እየተደረግኩ የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት ገቢ እናሰባስባለን።


ከምሽቱ 3፡00 ሲል እንገናኝ!
.
@fuadmu
👏134
Live stream started
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት ተሳትፎ
Live stream finished (3 hours)
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 2

አልሀምዱሊላህ በእናንተው ተሳትፎ አንድ መቶ ሺህ ብር ደርሰናል።

አሁንም አንድ ላይ እንችላለን!
.
@Fuadmu
45
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ....

#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
3😘1
የ 500 ብር ዋስ ማቅረብ አቅቶት የታሰረ አለ ብንል ታምናላችሁ?

#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
7🔥6
ትልቁ የዋስ ብር 5000 ብር ነው።

5000
4000
2000
500

ከተሰጡን ዝርዝሮች ውስጥ የሰፈሩት የገንዘብ መጠኖች ከላይ የሰፈሩት ናቸው።

#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
ውሎዬን ላጋራችሁ 1
(ፉአድ ሙና)
.
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እስረኞችን ለማስፈታት ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር መወያየት ጀምረን ነበር። የክፍለ ከተማው የእስረኞች ኃላፊ ባሳለፍነው ሳምንት በነበረው በዓል ምክንያት ጉዳዩ ወደዚህ ሳምንት እንዲዞር ጠይቆን ትናንት እና ዛሬ በአላህ ፈቃድ አመርቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንገኛለን።

በዛሬው ዕለት ክፍለ ከተማው በገንዘብ እንዲወጡ ተፈርዶላቸው ገንዘብ ያጡ እስረኞችን ዝርዝር ከገንዘብ መጠኑ ጋር አቅርቦልናል። ሆኖም የዋስ መክፈቻ ወረቀቱ ላይ የሚፈርም የታሳሪ ቤተሰብ አልያም የእስር ቤት አዛዥ አስፈላጊ ስለነበር (እኛ ከፈረምን ታሳሪው ከጠፋ ወደኛ እንደሚዞር ስላስጠነቀቁን) በነገው እለት ጠዋት ላይ ኃላፊዎችን እንደሚጠራ ገልፆልን ለጠዋት ተቀጣጥረናል።

የ27 ታሳሪዎችን ስም ዝርዝር ከወንጀሉ አይነት እና የገንዘብ መጠን ጋር ተቀብለናል። ፖስት የማናደርገው በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጭ ስለተጠየቅን ነው።

ነገ ጠዋት የአላህ ፈቃድ ከሆነ ክፍያ እየፈፀምን ታሳሪዎቹ ይለቀቃሉ።

በአላህ ፈቃድ አንድ ላይ እየቻልን ነው!!!

#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
👏8217🥰6
2025/07/08 23:25:24
Back to Top
HTML Embed Code: