እስር ቤቱን ጎበኘን!
.
የእስር ቤት ኃላፊው ገንዘብ የምናገኝ ከሆነ ለእስረኞች የሚተኙበት ሰሌን እና እንደ በረኪና፣ መጥረጊያ፣ መወልወያ ያሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንድናሟላ እንዲሁም የእስረኞችን ክፍል ቀለም እንድናስቀባ ጥያቄ አቀረበልን። አስፈላጊነቱን ለመገምገም እስር ቤቱን እንጎበኝ ዘንድ ጓደኛዬ ጥያቄ አቀረበ። ተፈቀደልን።
ወደ እስር ቤቱ ስንገባ ያገኘን ሽታ ..... ጀሀነም እንዴት ሊሆን ይሆን? በውስጡ ያገኘናቸው ሰዎች በሙሉ ከጀርባችን «እኛንም አትርሱን!» እያሉ ይከተሉናል። ፖሊሱ አባረራቸው። ወደ ክፍሎቹ እያስገባ ስፋታቸውን አሳየን። እኔ የሚሰማኝ ሽታው እና የሚተኙበት ቅዝቃዜ ነው። ፍራሽ ማስገባት ስለማይፈቀድ አንዳንዶች ብቻ ሰሌን ላይ ተኝተዋል።
ወደ ሽንት ቤቱ ስንደርስ ሆዴ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባ። ፖሊሱን ጠየቅኩት።
«ሽንት ቤቱ ለምንድን ይሸታል? በየተራ እንዲያፀዱ ለምን አታደርጉም?»
ፖሊሱ «የኛ ድክመት ቢኖረውም .... በውሀ ብቻ መፀዳቱ ሽታውን አያጠፋውም በረኪና ያስፈልጋል። የፅዳት ቁሳቁሶች እንፈልጋለን።» ሲል መለሰ።
ጉብኝቱን እንደጨረስን ከኡሚ መረዳጃ ከመጡት አመራሮች ጋር መከርን። ቀለም ብንቀባ መልሰው ይፅፉበታል። ከቻልን ለጤናቸው የሚጠቅሙት ላይ እናተኩር! መተኛ ሰሌን እና የንፅህና ቁሳቁስ እናሟላ! በዚህ ተስማምተን ተለያየን!
ከ27 እስረኞች የሚተርፈንን ገንዘብ በዚህ ስራ ላይ ለማዋል አስበናል። የቻላችሁትን በማዋጣት ሲዖል የሚመስለውን ኑሮ ትንሽ እናቅልለው!
#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu

እናትየው የስኳር ህመምተኛ ናቸው። ደውዬ ገንዘቡን የሚከፍል ሰው እንደተገኘ ስነግራቸው ማመን አልቻሉም።
«ታማሚ ነኝ እያረፍኩም ቢሆን እመጣለሁ።» አሉ።
#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
«ታማሚ ነኝ እያረፍኩም ቢሆን እመጣለሁ።» አሉ።
#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
ቀኑን ሙሉ ሲሯሯጥ ከዋለው ቡድን ጋር አመሻሹን አረፍ ከማለታችን ስልኬ ጠራ።
«አቤት?»
« ጨረስን እኮ ወጣ። አናግረው! »
ስልኩን ወደ ጓደኛው አሳለፈው።
«አመሰግናለሁ እሺ አባቴ! ወጣሁ እኮ! አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ብድር መላሽ ያድርገኝ።»
ለምስጋናው ቃላት እያጠሩት ነው። ገና ከእስር ተፈቶ መውጣቱ ነበር።
በእርግጥ ምስጋናው ለእናንተ ነበር!

ወራቤ ወራቤ ወራቤ!!!!
ኢፋዳ ወራቤ ላይ ለምትፈልጉ ሪያድ ሆቴል ፊት ለፊት ፒያሳ ስቴሽነሪ ማግኘት ትችላላችሁ። ቦታው ከጠፋችሁ 0939240653 ደውሉ!
መፅሀፉን @ifadasales ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ።

ስልኬ ጠራ። የማላውቀው ቁጥር ነበር።
«አቤት ... »
«ልጅቷን እኮ አልፈታም አሉን!»
«ለምን?»
«አንፈታም አሉ። መፍቻ አልፅፍም አለኝ ኢንስፔክተሩ!»
ዋስትናዋን ከፍለንና ትፈታ የሚል ደብዳቤ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት አውጥተን ወደያዛት ጣቢያ ልከናቸው ነበር።
እስኪ ዱዓ አድርጉላቸው።

ሳቂታችን የእውነት ፈካች!
(ፉአድ ሙና)
***
ለከርሞው በብዛት ወደምንጠቀምበት ካፌ አመራን። ከወዳጄ ጋር ውጪ ላይ እንደተቀመጥን የምንወዳት አስተናጋጅ እየተፍለቀለቀች መጣች።
ወደ ካፌው መጥተን እሷ ካላስተናገደችን ይከፋን እንደነበር አስታውሳለሁ። ወይም የመጣውን አስተናጋጅ «እሷን ጥራልን!» እንላለን።
«ምነው ጠፋህ?»
«ሌላ ካፌ በዛ እኮ!»
ትንሽ ካወራችን በኋላ
«ስማ ፉአድ .... »
«ወዬ?»
«ሰለምኩ እኮ! »
«ፍዝዝ ብዬ አየኋት!»
«እንዴ ማሻአላህ አትሉኝም እንዴ? ማሻአላህ ሲሉኝ ደስ ይለኛል!»
«ቤተሰብ ምን አለሽ?»
«ገና አልነገርኳቸውም!»
«ሲያውቁ ፈተና ሊኖረው ይችላል በርቺ እሺ!»
ደስ ብሎኛል ልቤም ደግሞ ከዚህ በኋላ ስለምትጋፈጠው ትግል ተጨንቋል።
ስልኳን ተቀብለናት ወጣን።
እና ለዚህች አዲስ ሰለምቴ እህታችን ስጦታ ብንሰጣት ብለን አሰብን። አንድ እህት 5K ነይታለች። እስኪ ሌሎችም ካላችሁ ነይቱና እናስደስታት።
ማዋጣት የምትችሉ @Fuadmuna ላይ አናግሩኝ።

በየእስር ቤቱ ክፍሎች ተዘዋወርን። እስረኞች እንመዘግባቸው ዘንድ ተሻሙብን። ዋስ የተፈረደላቸውን ሁሉ መዘገብን።
በሰጡን ስልክ ቤተሰቦቻችን ናቸው ያሏቸው ጋር ደወልን።
አይነሳም ....
አይሰራም ....
«ኧረ አላውቀውም .... »
«አዎ ቤተሰቡ ነን መጣን!»
ብዙ አይነት ምላሾችን አስተናገድን።
ቤተሰቦቻቸው የመጡላቸውን እየከፈልን ነው።
ገንዘባችሁ ....
ብዙ ሰው ነፃ እያወጣ ነው።
#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
በሰጡን ስልክ ቤተሰቦቻችን ናቸው ያሏቸው ጋር ደወልን።
አይነሳም ....
አይሰራም ....
«ኧረ አላውቀውም .... »
«አዎ ቤተሰቡ ነን መጣን!»
ብዙ አይነት ምላሾችን አስተናገድን።
ቤተሰቦቻቸው የመጡላቸውን እየከፈልን ነው።
ገንዘባችሁ ....
ብዙ ሰው ነፃ እያወጣ ነው።
#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu