ቀኑ ጁሙዓ ነው!
ከቀናት ሁሉ ቁንጮ የሆነው ጁሙዓ!
በዚህ ቀን አደም [ዐሰ] ተፈጠሩ። በዚህችም ቀን ሞቱ።
በዚህችም ቀን ጥሩምባይቱ ትነፋለች! ቂያማ ይቆማል።
የልብ ትርታ በሆኑት፤ የልቅና መላቅ ምክንያት ላይ ሰለዋትን አብዙ።
እርሳቸው ሰለዋታችሁ ይቀርብላቸዋል።
ጁሙዓ ሙባረክ!
የጁሙዓ ሰደቃችሁን ከዚህ በፊት በፖሰትነው ሰደቃ ላይ ብታውሉ ደስ ይለናል።
.
@Fuadmu

አውፍ በሉኝ!
(ፉአድ ሙና)
.
በሶሻል ሚዲያ የማውቃችሁ ወይም የምታውቁኝ ወንድም እና እህቶቼ በፅሁፎቼ ውስጥ ሳላውቀው አስከፍቼያችሁ፣ ወደ ወንጀል ከትቼያችሁ አሊያም ስሜታችሁን ጎድቼ ከሆነ ለአላህ ብላችሁ .... ለይቅር ባዩ ጌታችሁ ስትሉ አውፍ በሉኝ።
ምናልባት በአካልም ያስቀየምኩት ካለ ለአላህ ሲል አውፍ ይበለኝ። በእርግጥ በአመታት ውስጥ የሰው ልጅ የአስተሳሰብም ሆነ የብስለት ሁኔታ ይለወጣል። ነገራቶችን የምንረዳበትም ሁኔታ ይቀየራል።
ምን አልባት የተመፃደቅኩበትም ካለ....
በንፅህናዬ ውስጥ የእርሱን ቁሸት ልነግረው የቃጣኝ ...
ሙሉ መስዬ ያጎደልኩት...
ሁላችሁም ለአላህ ብላችሁ ይቅር በሉኝ። ይቅርታችሁ ያስፈልገኛል።
ما زاد الله عبدًا بعفو إلا عزًّا
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ

አይጠሩንም ወይ?
(ፉአድ ሙና)
.
አሰላሙ አለይክ
የኔ ተናናሽ፣ የኔ በሻሻ፣
አይጠሩንም ወይ
ባልጠና ኢማን፣ መምጣት ብንሻ?
አላህ ሲፈጥርዎ
ሁቦን ለኢማን፣ ከትቦታልና፣
የጀነት መንገድ
ያለርስዎ ፍቅር፣ ማልዶ ቢጠና፣
አይጠሩንም ወይ
ልባችን ቢያስብ፣ ከና`ዳፋችን፣
እርስዎን ዘይረን
ብትነሳልን፣ ሙቷ ቀልባችን።
አሰላሙ አለይክ
የተሸሁድ በር፣ የኛ ልቅና፣
በሰላምታዎ
ወንጀል አሰራይ፣ ጭንቅ አባ ከና!
የጠይባ ሩኋ
መግለፅ ያቃተው፣ የሸውቅ ስሙ፣
እርስዎን መናፈቅ
ሽተናል እኛም፣ አርሒብ ታተሙ።
ግቡባት ልቤን
እንደው ቢያሰራት፣ ናፍቆትዎ ደጉ፣
እንደ አፍቃሪዎ
እንደው ብትበጅ፣ ለኸይር ጉጉ።
አሰላሙ አለይክ
ጦይባ ተቀምጦ፣ ልብ ኮርኳሪ፣
በሰለዋቱ
ልቅና አልባሽ፣ ፅዱ ሰው ሰሪ።
አባ አይጠየፍ
የአረብ የአጀሙ፣ የደሀው ጌታ፣
ሰው አስተካካይ
ሁሉን አቅራቢ፣ በአንድ ገበታ፣
የዱንያ ምክንያት
ስስተ ሰሀባ፣ የጌታው ውዱ፣
አይጠሩንም ወይ
ሊያቋድሱን፣ ከኢማን ማዕዱ።
አሰላሙ አለይክ
ንጉስ ሲጠፋ፣ ባለንግስና፣
በዚህም በዚያም
የእፎይታ ምንጭ፣ የደስታ ዋና።
ማፍቀርን ስተን
ከሁብዎ ከስተን፣ ብንወላውልም፣
እግራችን ቢሳብ
መንገድዎን ይዞ፣ እንደው ቢዝልም፣
እንደ አፍቃሪዎ
በሁብ መክነፍ፣ እኛም ናፍቀናል፣
እኛ ዝግጁ
እርስዎ መች አሉ? መች ይጠሩናል?
ናፍቆት ናፍቆናል!
ጀንበር በነጋች፣ ጠሀይ በወጣች፣ ጥንካሬዋ በተለዋወጠ፣ ባዘቀዘቀች፣ ጨረቃ በወጣች፣ በጎደለችም በሞላች፣ ኮከቦች ባበሩ፣ ከዋክብት በተወረወሩ፣ ሰማይም በጠራች፣ ከጀንበር በተገናኘች ጊዜ ሁሉ የአላህ ሰላትና ሰላም በአለማት እዝነት ላይ ይውረድ።

ተወለደ!
(ፉአድ ሙና)
.
ተወለደ ... የህይወት ቅመም... የናፍቆት ጌታ... የመወደድ ፅንፍ ... የአለማት እዝነት ... የጀነቴ ሸምጋይ ... ተወለደ!!!
አላህ ልቅናውን ሊያሳየን ሰላምታውን ከራሱ ጀመረ። በመላዕክቶቹ አስቀጠለ። በእኛም ላይ ትዕዛዝን አወረደ።
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ (አህዛብ፣56)
ተወለደ ... የከውኑ ሰበብ ... የፅልመት ጎህ ... የፍትህ ጀምበር ... የደካማዎች ብርታት ... የኸዲጃ ፍቅር ... የአዒሻ ቅናት ... የቢላል ሞገስ ... ተወለደ!!
የተወለደው ነብይ የአለም ፅልመት ኑር ነበር። ከአሚናት ማህፀን የፈነጠቀ የፍቅር ብርሀን! ድባቴና ፅልመት የወረሰውን አለም በብርሀኑ ያበሰ ... ያፈካ ነብይ ነበር። ጌታው የወደደውን መልዕክተኛውን ብርሀን ሲል ገለፀው።
قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ
ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (ማኢዳ፣ 15)
የተወለደው ነብይ ... እዝነት ነው። የአለማት ጋሻ! ኡመቴን ኡመቴን የሚል አልቃሻ! እንደው መንሰቅሰቁ ቢከፋበት ጌታው «ሙሀመድ ሆይ! በህዝቦችህ ጉዳይ አናሳዝንህም! (እናስደስትሀለን)» ብሎ ያባበለው ነብይ ነው። የኛ ሙሀመድ [ሰዐወ] .... አልቃሻው ነብይ!
ተወለደ ... የነብዩሏሂ ሙሳ [ዐሰ] እንባ ... የነብያት ኢማም ... በእርሱ ጋሻ ስር አለማትን ያስጠለለው ነብይ ... የእዝነት ምንጭ... የርህራሄ ጀሰድ... ተወለደ!
ጌታው ደረጃውን ሲነግረው ... «ሙሀመድ ... አንተ ደጉ ሰው... ባንተ ውስጥ እኮ የፍጥረተ ዓለሙ እዝነት አለ።» አለው።
وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ
(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም፡፡ (አንቢያ፣ 107)
ተወለደ ... የናፍቆት ሩህ... ለበዳዮቹ የሚያነባው ነብይ... የፍቅር አይነ ውሀ ... የሀውድ አለቃ... የጀነት ጥፍጥና... ተወለደ!
አላህ ደረጃውን ቢያልቀው ... የነካው ሁሉ እንዲባረክ... የወደደው ሁሉ እንዲወደደ ሆነ። የአላህ መውደድ ጅምላ አከፋፋይ አደረገው። የአላህ ፍቅር ማግኛ መንገድ ሆነ።
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» (ኢምራን፣ 31)
ተወለደ ... የአረቢያን ምድር አሸዋ እየጫረ ... ሰውነቱ በእንባ ሳግ እየተቆረሰ ... «ወንድሞቼ ናፈቁኝ» ... ያለልን ነብይ... ተወለደ!
ሳያዩኝ ያመኑብኝ ወንድሞቼ ናፈቁኝ ያለላቸው ህዝቦቹ ሆድ እንዳይብሳቸው፤ በእርግጥ የምስራች ተበሰረ። ነብያቸው የሞት ግርዶ እንዳይሸፍነው ሆኖ ላቀ።
وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ ۚ
በውስጣችሁም የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ፡፡ (ሁጁራት፣7)
ኸበሩ በሌላም አንቀፅ ቀጠለ።
وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمْ وَأَنتَ فِيهِمْ ۚ وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ
አላህም አንተ በውስጣቸው እያለህ (ድንጋይ በማዝነብና ባሳማሚ ቅጣት) የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ (አንፋል፣ 33)
ጀሰዱ ብትለየንም ... ናፍቆታችን ሁሌም በቀብሩ ውስጥ ህያው ነው! ለዚያም ሲባል በመስጂዱ ዙሪያ አሁንም በህይወት እያለ እንደታዘዝነው ድምፃችንን ዝቅ እናደርጋለን።
አንዱ አዕራቢይ ጀነት ውስጥ ምን አለ ሲባል «የአላህ መልዕክተኛ» እንዳለው ... በእርሷ ውስጥ አንቱ ያሉባትን ጀነት እንመኛለን።
ተወለደ!!!!!

ነገረ ረቢዕ!
(ፉአድ ሙና)
.
ረቢዕ ሲመጣ ሁለት ስል ብዕሮች ይመዘዛሉ። አንዱ ነብያችንን [ሰዐወ] ለማወደስ ሌላው ደግሞ በነብዩ የውዳሴ ፖስቶች ስር የኡመርን [ረዐ] ሀዲስ ለመኮመት!
እስኪ ነገሩን በስክነት እንመልከተው። ረቢዕ ላይ ነብዩን [ሰዐወ] አብልጦ ማስታወሱ መውሊድን ከማክበር ጋር የሚያያይዘው ምንድነው? ረቢዕ አስራ ሁለትን እንደ ኢድ መደገሱን ምናምን እንተወውና እስኪ ረቢዕ ላይ ነብዩን [ሰዐወ] ማውሳት ላይ ብቻ እናውጋ!
በአንድ አጋጣሚ ከኢትዮጵያ ውጪ አንድ ሀገር ላይ ተገኝቼ ነበር። የከተማው መስጂድ ውስጥ የተብሊግ ጀመዓ አለ። የመስጂዱ አስተዳደር እና ኢማም ደግሞ ሱማሌ ሰለፊይ ናቸው። መቻቻላቸውን እያሰብኩ ተደንቄ ሳልጨርስ ረቢዕ ደረሰ። እንዴት ይሆኑ ይሆን ብዬ ስሰጋ ጭራሽ ለእልህ ይመስል ረቢዕ 12 ጁሙዓ ቀን ገጠመ።
ኢማሙ እንደ ሀገሬ ሰለፊዮች ስለ ቢድዓ ይኾጥባል ብዬ ጠብቄ ነበር። ግን ጭራሽ «ዉሊደል ሙስጠፋ» ብሎ ጥግ በደረሰው የአረብኛ ግጥም ችሎታው ኹጥባውን አደመቀው። እሱ መውሊድ የሚያከብር ሰው አይደለም። ግን ደግሞ ሁሌም ከታሪክ ጋር የሚገናኝ ነገር ሲኖር ለመኾጠብ እንደማያመነታው ረቢዕ ነው ብሎ አልሰጋም።
እናም የሀገሬ ሙስሊሞች ችግርም እልህ እንጂ ዲን አይመስለኝም። አሹራ ላይ ስለ ሙሳ ስንፅፍና ስንገጥም እንደነበረው ረቢዕም የነብያችን [ሰዐወ] ውልደት የተሰነደበት ወር ነውና ስለ እርሳቸው እንባክናለን። ለማንም ከምንሆነው በላይ እንሆናለን። ይኼ ደግሞ መውሊድ ከማክበርና ካለማክበር ጋር የሚያያዝ አይመስለኝም።
ሌሎች መውሊድ ያከብራሉ ብሎ በዚህ ልክ ረቢዕን ማባከን አግባብ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? አክባሪውም ያክብር የማያከብረውም ታሪኩን እያሰበ ያሳልፍ! ምንም የሚያጋጭ ነገር የለውም። በበኩሌ ነገሩ የፊርቃ ኡስታዞች እልህ እንጂ ዲን አይመስለኝም።
እስኪ እናንተም ሀሳባችሁን በጨዋ አማርኛ አካፍሉን።
ማስታወሻ: ‐ ለባለጌ ቦታ የለንም።

ኑር
(ፉአድ ሙና)
.
የጌታው ምስጉን
የአምላኩ ምርጫ፣
ስሙን
ቢለኮስ ጊዜ
የውልደቱ ችቦ፣
ጣዖቱን ሁላ
የጣለው ሰልቦ።
የነቀለልን
የኢብሊስን ዙፋን፣
እሱ ታላቅ ነው
እኛ መች ጠፋን!
የአላህ ሰላት እና ሰላም በጭንቁ ቀን አማላጅ፣ በጠላቶቹ ወዳጅ፣ በሰላሙ በሚያቀና፣ በጦር ቀኑ ጀግና፣ በውዱ ነብይ ላይ ይስፈን!
.
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
የጌታው ምስጉን
የአምላኩ ምርጫ፣
ስሙን
ማይጠራው
ያለቁልምጫ፣
ወስዶ ያቆመው
ኢማም አድርጎ፣
ከነብያቶች
ደረጃው ልቆ።
ገና ሲወጣ
ከአሚናት ማህፀን፣
ሱጁድ አድርጎ
ጌታ
ሚማፀን።ቢለኮስ ጊዜ
የውልደቱ ችቦ፣
ጣዖቱን ሁላ
የጣለው ሰልቦ።
የነቀለልን
የኢብሊስን ዙፋን፣
እሱ ታላቅ ነው
እኛ መች ጠፋን!
የአላህ ሰላት እና ሰላም በጭንቁ ቀን አማላጅ፣ በጠላቶቹ ወዳጅ፣ በሰላሙ በሚያቀና፣ በጦር ቀኑ ጀግና፣ በውዱ ነብይ ላይ ይስፈን!
.
@Fuadmu
ድህነቴዋ
(ፉአድ ሙና)
.
ገና በልጅነት
መጎተት ሙስበሀ፣
ገና በጠዋቱ
መርጠብ በውዱ
የክብሯን ቂሳ፣
ምሎ `ሚነግራት
ሴት ሰው ነች ብሎ፣
አልነበራትም
የአባት ባተሎ።
ዛሬ ላይ አድጋ
ነቢ ትላለች ነቢ አባቴ፣
ዋስ መከታዬ
የህይወት ስልቴ!
ነቢ ትላለች
እያዘነበች የናፍቆት እንባ፣
ምን ይቆርጠዋል
በነቢ ናፍቆት፣ ሆዷ ሲባባ?
የቲም ናት...
«ነቢዋ ውዴ
ነቢ አባቴ፣ የመኖር ፍርዴ፣
ናፍቆትዎ ፈጀኝ
እንደው በመናም፣ ባየሆት አንዴ!»
ይኼ ነው ቃሏ
የሚደገመው ከመስገጃዋ፣
አባት አታውቅም
ነቢ አባቷ፣ ነቢ ነብይዋ!
የአላህ ሰላት እና ሰላም በሴቶች ጠበቃ፣ በየቲሞች ከለላ፣ በውዱ ነብይ [ሰዐወ] ላይ ይስፈን!
.
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
ገና በልጅነት
መጎተት ሙስበሀ፣
ገና በጠዋቱ
መርጠብ በውዱ
ውሀ።
አባ ሲል ተርታ ሰው
አባ ማለት ረስታ፣
ሰለዋት ጀመረች
መስገጃ ላይ ወጥታ!
በእርግጥ አባ ትለው
ሞቷታል አባቷ፣
በነብዩ ነበር
በህይወት መቅረቷ።
ከቀብር አፋፍ ላይ
ሲያዘጋጇት ለለህድ፣
ህይወቷ የተረፈ
በነብይዋ መፍረድ!
ለሞት ሲያሳጫት፣
ደርሶ ሴትነቷ፣
ትንፋሿ ሲታፈን
ሲስተጓጎል ምቷ፣
ደርሰው ቢያነሷት
ህይወቷ ከበረ፣
ያለ ነቢ አታውቅም
አባት ምን ነበረ?
የቲም ናት...
አልነበራትም
አቅፎ የሚያነሳ፣
ነግሮ
ሚያሳድግየክብሯን ቂሳ፣
ምሎ `ሚነግራት
ሴት ሰው ነች ብሎ፣
አልነበራትም
የአባት ባተሎ።
ዛሬ ላይ አድጋ
ነቢ ትላለች ነቢ አባቴ፣
ዋስ መከታዬ
የህይወት ስልቴ!
ነቢ ትላለች
እያዘነበች የናፍቆት እንባ፣
ምን ይቆርጠዋል
በነቢ ናፍቆት፣ ሆዷ ሲባባ?
የቲም ናት...
«ነቢዋ ውዴ
ነቢ አባቴ፣ የመኖር ፍርዴ፣
ናፍቆትዎ ፈጀኝ
እንደው በመናም፣ ባየሆት አንዴ!»
ይኼ ነው ቃሏ
የሚደገመው ከመስገጃዋ፣
አባት አታውቅም
ነቢ አባቷ፣ ነቢ ነብይዋ!
የአላህ ሰላት እና ሰላም በሴቶች ጠበቃ፣ በየቲሞች ከለላ፣ በውዱ ነብይ [ሰዐወ] ላይ ይስፈን!
.
@Fuadmu
بلغ العُلا
(ፉአድ ሙና)
.
ሰውነት ፋይዳ ያገኘው በእርስዎ ነው። የእርስዎ መገኘት ባልተፈጠረ የመኖር ትርጉም ጣዕም አልባ ነው። ስምዎን ስንሰማ የሚታገለን ሳግ ባልኖረ ለህይወት መጓጓት ምንም ነው።
እስልምናን ታግለን ያገኘን አይደለንም። ስለእምነትዎ እርስዎ እንደተወገሩት የሚወግረንን ችለን የተቀበልነው እምነት አይደለም። በአላህ ችሮታ ደም ሳይፈሰን በተፈጥሮ እምነታችን ላይ ቀጥለናል። ምናልባት የእኛንም መወገር ስለተወገሩት ይሆናል። መሰደብን ሁሉ እርስዎ ላይ ስላዘነቡም....
እንደ ሰልማን [ረዐ] ትክክለኛውን እምነት ፍለጋ አስር ጊዜ በባርነት አልተሸጥንም። እንደ አብዱላህ ዙል ቢጃደይን [ረዐ] ስለ እስልምና ሀብታችንን ተቀምተን በጆንያ አልተጠቀለልንም። እንደ አባታችን እንደ ቢላል [ረዐ] የባላባት አለንጋ እየሞሸለቀን አሀድ አሀድ አላልንም። እንደ ሰውባን [ረዐ] ከአይናችን ሲጠፉ ናፍቆትዎ በሽተኛ አላስመሰለንም። ግን ናፍቆትዎን እንናፍቃለን። በስምዎ ሀሴት እናደርጋለን።
ይህ ሁሉ የኢስላም ስኬት ከስምዎ ጋር የተቀራኘ ነው። አላህ ወዶ አስወደደዎ! የኛ ላኢላሀኢለሏህ የእርስዎ ድንጋይ ማሰር ውጤት ነው። ለእኛ እምነት የእርስዎ ጥርስ መሰበር ክፍያ ነው። ሚስኪኑ ነብይ!
እንደው ደግነትዎ ግዘፍ ቢነሳበት ሰብዓዊነትዎ ቢያስደንቀው ይመስለኛል ገጣሚው የእርስዎን ጉዳይ እንዲህ ሲል የገለጠው: ‐
بلغ العُلا بكمالـــــــهِ
كشف الدُجى بجمالـهِ
حَسُنت جميعُ خصالهِ
صَلُّوا عليه و آلــــــهِ
በምሉዕነት
ላይ የታከከው፣
ውበቱ ፅልመት
የገሸለጠው፣
ያማረችለት
ሙሉ ተፈጥሮው
ይውረድ ሰለዋት
በርሱም በአህሉ!
ቢፅፍዎት ቢያወድስዎት ህመም መቀስቀስ እንጂ ከልብ እንኳን አያደርስም! የካዝናው ባልተቤት ምንዳዎን አብዝቶ ይክፈልልን! አንቱ የጀነት ጌጥ!

ሩሂ
(ፉአድ ሙና)
.
የእርስዎ አይነት መልካም በአይኔም አላለፈ፣
ከእንስት መሀፀን አንቱን መሳይ ቆንጆ ከቶ አልተፀነሰ፣
ተፈጥረዋል ጠርተው ከነውሩ በሙላ፣
እንዳሹት ይመስላል፣ ፍጥርጥርዎ ሁላ።
በምስሉ ላይ የተያያዘው የሀሰን ኢብኑ ሳቢት(ረዐ) ግጥም ውርስ ትርጉም ነው።
እስኪ ውዳችንን የሚያወድሱ የምታስታውሷቸውን ግጥሞች ኮመንት ላይ አስፍሩ።
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉላህ!