ትዝ ይላችኋል?
በጎደሉ አሉ ጅማ ዞን ሳኮሩ ወረዳ 2015 ላይ ያስቆፈርነው የመጀመሪያው የውሀ ጉድጓድ ትዝ አላችሁ?
ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለመመልከት ወደ ቦታው ተጉዘን ነበር። ገንዘባችሁ ከሁለት ዓመት በኋላ ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ ይመስላችኋል።
አልሀምዱሊላህ በደንብ እየሰራ ነው።
ሊንኩን በመጫን የጉዟችንን ቪዲዮ ተመልከቱ።
https://vm.tiktok.com/ZMk5GQEPQ/

TikTok
TikTok · Ifada Islamic Organization
797 likes, 92 comments. “ከአዲስ አበባ ወደ ጅማዋ ዞን ወረዳ ሶኮሩ ተጉዘን ከሁለት ዓመተ በፊት በጎደሉ አሉ ፕሮጀክት የተገነባ የውሀ ጉድጓድ ያለበትን ሁኔታ ገምግመናል።”
የኔ ሰው
(ፉአድ ሙና)
.
መቶ ብር ለታክሲ
ሀምሳ ለማስቲካ፣
ካፌ ተሰብስቦ
ሞኝ ሲያውካካ።
መቶ ብር ለጀነት
አለች እጅ አውጥታ፣
ካፌ ትሰጣበት
ጊዜ መች አግኝታ።
መቶ ብር ለጀነት!
አይኗን አውቀዋለሁ
አያይም ደግ እንጂ፣
ጥርሷን አውቀዋለሁ
ነጭ የፍቅር ፈንጂ!
ሰለዋት ተሞልቶ
አይገዳትም ሆዷ፣
የጀነት ስራ ነው
የህይወት መንገዷ!
መቶ ብር ለጀነት!
የታሸገ ውሀ
ብትጠጣም አማርጣ፣
ጭንቀቷ ላጣው ነው
ይህን የሪዝቅ እጣ!
ያብሰለስላታል...
እንቅልፍ ይነሳታል...
የወንድሟ ጥማት
የእህቷ መደፈር፣
በጠብታ ውሀ
የሚስኪኑ መክፈር።
ያማታል ቆንጆዬን
እንቅልፏስ መች መጥቶ፣
ከጀነት ሲጨለፍ
ሰው ደጋፊ አጥቶ።
ያስነባታል በጣም!
መቶ ብር ለጀነት!
ገረፋት የሰው ፊት
ብታደገው ብላ፣
ሺህ ሰው ረገጠው
ያንን ቅዱስ ጥላ።
መቶ ብር ለጀነት
ትላለች የኔ ሰው፣
ኩፖኗን ይዛ ነው
`ምትመላለሰው።
መቶ ብር ለጀነት!
በቆሻሻ ውሀ
በሽታ እየጠጣ፣
ህይወቱ ለሚያልፈው
ህክምና እያጣ!
ያ ረቢ ለሚለው
ገጠር ተቀምጦ፣
እንዳይጫንበት
እንዲያምን መርጦ!
ትሽከረከራለች
ከኩፖኗ ጋራ፣
ወትሮም አንደኛ ናት
ለጀነት ሰው ስራ!
መቶ ብር ለጀነት!
መቶ ብር ለኔ ሰው፣
ፊት እየገረፋት
ኩፖኖቿን ሸጣ ለምትመለሰው!
***
መታሰቢያነቱ
በየገጠሩ የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ኩፖን እየሸጡ የሰው ፊት ለሚገርፋቸው ኢፋድዮች ይሁንልኝ! የኔ ሰው እናንተ ናችሁ!
.
@Fuadmu

ከ2 ዓመታት በፊት ሀረማያ ላይ ያስቆፈራችሁት የውሀ ጉድጓድ ያለበትን ሁኔታ ለማየት ተጉዘን ነበር። የጉዟችንን ቪዲዮ በሊንኩ ተከታተሉ።
https://vm.tiktok.com/ZMkQeqnAS/
https://vm.tiktok.com/ZMkQeqnAS/
TikTok
TikTok · Ifada Islamic Organization
652 likes, 117 comments. “#creatorsearchinsights #islamic_video #islamic #yourpage #ethiopianmuslim #charity #fyp #ifada ”
ሀረማያ ተገኝተን 2015 ላይ በጎደሉ አሉ ፕሮጀክት የተቆፈረውን ሌላኛውን የውሀ ጉድጓድ ጎብኝተናል። ቪዲዮውን ተከታተሉ።
https://vm.tiktok.com/ZMkQx3jSa/
https://vm.tiktok.com/ZMkQx3jSa/
የሙዕተሲሙን ጉድጓድ የደረሰበትን በቦታው ተገኝተን ገምግመናል። ተከታተሉትማ!
https://vm.tiktok.com/ZMkCscbp6/
https://vm.tiktok.com/ZMkCscbp6/
ወደ ቲክቶክ ላይቭ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻችን ተቀላቀሉ። በሰደቃ ቋንቋ እናውራ!
https://vm.tiktok.com/ZMkCcdC3J/
https://vm.tiktok.com/ZMkCcdC3J/
ውሀ የሌለባቸውን ገጠራማ አካባቢዎች ውሀ ለማዳረስ የጎደሉ አሉ ብለን ፕሮጀክት ከጀመርን ቆየን!
በጅማ ሳኮሩ ወረዳ አንድ የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሐረማያ ሁለት የውሀ ጉድጓዶችን አስቆፈርን።
በመሀል እስረኞችን ነፃ በማውጣት የጎደሉ አሉ ሁለትን አካሂደን ነበር።
አሁን ሰዓቱ የውሀ ነው። የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!
አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!
መልካም ሰኞ!

ከመክበር በር ላይ!
(ፉአድ ሙና)
.
ጊዜው በረታ ..... የአይናቸው ማረፊያ ኸዲጃን እና ከለላ አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ቀበሩ። የመካ ሰዎች ነገር ከቀን ወደ ቀን ቢጠናቸው፤ ነብይ በሀገሩ አይከበርምና የሌላ ቀዬ ሰዎች ከተመለሱልኝ ብለው ወደ ጧዒፍ ከዘይድ ኢብኑ ሀሪሳ ጋር ተጓዙ።
ከጧዒፍ ቀዬ ቆሙ .... እኒያ የልቀት ልክ ... ለአይን የሚታፈሩ ነብይ .... ለተላኩበት ጥሪ ሲሉ የጧዒፍ መሪዎችን ተዋደቁ። እናንተ የጧዒፍ ሰዎች ሆይ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ወዲያ በሉና የአላህን አንድነት አውጁ ሲሉ ለፈፉ። የጧዒፍ ሰዎች በእጄ የሚሉ አይነት አልነበሩም። ይልቁንስ የተከበረውን ነብይ እና ዘይድ ኢብኑ ሀሪሳን በድንጋይ ይወግሯቸው ገቡ። ህፃናት እና እብዶቻቸውን አሰማሩባቸው። ከውዱ ነብይ ገላ ደም ፈሰሰ። ጫማቸው በደም ሞላ። ዘይድ በቻለው አቅም ከለላ ሊሆናቸው ይሞክራል። በዚህ መልኩ ከጧዒፍ ከተማ ለቀው ወጡ። ተደብድበው .... ተዋርደው .... ጧዒፍን ለቀቁ።
ከጧዒፍ ወጣ እንዳሉ መልዕክተኛው በተሰበረ ልብ ወደ ጌታቸው ተጣሩ።
«اللهم إليك أشكو ضعف قوتي، وقلة حيلتي، وهواني على الناس، يا أرحم الراحمين، أنت رب المستضعفين، وأنت ربي، اللهم إلى من تكلني؟ إلى بعيد يتجهمني، أم إلى عدو ملكته أمري؟ إن لم يكن بك غضب علي فلا أبالي، غير أن عافيتك أوسع لي، أعوذ بنور وجهك الذي أشرقت به الظلمات، وصلح عليه أمر الدنيا والآخرة، أن ينزل بي سخطك، أو يحل علي غضبك، لك العتبى حتى ترضى ولا حول ولا قوة إلا بالله
አላህ ሆይ! የአቅሜን ደካማነት፣ የዘዴዬን ማነስ፣ በሰዎች ዘንድ መዋረዴን ወደ አንተ አቤት እላለሁ! አንተ የአዛኞች አዛኝ የሆንክ ጌታ ነህ! አንተ የደካማዎች ጌታ ነህ! አንተ ጌታዬ ነህ! አላህ ሆይ ወደማን ታስጠጋኛለህ? ፊቱን ወደሚያጨፈግግብኝ ባዕድ ወይስ በጉዳዬ ላይ ስልጣን ለሰጠኸው ጠላት? አንተ ካልተቆጣህብኝ ግድ የለም። ግን ከአንተ የሆነ ጤንነት እና ደህንነት ለኔ በጣም ሰፊ ነው። የአንተ ቁጣ እንዳይወርድብኝ ጨለማዎች በበሩበትና በሱ ላይ የአዱንያና የአኼራ ጉዳዮች በተበጁበት በፊትህ ብርሀን እጠበቃለሁ። እስከምትወድልኝና እስከምትቀበለኝ ድረስ ስሞታዬን ለአንተ አቀርባለሁ። በአንተ እንጂ ዘዴም ሆነ ኃይል የለም።»
ከዚህ ዱዓ በኋላ የአላህ መልዕክተኛና ባልደረባቸው ወደ መካ ጉዟቸውን ቀጠሉ። መልዓኩ ጂብሪል (ዓሰ) ወደ ነብያችን በመምጣት «ሙሀመድ ሆይ ህዝቦችህ ያሉህን ጌታህ ሰማ፣ ማስተባበላቸውንም አየ! ጌታህ የተራራ መልዓክትን የምታዛቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ወዳንተ ልኳል!» አላቸው።
የእዝነት ተምሳሌቱ ነብይም «ከልጅ ልጆቻቸው እንኳን ቢሆን አላህን በብቸኝነት የሚገዛ ይወጣ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።» ሲሉ የእልቂቱን ደመና አነሱ። ላደማቸው .... ለደበደባቸው .... ላዋረዳቸው ህዝብ ምላሻቸው ይህ ነበር። የአላህ ሰላት እና ሰላም በእዝነተ ሰፊው ነብይ ላይ ይሁን!
ወደ መካ ሲደርሱ በሀገሩ ከለላ የላቸውምና ቁረይሾች እንደሚገድሏቸው ገባቸው። በጃሂሊያ ጊዜ የነበረ ውብ ባህል ነበራቸው። ከለላ መስጠት! የአለሙ ጌጥ ከለላ ይሰጧቸው ዘንድ ሶስት ሰዎች ጋር መልዕክት ላኩ። ሁለቱ አሻፈረኝ ቢሉም ሙጥዒም ኢብኑ አዲይ ጥሪውን መለሰ። ልጆቹን አስታጥቆ ውዱን ነብይ አጅቦ ወደ መካ አስገባ። ነብያችን የበድርን ጦርነት ካሸነፉ በኋላ ይህን ሰው አውስተዋል። «ሙጥዒም በጠየቀኝ ምርኮኛዎችን ሁሉ በፈታሁለት ነበር!» ብለዋል። ነገር ግን ሙጥዒም ከበድር በፊት ወደማይቀርበት ወደ ቀጣዩ አለም ተጉዞ ነበር።
ከጭንቅ በኋላ ብስራት እንዳለ ለዓለም ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ አላህ (ሱወ) በረጀብ በ27ኛው ለሊት የኢስራዕ ወል ሚዕራጅን ድግስ አሰናዳላቸው። ምድር ላይ በሰው ከተዋረዱ በኋላ ሰማይ ላይ ወስዶ አከበራቸው። ቡራቅን ተጭነው «ሀዬ» እያሉ ከጅብሪል ጋር በምድር ወደ መስጂደል አቅሳ ጋለቡ። ቡራቅ የሚሉት ጉድ አይኑ ማየት የሚችለውን ያህል በብርሀን ፍጥነት ይራመድ ነበር። አላህም በኢስራዕ ምዕራፍ ገድሉን ዘከረ።
«سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡»
(ኢስራዕ፣ 1)
ጧዒፍ ላይ በድንጋይ የተደበደቡት ነብይ በተቀደሰው ቤት ነብያትን ኢማም ሆነው አሰገዱ። ከዚያም ሚዕራጅ ተከተለ። ከጅብሪል ጋር ጉዞ ወደ ሰማይ ቤት! በየሰማዩ የተለያዩ ነብያትን እያገኙ ወደ ሲድረተል ሙንተሀ አቀኑ።
«مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَى๏أَفَتُمَارُونَهُ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ๏ وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ๏ عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ๏ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ๏ إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ๏ مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ๏ لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም። ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡»
(ነጅም 11 –18)
በዚህ ጉዞ ሲድረተል ሙንተሀ ላይ ሲደርሱ ጅብሪልን በተፈጠረበት ቅርፅ ተመልክተውታል። ከጌታቸው ጋር አውግተውም ሰላትን እና የላሚቷን ምዕራፍ የመጨረሻ አንቀፆች ተቀብለዋል።
ውዱ ነብይ ወደ ምድር እንደተመለሱ ይህንን ተዓምር ተናገሩ። ሰው ይሳለቅ ገባ። ጭራሽ በአንድ ለሊት ከመካ በይተል መቅዲስ ድረስ ዘለቅኩ፤ ወደ ሰማይም አረግኩ አለ ብለው ተሳለቁ። ይህ ወሬ የአቡበከር ጆሮ ደረሰ። «እርሱ ይህን ብሏል?» ሲሉ ጠየቁ። «አዎን ብሏል!» የሚል ምላሽን አገኙ። «እንግዲያማ ብሎ እንደሆን እውነቱን ነው።» ሲሉ ተቀበሉ። ሲዲቅ የተባለውን ማዕረግ ያስገኛቸው ይህ ነበር። «ከሰማይ መልዕክት ይመጣልኛል ሲለኝ ያመንኩትን ሰው ወደ ሰማይ ሄድኩ ቢለኝ ምን ይገርመኛል።» ሲሉ እምነታቸውን አረጋገጡ።
ከነብዩ የኢስራዕ ወል ሚዕራጅ ጉዞ አንድ ትልቅ ትምህርት እንማራለን። ከችግር በኋላ በእርግጥ ድሎት አለ።
«ምንድን ቢከፋህ
የበደል በትር፣ ቢያሳጣህ አቅም፣
አደራ አስታውስ
ከሚዕራጅ በፊት፣ የጧዒፍ በደል እንደሚቀድም! »
በአለማቱ ጌጥ .... በክብራችን መሰረት .... በእዝነቱ ቁንጮ .... በመወደድ ሚዛን .... በድሀው ነብይ ላይ የጌታው ሰላት እና ሰላም ይውረድ!

የኢፋዳ መፅሀፍ የመጨረሻ የቅናሽ ሽያጭ!
ኢፋዳ መፅሀፍም በ20% ቅናሽ 400 ብር @ifadasales ላይ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
ፒካፕ ሎኬሽን ላይ የቀሩን መፅሀፍት ከ50 አይዘሉም። ፈጥናችሁ የራሳችሁ አድርጓቸው።
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@ifadasales

ወደ ራሳችን ስንመለስ!
.
ለኡሚ 10,553 ብር አስተላልፈናል። አሁን ወደ ውሀ ጉድጓድ ዘመቻችን እንመለሳለን። የጎደሉ አሉ 3 በኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር አባላት በኩል 7.6 ሚሊየን ብር የተሰበሰበበት ፕሮጀክት ነው።
ሆኖም የጎደሉ አሉ 1 ፕሮጀክት የመጀመሪያ ፈንድ አድራጊዎች እዚህ ላይ ያላችሁ ውድ አባሎች ነበራችሁና በዚህ ቻናል ቤተሰቦች ስም አንድ ጉድጓድ ማስቆፈር አለብን።
እስካሁን የ29 ጉድጓድ ገንዘብ ተሰብስቧል። የእኛ 30ኛው መሆን አለበት።
100ሺህ ብር ደርሰናል። አሁን የቀረንን ገንዘብ ለመሙላት እንጣር! እንደተለመደው በአላህ ፈቃድ አንድ ላይ እንችላለን!
አካውንት @fuadmuna ላይ ውሰዱ!

ከተዉሽኝ በኋላ
(ፉአድ ሙና)
.
ካጣሁሽ በኋላ ፣ አንቺን ከተለየሁ፣
መወደድ ሚገባዉ ፣ ሌላ አካልን አየሁ።
ሰርክ ስለዉበትሽ ፣ስለፍፍ እንዳልኖርኩ፣
ፀባየ ሸጋ ናት፣ ብዬ እንዳልተናገርኩ፣
ከጠዋት እስከ ምሽት፣ አንቺን እንዳላሰብኩ፣
ካጣሁሽ በኋላ ፣ሌላ አካል አፈቀርኩ።
እሰይ ተቃጠዪ!!
.
ሊያዉም ካንቺ የላቀች፣ ለሁሉም የምትበጅ፣
የልብ ሰላም ሆና፣ ለህይወት ምትመች።
በደንብ ተቃጠዪ!!
.
ደሞ እኮ የሚገርምሽ ፣ታስሬልሽ ስኖር ፍቅር ባልነዉ ገመድ፣
አይቻት አላዉቅም ፣ፍፁም በዚህ መንገድ።
ቆይ ስለሷ ተይዉ ፣ኋላ ላይ ይደርሳል፣
ልክ ማጣቴን ሳዉቅ፣ ወዴት እንደሄድኩኝ፣ ብነግርሽ ይሻላል።
በቃኸኝ ብለሽኝ ፣ልቤን ሰባብረሽዉ አንብቼ እንዳበቃሁ፣
ወደምንዉልበት ፣ወደ ካፌ አቀናሁ፣
ሰላም ናት ያቺ ልጅ ፣ ሁሌ ምን ልታዘዝ ማለት የማይደክማት፣
ከነሳቋ አለች ፣የጓደኛ ያህል በጣም የምንቀርባት፣
ወንበሩን አየሁት ፣ያንቺ ቦታ እንደሆን ሁሉም ያመነዉን፣
ያንቺን ጠረን ማግኘት ፣ሰርክ የታደለዉን።
ሳሸተዉ ወንበሩን፣ አንቺን አንቺን ይላል፣
ስትስቂ ይታየኛል ፣ ትዝታዬ ይጫራል።
ተቃጠልኩ!!
.
ደሞ ተነስቼ ያንን መናፈሻ ላየዉ እሄዳለሁ ፣ አንቺ የምትወጂዉን፣
አብረን ተቀምጠን ፣ ፍፁም ላትለዪኝ ስትምዪ የሰማዉን።
ጠወላልጓል አበባዉ ፣ ይመስላል በረሀ ነገር፣
ለካ ጥላ ሆኖ፣ ቦታዉን ያስዋበዉ ፣ ያንቺ እዛ መኖር ነበር።
ከዛም ተከዝኩና
ትናንት ሁሉ ቅዠት ፣መሆኑ ሲገባኝ፣
እዉነታዉ ከፊቴ ቆሞ ፣ሁሉንም ሲያስረዳኝ፣
ብዙ አሰብኩኝና ፣ "እምነትን" አፈቀርኩኝ፣
ፍፁም ላልለያትም፣ ለራሴ ፅኑ ቃል ያዝኩኝ።
ተቃጠዪ!!
.
"እምነት" ዉብ የሆነች ናት፣ ከቆንጆዎችም ቆንጆ፣
ልቡን ላሳመነ ሰዉ ፣ህይወትን ከእዉነት ፈርጆ።
አወይ "እምነት" ዉበቷ ፣ ማይወዳት የለም በሀገሩ፣
ፍቅሬን ተቀብላለች ፣ እስኪ ጠላቶች ይረሩ።
በደንብ እረሪ!
.
ብቻ ለማንኛዉም ፣ ትተሽኝ የሄድሽ ጊዜ እዉነታዉን አወቅኩኝ፣
"እምነትን" ወደድኩኝና ፣ወደ ጌታዬ ቀረብኩኝ።
የእዉነት ሀዋዬን እስካገኝ ፣ ለኔ በልክ የሰፋትን፣
በወጉ እስከማገባት ፣ እሱዉ ለኔ ያላትን፣
ማፍቀር ሱሴ ነዉ እና፣ ጌታዋን አፈቅራለሁ፣
ገና ያላወቅኳት ግጣሜን ፣ሰላም አኑራት እላለሁ።
ተቃጠልሽ?
.
ፍቅር ሱስ ለሆነበት ፣ ጥሩ ማብረጃ ሚሆነዉ፣
ሀዋዉን እስኪያገኝ ድረስ፣ በጌታዉ ፍቅር መዉደቅ ነዉ።
ከዛ በኋላ
ሀዋዉን ያገኘ ዕለት፣ የድርሻዋን አፍቅሮ፣
ፈጣሪን ይበልጥ ያወዳል፣ የዋለለትን ቆጥሮ።
ባለሽበት ደህና ሁኚ ፣ ትተሽኝ ሄደሽ ጠቀምሽኝ፣
የዘነጋሁትን ታላቅ ጌታ ፣ እንድታረቀዉ ምክንያት ሆንሽኝ።
ደህና ሁኚ!!