ይህች ልጅ አይፎን ገዛች።
አባቷ ሲያይ "ስልኩን ከገዛሽ በኋላ ያደረግሽው የመጀመሪያው ነገር ምንድነው?" ብሎ ጠየቃት።
እሷም "የስክሪን እና የጀርባ ከቨር/ሽፋን ገዛሁ" አለች።
"ሰው አስገድዶሽ ነው?"
እሷም "አይ" አለች።
አባቷ “ይህ አምራቹን ያስከፋል ብለሽ ታስባለሽ?” ሲል ጠየቃት
እሷም “አይ! አምራቹ እንደውም መሸፈኛ እንዲደረግ ይመክራል” አለች።
"ርካሽ እና አስቀያሚ ስለነበረ ነው የሸፈንሽው?"
"አይ አባዬ! ስልኬ ምንም ጉዳት እንዳይደርስበት እና ዋጋውን የሚቀንስ ነገር እንዳይገጥመው ነው የሸፈንኩት።"

"ሽፋኑን ሲታደርጊለት iPhoneኑ ውብቱ ቀንሶብሻል?"

"አባዬ የአዲሱ አይፎን ስልኬን ውበት እና ዋጋ ነው ጨምሮልኛል"
አባትየው ወደ ሴት ልጁ በፍቅር እየተመለከተ
“ከአይፎን ስልክሽ በጣም ውድ የሆነውን ገላሽን እንድትሸፍኚ ብጠይቅሽ ትስማሚያለሽ ልጄ?” አላት።

ዝም አለች። . . .

ተገቢ ያልሆነ አለባበስ እና ሰውነትን ማጋለጥ የሰውን ዋጋ እና ክብር ይቀንሳልና የሚያምርብንን እንወቅ።

መልካም ምሽት!

@funyhaha
@funyhaha
አብዛኛው ሰው ቤት ሲገባ የመጀመሪያው ጥያቄ......

እናቴ የታለች ❤️

ፈልጊያት ሳይሆን
በቃ ሳያት ሰላም ስለሚሰማኝ ነው።

@funyhaha
"አብሮ ማደግን ፉርሽ አደረግናት"

- አዳም ረታ



@funyhaha
Forwarded from ቀልድ እና ቁም ነገር@ (m M)
አሜራካዊው ገጣሚ ቻርለስ ቡኮቮስኪ አንድ መስመር አለው!

"ደስታ አንፈልግም ግን ሕመማችንን ቀንሱልን!" እናም.....
#አይዞን_ሁሉም_ያልፋል!

ከሳሙኤል በለጠ (ባማ)


@funyhaha
@funyhaha
አለመሳቅ እኮ ይቻላል
አለማልቀስ ነው ጭንቁ፤
የመንፈስን እንጉርጉሮ
በመንፈስ እምባ ማመቁ፤
ውስጥ ውስጡን እየደሙ
በቀቢፀ ተስፋ መድቀቁ፤
ለተስለመለመች እውነት
የደም ደብዳቤ ማርቀቁ፤
 በቅሬታ ሰደድ እሳት
ህዋሳትን መጨፍለቁ፤
አለመሳቅ እኮ ይቻላል 
አለማልቀስ ነው ጭንቁ!።

    
 
፦ ደበበ_ሰይፉ



@funyhaha
You Don't  Know When To Die, So Be Thankful For Everything And Live Today.

መቼ እንደምትሞት አታውቅም፤ ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር አመስጋኝ ሁን እና ዛሬን ኑር


@funyhaha
  🌙እንኳን ለ 1444ኛው የ ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ⭐️

@funyhaha
👫 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ !

🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ።



🔰 መጋበዣ ሊንክ : https://www.tg-me.com/hulepay_official_bot?start=r0829217253

ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ።
. . የ ተ ቀ ማ   ጩ ኸ ት . .

[ኤፍሬም ስዩም]

ያን'ምስኪን ገበሬ..
ሸመቁበት አሉ ካገር ሊያሳድዱት
ከገዳም ከደብሩ እትብቱ ካለበት፤


መሸመቁ ሳያንስ..
የወይኑን አጸድ እየነቃቀሉ
ስለወይን ፈንታ ቀጋ እየተከሉ
ካ'ባቶቹ እርስት አሳደዱት አሉ፤


መሰደዱ ሳያንስ..
ከትብቱ ተነቅሎ ከቤቱ ቀዬው
የምስኪኑን በደል ጩኸቱን ቀምተው


“የገበሬው ስደት ከየት እስከ የት ነው..”

  የሚል መፅሀፍ ጽፈው
ይሸጣሉ አሉ ገብያ አውጥተው!።




    @funyhaha
አይኔን ሁሉ ከመንደሩ
ቅላት ንጣት አማረረው
ጠይም ሴት ግን እንደ ታሪክ
ደብዝዛ ነው የምታምረው
ምን አሳቃት እስቲ አሁን
መሽኮርመምን ምን አመጣው
ጥቁር ፀጉር ጥቁር አይን
ጥርሷ ብቻ ለሚነጣው
ጠይም ገላ እያሳየች
ልስልስ ቆዳ እያስነካች
ለሚያስተውል ንፅህናን
በአካኋኗ  እየለካች
እየቀባች ስትደልል
አመንኩላት ቀኗ ይፍካ
ወዟ ከሩቅ ቢታይ እንጂ
እንደ ግዑዝ አይነካ
ባይዳሰስ ገፀ መልኳ
ፊቷ ታጥቦ ሰው ይሰራል
አይ እውነቴን የማቀው ግን
የጠይም ልጅ ሳቋ ያምራል!

@mikiyas_feyisa
የሰው ልጅ የሚጎዳው ባመነው እና የራሴ ባለው ሰው ነው። ጥቃት የሚደርስበት ጥላዮ ነው ባላችሁት አማካኝነት ነው። ዩሱፍ የተካደው በወንድሞቹ ነው። አንዳዴ የኔ ነው ለምትሉት ሁሉ የምትዘረግፉት ሚስጥር እናንተን ጎርፍ ሆኖ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ ራሳችሁን ከኔም ከምትሉት ሰው ጠብቁ…

ሰብሃል ከይር
ቆንጆ ሴቶች ያሳዝኑኛል ምክንያቱም
1#ተይዘዋል ብሎ ስለሚያስብ ሚያናግራቸው ይጠፋል በ እሺ አትለኝም ፍራቻ ሚመኛቸው ሚፈልጋቸው ዕንኳ አይኖርም
2# አትመልስልኝም ብለው ወንዶች ስለሚፈሩ  onlin ሆነው ዕንኳ text ሚልክላቸውን ሠው ይናፍቃሉ
3# ባላቸው ውበት ከመደሠት ይልቅ ከነሡ ሚበልጡትን እያሠቡ ደስታ ከነሡ ይርቃል
4#ሠው ሁሉ ዕነሡን ሚያይ ስለሚመስላቸው አላማረብኝም ብለው ያሠቡ ቀን አረማመዳቸው ዕንኳ ጠፍቶባቸው ዕግሮቻቸው ዕርስ በርሣቸው ይደነቃቀፋል
5# ለኔ ሚሆን ልኬ መጠኔ ብለው ሚያስቡትን ወንድ በመጠበቅ ዕድሜአቸውን አባክነው ፈላጊ ዕንኳ ያጣሉ
ምንጭ የመሠለኝ andi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ማቶሳላ ... 900 ዓመት ኖረ ፣
#የ200 መቶ አመት አፍላ ወጣት ሆኖ
#የ160 ዓመት .... ኮረዳ አፈቀረ ።
እሷም ሳታውቅለት እየተሰቃየ
በዓይን ፍቅር ብቻ ለ20 ዓመት ቆየ ።

ከዛም የሆነ ቀን እንደምንም ደፍሮ
ብቻዋን እንዳለች ማፍቀሩን ቢነግራት
ትንሽ ግዜ ስጠኝ ...
30 ዓመት ብቻ ላስብበት አለች ።
ከዛም እሺ ብላው #ለ65 ዓመት እየተጠናኑ
ሰውን በሚያስቀና ደስ በሚል አይነት ፍቅረኛሞች ሆኑ ።

ምንም ሳያስቡት 100 ዓመት አለፈ
ከዛም የሆነ ቀን አሰብ አረገና ፀጉሩን እያከከ
ሌላ ሰው ሳይጠልፋት ...
ለሃብታም ሳይድሯት ሽማግሌ ላከ ።

ታዲያ በዚህ ግዜ 375  ,, 400 አልሞላት
የአሁን ልጅ ፈጣን ነው እሷን ደስ እንዳላት
ምን ማድረግ ይቻላል ከተፈቃቀዱ ...
አሉና አባትዬው እጇን እየሳሙ
እቺ አንድ ፍሬ ልጅ ...
ለዚህ በመብቃቷ በጣም ተገረሙ❗️

#ጥያቄ 
#ማቶሳላ ፀጉሩን ለስንት ዓመት ነው ያከከው 🤣🤣
ታላቁ የቱርክ ባለቅኔ ከዕለታት በአንዱ ቀን አርቲስት ጓደኛው አቢዲን ዲኖንን "የደስተኝነትን ስዕል" እንዲስል ጠየቀው፡፡

ከዚያም ጓደኛው ከላይ የምትመለከቱትን ስዕል ሳለ። ስዕሉም የሚያንጠባጠብ ጣሪያ ባለው ቤት ውስጥ በተሰበረ አልጋ ላይ ተደራርበው ተኝተው ፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ የቤተሰብ አባላት ፊት ላይ ውብ ፈገግታ የሚታይበትን የአንድ ቤተሰብን ስዕል ሳለ ፣ ሰዓሊው ደስተኝነትን እንዲህ ገለጠው።

ደስታ የመከራዎች መቅረት አይደለም ነገር ግን መከራዎችን በምስጋና መቀበል ነው !!!!

Objectivism Art ይባላል !

@funyhaha
@funyhaha
. #ኢትዮጵያዊ_ነኝ!

......“ኦሮሞ” ነኝ እኔ! . . .
ጎንደር ከተማ ላይ ከፋሲል ግንብ ጎን ቤቴን እሠራለሁ፣
ከአንተ እህት ከእኔ ፍቅር ልጆች አፈራለሁ፣
“ወግድ!” ትለኝ እንደሁ እስኪ አይሃለሁ፤

……… “አማራ” ነኝ እኔ! …….. ግና…..
ጂማ አባ ጅፋር ጎን ቤቴን እሠራለሁ፣
ከአንተ እህት ከእኔ ሚስት ደሜን ‘ቀይጣለሁ፣
“ዴሚ!” ትለኝ እንደሁ እስኪ አይሃለሁ፤

. . . “ከትግራይ” ነኝ እኔ! . . . ግና . . .?
ከወላይታዋ የንጉስ ጦና ሃገር ቤቴን እሠራለሁ፣
ከታናሽ እህትህ ከባለቤቴ ደም ዘሬን እተካለሁ፣
የምታመጣውን እስኪ ጉድ አያለሁ፤

……… “ሲዳማ” ነኝ እኔ! …….. ግና…..
አክሱም ጽዮን ማርያም ከአፀዱ በስተቀኝ ቤቴን እሠራለሁ፣
ለአንተ እህት ለእኔም 'ውድ' ከሆነችው ፍቅሬ ልጆች እወልዳለሁ፣ . . .

@funyhaha
@funyhaha
በመላው አለም ለምትገኙ የአስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ‼️


Greetings to all followers of Islam all over the world for the 1445th Eid al-Fitr!

Eid Mubarak‼️


@funyhaha
@funyhaha
ሁለተኛ ዙር እድል በራችሁ ላይ ቆሟል.... Notcoin ላመለጣችሁ ነው... ደግማችሁ አትሳሳቱ - ከፍታችሁ አስገቡት::

Tapswap - #Verified የሆነ የSolana ያልተማከለ Blockchain ሳንቲም መሰብሰቢያ ጨዋታ (Token TAPS) ነው::

አዲስ በመሆኑ ምክንያት ከነብዙ ስህተቱና ድክመቱ #Notcoin Tap በማድረግ በመነሻ ዋጋው ሲሰላ ከ$2000 USD በላይ ያገኙ አሉ::

ስለሆነም በዚህ Solana #TapSwap በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ መሰብሰብና ለራሳችን ሥራ መፍጠር አለብን:: ፈጽሞ ችላ አትበሉት::
ከታች ባለው ሊንክ ስትጀምሩ 2500 ታገኛላችሁ:: እናንተም ሌሎች ሰዎችን ስታስጀምሩ  መጫወቻው ላይ #ref የሚለውን በመንካትና ሊንክ #Generate በማድረግ ላኩላቸው:: ሊኝካችሁን በተለያዩ መንገዶች ለሌሎች አጋሩ:: አሁንኑ ጀምሩ !👇👇

https://www.tg-me.com/tapswap_bot?start=r_443621019
🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

አንደ ከዚህ ቀደሙ ታስኮችን ስሩ !

Autoclicker ተጠቀሙ !

ብዙ እንድትሰበስቡ ብዙ Boost አድርጉ!



@funyhaha
@funyhaha
2024/04/29 10:39:34
Back to Top
HTML Embed Code: