Telegram Web Link
መለየት

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡

By እውቀቱ ስዩም

@gGetem
@gGetem
👍1
የ'ግዜርን ነፍስ ሴጣን ልብን አድሏታል
ላይዋ ታቦት ታቿ ጣዖት ተዋርሷታል

ልጅ እያለች ስትድህ ገና ያወቀችዉ
አፏን ገና ስትፈታ በቀል የሚል ቃላቶች ነዉ ያወጣችዉ

በ።ቀ።ል
እልል...............

በእናቷ እቅፍ ገብታ በአንቀልባ ዉስጥ እያለች
ስለአባቷ መርዛማነት በጡጦ አርጋ ጠብተዋለች

ጥ።ላ።ቻ
እልል..................

እሹሩሩ አታዉቅ እናት
አባቷን ነዉ ምጠራላት

ህ።መ።ም
እልል...................

እልል
        ዛሬ
            ነፍስ አወቀች
             ፍቅርን ሻተች
              ምን ታደርገዉ ሴጣን ልብን             ተዋርሳለች
የአዳም ፍጥረት ትጠላለች


@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
ተራማጅ ነን እኛ!
.
በመንገዱ ኹሉ - እሾህ እየወጋው፣
ባዕድ እየኾነ - የከረመ ሥጋው፣
(እንዴትም ቢያሰጋው፣)
እየተገጫጨ፣
ደም እየተረጨ፣
ያብሮነት ሕልማችን - ቁስል ቢያስነክሰው፣
ተስፋ አይቆረጥም - በ’ርምጃና በሰው።



@gGetem
@gGetem
Just because i smile
.............doesn't mean i don't cry
Just because i laughing .............doesn't mean i don't alright
If u really know me babe that's a lie.

@Joyfull
@gGetem
@gGetem
@tamFidel
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እረፉ

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
ተለያይቶ ማፍቀር
በህልም እንቆቅልሽ ዘላለም ማሽቀርቀር
ይህም ይቅር ፍቅሬ  በኑሮ መታጠር
ታሰረ ፍቅራችን ልክ እንደዘራችን
ዘመመ  ቀናችን


@Joyfull
@gGetem
@gGetem
@tamFidel
*
የሚበድላት ሰው
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።

የትኛውን ትመን?

መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!

ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።



@getem
@getem
👍1
(መልክ ልስራ ይቅር?)
ለጌጥ ልኑር ለውበት?
     ውስጥ አዳክሞ እላይ ኩራት
ልዋብ ለታይታ ለሰዎች እይታ?
      ላይቀርፍልኝ የእንባዬን ጠብታ
ሆዴ ባዶ ከአንጀቴ ተጋምዶ
            የኔ ይሉኝታ ጉድለቴን አይፈታ!
ልተወው ታዲያ የላይኛውን ውበት?
          ልመገባት የማምሻዬን እራት?
ይገምቱኝ በአሁኔ ገፅታ?
        ልተው  ጭንቄን ማሰብ ለይታ?
ይቦጭቁኝ በወሪያቸው?
          ያስለቅሱኝ በሳቃቸው?
      እሺ ምን ይሻላል??
  ሰው ለአይን ውበት
         ፆሙን እንዴት ያድራል??!
ግራ ገባኝ ከራሴው ስማከር
      እስኪ እናተስ መልክ ልስራ፥ ይቅር??
           ,,,,,,,,,,,,,,,,,,
@gGetem
@gGetem
@gGetem
Forwarded from 🎸 Joye see
ዳግም አፈቀርኳት
አየወደድኩ ወደድኳት
እየረሳው አስታወስኳት
እንዴት ብዬስ ይህን ልንገራት
ያስገርማል ዳግመኛ ወደድኳት


ብዬ ልፃፍልሽ ወይስ
............................

የኔ ውድ የኔ ሳቂታ የኔ ፍልቅልቅ እንዴት ነሽልኝ እኔ ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን። ይህንን ደብዳቤ ስፅፍልሽ በብዙ ሀሳብ ተወጥሬ በስራ ገመድ ታስሬ ብቻ በፍቅርሽም ሰክሬ አለው እየተንገዳገድኩ መቆም ተስኖኝ በሁለት እግሬ😁😁😁...ok be serious በቻ እንዴት ብዬ እንደምነግርሽ ባለውቅም ዛሬም አየረሳው አስታውስሻለሁ እያፈቀርኩ አፈቅርሻለሁ .....አረ ጆ ተረጋጋ የምን ግጥም ነው ደብዳቤ ፃፍላት እንጂ ቢለኝ ልቤ ልፅፍልሽ ስነሳ ብዕሬ ገንፍሎ በንዴት አረፋ ደፍቆ ወረቀቴን ቢጨማልቅብኝ ቀለም ካልነካው ቦታ ጥግ ላይ.......❤️ ብዬ ደብዳቤዬን በስንብት ዘጋው።
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍2
ለየ - ቅል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
የየግል ብሶት ፣ የየግል ችግር
የየግል ሩጫ ፣ የየግል ውድድር
የየግል ሀይማኖት ፣ የየግል ብሔር
የየግል አላህ ፣ የየግል እግዜር
የየግል ሀገር ፣ የየግል ስልጣን
የየግል መልአክ ፣ የየግል ሰይጣን
ይዘን እየወጣን...
በየ ግል ቆስለን ፣ የጋራ ፈውስ አጣን!!!

@gGetem
@gGetem
@tamfidel
👏3
ለጤዛ ተዋድቀን
👤 በእውቀቱ ስዩም

እድሜያችን ሰባ ነው - ቢበዛም ሰማንያ
ይህም ኑሮ ሆኖ - ጠዋት ማታ ፍልሚያ

አንዱ ካንዱ ፅዋ - ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ - ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደቄጤማ - እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ - በአጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ - ባሰለፈን ቁጥር

ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የት ገብተን እንረፍ?

በዶፍ ዝናብ አገር - ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን - ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን - ያከትማል አድቀን።
@gGetem
@gGetem
@tamfidel
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
የጋራ መኖሪያ ።

በቤተ ዘመድ ፊት ... ቃል ቢገባልሽም
እሱም ቤት አልገባም...አንቺም ቤት የለሽም
የባልሽ ንግግር ... ቅኔው ተፈታልሽ
እሰራልሻለው ... እንዳለው ሰራልሽ

@gGetem
@gGetem
@gGetem

በሙሉቀን ሰ•
ለየ - ቅል

.
.
የየግል ብሶት ፣ የየግል ችግር
የየግል ሩጫ ፣ የየግል ውድድር
የየግል ሀይማኖት ፣ የየግል ብሔር
የየግል አላህ ፣ የየግል እግዜር
የየግል ሀገር ፣ የየግል ስልጣን
የየግል መልአክ ፣ የየግል ሰይጣን
ይዘን እየወጣን...
በየ ግል ቆስለን ፣ የጋራ ፈውስ አጣን!!!

@gGetem
@gGetem
ፍቅር ነው አውቃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።
መራር ፅዋ በመንገዴ፣
አንቺ ነሽ ወይ የኔ ገዴ።
እንደእንቅፋት እየመታሽ፣
ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ወጣሽ።
ዝብርቅርቋ አንቺ አለሜ
አለሽ ስልሽ የሌለሽው፣
ቢታየኝም ባይታየኝ
ፍቅርሽ እኮ አለ እላለው።

መች መሰለሽ፣

እንደ እሳት፣
ሲያደምቀኝ ወይ ሲያሞቀኝ ፣
ሌላ ጊዜ ስታስከፊኝ፣
ንዴት ሆኖ በግለት መልክ ሲያተኩሰኝ።

ፍቅሬ ሙሉ
ከልብሽ ውስጥ የጎደለለው፣

እንዳልተውሽ፣
ተዋት የሚል ዝግ ሀሳቤን
አይምሮዬ እየተወው፣
እራኩሽ ስል፣
ሸፋፋ እግሬ
እየዞረ ካንቺ ስር ነው፣
ልቤን ካንቺ
ፍቅርሽ ካልኩት እንዳስጥለው፣
ሳሰላስል
ካንድ ሀሳብ ጋር ተገናኘሁ፣

ሀሳቡ፣

አምላክ ወዶን
ፍቅርን በሞት ከገለፀው፣

ለምን ታዲያ፣
በሞት ማግስት በፍርድ ወንበር
ወደሲኦል የምንወርደ፣
ገባኝ፣ ለካ ፍቅር ትርጓሜው
መያዝም ነው መልቀቅም ነው።

ፍቅር ይዤ ባትመረጪኝም
ምርጫሽ ይሁን ፈቅጃለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለው
ለወደድሽው ትቼሻለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለሁ
እረስቼሻለሁ ይቅር ብዬሻለሁ፣

ፍቅር ነው አውቃለሁ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
አለም እንደ ልቧ
ያሻትን አክብራ
ያሻትን ማሽቀንጠር፤

ህይወት ቅራቅንቦ
ዝም ብሎ ኖሮ
ዝም ብሎ መቀበር።

01|07|2017

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍2
     ( ሚስትህ የኔ እኮ ናት )

አገሬው ቢተቸኝ በገዛ ድግሴ ሳለሁ ተባርሬ ፤
ስቀህ ብታየኝም አንተ ተደስተህ ሳልፍ ተማርሬ ፤

አዎን ያንተው መውደድ የራስህ ያረካት ፤
ሳታገባት በፊት ለኔ ሚስቴ እኮ ናት ፤

      የምሬን ስነግርህ......

አብልጬ ምወዳት ከራሴ ከሁሉ ፤
ሚስትህ ሚስቴ ደሆነች ባያውቅልኝ ሁሉ ፤
የሰው ሚስት ተመኘ ይለኛል ሰው ሁሉ ።

ግዴለም ይበሉኝ እነሱ ያሻቸውን ፤
ቆርጠው ይቀጥሉ ያለ የሌለውን ፤

አንተ ግን አደራ እንዳትዘብተኝ ፤
ደርሰህ በነሱ ፊት እንዳትቦጭቀኝ ፤

ወዳጅን መቀማት ፤
በለሆሳስ ማጥቃት ፤
ሳይቆፍሩ መቅበር ፤
ያውም ባንድ ጀንበር ፤
ሙሾም ሳይወረድ ፤
ምነው ሳይረገድ ።

ሰሚ ባይሰማልኝ ባላቆም ጠበቃ፤
ይኸን ሁሉ ነገር አርገህ ስታበቃ ፤

ሚስቴን ቀማኝ ብለህ ብትሄድ አቤቱታ ፤
ለወናፍ አፍ ሁሉ ብታቀርብ ስሞታ ፤

የምሬን ነው ምልህ ዳኛውም አይፈርድም ፤
እኔ አልከሰስም እኔ አልወቀስም ፤

ከቻልክ የሚስቴ ባል ምላስህን ሰብስብ ።


@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1🤷1
እናፍቅሽ ይሆን

~   ~   ~   ~   ~  ~
ስቀሽ ስትለይኝ ስትሄጅ ካጠገቤ
ስትሰናበቺ ከሚወጅሽ ልቤ
ያመጣሽ ጎዳና ሲመልስሽ ወስዶ
መፋቀርን ክዶ ነግርኝ ሲሄድ መርዶ
እናፍቅሽ ይሆን ?

ታውቂው የለም እንዴ 🤔
ሀዘኔን ልረሳው መፍራቴን ልደብቅ
አጥብቄ  መያዜን የቀሚስሽን ጨርቅ
ገና ሳትቀልጂ በመምጣትሽ
ብቻ እንደምፍለቀለቅ ።

ትውስ ይልሽ ይሆን ?
እናፍቅሽ ይሆን ?
እንደምሳሳልሽ ትሳሽልኝ ይሆን ?
እኔማ .....
እወድሽማለሁ አፈቅርሽማለሁ
አስብሽማለሁ ናፍቅሽማለሁ
አንቺስ አንቺ ሆዬ  እናፍቅሽ ይሆን ?
እናፍቅሻለሁ ?




@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1🥰1
( ነዳይ ... )
============

ውዴ ....

እግዜርን ፍለጋ በዱር በተራራ
ምድሩን አታስሽው
በምናኔ ጉዞ ዋሻ ለመገስገስ
እግርሽን አታንሽው
መውረድ ከጀመረ የማይቆም እምባሽን
ይቅር አታፍስሽው

ጽድቅ ያማረሽ እንደው
ነዳይ ልቤ ፊትሽ
ደጅሽ ወድቋል አንሽው  !!!



@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1👏1
#ጥርጣሬ

እጄ በካቴና፣ ታስሮ ተሸብቦ
በድን ሰውነቴ፣ በፖሊስ ታጅቦ
እስር ቤት ስነዳ ያዩኝ ሰዎች ሁሉ፣
“ያው ሌባ! ሌባ!” አሉ።

የኔን ንፅህና፣ እኔው እያወኩት
'ብዙኃን ይመውኡ!'
ምስክር እራሴን እኔ ውስጥ አጣሁት።

«እንዴት ይህ ሁሉ ሰው ይዋሻል ባንድ ቃል?
ብሰርቅ ነው 'ጂ እንግዲህ ማን ያውቃል?»



@gGetem
@gGetem
2025/07/08 22:12:02
Back to Top
HTML Embed Code: