Telegram Web Link
Live stream finished (48 seconds)
Audio
ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹:
ይሄንን ግጥም ሰሞቶ የማይነዝረው ማነው?🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ዋ_አድዋ
#ሎሬት_ፀጋዬ_ገብረመድህን

ዋ!!!!!!!!!
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሶሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ! ባንቺ ብቻ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና................

ለወዳጆ ያጋሩ #ሼር #ሼር

@gGetem
@gGetem
ክህደት ክፍል 07 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_07

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
ወዬ ለኔ

ዘንድሮን ሁዳዴ
ሳልሰስት ለሆዴ
ንፍሮዉን አንፍሬ
ዳቤዉን ጋግሬ
ቢጫ ቆቤን ገዛዉ
መቋሚያም አሰራዉ
ዳሩ ምን ያደርጋል...........

ሠዉ'ነቴ አደፈ
ቃሌ ገረጀፈ
ሀሳቤ ሸፈፈ
ምን ያደርግልኛል ንፍሮ መቀቀሉ
ኑሽሮን እንብላ እስኪደርስ በአሉ።

@gGetem
@gGetem
ክህደት ክፍል 08 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_08

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
ክህደት ክፍል 09 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_09

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
ሩህሩ ነበር ልብሽ፣
የዋህ የጨው እቃ፣
የማይከብድ ቀንበር፣
ተመቺ ለጫንቃ፤
አቃፊ ደጋፊ፣
ፈገግታ መጋቢ፣
የምሕረት ገባር፣
ከእውነት አጋቢ፤
ተናፋቂ ውበት፣
ውስጣዊ ብርሓን፣
የማይጨልም ትጋት፣
የሚደነቅ ልሳን፣
አቆራኝቶ ይዞ፣
ሰውረሽ ይዘሽው፣
የመወደድ ፅዋን እንዳይጎል ሞላሽው።



@gGetem
@gGetem
[በሠላሳ ክረምት]
.
.
ከቦኛል ፍርሀት ከቦኛል እርጅና
የጉብዝናው ወራት
በወጉ በወጉ አላለፈምና።
ያወዛውዘኛል የአዝማናት ነፋስ
መደገፊያ ምርኩዝ ከማን ብርቱ ልዋስ?
እነሳ የነበርኩ ተስፈንጥሬ እንዳነር
እራመድ የነበርኩ በግሮቼ ጀግኜ
ክንፌን ቆርጬ ጣልኩ ከፍርሀት ወግኜ።

ሳዘግም
እግሮቼ ሲርዱ
ስተኛ ጭኖቼ ሲበርዱ
የገላዬ ሙቀት ሲሸሽ ቀን ጠብቆ
ቆፈን ሲዳበለኝ እንደስም ተጣብቆ
እትቱ ዘፈኔ
ፀደይ እንዳልወጣ በጋን እንዳልገፋ
ግንባሩ ላይ ይዟል የማለፍ ወረፋ።

በሰላሳ ክረምት በሰላሳ በጋ
ገሚሱ የርግማን ጥቂቱ የፀጋ
ተብዬ ብጠየቅ “ምን አደረክበት?”
መልሴ
እንደሞላለት ሰው ዝም ብዬ ኖርኩበት።


@gGetem
@gGetem
“ቀንሽ ነዉ“ እያሉ ሲፎክሩ
               ሰማዉ
ዉዴ እንዳትሰሚያቸዉ ቀንሽ
ነዉ የሚል ነዉ ቀንሽን የቀማዉ

ቀንሽማ ዕለት ነዉ በብዙ
መስፈሪያ ህይወት ላይ ሚገለፅ
እድሜሽን የገበርሽ ወንዶችን
            በመቅረፅ !!!

ሁሌም የሴቶች ቀን ❤️❤️❤️

@gGetem
@gGetem
.......


የሄዱትን ሁሉ
የገፋንን ሁሉ
ስቀን ሸኘናቸው
ስመን ጠቆምናቸው
በተዘጋ ጎጆ
በእንባ እየተራጨን
ከመገፋት ጽዋ
በቀል ተጎነጨን
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን
መልከጥፋ መልካም
ብጉራም ቀፋፊ
ጎባጣ አንገት ደፊ
ነን ብለን አመንን
ውበትን ለመንን
የሄዱትን ሁሉ
የገፋንን ሁሉ
ስቀን ሸኛናቸው
በእናባ ጸለይናቸው
ፍቅርን ተሳልን
በበቀል ቆሰልን
ሳሚ ያጣ ከንፈር
አቃፊ ያጣ ገላ
የወደድነው ሁላ
ጸጸት አስጎነጨን
ስቆ ለእንባ እያጨን
አሸሸ መዳፋን
ነፈገን እቅፋን
ጸደቁብን በቃል
ውበት ልብ ይበቃል
ብለው ልብን ሸሹ
ገፍተው አቆሸሹ
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን
መልከጥፋ መልካም
ብጉራምም ቀፋፊ
ጎባጣ አንገት ደፊ
ጉለት ሆንን ያምላካቸው
ያምላካችን
በመልካችን
ለወደድነው አነስን
ለአፈቀርነው እረከስን
ተጎነጨን መገፋትን
መተፋትን
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ክህደት ክፍል 10 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_10

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ

ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ

ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)

አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ

እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር

በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)

ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ


@gGetem
@gGetem
@gGetem
..........



አላቅም
አታቅም
የልቧን ተናግራ
ዝምታ ሰብራ
ጭምት ነበረች
እኔን ስታገኝ
ቃላት ፈጠረች
የፊደል አይደል
የቋንቋ በደል
ውሸት ነው የሚሉት
ነገ ላይ ደርሰው
ክደው
አፍርሰው
የቋንቋ አይደለም
በፍቅር ቀለም
ከገጽ ከአካሏ
ምልክት ስላ
ከሩቅ ነበረ ያናገረቺኝ
ደምቃ የታየቺኝ
አታቅም
አላቅም
ሴት አሽኮርምሜ
ከንፈር ተስሜ
ገላን በጠረን
ናፍቆት በዘፈን
አላባበልኩም
አላጫወትኩም
ጭምት ነበርኩኝ
ሰው የሚሞቀኝ
ወሬ የሚርቀኝ
ጥርሶቼ ስቀው
እግሬ ቦርቀው
ቀን ያላለፉ
አንቺ ጋር ደርሰው
ተኮላተፉ
መሳም አማረኝ
ያማረ ጉንጯን
አገጭ.....አገጯን
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
መኖር እየሳሙ
ከእቅፏ
ከአፏ
ህይወት ታዘንባለች
መኖር ታስርባለች
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
ክፉዋን ሳይሰሙ
አምላክ እንደው ጨካኝ
ክፉ
ዐዕላፍ ሳይረግፋ
የሰው መንጋ
ሞት ከደጇ ላይጠጋ
ገዝቼላት ሞትን
መለየትን
ከዘር እዳ ልነጥላት
እኔው ሞቷን ልሙትላት
ዕድሜ አውሼ
ተውሼ
ከእባብ ከሚዳቆ
ከዛፍ ከሸንበቆ
ትንሽ ዕለት
ትንሽ አመት
ተመጽውቼ
ልሙትላት
ሞቷን ትቼ
አላቅም
አታቅም
ብቻ በሰው አቅም
አኛን አንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን
የጭምቶች ፍቅር
የአይናፈሮች ሀገር
ማገር
ሆነልኝ አለማወቋ
አታቅም እንጂ
ያሰግራል ሳቋ
ሀቋ
ከፊቷ ላይ ቅራኔ የለም
የኔ አለም
ባታቅም
ባላቅም
በሰው አቅም
እኔና እሷን እንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን



@gGetem
@gGetem
@gGetem
Audio
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ምርጥ ግጥም
🎙🎙🎙ናትናኤል
ለሃሳብ እና አስተያየት
Rip የኔ ጀግና ወንድም ስራህ በልቤ ከፍ ብሎ ይደመጣል።🎙🎙🎙ናትናኤል
@gGetem
@gGetem
Audio
🎙🎙ናትናኤል
@gGetem
@gGetem
መለያየት ማለት

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

By Efrem seyoum

@gGetem
@gGetem
እሙ...አንቺን እያሰብኩኝ
ግጥም ልፅፍ ተነሳሁኝ
ግና ደግሞ አንዴት ብዬ...
........እንዴት ብዬ እንደምገልፅሽ ግራ ገባኝ
ቃሉ ሁሉ አነሰብኝ
ትናንትና ስለ ፍቅር ብዙ ፅፌ
እልፍን ስንኝ አሰልፌ
ነፍስን ከስጋ ስነጥል
ከጨረቃ ግድም ሳውል
ፍጡሩን ሰው ከፀሃይ ጋር ሳስተካከል
በባዶነት ለታሰረው የተስፋን ጠል ሳወርድለት
ሀዘን ሰብሮት ለሚያለቅሰው መፅናናትን ስሆንለት....እንዳልነበር
ዛሬ ግና.....ላንቺ የሚሆን ፈልጌ አጣው
እንዴት ብዬ አሙን በቃል
እንዴት ሊሆን....?እንዴት አንቺን በቃል
የለም እኮ የሚገልፅሽ ከስነ-ቃል
የለም እኮ......የለም
ገጣሚ ጆሲ(Joy see)

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ════
2025/07/08 09:16:33
Back to Top
HTML Embed Code: