Telegram Web Link
#Title_Bitale_Alansam
#poet_Leo_Mak (yegual🤔)
Yehoheyat heber🦋🦋🦋🦋
#Editor_Sebel_Adis
#for_u🙉
@gGetem ..join us
@leoyri ...comments
ጭምት_ሴት
ከዝምታሽ ድባብ ከቃላትሽ ህብር
በጭንቅ ተውጣ በኑሮ ውዥንብር፤
ብዙ ጩኸት አለ
ብዙ ህመም አለ
ለተመልካች ወርዶ ለሷ ያልቀለለ።
ከዝምታሽ ጀርባ፤
ብዙ ጩኸት አለ!!!
ሊዮሪ
📷ማማ 04/09/2013ዓ.ም
08:35am
@leoyri
@gGetem
#MOM
Audio
ራሰ
ክፍል ፫(3)

@gGetem
@gGetem
ልቤ እኮ ተራ ነው
የበረዶ ክምር…
በድምፅሽ ይቀልጣል
ይሄ ሁሉ ግግር።

ብሽቅ ነው አንጀቴ
ቢመስል ጠንካራ
ተቆራርጦ ይወድቃል
ከመምጣትሽ ጋራ ።

ዉሸት ነዉ ካባዬ
ጥይቱም ፣ ዝናሩ
(ካላመንሽ ሳቂማ)
መሬት እ..ን...ዲ...ዘ...ሩ።

ስስ የኔ ኩራት
ቀረርቶ ሽላዩ
እውሸለሸላለሁ
ጣቶችሽ ቢታዩ !

እውነቱን ልንገርሽ?

አላምንም ዙሪያዬን
ሰዎች ሲሉኝ ብርቱ
አንደበት ቃላቴ
ታዳሚን ሲረቱ …

አጀብ ቢባል አወይ
የግንባሬ ክርክር
ከፊቴ ለመቆም
ብዙ ሰው ቢያሰክር

ለመቅረብ ቢያስፈራ
የኔ ቦታ ፣ ሹመት
ሁሉ ባዶ ይሆናል
ከታየሽ በድንገት ።

እናም ማነው ሲሉ
በአንበሳ ፣ በነብር
ገፄን ሲመስሉ
:

ገርሞኝ የምስቀው
'የብዙዎች ጀግና'
‘የ'ነ እንቶኔ ንጉስ …’

እንደዚህ ሳስብ ነው

“ይዘውሽ ቢመጡስ?🤔
@gGetem
@gGetem
አንነቃነቅም

መንግስተ ሰማይን- እጅግ ብናደንቅም
የእረፍቱን ኑሮ-ዞትር ብናፍቅም
እዛ ያለ ደስታ- እዛ ያለ ጥቅም
ከበለጠው በልጦ- ከላቀው ቢልቅም
"ፃድቃን" እንደሆንን- ልቦናችን ቢያውቅም
ዛሬ “ኑ!" ብንባል አንነቃነቅም


📚መጽሐፍ (እንኳን መሀይም ሆንኩ....)
😀ደራሲ (በለው ገበየሁ)
@gGetem
@gGetem
@gGetem
@gGetem
@leoyri
Audio
ራሰ
ክፍል ፬(4)

@gGetem
@gGetem
( ልመርቅሽማ ... )
===============

እማ .....
የተረሳው ማንነቴን
እንዳወጣሽ ከጨለማ
ልትጠይቂው ያሰብሽውን
ቃል ሳይወጣሽ ጌታ ይስማ

እንደሸፈንሽ ገመናዬን
ስሜ ባገር ሳይ'ታማ
ኃፍረት አሳር ያገኘሽ ለት
ትከልልሽ ጸሐይ ጸልማ

ቀን ሲጥለኝ ላጽናናሽኝ
እስኪረሳኝ ክፉ ግብሬ
የሰማይ ዘብ መላዕክታን
ያረጋጉሽ በዝማሬ ... 

ወድቄ አይተሽ እንዳልናቅሽኝ
ከሰው ተራ በታች ስገኝ
ቀን ሰምሮልኝ ከብሬ እንኳ
አገልጋይሽ ሎሌሽ ያርገኝ ...

አሜን !!!



@gGetem
@gGetem
❤️😷የታፈነ ፍቅር😷❤️❤️
ደራሲ፡ዮሲ ማን&ሊዮ ማክ
ጊዜዉ 2000 ዓ/ም ነበር።ወራቱ ደግሞ ጥር ሲሆን ሰረግ የሚበዛበት ወቅት ነው ጆርጅም የብቸኝነት ሀያል አቅም የተገነዘበበት ወቅት ነበረ። ሶስት ጓደኞች ነበሩት። ከነዛም መሃል በነሱ ኣጠራር ሀብትሽ የሚሉት ግን የስም ሀብታም የሆነ የሚኖረው ኑሮ ከእጅ ወደ ኣፍ የሆነ ለስሙ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ጓደኛቸዉ ነው እና ሀብትሽ ከሌለ ሰዓታቸዉ እና ጊዜያቸው ያለ እርሱ የማይደምቅ ነው። ሌላው ጓደኛቸው ደግሞ አበራ እጅግ የተለየ ቁም ነገረኛ እና በእድሜው በሰል ያለ ሲሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በጭንቅላቱ ላይ እና ሁሌ ከአገጩ ስር የማይጠፋው እጁን ከእርሷ ላይ ለደቂቃ እንኳን የማያነሳባት ፂሙ ላይ አለፍ አለፍ ብሎ ወደ እርጅና የእድሜ እርከን። መግባቱን ማሳያ የሆኑ ነጫጭ ሽበቶች በኑግ መሀል ተደባልቆ እንደበቀሉ ሱፎች ከእርቀት ይታያሉ። ሌላኛው እና የመጨረሻው በእነርሱ ዘንድም እንኳ እንብዛም ቦታ የማይሰጡት ሰለሞን እጅግ ሩህሩህ ከእራሱ በላይ ለሰው የሚኖር ሰዉ ሲሆን በጣም ምስኪን ደሀ እናቱን ያለ እረዳት የሚጦር መልካም ሰው ነው።እናም ከጆርጅ በስተቀር ውሀ አቅጣጫቸውን በማግኘት የትዳር ረጅም እና ጣፋጭ መንገድ ጀምረዋል። ለዚህም ይመስላል የጆርጅ ከወትሮ በተለየ ለትዳር ያለው ጉጉት እና ተነሳሽነት የጨመረው። ጊዜው ይብዛም ይነስ እንጂ ዕለት ከዕለት የጓደኞቹ ጉትጎታ ና ንዝነዛ ከእነርሱ እርቆ አያዉቅም ነበር።ከዚህም የተነሳ እርሱ የሚያገባት አይነት ሴት ፈልጎ እንደ አጣ ከማስረዳት ቦዝኖ አያውቅም። ግን አንድ ቀን........
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል
ዮሲ ማን👉 @yosika
Leo Mak👉@Leoyri
@gGetem
@gGetem
ተፃፈ 6/5/2012 ዓ/ም
💫
.....እኔ ለወሎ ልጅ..
#ገጣሚ_ሚካኤል_አስጨናቂ
#አንባቢ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tg-me.com/leoyri
www.tg-me.com/gGetem
💯 quality 👉👌
Plc share&Join
🎬&📶
#Mâŕťå_Žèŵđų (ማርዘዊ)
"ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር"


.
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
# አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
# ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.
.
.
.
.
©ኤፍሬም ስዩም(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር)
www.tg-me.com/gGetem
www.tg-me.com/leoyri
ሽርተት
<unknown>
ሸርተት በገዛ አንደበት...
ገጣሚ፦ ሊዮ ማክ
አንባቢ፦ አዚታ
🧑‍💻ማህዳ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#እንደ ህያዋን_
ማህሌተ ገንቦ

ባጭር ቀረን ስንል፣ እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን

ቺርስ!!

ፊታችንን አይተው እንደተቸገርን፣
ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስከንለምናቸው፣
ቆመው ላልጠበቁ

ቺርስ!!

ወድቀው ለማይጥሉ፣ ነግሠው ለሚያነግሡ ነውራችንን አይተው፣ ልከ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው፣ ፈጥነው ለሚረሱ

ቺርስ!

ላባ ላረጉልን፣ የመከራ ሸከሙን
ቀልደው ላሳቁን፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ
ሥጋ ለበስ ትንግርት፣ ሆነው ላስደመሙን

ቺርስ!!!!

#Bewke_S 🤔

@gGetem
@gGetem
@leoyri
ፍቅርን ፈራን
(ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን)

ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነት ለመድን

“ፈራን”
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን

“ናቅን”
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን

“ናቅን”
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን

“ጠላን”
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ

“ራቅን”
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

@gGetem
@gGetem
ያየሁሽ ለት
ያየሁሽ ለት በልቤ ላይ የተፀንስሽ
በራሴው ልክ የተሰራሽ
የፍቅርን ጥግ የማይብሽ
አንቺ ለአኔ የኔ የሆንሽ
መስሎኝ ነበር......
ህያው ሆኜ በእቅፍሽ የምሰወር
ያየሁሽ ለት....
ሳቅሽ ቀልቤን የማረከ
ገላሽ ውስጠ ሀይሌን የሰረቀ
ቃልሽ እስትንፋሴን የነጠቀ
ካንቺ ብለይ ግዑዝ ሸክላ ሆኜ የምቀር
መስሎኝ ነበር.....
ግና ደግሞ ስህተት ነበር
ፍቅርሽ ሸንበቆ ነው ቢደገፉት የሚሰበር
ሳቅሽ ወጥመድ ሆኖ ውጦ የሚስቀር
ገላሽ የገሃነም መዓድ አጉራሽ
ቃልሽ መልካሙን ሰው የሚያጠለሽ ።
Poem by #Joysee
@Joyefull
@gGetem
@gGetem
ዘመንም እንደሰው...
.
.
.
.
የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል
መጤ ከደጅ ቆሞ ቤተ'ኛ ነኝ ይላል.
.
.
ልቀቁ እያለ...
.
.
ፍርድ የለሽ ንግስና ሲሰፋ ባ'ገሩ
የሰውነት ልኬት ሲገፋ ድንበሩ
ለሚነጋ ለሊት...
በግብር አንሰው ወርደው ካ'ውሬ ዘንድ አደሩ።

እረፍ ባይ ሲታጣ በተስፋ መጠውለግ
የኡኡታ ሲቃ እንዲውጥ ሲደረግ
ያኔ ነው መሰደድ ቢሻ መፈናቀል
ጎራ እየመረጠ...
ዘመንም እንደ ሰው ጠብቆ ሲበቀል።
#እግዚኦ 😥

ሊዮሪ©
14/09/2014ዓ.ም
@www.tg-me.com/gGetem
@www.tg-me.com/gGetem
👧እንደ ፀሐይ🌞
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
ሙዚክ፦ማህደር እንዳለ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

👉 #የመድረክ ስራ
#LIVE ...
@gGetem
@gGetem
@sirak6

👉በመድረክ ላይ እንደቀረበ_
2025/07/05 23:52:14
Back to Top
HTML Embed Code: