Telegram Web Link
የመሃን መሓላ
(የሞገሤ ልጅ)
ከጠበልተኞች ደጅ፣
ደጅ ጠኚ መሃል፣
ሱባኤ ሳትይዝ ሰርክ ሳትጠበል፤
መታመሟን አውቃ፣
ላለመዳን አምና፣
ከእምነቷ ሳስታ አለመቻል ታጥና፤
ቅናትን ስራ አርጋ፣
ብቸኝነት ወርሷት፣
ሠው መሃል ሠው አታ ሠው መፈለግ ታክቷት፤
ዐይኗን አደራርቃ፣
በልቧ እያነባች፣
ድካሟ ደግፏት ጽናቷን እያጣች፤
ከጠበልተኞች ደጅ፣
ስለት ደርሶ ልታይ፣
ንግሥ ኪዳን ሳትል ከደጀሠላም ዋይ፤
ተሥፋ የገረፋት፣
ማግኘቷን አርቆ፣
ማሕጸን ለማርጠብ እልፍ አስጠብቆ፤
ያሰለቸ ተሥፋ፣
ሚራዡ ምትሓት፣
ልጄን ይንሳኝ የሚል መሓላ አስለመዳት።

ብትዋሽ ሟች የለ፣
አይመሰክር ቆሞ፣
ጠፊም መጪም ሳይኖር ቃልኪዳን ታትሞ፤
ልጄን ይንሳኝ ፍርሚያ፣
ዋጋ ያላገኘ፣
ተሥፋን ባጣች መሃን አንደበት የዋኘ፤
ቢዋሽ ጉዳት አልባ፣
ባይዋሽም ምንም፣
የሌሎች ዶግማ ቃል ለመሃን አይከብድም።
የሌላት አይሞትም፣
የሌላት አይመጣ፣
ናፍቆት ቅናት በልቷት ከተሥፋ ተቋርጣ፤
ልክ እንደወለዱት፣
መሆን እያማራት፣
ልጅ አፏን እንዳይሸሽ መሃላዋ ይዞት፤
ዋሽታም “ልጄን ይንሳኝ”፣
ለእውነትም “ይንሳኝ”፣
ልማድ ሆኖባታል ላታጣም ላታገኝ።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@paappii
👍4011😢10🔥1
የናፈቀኝ ነገር
ያልኖርኩበት ሃገር!
ማንም ሰው ሳያውቀኝ÷ ከዜሮ መጀመር
ጠዋት የምሰማው
የማላውቃትን ወፍ፣ አዲስ አዘማመር።

የፈለግሁት ነገር
መኖሪያ መቀየር
ልብሴንም መቀየር
ለየት ቢልልኝ
የምጠጣው ውሃ÷ የምስበው አየር።

መራመድ የሚያምረኝ
በአዲስ ጎዳና ላይ ÷ በኔ እግር የነቃ
ባገኝ አዲስ ሃሳብ
አዲስ አይነት እውነት ÷ ወይም አዲስ ቋንቋ።

ማየት የምመኘው ÷ያልራቀ ወደላይ
ሰማያዊ ሳይሆን ÷አዲስ አይነት ሰማይ
በማላውቀው ቀለም ÷ አዲስ አይነት ፀሃይ።
.
.
.
የማውቀውን ሁሉ
መተካት በመሻት
ወደማይታወቅ
ህይወቴን ብሸሻት
የማልሰለቸውን ÷ አጣሁት ፈልጌው
(ስገምት ችግሩን)
አዲሱን የሚያስረጅ ÷ እኔ ነኝ አሮጌው።

በርግጥ እንኳን ማርጀት ÷ መኖር ይለመዳል?
መሰልቸትን መቻል÷ ከናፍቆት ይከብዳል?

በማውቀው አኗኗር÷ መኖር ከከበደኝ
ወደማይታወቅ ÷ ልቤ ካሰደደኝ
እኔ የሌለሁበት ÷ ማንስ በወሰደኝ?
ወላጅ ባገኘሁኝ
በሆነ አይነት ታምር÷ ዳግም በወለደኝ??

By Haileleleul Aph

@getem
@getem
@getem
👍5842😱4🔥3😢3
ጥለሺኝ እየሄድሽ
.....
መንገዷን ጨርቅ አርገው፣
ህይወቷንም ቀና፤
የምል አይነት እንከፍ,
የምል አይነት ጀዝባ ፡ አይደለውምና፦

ኋላ አደናቅፎኝ
ከፎቅ ላይ ብጥልሽ
ስለምትጎጂ፤
ከተፋታን ወዲህ
መንገዱ ያሰጋል
ተጠንቅቀሽ ሂጂ።

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
😁70👍2110🔥10🤩3👎1
ባለቅኔ ነበርኩ
ባለኝ ሰዓት ቅኔ
ያ...ኔ!

ቅኔ ይሏት እርግብ
አፍኜ ስመግብ
ስታዜም ስሰማት
መዝሙሯን ስቀማት
ቀምቼ ሳፏጨው
የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤
የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ
ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤
እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል
ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል
የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ
ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ
ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ
በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ።

ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ
ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ
የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ
ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ
በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል
ምስኪን! ኪን እርግቤ
እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል?

ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን
ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን
ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት
በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥

ግን አልሆነልኝም
አልጮህ ድምፅ የለኝም
ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል
አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል?
ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል?

እውነት!

ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ!
ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ
ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ
አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ
ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ
ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ
አንድ እርግብ ነበረች፤
አሁን ግን የለችም!
ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች።

ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ

ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ
ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ።

By Red-8

@getem
@getem
@paappii
35👍32🔥15😢2
በነጭ ምዕመናን ታቦቷ ታጀበ
ዲያቆኑ ተነሳ ሊቃችን ወረበ

ጭብጫቦ እልልታው
     ዝማሬው ይበልጣል
ማርያም ማርያም ሲባል
      ስምሽ ይጣፍጣል።

ማርያም

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
178👍25👎7🔥7🤩7😁3
ነይ


በሰማያዊ ሰማዩ ላይ አንሳፈፍ
በፍቅራችን ምናብ እንበል እና ከፍ
መኖር ውልክፍክፉ ሳያደናቅፈን
ነይ ሀሴት እናድርግ
በመውደድ ተቃቅፈን
ነይ አብረን እንብረር
ይህ መኖር ሳይጠልፈን

በህይወት ውበቷ የመኖርን ክርታስ
ሰብረን እንጣለው መኖርን አናስታውስ

በአብሮነታችን አለምን እንራሳ
ለኛ አይገባንም ያለም ግሳንግሷ
መኖርን እንካድ
ፍቅርን እናሳድ
እግዜር ይቀዬመን ሀጥያታችን ይብዛ
አብረን እንጥፋ እና አለምን እንግዛ

ነይ

መዓት ይውረድብን ሀጥያታችን በዝቶ
አንድ አንቺ ካለሺኝ ምን ሊጎድለኝ ከቶ
ነይ....................



by kerim

@getem
@getem
@getem
23👍16👎11😱4
...............


ሰአሊው በሸራው ዕርቃን መሳል ከለመደ
ጸሀፊውም በብዕሩ ዳሌና ጭን ከወደደ
አትሸፍኝው ከአደባባይ
ተጸየፊው ጨርቅሽን ጣይ
ጥበብ ይሆን የአምላክ ስእል
ዕርቃን መቆም ከአደባባይ
ስጋና ነፍስ ከአንድ አስራ
ለዘሞተች ገሀድ አለም
ውቡ ገላሽ ውበት ይሁን
የተፈጥሮ ንጽህ ቀለም
ምክንያት አሽቶ ቢመኝሽም
ዕርቃኗን ነች በሚል ቀመር
ልባስ የወሲብ ሽፋን ቢሆን
እንስሳ እንስን ቢደፍር ነበር
የለም የለም
አንቺን አይቶ ዝሙት የለም
እልፍ ብጥይ ጥለት ገፈፈሽ በሸራው
ተዳራሽ በብዕር በገሀድ በሰራው
ውል ለሌለው ሀሳብ የገፈፉት ገላ
አደባባይ ስትቀርብ ጥበብ ነች ተብላ
ጣይና ጨርቅሽን
ሁኚው የገሀድ ቀለም
የለም የለም
አንቺ አይቶ ዝሙት የለም

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍327👎5
አበባዬ ነበርክ የትንፋሼ ፊደል
የመኖሬ ምክንያት የነፍሴ መታደል
መጨከን የምችል አይመስለኝም ነበር
እስክትቃወመው የመውደዴን ነገር
ምንም ብታፈቅረኝ ውበቴን ብታደንቅ
ትችል አልነበር ወይ ህጎቼን መጠበቅ
አሁን ስናፍቅህ ከፍቶህ ስትጨነቅ
በቀረ ትል ይሆን ምናል ብጠነቀቅ

እራሴን እንደምን አረኩት ብቸኛ
መልካም ሰው ያገኘች ነበርኩ እድለኛ
ወራት አልፈው ነበር ብዙ ሳትጠጋ
ድንገት ተቀበልኩህ አንድ ሆንኩኝ ካንተጋ
የለሰለሰችው የልጅነትህ ፀሀይ
ለመሆን መረጥኩኝ የፍቅርህ ተከታይ

ይቅርታህም በዛ የከበደህ ሲቀል
እኔም ተበዳይ ሆንኩ በራስ የመታለል
እንዳልተማመንኩኝ እንደማልጎዳ
ያ ምቹ እቅፍህ ሆነብኝ እንግዳ
አይንይህም ከአይኖቼ በድንገት ተለየ
ያልከውን ለመሆን እጅጉን ዘገየህ

ይቅር እንደምልህ የተማመንክበት
ምን ይሆን ያሸሸህ ከሰጠሁህ ገነት
ምንድነው ያስናቀህ የጠለቀ ፍቅሬን
ለምን አልበቃህም ስትስም ከንፈሬን
እኮ እንዴት ችለህ እንዳልሳሳህልኝ
ጭንቀቴን አበዛህ እንዴት ጨከንክብኝ

እንደምን ልርሳልህ ያን የውሸት እንባ
ሀሳቤን ስትቀይር ሆዴን ስታባባ
እኔም ተንደርድሬ ከአእቅፍህ ስገባ
ቃልህ ተሰበረ ሆንክ የእምነት ሌባ
እኔስ ተሞኝቼ ከልቤ አፍቅሬ
እፊትህ ማለቅሰው ነበረ የምሬን

ለማትስተካከል ላትቀየር ነገር
እኔንም ስታገኝ ከሰነፎች ሀገር
ድካሜን ሳሳይህ አክመኧኝ ነበር
የተጠገነ ልብ ዳግመኛ ሊሰበር
እጆችህን ይዤ አይኖቼን ጨፈንኩ
መራኧኝ ወዳንተ ከራሴም ራቅኩ

ተደበቄ ሳለሁ ካንተ ተለጥፌ
ሙቀትህን ስሰርቅ ስዳስ በመዳፌ
አበባና ሻማው በድንገት ተረሳ
መልክህ ተለወጠ እጅህም ተነሳ
ልቤም ደነገጠ እየጠረጠረ
ለማመን ከበደው ልክ እንዳልነበረ
ያደረከው ነገር ሰበቡን ባቶስድም
አስለመደኧኛል ስህተት መደጋገም
ፍቅሬን ያቆሸሽከው ሳታውቅ አልነበረም

By - @mondalit

@getem
@getem
@paappii
👍2621😢10😱2
#ሩብ_አንድ_ሌሊት

መነሻ ሀሳብ
ስብሃት /እግዚአብሔር
(
ሌቱም አይነጋልኝ 1993 / )
.
.
እቱ፤
ይቅር ምናባቱ፣
አይነጋ ሌሊቱ።
ይለፍ እንደዘበት፤
ይጠቅለል ዐመቱ።
ሀሳብ እንደረሳ፤
እንደ ግልገል ሞሳ፤
'ቅፍሽ ስር ልክረም።
ሀሳቤን ሰብስቤ፤
በለዛሽ ተስቤ፤
ከልብሽ ማዕጠንት
ሰግጄ ቆርቤ፡፡
በጨዋታሽ ስጥም፣
ሎሚ ጉንጭሽን ሳም፤
ልዛል እንደገና
በመዓዛሽ ድክምም፣
ባለንጋ ጣቶችሽ
እሽት አከም አከም፤
እወገቤ ግድም፤
ቧጠሺኝ ደም በደም፣
ከዛ.....
ጡትሽ መሃል ጋደምምም።

በአይኖችሽ ስበት፤
በንግስናሽ ውበት፣
በትንፋሽሽ ሙቀት፤
በእጆችሽ ዳበሳ፣
በከንፈር ቀመሳ።
በጣት መነካካት፣
አፍንጫ መለካት።
ከዛ ደሞ መሳቅ፣
ከአይኔ ለመራቅ።
ከዛ ደሞ ማፈር፣
ሽጉጥ አንገቴ ስር።
በፍቅርሽ ........ም፣
እል.............................ም፣
እል.............................ም፣
እል.............................ም፣
ወዲያ ወደ ጥልቁ ወደ ፍቅርሽ አለም፡፡

እሰ...............ይ፤
እሰ...............ይ፤
እሰ...............ይ፤
ሽንቅጥቅጥ ዘመናይ፣
ቁጥብ አሳ መሳይ፤
አደብ አስገዢልኝ
ሽርክቱ አመሌን፣
እንደ ፀደይ ልፍካ
ደባብሺው አካሌን፡፡
ያድነኝ የሰራሽ
ከነፍስሽ ላይ ቆርሶ፣
ልጠግን መንፈሴን
ካንቺ ላይ ተገምሶ፡፡

እኔ.......፤
በስሉስ ተክኜ፤
ለሳቅሽ መንኜ፤
ዳማ ፈረስ ጭኜ፤
ሽምጥ መጋለብ፣
ሳቢ ደረትሽ ላይ፤
ድንግል መሬትሽ ላይ፤
ሰንደቄን ማውለብለብ፡፡

ግልብ
ጋለብ
ብትን
ስብስብ
ያዝ
ለቀቅ
ጋለል
ንቅንቅ
ልጓም
ንጥቅ
ጦሬን
ነቅነቅ
እልም
ውርውር
አንገት
ስብር
ናጥ
በጥበጥ
እፍር
ቅብጥ
ጨምቅ
ቁንጥጥ
እሽት
ጭብጥ
እቅፍ
ቧጠጥ
ስንን
ሰክን
ስፍስፍ
ጥንን
ፍትት
ጥግን
ፈንቀል
ጀነን
በላብ
ስጥም
ሳቋ
ሲጥም
.
.
ሳም
ንክስ
ብትን
ቅስስ
ጭልጥ
መለስ፣
ሳብ
ግፍትር
ለስለስ
ግትር፡፡
ጎንበስ
ቀና
ፍርት
ዘና
ከዛ ተንፈስ
ሻጥ መለስ
እንደገና፡፡
.
.
የእግዜር መና።

አይይይ ቁንጅና!

አቤት ውበት፤
ሴት የሆነ የሴት ገላ፣
የሚመጠጥ ማር ወለላ።
መቃ መሳይ ያንገት ማኛ፣
መለስለሷ ማያስተኛ።
በየት በኩል በየት ገና፣
አንገቱዋ ስር ትኩስ ዳና።
ደረቱዋ ላይ መጋል ፍሬ፣
ነዳፊ ንብ ጥርኝ አውሬ፣
ትላንት ናፍቆት ምን ነሽ ዛሬ?

መጠንሰሻ የዳማ ምንጭ፣
የመሰንበት የመኖር ፍንጭ፣
ጡቷ ግድም ጥቁር ነጥብ፣
ፍም ትንፋሽዋ የሚያስጥም።
ሴት አካሏ ምትሃተኛ፣
መልኳ ድርብ የመልከኛ።
ልዝብ ሳቋ የሚደረጅ፣
መዓዛዋም የደብር ደጅ።

እይት
ሰረቅ
ዳሌ
ነቅነቅ
ጥርስ
ገለጥ
ጥብብ
መሰጥ
ከላይ
ረጋ
ከታች
ጠጋ
አይን
ጭፍን
ድርብ
ሽፍን
ብትን
ብትን
ደሞ
ስብስብ
እቅፍ
እስብ
ትንፋሽ
ስርቅ
ልብ
ድልቅ
ጉስም
ጉስም
ግርሽት
ድፍርስ
ፀጉር
ነስነስ
.
.
"ኸረ ቀስ"
"ኸረ ቀስ"
.
.
ሶስቴ
መሄድ
ለመመለስ።
.
.
ዘራፍ ወንዱ......!!!


✍️ ዓቢይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
👍5720🔥18😱9🤩7👎2
ተከታይ የሌለው አንድ
(ሳሙኤል አለሙ)


መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።
መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለተገዢው ልቤ
ክዳው ለማትገባው።
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።

ቀርበው ሲጠይቁኝ...
አንዱን ልቤን
እያስለካው፤
አንዴ ልየው ሲሉኝ...
አንዱን ልቤን
እያስጠጋው፤

ስኖር...አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
ላንዴ...ስኖር...ስኖር...ስኖር...ስኖር
ስኖር..አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
በስንቱ አንዴ-ዎች
አንዱን ልቤን፥ ላንዴ ሳስሞክረው፤
አለሁኝ በተስፋ
ገዢ እንደቸገረው።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu


@getem
@getem
@getem
👍15🔥65😢3
( ቆየን አይደል .. )
==============

ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...

ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ
በመደሰት ካስተዋልን ....

ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....

ቆየን አይደል ?

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
72👍37😢14🔥2🎉2
እኔ እማ

ወይ አልሞት ወይ አልድን፣
በናፍቆቷ ስዝል በፍቅሯ ስታጠን፤
ገለባው መውደዴ ወይ ከሷ ራስ አይወልቅ፣
ዋጋ አልባ ተሥፋዬ አይለቅ አይላቀቅ፤
የሸበተ ጸጉሬ ማመሃኘት አይተው፣
ላስረጀችኝ እሷ ከገዳም አልገባው፤
ወይ አልሞትኩ ወይ አልዳንኩ ግራ ነው ነገሬ፣
ካንዱ ልጠጋ ነው ከዛሬ ጀምሬ።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@getem
27👍11😁8🤩2
መሳቀቅ
ካልወሉበት ዉለው ባለቤቱን ማነቅ
መደንገጥ
ያለርባን አሳቦ ልብ ምት ማቋረጥ
መታመም
አሜን ለማይል ልብ ሰርክ ሁሌም መሳለም
ማርገብገብ
ለነደደ እሳት ለዕፍታ መስገብገብ


ለማትረጋ እርግብ ጎጆ እየቀለስን
በበረረች ቁጥር ስንት ጊዜ አለቀስን
እያወቅን ስራችን እንደሌለው ጥቅም
በጨዋታ መሃል ስቀን አናስቅም
ማርገብገብ ለምዶብን ለጊዜ ተቀማጭ
እንራወጣለን እስክንሆን ተለዋጭ
መሆንን ሳናውቀው ኑረን በጉድ ሀገር
ደሃ አድርጎ አስቀረን ልማድ ሚሉት ነገር

ለመሆን ሳንጥር ስንት ጊዜ ፈጀን
       በማስሆን አረጀን
ለነዋሪ ጊዜ ሆነን አኗኗሪ
         አደረገን ቀሪ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍336
በእናትህ እቀፈኝ

ለልጅህ እጅ ዘርጋልኝ ማደፌን አይተህ ላታልፈኝ፣
ጌታ ሆይ አምላኬ ባክህ በእናትህ አግዜር እቀፈኝ።

በእናትህ እቀፈኝ ...

ከክንድህ አፈንግጫለሁ በተግባር ከቤትህ 'ርቄ፣
በሀጥያት ተጎሳቁዬ ቆሽሼ በአለም ወድቄ፣
አትሁን ያልከኝን ስሆን አትስራ ላልከኝ ስተጋ፣
ጎንህን እንደ ለንጊኖስ አድፌ አንተን ስወጋ፣
መቅደስህ ውብ ሰውነቴን በእርኩሰት እቆሽሻለሁ፣
በእናትህ እቀፈኝ ጌታ ካቀፍከኝ እመለሳለሁ።

ለበደልኩህ በደል ላደረስኩብህ ግፍ፣
በምህረት ካልመጣሁ ከላይ መቅሰፍት አርግፍ፣
አንደበቴን ዝጋው ቅስሜንም ሰባብረው፣
ሃሳቤን አጨልም እውቀቴን ቅበረው።
መዝለሌን ግታልኝ ለሀጥያት ምርኮ፣
አቅሜን አንበርክከው ለክርብርህ አምልኮ፣
የአለም ጉልበቴን በሽንፈቴ ተካ፣
አለምን ልናቃት በስምህ ልመካ፣
ሰው አርገኝ ጌታዬ ልጅህን አትርፈኝ፣
አምላኬ በድንግል በእናትህ እቀፈኝ፣

ማወቄ አልጠቀመኝም ማደጌ እያደር ጎዳኝ፣
መናገር ከንቱ ልፋት ነው ለነፍሴ አንድም አልረዳኝ፣
ባውቀውም ምን እንደማደርግ በሀጥያት እንደተመራሁ፣
መመለስ ባለመቻሌ ለነፍሴ አሁንስ ፈራሁ፣
ፍርሀቴን ተቀበልና ለቤትህ ለንስሀ አብቃኝ፣
በእናትህ ጌታዬ እቀፈኝ ከእቅፍህ መራቈ በቃኝ።
በእናትህ እቀፈኝ ...
Join(@gitimtm)
ይቴ (@gtmwustie)

@getem
@getem
@gitimtm
👍5537
ፍቅር በቃኝ
እኔ ልበ ስንኩል ማፍቀር የተሳነኝ
የወደድኩትን ውድ ጨርሼ ማልገኝ
መውደድን ለመውደድ ኃይል ያጠረኝ

ካቅሜ አንጠፍጥፌ ልጠቀለል
ባንድ ሰው ሥር አረፍ ልል
ብጥር ብጥር
ለጨዋታ ሆኗል አሉ የፍቅር ነገር 
እውነት ቀርቶ በትብብር

እንደውም
ሰዶ ማሳደዱም ደክሞኛል ሰጥቶ መቀበሉም እንዲሁ
የገባው ሰው እስኪመጣ የራሱ የፍቅር ትርጉሙ
መፅሐፉ ላይ የተፃፈው እንደዚህ ነው የተባልነው 
እርሱ ሰው ተገኝቶ እስከሚያሳርፈኝ
ፍቅር በቃኝ

By yodan

@getem
@getem
@getem
31👍28🔥5👎2
* ስትፈጥን አትቸኩል *


አበው የተረቱት ቃላቶችን መርጠው
ከመናገር አልፈን ውስጥ ውስጡን ብናየው
የቃላት መረጣ የአስተሳሰብ ርቀት
የምሳሌ አይነታ ይንግግር ምጥቀት
”የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል”
የሚለውን ስናይ ውስጡን ስንመረምር
ከቃላት ዉስጥ መርጠን ትርጉም ስንበረብር
የተጠቀሙት ቃል ስህተቱን መግለጫ
ጥፋት ሁኖ አገኘን የ ችኩል መቋጫ


እዚጋር ልብ አድርግ
ላዩ ግልጽ ቢመስልህ ሃሳቡ እንደ ጀንበር
ትርጉሙ ረቂቅ ነው እንደ ወርቅ ሚቆፈር
የጅቡ ጥፋቱ የጅቡ ስህተቱ
አይደለም ፍጥነቱ ...


ፍጥነት መሄጃ ነው የጊዜ መለኪያ
የማስተዋል ስራ የሰአት ማትረፊያ
ፍጥነት ግዜያችን ነው ቶሎ መገስገሻ መሪያችንን ሳንለቅ በሰአት መድረሻ
ችኩልነት ግን የማስተዋል እጥረት
የዉሳኔ ችግር የቅንብር ድክመት
በጎን የሰሩትን በሌላው ጎን ማፍረስ
ሲለቅሙ የዋሉትን ከመሬት ላይ ማፍሰስ
ወደ ግራ ወደ ቀኝ ከፊት ወደ ኋላ
ዙርያን ሳያጤኑ እንዲያው በችኮላ
መራመድ ግብ አድርጎ ወደ ፊት መገስገስ
መድረሻ እያሰቡ እዛው መንከላወስ...


ዛሬን እያሰበ ነገውን ዘንግቶ
ነገን እያሰበ ዛሬዉን ረስቶ
እንደ ችኩሉ ጅብ መያዙን አስቦ ቦታዉን የሳተ
ዛሬን እያሰበ ነገን ያልገመተ
ከአደኑ በላይ ሌላ ስራ ፈጥሮ
በአደነው እንስሳ ቀንድ ተቸንክሮ
አለያም ...
መብላቱን አስቦ ረሀብ ጠንቶበት
ጠኔዉን ሊያስታግስ ሆዱን ሊያጠግብበት
ነገን እያሰበ ዛሬዉን ረስቶ
ቦታ ስቶ ቢነክስ ማስትዋል ዘንግቶ
ፍጹም ከገመተው ነገር ተዟዙሮ
እራሱን አገኘው በደሙ ተነክሮ


እናም አደብ ግዛ ማስተዋሉን ይስጥህ
ፍጥነትን ስታስብ ችሎታው ይኑርህ
የመወሰን ብቃት መሪው አይለይህ
የአበውን ተረት በጥልቀት ስናየው
አትፍጠን ሳይሆን ...
ስትፈጥን አትቸኩል ሁኖ አገኘነው።

By ዘይድ ሁሴን
ቅዳሜ ፣ ጥር 24 ፣ 2017 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍6242🎉9🔥3😢2🤩2
አካል ቡጢን ፈርቶ
በምላሴ ሸጥኳት
እህቴ ናት ብዬ
እኔው ሚስቴን ዳርኳት

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
😁53👍28😢119
ማጉያ

ያንዳንዷ ቆንጆ ሴት:
ውበት የሚጎላው:
በምታስከትላት:
አስጠሊታ ሴት ነው::

By yisimak worku

@getem
@getem
@paappii
😁82👍4022👎9🤩6🔥4😱4
📌 Free entry

Short movie
Comedy
Music ( full band )
Poem
Magic
Live painting & other ..

0935697143

for previous show, Check our channel 👇

https://youtube.com/channel/UC9ItbVvxXMLV7QIT-rCJyTg?si=Mj5GlhjsE1ZvBtjM


@getem
👍192🔥1
ስንብት
----------------- ተሰነባብተንም አይቆሮጥልኝ ፍቅርህ በኔ ላይ ካስቻለህ ያው መንገዱ ይቅናህ ። ሁሌ ማወዛገብ ሁሌ ማስፈራራት ሁልጊዜ መታመም ሁሌ መሰቃየት ለኔ ካሰብክልኝ እስኪ ልቤን ያዛት ። ጭንቀትህን ንገረኝ ህመምህን ልታመም ልሞት ነው አትበለኝ .......... ፍቀድልኝ እና እንይ ይቺን አለም። እጅህን ልያዛት ከሞትንም አብረን ነው አይተን ያለም ግዛት። እየተሰናበትክ ነፍሴን አስጨነካት የኔ ፍቅር ፍቀድልኝ እና ነፍስህን ልያዛት ።

by Bline asefa

@getem
@getem
@paappii
51👍21👎11🔥1
2025/07/10 11:43:38
Back to Top
HTML Embed Code: