Telegram Web Link
ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ

ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ

ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)

አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ

እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር

በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)

ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
20👍17🔥2
ላረፈድሽው


እኔማ ጠባቂሽ
ማርፈድሽን አላይም መምጣትሽን ብቻ
ድረሽልኝ እንጅ
በዘመኔ ማብቂያ በዕድሜዬ መባቻ

ፀጉሬ ቢሸበባብት ስጋዬ ቢጃጅም
ይበስል እንደሁ እንጅ
መንፈስ አያረጅም
ነይ ፍቅሬ ወጣት ነው ልቤም እቶን እሳት
የተገላቢጦሽ ቢያደርገውም ቅሉን
የዘመን መሳሳት
ከመቅረት ይሻላል ከመጣሽ ቢረፍድም
ፅልመት ካልገፈፈ ወትሮም ጎህ አይቀድም

By @poem2513

@getem
@getem
@getem
36👍20😢3🔥2
..........



አላቅም
አታቅም
የልቧን ተናግራ
ዝምታ ሰብራ
ጭምት ነበረች
እኔን ስታገኝ
ቃላት ፈጠረች
የፊደል አይደል
የቋንቋ በደል
ውሸት ነው የሚሉት
ነገ ላይ ደርሰው
ክደው
አፍርሰው
የቋንቋ አይደለም
በፍቅር ቀለም
ከገጽ ከአካሏ
ምልክት ስላ
ከሩቅ ነበረ ያናገረቺኝ
ደምቃ የታየቺኝ
አታቅም
አላቅም
ሴት አሽኮርምሜ
ከንፈር ተስሜ
ገላን በጠረን
ናፍቆት በዘፈን
አላባበልኩም
አላጫወትኩም
ጭምት ነበርኩኝ
ሰው የሚሞቀኝ
ወሬ የሚርቀኝ
ጥርሶቼ ስቀው
እግሬ ቦርቀው
ቀን ያላለፉ
አንቺ ጋር ደርሰው
ተኮላተፉ
መሳም አማረኝ
ያማረ ጉንጯን
አገጭ.....አገጯን
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
መኖር እየሳሙ
ከእቅፏ
ከአፏ
ህይወት ታዘንባለች
መኖር ታስርባለች
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
ክፉዋን ሳይሰሙ
አምላክ እንደው ጨካኝ
ክፉ
ዐዕላፍ ሳይረግፋ
የሰው መንጋ
ሞት ከደጇ ላይጠጋ
ገዝቼላት ሞትን
መለየትን
ከዘር እዳ ልነጥላት
እኔው ሞቷን ልሙትላት
ዕድሜ አውሼ
ተውሼ
ከእባብ ከሚዳቆ
ከዛፍ ከሸንበቆ
ትንሽ ዕለት
ትንሽ አመት
ተመጽውቼ
ልሙትላት
ሞቷን ትቼ
አላቅም
አታቅም
ብቻ በሰው አቅም
አኛን አንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን
የጭምቶች ፍቅር
የአይናፈሮች ሀገር
ማገር
ሆነልኝ አለማወቋ
አታቅም እንጂ
ያሰግራል ሳቋ
ሀቋ
ከፊቷ ላይ ቅራኔ የለም
የኔ አለም
ባታቅም
ባላቅም
በሰው አቅም
እኔና እሷን እንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍6626😁3
መለያየት ማለት

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

By Efrem seyoum

@getem
@getem
@paappii
38👍17😢8🔥1🎉1
መለየት

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡

By እውቀቱ ስዩም

@getem
@getem
@paappii
52👍30😢9🔥6🎉2
የ'ግዜርን ነፍስ ሴጣን ልብን አድሏታል
ላይዋ ታቦት ታቿ ጣዖት ተዋርሷታል

ልጅ እያለች ስትድህ ገና ያወቀችዉ
አፏን ገና ስትፈታ በቀል የሚል ቃላቶች ነዉ ያወጣችዉ

በ።ቀ።ል
እልል...............

በእናቷ እቅፍ ገብታ በአንቀልባ ዉስጥ እያለች
ስለአባቷ መርዛማነት በጡጦ አርጋ ጠብተዋለች

ጥ።ላ።ቻ
እልል..................

እሹሩሩ አታዉቅ እናት
አባቷን ነዉ ምጠራላት

ህ።መ።ም
እልል...................

እልል
ዛሬ
ነፍስ አወቀች
ፍቅርን ሻተች
ምን ታደርገዉ ሴጣን ልብን ተዋርሳለች
የአዳም ፍጥረት ትጠላለች።


@Tizita21


@getem
@getem
@getem
31👍23😢7🤩2🔥1🎉1
ተራማጅ ነን እኛ!
.
በመንገዱ ኹሉ - እሾህ እየወጋው፣
ባዕድ እየኾነ - የከረመ ሥጋው፣
(እንዴትም ቢያሰጋው፣)
እየተገጫጨ፣
ደም እየተረጨ፣
ያብሮነት ሕልማችን - ቁስል ቢያስነክሰው፣
ተስፋ አይቆረጥም - በ’ርምጃና በሰው።

By abere ayalew

@getem
@getem
@paappii
👍3318🔥6
*
የሚበድላት ሰው
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።

የትኛውን ትመን?

መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!

ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።


by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
👍3521😢7🔥5
ተለያይቶ ማፍቀር
በህልም እንቆቅልሽ ዘላለም ማሽቀርቀር
ይህም ይቅር ፍቅሬ በኑሮ መታጠር
ታሰረ ፍቅራችን ልክ እንደዘራችን
ዘመመ ቀናችን

by almseged wolde

@getem
@getem
@getem
👍37😢128
የመረጥኩት
========
----------------
በበለሱ ቅጠል
በፍሬ ያገኘሁት፣
ምርጫ ሆኖ ሳለ
ግዴታ ያደረኩት።
ሞት ይሉት ጨለማ
የአለም ህይወት ገደብ፣
ወደድኩም ጠላሁም
ከሱ ባላመልጥም።
ህይወት ይሉት ስካር
ህመም ያሉትም ጣር፣
ስቃይ ያሉት ስሜት
የብቸኝነት ቃር ፣ አንዳንዴም ከሰው ጋር።

በአለም ባህር ተጠምቄ
ጨዋማነት የመረረኝ፣
ምርጫ ያጣሁ እንደሆነ
ሞትን መምረጥ የሚያሰኘኝ።
እኔ ስሱ የትብያ ልጅ፣
የሞት ፅዋ የምጎነጭ።
ምሬት በዝቶ መግቢያ ባጣ፣
ሞትን ደብል ጠጣኋታ።

ከሞት በፊት ከምርጫዬ የረሳሁት፣
ሞቼ ሄድኩኝ ከሚወደኝ አምላኬ ፊት።
የመረጥኩት፣
   ካልመረጥኩት አምላኬ ጋር አገናኘኝ፣
የመረጥኩት፣
    ከአምላኬ ጋር አለያየኝ።
ምናለ ብዘገይ።



ሞት ምርጫ አይደለም
  ግዴታ ነው።


@abela_black

@getem
@getem
@getem
👍3112🎉3🤩1
እየወደድኩ ብለያትም
                 እንዳልነበር ስንት ስሳል
       "ዛሬ አትበልጥም ካንቺ አምሳል"
እያልኩሽ ይነጋል.....
በውበት የናኘ
ውበት ያከነፈው
ምስኪን ልቤን ይዤ
"ብለያትም ምንም እንኳ
ዛሬም እኮ ያምራል መልኳ
ባፈቅራትም እስአ ጥጉ
ማን ይደርሳል ከዛች እንቁ"

እላለሁ ተክዤ።

እየናፈኩ ብርቃትም
እንዳላልኳት ከኔ አትራቂ
"አትደርስም ካንቺ ፀዳል
ትበልጫለሽ ስትስቂ"
እያልኩሽ ይነጋል

ይነጋል
ይነጋል
ይነጋል

ለይስሙላ ኑሬ ከክንዶችሽ እቅፍ
የማልመው እሷን በዕውን በእንቅልፍ

ያገረሻል ቢይልፍም ፍቅሯ
አይረሳም ስር ጥንስሷ
ሌላ ቢያቅፍም ክንድ አካሌ
ትናፍቃለች ደጋግማ እሷ

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
17👍13🔥9
(መልክ ልስራ ይቅር?)
ለጌጥ ልኑር ለውበት?
     ውስጥ አዳክሞ እላይ ኩራት
ልዋብ ለታይታ ለሰዎች እይታ?
      ላይቀርፍልኝ የእንባዬን ጠብታ
ሆዴ ባዶ ከአንጀቴ ተጋምዶ
            የኔ ይሉኝታ ጉድለቴን አይፈታ!
ልተወው ታዲያ የላይኛውን ውበት?
          ልመገባት የማምሻዬን እራት?
ይገምቱኝ በአሁኔ ገፅታ?
        ልተው  ጭንቄን ማሰብ ለይታ?
ይቦጭቁኝ በወሪያቸው?
          ያስለቅሱኝ በሳቃቸው?
      እሺ ምን ይሻላል??
  ሰው ለአይን ውበት
         ፆሙን እንዴት ያድራል??!
ግራ ገባኝ ከራሴው ስማከር
      እስኪ እናተስ መልክ ልስራ፥ ይቅር??
           ,,,,,,,,,,,,,,,,,,   #መሳይ ግርማ
@getem
@gexem
@getem
👍2313🔥3
#አወቅቴ (Déjà_vu)
.
.
ለመጥለቅ ጨረሩን፥
ሲሰበስብና፥ ማልዶ ሲዘረጋ
ወጋገን ያምታታል
ብርሃን ያምታታል...አድማስ ከተጠጋ
የገባው ይንገረኝ...
እየመሸብን ነው? ወይስ እየነጋ?

By Rediet Aseffa

@getem
@getem
@paappii
41👍22🔥6
አንዲት ውብ አበባ የተኮተኮተች:
መዐዛዋ ጥዑም ናርዶስ የሸተተች
አላፊ አግዳሚ መቀንጠስ ሚመኛት
ዛሬ ጠወለገች ምነው ምን አገኛት?
ጠፋ ያማረለት ጥቂት ዘመን በርካች
ከጥውልግ ጥግ አምላጭ
መልኩን አሰማምሮ ካባውን ደርቦ
እርቃን ነብሱን ገላጭ
ባይሆን መጨረሻው የሰው ልጅ ዳር ድንበር
የተኮተኮተች ያቺ ፅጌሬዳ ዛሬም ትኖር ነበር::
ብኩን ያልተረዳ አንብቦ ያልገባው
ማወቅ መረዳቱ እምነቱ ያልረባው
ሰላላ ሰው ሲያይ ደረቱን ይደቃል
የዛፍ ፍሬው መድረቅ መች አሳስቦት ያውቃል
አለም ትንሽ አለም ገፊ አለም ታካች
ምርቁዝ ቁስል ፈዋሽ ደሞ ራሷ ፈንካች
የተፈነከተ ልቡ ያባበጠ ሰንካላ ቁስለኛ
ፍሬዋን ቀጣፊ ደሞ ደሞ አድፋፊ
መሆኑ ቀማኛ
ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደለ የአለም
የማለዳ ደስታ የማለዳ ውበት ጀምበር ስትጠልቅ የለም
በሳቅ በውዳሴ እሰይ እሰይ ብሎ
ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ውብ ቃላት ደልድሎ
ለሀገር ያሽቃብጣል ላይ ታች ይሯሯጣል
ፍሬውን ገና ሲያይ ከነ ስሩ ይቆርጣል
እናማ.....ትናንትና ያበበ ዛሬ ከደረቀ
ከለጋው ቅርንጫፍ ፍሬው ከለቀቀ
የለመለመው መስክ ድንገት ከከሰመ
ተቃናልኝ ያሉት ደግሞ ከጠመመ
ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደል የአለም
የማለዳ ተስፋ የማለዳ ትጋት አመሻሽ ላይ የለም::

By kidist

@getem
@getem
@getem
👍4318🔥2
ለየ - ቅል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
የየግል ብሶት ፣ የየግል ችግር
የየግል ሩጫ ፣ የየግል ውድድር
የየግል ሀይማኖት ፣ የየግል ብሔር
የየግል አላህ ፣ የየግል እግዜር
የየግል ሀገር ፣ የየግል ስልጣን
የየግል መልአክ ፣ የየግል ሰይጣን
ይዘን እየወጣን...
በየ ግል ቆስለን ፣ የጋራ ፈውስ አጣን!!!

@getem
@getem
@paappii
👍11835😢10🔥9
ፍቅር ነው አውቃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።
መራር ፅዋ በመንገዴ፣
አንቺ ነሽ ወይ የኔ ገዴ።
እንደእንቅፋት እየመታሽ፣
ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ወጣሽ።
ዝብርቅርቋ አንቺ አለሜ
አለሽ ስልሽ የሌለሽው፣
ቢታየኝም ባይታየኝ
ፍቅርሽ እኮ አለ እላለው።

መች መሰለሽ፣

እንደ እሳት፣
ሲያደምቀኝ ወይ ሲያሞቀኝ ፣
ሌላ ጊዜ ስታስከፊኝ፣
ንዴት ሆኖ በግለት መልክ ሲያተኩሰኝ።

ፍቅሬ ሙሉ
ከልብሽ ውስጥ የጎደለለው፣

እንዳልተውሽ፣
ተዋት የሚል ዝግ ሀሳቤን
አይምሮዬ እየተወው፣
እራኩሽ ስል፣
ሸፋፋ እግሬ
እየዞረ ካንቺ ስር ነው፣
ልቤን ካንቺ
ፍቅርሽ ካልኩት እንዳስጥለው፣
ሳሰላስል
ካንድ ሀሳብ ጋር ተገናኘሁ፣

ሀሳቡ፣

አምላክ ወዶን
ፍቅርን በሞት ከገለፀው፣

ለምን ታዲያ፣
በሞት ማግስት በፍርድ ወንበር
ወደሲኦል የምንወርደ፣
ገባኝ፣ ለካ ፍቅር ትርጓሜው
መያዝም ነው መልቀቅም ነው።

ፍቅር ይዤ ባትመረጪኝም
ምርጫሽ ይሁን ፈቅጃለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለው
ለወደድሽው ትቼሻለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለሁ
እረስቼሻለሁ ይቅር ብዬሻለሁ፣

ፍቅር ነው አውቃለሁ።


@abela_black

@getem
@getem
@getem
👍5822🔥1🤩1
አለም እንደ ልቧ
ያሻትን አክብራ
ያሻትን ማሽቀንጠር፤

ህይወት ቅራቅንቦ
ዝም ብሎ ኖሮ
ዝም ብሎ መቀበር።

01|07|2017

By ኢዮብ(ዮ_ሚን)

@getem
@getem
@getem
👍6220🔥8🎉2
ኩሬ ብሆንም ፥ ባህር ይሉኛል
ለዐይን ባልሞላም ፥ ውብ አርገውኛል

ከንቱ ሆኜ ሳል ፥ "አንቱ" ነው 'ምባል
ዝምታዬ እንኳ ፥ ለጉድ ተነቧል

ኧረ ይሄ ነገር ፥ ግራ ያጋባል ...
እንዴት ሁሉም ሰው ፥

በሌለኝ አቅም ይተማመናል ?
እንግዲህ እንጃ ፥
ባንቺ ልብ አልፈው ፥ ቢያዩኝ ይሆናል።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
46👍11🔥1
አንቺና ጨረቃ
=========
መብረቅ ብልጭ ብሎ
ምስልሽን ሲፈጥር፤
ፀሀይ ስትስቅ ነው
አንቺን የምትመስል፣
ኩልል ያለ ውሃ
ሲያይሽ ይጠራል፣
ከዋክብትን አይተሽ
ስንቴ አሽኮርምመሻል።
ጨረቃ ደግሞ አይታ፣
ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣
እንደዘብ ጠባቂ
አንቺን ተከትላ፣
ከአጼ ቤት ጎጆ
ገባች ሰተት ብላ።
አውቀሽ ነው ቢባልም
አሁን አምኛለሁ፣
አንቺን ለመፈለግ፤
አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ።
ሰአሊ እንዳይስልሽ
ቀለምሽ አይገባም፣
ገጣሚ እንዳይገጥምሽ
ያለው ቃል አይበቃም።
ሆኖብኝ ነው እንጂ
እንደ አጼ ቤት ልጆች፣
መች እዋስ ነበረ
ዋንጫና ቁልፊቶች።
አውቃለሁኝ አዎ
በዚ ውስጥ አትቆዪም፣
በፍቅርሽ ተይዤ፤
በልቤ ብልቃጥ ውስጥ
አንቺን ባስቀምጥም፣

ሰበርሽው እሱንም፣

አንቺና ጨረቃ
ጭራሽ አትያዙም፣
ድንገት ብትያዙ፤
የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣
አንቺና ጨረቃ
መስበርን አተዉም፣
አንቺም ጨረቃም
ወደኋላ አትሉም።


@abela_black


@getem
@getem
@getem
👍54🔥65👎1
2025/07/09 06:02:31
Back to Top
HTML Embed Code: