Telegram Web Link
     ( ሚስትህ የኔ እኮ ናት )

አገሬው ቢተቸኝ በገዛ ድግሴ ሳለሁ ተባርሬ ፤
ስቀህ ብታየኝም አንተ ተደስተህ ሳልፍ ተማርሬ ፤

አዎን ያንተው መውደድ የራስህ ያረካት ፤
ሳታገባት በፊት ለኔ ሚስቴ እኮ ናት ፤

      የምሬን ስነግርህ......

አብልጬ ምወዳት ከራሴ ከሁሉ ፤
ሚስትህ ሚስቴ ደሆነች ባያውቅልኝ ሁሉ ፤
የሰው ሚስት ተመኘ ይለኛል ሰው ሁሉ ።

ግዴለም ይበሉኝ እነሱ ያሻቸውን ፤
ቆርጠው ይቀጥሉ ያለ የሌለውን ፤

አንተ ግን አደራ እንዳትዘብተኝ ፤
ደርሰህ በነሱ ፊት እንዳትቦጭቀኝ ፤

ወዳጅን መቀማት ፤
በለሆሳስ ማጥቃት ፤
ሳይቆፍሩ መቅበር ፤
ያውም ባንድ ጀንበር ፤
ሙሾም ሳይወረድ ፤
ምነው ሳይረገድ ።

ሰሚ ባይሰማልኝ ባላቆም ጠበቃ፤
ይኸን ሁሉ ነገር አርገህ ስታበቃ ፤

ሚስቴን ቀማኝ ብለህ ብትሄድ አቤቱታ ፤
ለወናፍ አፍ ሁሉ ብታቀርብ ስሞታ ፤

የምሬን ነው ምልህ ዳኛውም አይፈርድም ፤
እኔ አልከሰስም እኔ አልወቀስም ፤

ከቻልክ የሚስቴ ባል ምላስህን ሰብስብ ።

#ኢዮብ_አሰፋ
@yomin1_2

@getem
@getem
@getem
😁46👍4119😢10🤩1
እናፍቅሽ ይሆን

~ ~ ~ ~ ~ ~
ስቀሽ ስትለይኝ ስትሄጅ ካጠገቤ
ስትሰናበቺ ከሚወጅሽ ልቤ
ያመጣሽ ጎዳና ሲመልስሽ ወስዶ
መፋቀርን ክዶ ነግርኝ ሲሄድ መርዶ
እናፍቅሽ ይሆን ?

ታውቂው የለም እንዴ 🤔
ሀዘኔን ልረሳው መፍራቴን ልደብቅ
አጥብቄ መያዜን የቀሚስሽን ጨርቅ
ገና ሳትቀልጂ በመምጣትሽ
ብቻ እንደምፍለቀለቅ ።

ትውስ ይልሽ ይሆን ?
እናፍቅሽ ይሆን ?
እንደምሳሳልሽ ትሳሽልኝ ይሆን ?
እኔማ .....
እወድሽማለሁ አፈቅርሽማለሁ
አስብሽማለሁ ናፍቅሽማለሁ
አንቺስ አንቺ ሆዬ እናፍቅሽ ይሆን ?
እናፍቅሻለሁ ?

By ኢዮብ_አሠፋ(@yomin1_2)


@getem
@getem
@getem
50👍41🔥8👎1
( ነዳይ ... )
============

ውዴ ....

እግዜርን ፍለጋ በዱር በተራራ
ምድሩን አታስሽው
በምናኔ ጉዞ ዋሻ ለመገስገስ
እግርሽን አታንሽው
መውረድ ከጀመረ የማይቆም እምባሽን
ይቅር አታፍስሽው

ጽድቅ ያማረሽ እንደው
ነዳይ ልቤ ፊትሽ
ደጅሽ ወድቋል አንሽው !!!

By @kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍4128🔥1
#ጥርጣሬ

እጄ በካቴና፣ ታስሮ ተሸብቦ
በድን ሰውነቴ፣ በፖሊስ ታጅቦ
እስር ቤት ስነዳ ያዩኝ ሰዎች ሁሉ፣
“ያው ሌባ! ሌባ!” አሉ።

የኔን ንፅህና፣ እኔው እያወኩት
'ብዙኃን ይመውኡ!'
ምስክር እራሴን እኔ ውስጥ አጣሁት።

«እንዴት ይህ ሁሉ ሰው ይዋሻል ባንድ ቃል?
ብሰርቅ ነው 'ጂ እንግዲህ ማን ያውቃል?»

By Nureddin Issa

@getem
@getem
@paappii
👍5227🔥8🎉2
የማይነቃ ውሸት
(ሳሙኤል አለሙ)

እንደ ተወዛዋዥ ግንባር
በየምሶሶው የለጠፍሽው
"አለ" የምትለው አድባር፤
ሰርክ...
መዳኑን ብቻ አስለምደሽው፤
ሰርክ...
መኖሩን ብቻ አሳይተሽው፤
ሰርክ...
ሲስቅ...ሲጫወት
ይረሳዋል!
እንደሚሞት ካልነገርሽው።

@Samuelalemuu

@getem
@getem
@getem
👍1312🤩4
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
38👍32🔥6😢1
📢 NOTICE: Register Now for Xpert Training Institute’s Master Trading Program!

Are you ready to Master Trading with Experts? Xpert Training Institute, in collaboration with Jmad Capital Consultancy, presents a VIP & Mentorship Trading Program designed to equip you with essential and advanced Forex trading skills.

🔹 Programs Offered:

VIP Class – Comprehensive training covering essential trading concepts.
Mentorship Class (Online) – Advanced flexible learning with expert guidance from anywhere.
Mentorship Class (Offline) – In-depth coaching with hands-on learning experience.

📅 Program Details:

📌 Duration: 6 Weeks
📌 Class Type: Online & Offline (Flexible Schedule)
📌 Batch Limit: Only 20 Students Per Batch

📍 Registration & Contact Information:

📞 Call Us:
📲 +251953888882
📲 +251116504000

📧 Email Us: [email protected]

🌐 Register Now: Click Here to Register

🚀 Secure your spot today and start your journey to financial success!

Join our Telegram channel
https://www.tg-me.com/xpert_et
👍113🔥2🤩2
የመኖሬን ቅንጣት
በጥርሶችሽ ንጣት
ቀናውን እድሌን
በአይኖችሽ ብሌን
የነገዬን ድምቀት
በውበትሽ ስምረት
አየሁኝ ተስሎ
ነገ አንቺን መስሎ።
                 
By @poetkidus

@getem
@getem
@getem
61👍32🔥6😱2🎉1
ላይድን ቁስል፤
ጨዉ መነስነስ፤
ከድንጋይ ላይ፤
ዉሃ ማፍሰስ ፤
ለሟች ዘመድ ፤
ዳግም ማልቀስ፤
መኖር ካሉት፤
እንደዚህ ነው፤
ሳቅን ትቶ፤
መንሰቅሰቅ ነው።

By ዔደን ታደሰ

@topazionnn
@getem
@getem
69👍32🔥12
ብዬማ አልዋሽሽም

እኔ'ኮ ያላንቺ ምንም ነኝ ብዬ
ብዙ አልዘበዝብም
ስሚኝ አንቺ ሆዬ
ትተሽኝ ከሄድሽ
ልቤ ድንኳን ጥሎ
ደረቱን ይደቃል
ከሰው ተነጥሎም
ሀዘን ይቀመጣል
ከመኖር ተጣልቶም
ሞትን ይናፍቃል ።

ብዬማ አልዋሽሽም
ከተውሽኝ አልኖርም
ያላንቺ ምስቀዉ
ሳቄም ሳቅ አይሆንም
ስልማ አልዋሽሽም
ምን በወጣሽ ፍቅሬ
ባምላክ ትዕዛዝ እንጂ
ባንቺ አይደል መኖሬ ።

#ኢዮብ_(ዮሚን)

@getem
@getem
@getem
49👍37🔥1
ድህነት አስናቀኝ

መኖሬ መኖሪያው ጠፍቶበት እያንገዳገደኝ እያርበደበደኝ
ልክ እንደጥርስ ህመም እየጠዘጠዘኝ
ያኖረኝ ህመም እያመሳጠረኝ
ለከንቱ ትዝታ እጅ ስጥ እያለ ለዝሙት አኖረኝ
ውድቀቴን አፅፎ ህልሜን እያሳጣኝ
ህልሜን አስነብቦ ልቤን እያስደማኝ
ድህነት ያልኩትን የጥርሱ ህመሜን ዘላለም አስረሳኝ።

By አለምሰገድ ወልዴ

@getem
@getem
@getem
👍34🔥5🤩1
. ነፍስ

ምኞቷ መፈንጠዝ ወንጀልን ማትፈራ
የፈለገችዉን ገፍታ ምታሰራ
ከንቱ የሆነች ነፍስ ፍፁም የከሰረች
ስጋዬን የምታዝ መረን የለቀቀች
ደልቃ ደልቃ የደከመች ለታ
እኔን ትወቅሳለች...
የፈጣሪ ሎሌ የ ስሜቴ ጌታ።

ረቡዕ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍3216
ሥዕል ማሳል ለምትፈልጉ በሙሉ
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ


@seiloch
@seiloch
👍3616👎7🤩6🎉1
መባቻ ነው ይህ ኑሯችን የኖህ ሆኗል ዝማሚያችን
ግማድ ሆኗል ይህ ፍቅራችን
በዚች አለም የታሰረ ቅን ልባችን
ስማችን ነው እጣን ከርቤ ሙዳያችን
ከመረጥሽው አንቺ ካልሽው ካህን
ወጣንም ወረድን በደብተራ ምርኩዝ የተነከረብን
እኔ አንቺ ወይ ድውያችን
ታስሮ ኖሯል በደብተራ በመባቻ ፅኑ ኪዳናችን
እኔ እና አንቺ ወይ ድውያችን መሞቻ ቀናችን
በዘመን በታሪክ ስማችን ተመርጦ መደገሚያ ሆነ ለደብተራ ሸቶን

By አለምሰገድ ወልዴ

@getem
@getem
@getem
👍4213👎4🔥1😱1
መኖር
በፍላጭ ሰከንዶች፤
በሽራፊ ሰዓት፤
በደቂቃ ቅንጣት፤
እለት እየገፉ፤
ወራት እያለፉ፤
እየጣሉ አመታት፤
በዘመን ምትሀት፤
በአንዲት የጊዜ ጋት፤
መኖር መሳብ አይደል፤
ወደሞት መጠጋት ?
          
By @poetkidus

@getem
@getem
@paappii
37👍14
ፆመ እባላለሁ ፥ ፆሜን እየፈታሁ
(ሳሙኤል አለሙ)

እንቁላሉን፣ስጋውን እንዳልበላሁ
ሰው ያውቃል፤
ወተቱን ፣ እርጎውን እንዳልጠጣሁ
ሰው ያውቃል፤
ላግኘው ብየ
ልያዘው ብየ
እንዳልወጣኝ ፥ ክፉ ቃል
ሰው ያውቃል፤

አውቃለሁ አያውቁም
አያውቁም አውቃለሁ ፤
ስብሰለሰል ግዜ
ስንገበገብ ግዜ
የከንፈሬን ስሷን ቆዳ
--ልጬው እየበላሁ
ፆመ እባላለሁ ፥ ፆሜን እየፈታሁ።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@Getem
@Getem
@Getem
🔥31👍2421😁10😱1😢1
( የወጉት )
=============

ያኔ ....
አይሁድ በጭካኔ
ክንድህን ወጥረው
ለፍቅርህ ብድራት ለውለታህ ዋጋ
አምስት ችንካር ቆጥረው
ያለ ርህራሄ
በመስቀሉ አግድም
እጅህን ሲዘረጉት
አላወቁት እንጂ ...
ባንተ መዳፍ በኩል
እልፍ ልቦችን ነው በምስማር የወጉት !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
131👍26
ደህና ዋልሽ አልኳትኝ
የፈካውን ፊቷን በአይኖቼ እየካደምኩ
"እግዛቤር ይመስገን"
በጥፍጥ አንደበቷ በከንፈር ተማረኩ
"አንተስ እንዴት ከረምክ....ተስማማህ አየሩ"
ግርምታ እየያዛት ብመጣ በወሩ
"..ኧኧ....ይመስገን ጀሊሉ.."
     "ይመስገን ጀሊሉ"

"ምነው ጠፋህሳ ከሄድክበት ግድም
እንደው ቢቻል...ቢቻል
           አይደወልም አንድም"
"አፉ በይኝ አቦ....
ባይመቻችልኝ ነው መደወል መርሳቴ"
ተጠጋሁ ከፊቷ አሳረፍኩ አንጀቴን

"ይልቁንስ አንቺው
ከዛ ከሩቅ ሀገር ያመጣሁት አለ
ከተስማማሽ ላንቺ ብትለብሺው ምናለ"
   
      "ማርያምን..?......የታለ.."

"አለ ከሰነኩት...ከሻንጣዬ ግድም
ቢሆን ለደብርሽ ለባዕልሽ ግልድም"

"ደስ ይለኛል....ወላዲቷን"
ደስ ብሏታል የእውነቷን

"በል ና ቅመስ የቡና ቁርስ
       አልወረደም ገና አቦሉ"

"የለም ልሂድ.....ሌላ ጊዜ
ሳይብስብኝ ይህ ቀትሩ"

"ማይሆነውን....
እዚህ መተህ አትመለስ
የባታ ነው ፀበል ቅመስ"

"ወላሂ..ይቅርብኝ ሩቅ ነው መንገዴ
ባየሆን ልዝገን ካለው ባዶ እንዳይሆን ሆዴ"

ዘገንኩት ከቁርሱ ካፌ ላይ ወረወርኩ
ያመጣሁላትን ለገላዋ አስረከብኩ

"ባታ ትስጥልኝ አለሜ...."

"አሜን....ሙሃመዴ"



ዮኒ
    ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍5316🤩5
አልከነፍኩም ስላፈቀርኩ
          ተሰባበርኩ እንጂ የትም
መልስ የለሽም ለጥያቄ
             ልብሽ እኔን አያካትም
ያንቺ ፍቅር አሳነሰኝ
           ደጅ አስጠናኝ በዳጃፉ
ሰው እንደሆን ወሬ አያጣም
           ይለቅመኛል ሁሌ ባፉ
ህመም ብቻ ውስጤ እሳቱ
       አይዳፈን እየነደድኩ
መፈቀር ግን ህያው ሞት ነው
      ስቃይ ብቻ ማፍቀር ልኩ

አላመንሽም ያንደበቴን
        የማፍቀሬን ስር ትርጉሙን
አይወደኝም ሰርክ መልስሽ
      አላወቅሽም ጥግ ህመሙን
ተፈቃሪ ምን ግድ አለው
       ምን ቢፈቅር እንደሀገሩ
አፍቃሪ ነው ነገር ሚፈጅ
        የሚማገድ ለወደሩ


ትገርሚያለሽ አንቺ ብቻ
      አላመንሽም የኔን ፍቅር
አትወድህም ቢለኝም ሰው
     ከደጃፍሽ ዛሬም አልቀር

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍249🔥2
2025/07/09 01:06:12
Back to Top
HTML Embed Code: