Telegram Web Link
ደህና ዋልሽ አልኳትኝ
የፈካውን ፊቷን በአይኖቼ እየካደምኩ
"እግዛቤር ይመስገን"
በጥፍጥ አንደበቷ በከንፈር ተማረኩ
"አንተስ እንዴት ከረምክ....ተስማማህ አየሩ"
ግርምታ እየያዛት ብመጣ በወሩ
"..ኧኧ....ይመስገን ጀሊሉ.."
     "ይመስገን ጀሊሉ"

"ምነው ጠፋህሳ ከሄድክበት ግድም
እንደው ቢቻል...ቢቻል
           አይደወልም አንድም"
"አፉ በይኝ አቦ....
ባይመቻችልኝ ነው መደወል መርሳቴ"
ተጠጋሁ ከፊቷ አሳረፍኩ አንጀቴን

"ይልቁንስ አንቺው
ከዛ ከሩቅ ሀገር ያመጣሁት አለ
ከተስማማሽ ላንቺ ብትለብሺው ምናለ"
   
      "ማርያምን..?......የታለ.."

"አለ ከሰነኩት...ከሻንጣዬ ግድም
ቢሆን ለደብርሽ ለባዕልሽ ግልድም"

"ደስ ይለኛል....ወላዲቷን"
ደስ ብሏታል የእውነቷን

"በል ና ቅመስ የቡና ቁርስ
       አልወረደም ገና አቦሉ"

"የለም ልሂድ.....ሌላ ጊዜ
ሳይብስብኝ ይህ ቀትሩ"

"ማይሆነውን....
እዚህ መተህ አትመለስ
የባታ ነው ፀበል ቅመስ"

"ወላሂ..ይቅርብኝ ሩቅ ነው መንገዴ
ባየሆን ልዝገን ካለው ባዶ እንዳይሆን ሆዴ"

ዘገንኩት ከቁርሱ ካፌ ላይ ወረወርኩ
ያመጣሁላትን ለገላዋ አስረከብኩ

"ባታ ትስጥልኝ አለሜ...."

"አሜን....ሙሃመዴ"



ዮኒ
    ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
አልከነፍኩም ስላፈቀርኩ
          ተሰባበርኩ እንጂ የትም
መልስ የለሽም ለጥያቄ
             ልብሽ እኔን አያካትም
ያንቺ ፍቅር አሳነሰኝ
           ደጅ አስጠናኝ በዳጃፉ
ሰው እንደሆን ወሬ አያጣም
           ይለቅመኛል ሁሌ ባፉ
ህመም ብቻ ውስጤ እሳቱ
       አይዳፈን እየነደድኩ
መፈቀር ግን ህያው ሞት ነው
      ስቃይ ብቻ ማፍቀር ልኩ

አላመንሽም ያንደበቴን
        የማፍቀሬን ስር ትርጉሙን
አይወደኝም ሰርክ መልስሽ
      አላወቅሽም ጥግ ህመሙን
ተፈቃሪ ምን ግድ አለው
       ምን ቢፈቅር እንደሀገሩ
አፍቃሪ ነው ነገር ሚፈጅ
        የሚማገድ ለወደሩ


ትገርሚያለሽ አንቺ ብቻ
      አላመንሽም የኔን ፍቅር
አትወድህም ቢለኝም ሰው
     ከደጃፍሽ ዛሬም አልቀር

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
አወቅሽኝ

አወኩሽ
.
.
.
ተዋወቅን
በፍቅር ነጠቅን

ጨረቃን ዳሰስናት ኮኮቦችን ቆጠርን
ቅዳሴ እና አዛንን
አስቀደስን አፈጠርን
አወኩሽ
ወደድኩሽ
ከልብ ተመኘሁሽ
ለነብሴ ፈለኩሽ

አጌጥን በፍቅራችን አስቀናን ላገሩ
            ኮራን በመንደሩ
ወጣቶች ተያይተው
     "ሲያምሩ...ሲያምሩ" እየተባባሉ

ወደድሽኝ

ወደድኩሽ
.
.
.
ተዋደድን
በፍቅር አበድን
ነጎድን...ነጎድን...ነጎድን

ከአፍ ባልወጣ ቃል
መፋቀራችንን ሀገር ምድሩ ያውቃል
መገረም መደነቅ ለኛ ምንም ነው
         ተፋቅረን አየነው
ደላኝ ባንቺ ፍቅር
        ደላሽ በኔ ፍቅር
እኔ ለንቺ
አንቺ ለኔ ካለን ሁሉም ነገር ይቅር

አፈቀርሽኝ

አፈቀርኩሽ
.
.
.
ተፋቀርን
የዛሬን ትዝታ ለነገ ወቀርን።

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
"በይው ተቀየረ እንጂ  ትሪው አልተነሳም"

አሸናፊ ማስቲካ
በአርታዊ

ከ ሚያዝያ 18 -  ግንቦት 10

@seiloch
(የአብስራ ሳሙኤል)

ጥበብ ናት እሷ
ሽንሽን ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
ችቦ ናት ለአለም
ሳቋ
የድል ብስራት
ኩርፊያው እስራት
የአንገቷ ድሪ
ሸማ ቀሚሷ
ዜማ ናት እሷ
የህይወት ቃና
የመዳን ዜና
ከጡት ወተቷ
ከመቀነቷ
እያጎረሰች
ጎጆ የቀለሰች
ጥበብ ናት እሷ
ችቦ ነው ነፍሷ
ቁጣዋ ማዕበል
ዝም
ጭጭ ደርሶ
ክፋት ገርስሶ
ፍቅር የዘራ
ጥበብ ናት እሷ
የአምላክ ስራ
የእጅ የመዳፋ
እስትንፈስ የአፋ
የመዳን ድልድይ
የተስፋ ነብይ
መቀነት ፈታ
ጡቷን አሟሽታ
እያጎረሰች
ቀን ያደረሰች
ጥበብ ናት እሷ
ሸማ ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
ችቦ ናት የአለም
የመዳን ዜና
የመኖር ቃና
መራራ ወዟ
ድል ያስጎነጭን
የእኔን እንባዋ
ውስኪ ያራጨን
ቅድ ጥለቷ ገመና ጋርዶ
የመዳፍ ቁስሏ ትኩስ አብርዶ
ትውልድ ያኖረ
ችቦ ነው ሳቋ
ድል ያበሰረ
ጥበብ ናት እሷ
ሽንሽን ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
መርከብ የሆነች
ለጠፋች አለም
መቀነት ፈታ
ቀን ያሻገረሰች
ድል ያበሰረች
ጥበብ ናት እሷ
ዜማ ናት እሷ
ሷቋ
የድል ብስራት
ኩርፊያዋ አሰስራት


By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
ተዘነጋሽ አይደል ገፍተው አናናቁሽ
ከሳምንታት በፊት ንግሥቴ እንዳላሉሽ
የኔማ ሽሮዬ ብለው እንዳልተቀኙ
ጥለውሽ ነጎዱ ሚሽቱን ሲያገኙ
.
እኔን የኔ አበባ
እኔን የኔ እመቤት
50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት
.
እኔ የኔ አበባ
እኔን የኔ ንግስት
ሰው ብቻ አይደለም
ማግጧል ያም ብረት ድስት
.
ሁሉም ከድተውሻል
ሁሉም ትተውሻል
ትንሽ ብቻ ታገሽ 50 ቀን ቀርቶሻል
.
ያኔ ቀኑ ሲደርስ በእየንብርክካቸው
ማሪኝ ማሪኝ ሽሮ አይቀር ማለታቸው
.
እኔን የኔ አበባ
እኔን የኔ እመቤት
50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት
አለፈልን ብለው ቢያናንቁሽም
አትፍረጂባቸው!
የድሃ ብረት ድስት መቼም አይለቅሽም

#ስሜታዊ_ሆነው_ነው

[ ጥሩቤል ]
@ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
ህልም እልም
ሠዓሊ ስዩም አያሌው

በፈንድቃ
ከሚያዝያ 20 እስከ ግንቦት 4

@Seiloch
ከጎኔ ርቀሽ
ከሌላ ብትለምጂ ልሁን አልል ደባል
ብናፍቅ ይሻላል
የሚያፈቅሩትን ሰው አትናፍቅ አይባል

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
#አላት_መንገድ

አላት መንገድ የቁንጅና
አላት መንገድ ያንዳች ውበት



    ምትልበት

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
, ( ግዛትሽ ነኝ )

እንደ ሀይቅ ጠልቄ ከሃገር የሰፋሁ
አለሜን ስፈልግ ከአለም የጠፋሁ
በልብሽ መቅደስ ውስጥ አብሬ የተሰፋሁ
ሰፊ ግዛትሽ ነኝ
ወሰን ያልወጣልኝ ለክብሬ ዘብ ያጣሁ

ወሰንሽን ደፍረው ግዛትሽን ሳይወርሱት
በዳው መሬትሽን መንጥረው ሳያርሱት

ነይና ግዛትሽን አንቺው ዘብ ሁኝለት
መረቡን አስፊ እና ወሰን አብጂለት
ዳግምም አታገኝው ብትባክኝ በስለት
ችላ ያልሽው ግዛት ገዥ ሰው ያገኘ ዕለት

ውቢቷን ቀለሜን ውዲቷን ህይዎቴን
አለሜን ስፈልግ አለሜን ማጣቴን
ላንቺ እንዲህ መሆኔን አንቺ ግን አታውቂም
አንቺ ግን አንቺ ግን አንቺ ግን አታውቂም
እውነት እልሽ አለሁ ያለ እኔም አትደምቂም

By Habtish

@getem
@getem
@getem
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ

[ ጥሩቤል ]
@ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
አገኘሁ ብሎ ቀልቡ 'ማይጠፋ
አጣሁኝ ብሎ የማይከፋ
እንድሆን አርጎ ጌትዬው ካጨኝ
ብኖር ሸጋ ነው ፥ ብሞት አይቆጨኝ ።

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
የሰዉ ልጅ የሰራዉ
አብረቅራቂ መንገድ
ሳይታክት ይወስዳል
መዉሰዱ ሳይበቃዉ
አዙሮ አዙሮ....
እዛዉ ይመልሳል
እግዜር የፈጠረዉ
የሰዎች ዘመን ግን
አንድቀን ያበቃል
ሳይታሰብ
ያ  ል  ቃ  ል...........

By ዔደን ታደሰ

@ediwub
@getem
@getem
አንደበት

ከእሩምታው በላይ
እንደሀሳብ አታላይ
ከድርብ ገለባ....
በስማ በለው ላይ
ሰሚው ጆሮ ሊሰጥ
አክብሮ ቢገኝም...
በሀፍረት ባህር ውስጥ
ሰጥሞ ቢኳትንም....
ተናግሮ አናጋሪ
የዱር አጋፋሪ.....
ስስ ልቡን ለሰጠው
ጊዜ ቢታትርም
ለማገዶው እንጂ
ለቀን ለሌሊቱ...
አይቆረጥለትም።

          by ኢያሱ ከበደ
                ሚያዚያ 20 2017 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
( ለሆነ ሰው )
=============

ሁላችንም ....
ለሆነ ሰው መፈወሻ
ለሆነ ሰው ድብቅ ህመም
ለሆነ ሰው ጠባብ መንገድ
ለሆነ ሰው ግዙፍ ዓለም

የአንድ ስፌት ሁለት ህብር
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች

ለሆነ ሰው ክፉ መርገም
ለሆነ ሰው በረከቶች
ለሆነ ሰው መሸሸጊያ
ለሆነ ሰው ራቁቶች

ለፍርድ ቀን የማንመች
ግማሽ ጥቁር ግማሽ ነጮች !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
ሀቁን ሁሉም ሰው፡
ቢሸፍንም...
ሰው ካለም ክፋት ፡ እንዳይማር
በሴትነት ዘንድ የሚፈፀም
ትልቅ ወንጀል ነው፡
አለማማር!።
እንደ አምላክ በስም ባይመለክ
ባይሰዋለት ዘቢብ ፣ እጣን
ማንም ሸፋፍኖ የማይክደው
ውበት በሰው ላይ
አለው ስልጣን።
መልኳ ያልገነነ ምትደንቅ ሴት
ሀሳቧ አለሙን ቢያገናኝም
በቆንጆ ልጅ ሳቅ ይሸፈናል
ስባሪ ትኩረት ፡ አያገኝም፤
ምንም በህጉ ባይፀድቅ እንኳ
ቃል በቃል ሰፍሮ በትዕማር
ወደው እንዳረጉት የራስ ምርጫ
ትልቅ ወንጀል ነው ፡ አለማማር!።

by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
ግዴታ ሆኖ — ብለ፟ይሽ
ባላይሽ — ዳግም  ደግሜ....
የማይሞላን ባዶ ጊዜ....
(የቀረኝን ግንጥል ዕድሜ....)
በነፍስሽ ጠረን ትዝታ.....
በመንፈስሽ እኖራለሁ ፤
(አልጥልሽም አራግፌ..)
ተሸክሜሽ እዞራለሁ  ።

ባ`ካሌ — በስሱ ገላ...
በፊቴ — ደግሞ በኋላ....
በጣቴ — ጫፎች አሻራ....
በራሴ — በፀጉሬ ስፍራ ....
(ይዤሽ ነው — ዘመን ምሻገር !)
በልቤ  በደሜ — ማገር ፥
በሆንኩት — በቀረኝ ነገር ።

From: Charles Bokouski : “ Living on luck”¹
__
¹ =.......
ⁱᶠ ⁱ ⁿᵉᵛᵉʳ ˢᵉᵉ ʸᵒᵘ ᵃᵍᵃⁱⁿ
ⁱ ʷⁱˡˡ ᵃˡʷᵃʸˢ ᶜᵃʳʳʸ ʸᵒᵘ
ⁱⁿˢⁱᵈᵉ, ᵒᵘᵗ ˢⁱᵈᵉ
ᵒⁿ ᵐʸ ᶠⁱⁿᵍᵉʳ ᵗⁱᵖˢ
ᵃⁿᵈ ᵃᵗ ᵇʳᵃⁱⁿ ᵉᵈᵉᵍᵉˢ
ᵃⁿᵈ ⁱⁿ ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᵒᶠ ʷʰᵃᵗ ⁱ ᵃᵐ ᵒᶠ
ʷʰᵃᵗ ʳᵉᵐᵃⁱⁿˢ

By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
ሳትፈልጊ መስጠት ~ ፈልጎ እምቢ መባል አልለመደብሽም ፤

አጣሁ አልሸኝ እንጂ ~ አጣሁ የምትይው አልጎደለብሽም ፤

ትፈሪያለሽ እንጂ ~ ይታመምልሻል ያሳመመሽ ህመም ፤

የበደለሽ ሁሉ ~ ድሮ እንዳመለከሽ ፈፅሞ አይረሳውም ፤

እና ለኔ መውደድ ..? እና እምባ ከኔ ፊት..? ሀዘን ያጣላሻል ተይው ከመለኮት ... !

ሳትሞት አትተርፊም ግን ደግሞ ተርፈሻል ... እንኳን የኔ አይነት ሰው ሞት ይራራልሻል።

@getem
@getem
@paappii

By Natnael mulu
ካለብኝ ጸባይ

የግንባር ስጋ ነው እንደሚሉት አይነት ሆኖ ባህሪዬ
ነገሬ ፊት ለፊት ቀጥታ መጥራት ነው ሰውን ተፈጥሮዬ
አህያን አህያ ቅልን ቅል ብዬ😊😊

አንበሳን አንበሳ ቀፎውንም ቀፎ ብዬ የምጠራ ሁሉን በቀጥታ
ምን ይሉኛል ብዬ ሳይኖረኝ ይሉኝታ🤷‍♀🤷‍♀
  ተፈጥሮዬ ነዋ

"ጦቢያ"እንደጻፈችው

@getem
@getem
@getem
2025/06/27 16:25:32
Back to Top
HTML Embed Code: