Telegram Web Link
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
45👍22🔥4👎3
አወቅሽኝ

አወኩሽ
.
.
.
ተዋወቅን
በፍቅር ነጠቅን

ጨረቃን ዳሰስናት ኮኮቦችን ቆጠርን
ቅዳሴ እና አዛንን
አስቀደስን አፈጠርን
አወኩሽ
ወደድኩሽ
ከልብ ተመኘሁሽ
ለነብሴ ፈለኩሽ

አጌጥን በፍቅራችን አስቀናን ላገሩ
            ኮራን በመንደሩ
ወጣቶች ተያይተው
     "ሲያምሩ...ሲያምሩ" እየተባባሉ

ወደድሽኝ

ወደድኩሽ
.
.
.
ተዋደድን
በፍቅር አበድን
ነጎድን...ነጎድን...ነጎድን

ከአፍ ባልወጣ ቃል
መፋቀራችንን ሀገር ምድሩ ያውቃል
መገረም መደነቅ ለኛ ምንም ነው
         ተፋቅረን አየነው
ደላኝ ባንቺ ፍቅር
        ደላሽ በኔ ፍቅር
እኔ ለንቺ
አንቺ ለኔ ካለን ሁሉም ነገር ይቅር

አፈቀርሽኝ

አፈቀርኩሽ
.
.
.
ተፋቀርን
የዛሬን ትዝታ ለነገ ወቀርን።

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
46👍30👎3😁1
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
"በይው ተቀየረ እንጂ  ትሪው አልተነሳም"

አሸናፊ ማስቲካ
በአርታዊ

ከ ሚያዝያ 18 -  ግንቦት 10

@seiloch
👍12🎉3🔥21😁1
(የአብስራ ሳሙኤል)

ጥበብ ናት እሷ
ሽንሽን ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
ችቦ ናት ለአለም
ሳቋ
የድል ብስራት
ኩርፊያው እስራት
የአንገቷ ድሪ
ሸማ ቀሚሷ
ዜማ ናት እሷ
የህይወት ቃና
የመዳን ዜና
ከጡት ወተቷ
ከመቀነቷ
እያጎረሰች
ጎጆ የቀለሰች
ጥበብ ናት እሷ
ችቦ ነው ነፍሷ
ቁጣዋ ማዕበል
ዝም
ጭጭ ደርሶ
ክፋት ገርስሶ
ፍቅር የዘራ
ጥበብ ናት እሷ
የአምላክ ስራ
የእጅ የመዳፋ
እስትንፈስ የአፋ
የመዳን ድልድይ
የተስፋ ነብይ
መቀነት ፈታ
ጡቷን አሟሽታ
እያጎረሰች
ቀን ያደረሰች
ጥበብ ናት እሷ
ሸማ ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
ችቦ ናት የአለም
የመዳን ዜና
የመኖር ቃና
መራራ ወዟ
ድል ያስጎነጭን
የእኔን እንባዋ
ውስኪ ያራጨን
ቅድ ጥለቷ ገመና ጋርዶ
የመዳፍ ቁስሏ ትኩስ አብርዶ
ትውልድ ያኖረ
ችቦ ነው ሳቋ
ድል ያበሰረ
ጥበብ ናት እሷ
ሽንሽን ቀሚሷ
የዘመን ቀለም
መርከብ የሆነች
ለጠፋች አለም
መቀነት ፈታ
ቀን ያሻገረሰች
ድል ያበሰረች
ጥበብ ናት እሷ
ዜማ ናት እሷ
ሷቋ
የድል ብስራት
ኩርፊያዋ አሰስራት


By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
22👍18
ተዘነጋሽ አይደል ገፍተው አናናቁሽ
ከሳምንታት በፊት ንግሥቴ እንዳላሉሽ
የኔማ ሽሮዬ ብለው እንዳልተቀኙ
ጥለውሽ ነጎዱ ሚሽቱን ሲያገኙ
.
እኔን የኔ አበባ
እኔን የኔ እመቤት
50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት
.
እኔ የኔ አበባ
እኔን የኔ ንግስት
ሰው ብቻ አይደለም
ማግጧል ያም ብረት ድስት
.
ሁሉም ከድተውሻል
ሁሉም ትተውሻል
ትንሽ ብቻ ታገሽ 50 ቀን ቀርቶሻል
.
ያኔ ቀኑ ሲደርስ በእየንብርክካቸው
ማሪኝ ማሪኝ ሽሮ አይቀር ማለታቸው
.
እኔን የኔ አበባ
እኔን የኔ እመቤት
50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት
አለፈልን ብለው ቢያናንቁሽም
አትፍረጂባቸው!
የድሃ ብረት ድስት መቼም አይለቅሽም

#ስሜታዊ_ሆነው_ነው

[ ጥሩቤል ]
@ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
👍59😁3315🔥6👎1🤩1
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
ህልም እልም
ሠዓሊ ስዩም አያሌው

በፈንድቃ
ከሚያዝያ 20 እስከ ግንቦት 4

@Seiloch
👍274🔥1
ከጎኔ ርቀሽ
ከሌላ ብትለምጂ ልሁን አልል ደባል
ብናፍቅ ይሻላል
የሚያፈቅሩትን ሰው አትናፍቅ አይባል

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍2811😢5
#አላት_መንገድ

አላት መንገድ የቁንጅና
አላት መንገድ ያንዳች ውበት



    ምትልበት

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍2416
, ( ግዛትሽ ነኝ )

እንደ ሀይቅ ጠልቄ ከሃገር የሰፋሁ
አለሜን ስፈልግ ከአለም የጠፋሁ
በልብሽ መቅደስ ውስጥ አብሬ የተሰፋሁ
ሰፊ ግዛትሽ ነኝ
ወሰን ያልወጣልኝ ለክብሬ ዘብ ያጣሁ

ወሰንሽን ደፍረው ግዛትሽን ሳይወርሱት
በዳው መሬትሽን መንጥረው ሳያርሱት

ነይና ግዛትሽን አንቺው ዘብ ሁኝለት
መረቡን አስፊ እና ወሰን አብጂለት
ዳግምም አታገኝው ብትባክኝ በስለት
ችላ ያልሽው ግዛት ገዥ ሰው ያገኘ ዕለት

ውቢቷን ቀለሜን ውዲቷን ህይዎቴን
አለሜን ስፈልግ አለሜን ማጣቴን
ላንቺ እንዲህ መሆኔን አንቺ ግን አታውቂም
አንቺ ግን አንቺ ግን አንቺ ግን አታውቂም
እውነት እልሽ አለሁ ያለ እኔም አትደምቂም

By Habtish

@getem
@getem
@getem
28👍17
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ

[ ጥሩቤል ]
@ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
75👍37🔥10👎1
አገኘሁ ብሎ ቀልቡ 'ማይጠፋ
አጣሁኝ ብሎ የማይከፋ
እንድሆን አርጎ ጌትዬው ካጨኝ
ብኖር ሸጋ ነው ፥ ብሞት አይቆጨኝ ።

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
69👍21🔥8🤩1
የሰዉ ልጅ የሰራዉ
አብረቅራቂ መንገድ
ሳይታክት ይወስዳል
መዉሰዱ ሳይበቃዉ
አዙሮ አዙሮ....
እዛዉ ይመልሳል
እግዜር የፈጠረዉ
የሰዎች ዘመን ግን
አንድቀን ያበቃል
ሳይታሰብ
ያ  ል  ቃ  ል...........

By ዔደን ታደሰ

@ediwub
@getem
@getem
31👍25
አንደበት

ከእሩምታው በላይ
እንደሀሳብ አታላይ
ከድርብ ገለባ....
በስማ በለው ላይ
ሰሚው ጆሮ ሊሰጥ
አክብሮ ቢገኝም...
በሀፍረት ባህር ውስጥ
ሰጥሞ ቢኳትንም....
ተናግሮ አናጋሪ
የዱር አጋፋሪ.....
ስስ ልቡን ለሰጠው
ጊዜ ቢታትርም
ለማገዶው እንጂ
ለቀን ለሌሊቱ...
አይቆረጥለትም።

          by ኢያሱ ከበደ
                ሚያዚያ 20 2017 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍347👎1
( ለሆነ ሰው )
=============

ሁላችንም ....
ለሆነ ሰው መፈወሻ
ለሆነ ሰው ድብቅ ህመም
ለሆነ ሰው ጠባብ መንገድ
ለሆነ ሰው ግዙፍ ዓለም

የአንድ ስፌት ሁለት ህብር
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች

ለሆነ ሰው ክፉ መርገም
ለሆነ ሰው በረከቶች
ለሆነ ሰው መሸሸጊያ
ለሆነ ሰው ራቁቶች

ለፍርድ ቀን የማንመች
ግማሽ ጥቁር ግማሽ ነጮች !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
107👍34🔥15🤩4
ሀቁን ሁሉም ሰው፡
ቢሸፍንም...
ሰው ካለም ክፋት ፡ እንዳይማር
በሴትነት ዘንድ የሚፈፀም
ትልቅ ወንጀል ነው፡
አለማማር!።
እንደ አምላክ በስም ባይመለክ
ባይሰዋለት ዘቢብ ፣ እጣን
ማንም ሸፋፍኖ የማይክደው
ውበት በሰው ላይ
አለው ስልጣን።
መልኳ ያልገነነ ምትደንቅ ሴት
ሀሳቧ አለሙን ቢያገናኝም
በቆንጆ ልጅ ሳቅ ይሸፈናል
ስባሪ ትኩረት ፡ አያገኝም፤
ምንም በህጉ ባይፀድቅ እንኳ
ቃል በቃል ሰፍሮ በትዕማር
ወደው እንዳረጉት የራስ ምርጫ
ትልቅ ወንጀል ነው ፡ አለማማር!።

by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
👍2317😱6🔥3
ግዴታ ሆኖ — ብለ፟ይሽ
ባላይሽ — ዳግም  ደግሜ....
የማይሞላን ባዶ ጊዜ....
(የቀረኝን ግንጥል ዕድሜ....)
በነፍስሽ ጠረን ትዝታ.....
በመንፈስሽ እኖራለሁ ፤
(አልጥልሽም አራግፌ..)
ተሸክሜሽ እዞራለሁ  ።

ባ`ካሌ — በስሱ ገላ...
በፊቴ — ደግሞ በኋላ....
በጣቴ — ጫፎች አሻራ....
በራሴ — በፀጉሬ ስፍራ ....
(ይዤሽ ነው — ዘመን ምሻገር !)
በልቤ  በደሜ — ማገር ፥
በሆንኩት — በቀረኝ ነገር ።

From: Charles Bokouski : “ Living on luck”¹
__
¹ =.......
ⁱᶠ ⁱ ⁿᵉᵛᵉʳ ˢᵉᵉ ʸᵒᵘ ᵃᵍᵃⁱⁿ
ⁱ ʷⁱˡˡ ᵃˡʷᵃʸˢ ᶜᵃʳʳʸ ʸᵒᵘ
ⁱⁿˢⁱᵈᵉ, ᵒᵘᵗ ˢⁱᵈᵉ
ᵒⁿ ᵐʸ ᶠⁱⁿᵍᵉʳ ᵗⁱᵖˢ
ᵃⁿᵈ ᵃᵗ ᵇʳᵃⁱⁿ ᵉᵈᵉᵍᵉˢ
ᵃⁿᵈ ⁱⁿ ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᵒᶠ ʷʰᵃᵗ ⁱ ᵃᵐ ᵒᶠ
ʷʰᵃᵗ ʳᵉᵐᵃⁱⁿˢ

By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
👍3624🔥6🤩2😱1
ሳትፈልጊ መስጠት ~ ፈልጎ እምቢ መባል አልለመደብሽም ፤

አጣሁ አልሸኝ እንጂ ~ አጣሁ የምትይው አልጎደለብሽም ፤

ትፈሪያለሽ እንጂ ~ ይታመምልሻል ያሳመመሽ ህመም ፤

የበደለሽ ሁሉ ~ ድሮ እንዳመለከሽ ፈፅሞ አይረሳውም ፤

እና ለኔ መውደድ ..? እና እምባ ከኔ ፊት..? ሀዘን ያጣላሻል ተይው ከመለኮት ... !

ሳትሞት አትተርፊም ግን ደግሞ ተርፈሻል ... እንኳን የኔ አይነት ሰው ሞት ይራራልሻል።

@getem
@getem
@paappii

By Natnael mulu
25👍17🔥5🎉3
ካለብኝ ጸባይ

የግንባር ስጋ ነው እንደሚሉት አይነት ሆኖ ባህሪዬ
ነገሬ ፊት ለፊት ቀጥታ መጥራት ነው ሰውን ተፈጥሮዬ
አህያን አህያ ቅልን ቅል ብዬ😊😊

አንበሳን አንበሳ ቀፎውንም ቀፎ ብዬ የምጠራ ሁሉን በቀጥታ
ምን ይሉኛል ብዬ ሳይኖረኝ ይሉኝታ🤷‍♀🤷‍♀
  ተፈጥሮዬ ነዋ

"ጦቢያ"እንደጻፈችው

@getem
@getem
@getem
👍263👎3
ማር ወለላ ከከንፈሯ
ውበት አላት ከምግባሯ
ባነጋገር ምትቆርጥ ጥም
ስትቀመስ የምትጥም
ቅመሜ ናት ለመኖሬ
የወስጥ ቁልፍ የሚስጥሬ
ተፈጥሯዊ መልከ ሸጋ
ቀን ሲጨልም የምትነጋ
ባህሪዋ ወይናደጋ
የተሰጣት ፍቅረ ፀጋ
ከሷ
      ጋ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
🔥25👍1210
መተያየት በዝምታ
መተፋፈር ደግሞ ላፍታ
መፈራራት ለማናገር
ጉድ ሲቀለብ በጉድ ሀገር
መተያየት ዝም ብቻ
ፈገግ ማለት በፍራቻ
ፍርሃት ፍርሃት ለፍቅር ቃል
አላማውራት ያራርቃል


ዮኒ
     ኣትን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍5911🔥9🎉4🤩2
2025/07/08 22:24:20
Back to Top
HTML Embed Code: