Telegram Web Link
ማር ወለላ ከከንፈሯ
ውበት አላት ከምግባሯ
ባነጋገር ምትቆርጥ ጥም
ስትቀመስ የምትጥም
ቅመሜ ናት ለመኖሬ
የወስጥ ቁልፍ የሚስጥሬ
ተፈጥሯዊ መልከ ሸጋ
ቀን ሲጨልም የምትነጋ
ባህሪዋ ወይናደጋ
የተሰጣት ፍቅረ ፀጋ
ከሷ
      ጋ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
መተያየት በዝምታ
መተፋፈር ደግሞ ላፍታ
መፈራራት ለማናገር
ጉድ ሲቀለብ በጉድ ሀገር
መተያየት ዝም ብቻ
ፈገግ ማለት በፍራቻ
ፍርሃት ፍርሃት ለፍቅር ቃል
አላማውራት ያራርቃል


ዮኒ
     ኣትን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
ሰው ነበርኩኝ

ተወለድኩኝ
(ከመሀፀን ወደኩኝ )
አለቀስኩኝ
(ሀዘን ገባኝ ሰው ፈለኩኝ )
አፌን ከፈትኩ
(የሆድ ጥልቀት አወኩ )
በቃኝ አልኩ
( በእድሜ ሰከንኩ )
ጠረን ለየሁ
( ምቾት አየሁ )
ቋንቋ ለመድኩ
(በቆፈሩት ወረድኩ )
መልክ ለየሁ
(እኔን አወኩ  አዲስ ካየሁ )

አንተ ግን ለቤቴ
( እንግዳ ላጥንቴ )
ሆነህ የሩቅ ሩቅ
(እንደ ዘመድ እንቅ )
ለምን አደረኩህ ....?

ሴት ነበርኩኝ

የተጣፈ እጣዬ
( ግልጥ ጎባጣዬ )
ሊያውም በእኛ መንደር
( እንቢ ነው መግደርደር )
እያለ ከሚረግጥ
( በዘመን ረመጥ )
በዘር ማን ዘር እሳት
(የምትቃጠል ሴት) !!!

ጨዋ እኮ ነበርኩኝ

አፈነገጥኩልህ
( እራሴን ተውኩልህ )
ወፍ ሆንኩልህ ጫጩት
(ሳይበር እንደ ቀጩት )
ረግጬ ህጌን
(ገላምጬ ወጌን)

ክር እኮ ነበረኝ

የገባሁት ኪዳን
( የመነንኩለት ሀቅ በነፃ ለመዳን )
የወሰዳት ነፍሴን
( ያሳረፈኝ ምናብ ቆርጦ ግሳንግሴን )

ጌታ እኮ ነበረኝ

የልቤ ጉልበቱ
(ሰርክ መስዋእቱ )
የምገብርለት
(ያደረገኝ ዐለት )

ብዙ ነኝ 

የማላውቃት እኔ
( ተለየች ከጎኔ )
ወጣች አፈትልካ
( እኔን ላንተ ልካ )

እንደ ሰው ....
(ሞትን እንድቀምሰው)
እንደ ሴት
( እንዳምጥ  በምሬት )
እንደ ጨዋ
( እንድፈተን እንድሰዋ )
እንደ አማኝ
(እንድቀበል ሳይቀማኝ )
እንደ ድኩም
( እንዲያነቃኝ ህማም ኩርኩም )
እንደ ብዙ
(አንድ እንድሆን ጠፎ ጓዙ )
ህግ አዝዬ
(ትምክት ልቤን እንዳይንጠኝ )
ተኝቼ እንድነቃ
(አንተን መርጦ ሰጠኝ)

(በእምነት )

@getem
@getem
@getem
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።

ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።

ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።

ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።

By Hab Hd

@getem
@getem
@paappii
( የድሮ ባሏ )
==========

እባክህ አምላኬ ተሰምቶ የማያውቅ
ግለጥልኝ ቃላት
የቀደመ ባሏ ደራሲ ነው መሰል
የለም እኮ ያላላት  ....

እርሱ አሐዱ ብሎ
በሳመው ከንፈር ላይ እኔ እየደገምኳት
ቃላት አሽሞንሙኖ
የነገራትን ፍቅር እኔ እያስታወስኳት
መሰረት በጣለው
ስውር ርስቱ ላይ ሠርክ እየደከምኩኝ
ልቧ ላይ ምንኖረው
እርሱ እየደመቀ እኔ እየፈዘዝኩኝ !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
ብታውቂ!
***
ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ካዚም እስራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ
****
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባዔ
ፈላስፋውን ከጉባዔ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ !
**"
እንኳንስ በኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!

By በውቀቱ ስዩም

@getem
@getem
@paappii
ቁራኛ
ዘመን ያላዳነኝ
ያልፈታኝ ርቀት
ተአምር ያላነጻኝ
ያልፈወሰኝ ጥምቀት
ከናፍቆት ሚነጥል
የታጣልኝ ዳኛ
እድሜ ይፍታህ ያሉት
የፍቅር ምርኮኛ
ሆንኩልሽ ቁራኛ።
           

By @poetkidus

@getem
@getem
@paappii
ዘንባባን አስቀምጦ ከመናፍቅ
ጉዞ ዘላለም መበጠር
ፍቅር ሳያውቅ ኖሮ የካደ
አንደበት ከህልሙ መስፈንጠር
ሲቃዡ ነው ማደር
ስርን ነቅሎ መኖር
ስር ሰዶ መመንጠር
የፍቅር እናት ክዶ በውሸት
አብነት ዘላለም ማመስጠር

  by @ygolaw16

@getem
@getem
@getem
¯
..‎ተስማምቶኛል  ፀሀይነቷ
‎መጥፋትን አልሻም ከፊትለፊቷ
‎ ያለርህራሄ  ብትወርድም በላዬ
‎ንዳዷ ጥሞታል ለውርጫም ገላዬ

‎ልዩ አረገችኝ
‎ቀየረች ፍጥረቴን ፣
‎ከጥላ መሸሽ...
‎ከጥላ መጠለል አድርጋው ህይወቴን።


by @yoseph_Gezahegn

@getem
@getem
@paappii
ሁሉንም ነበረች
አለሌም ጭምትም
እሬትም ወተትም
እሾህም በለስም
በራድም ትኩስም
አሳቢም
ተግባቢም
ሳቂታም ፡ አልቃሻም
አሁን ምንም ነገር
ለመሆን አትሻም።

ኖራለች ከልቧ
ስታልም ስትነካ
ስትጨልም ስትፈካ
ሲቆላት
ሲደላት
ሲከፋት ሲመቻት፥
ለምን እንደሆን እንጃ
ሰው መሆን ሰለቻት!።

© @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
(የአብስራ ሳሙኤል)

1....
ተይው
መች ተናግሮ ያቃል
የልቡን
ሀሳቡን
ወንድ አይደለ
እያነባ ይስቃል
ደና ነኝ እያለ
አለ
መኖር ካሉት
በእግዜር ምስጋና ቢኩሉት
በፈገግታ ቢቀበር እንባ
ወንድ አይደለ
ይመስገነው ብሎ ገባ
በትጨልምም
በትዘምም
ዙፋኑ ናት
ጎጆው ..... ማጀቱ
ቤቱ
የጻፈበት ገድል
የኑሮ ድል
የወዝ ዋጋ የላብ ፍሬ
ደና ነኝ ለዛሬ
2....
ተይው
ወንድ አይደለ
መች ደህና ሆኖ ያቃል
ደህና ነኝ እያለ
በገረባው
በሲጃራው
በእጣን ጢሱ
የተረሱ
መአት ብሶት
የጭስ ለቅሶ
አይን ያሟሿል
ሌላን ደርሶ
ሆድ አስብሶ
ግን ግድ ነው
ዛሬ የዱአ ከተገኘ
ይመስገን ነው
ደህና ነን ነው
3....
ተይው
ወንድ አይደለ
ባሬላ ጭኖ
ኩንታል ተጭኖ
መሪ ጨብጦ
ከብቶች እረግጦ
ባመጣት ሀሴት
ላፈቀራት ሴት
የ አበባ ጉንጉን
የወግ የወጉን
የወርቅ ሀብል
የባዕድ መብል
በርገር
ቢዛ
ማክያቶ
ተገባብዞ
ተጎንጭቶ
ሩም ይዞ
ባናት ባናት መዳራት
ፍቅር መስራት
ከሰመረ ገላዋን
ካልሆነም ጸጸት ታቅፎ
ትዝታ በውሀ አራግፎ
ደህና ነኝ ነው
ወንድ አይደለ
የልቡን ጠባሳ የሚያወራ ማን ነው
4....
ተይው
አትጠይቂው
እንዴት ዋልክ እያልሽ ?
ላትጸድቂ በነፍሱ
ደህና ባይሆን እንኳ
ደህና ነኝ ብቻ ነው
የወንድ ልጅ መልሱ!

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
ደመናማ ገጾች.
(የሞገሴ ልጅ)
ምሽት እየጓጉ-
ጭለማን ተግነው - ብርሃንን ሽሽት፣
ብዙዎች ኖረዋል,
መታየት ፈልገው ጠልቷቸው መታየት።

ደመናማ ገጾች-
ተፈርተው መኖሩን - ከክብር ያልቆጠሩ፣
ጭለማን መዋያ፣
መጽናኛ አድርገው - ሲነጋ አደሩ።

By @tafachgitm

@getem
@getem
@getem
(የአብስራ ሳሙኤል) 


¶ዝም ብለሽ ስሚኝ¶
¶ዝም ብለሽ ሳሚኝ¶
፨ከንፈር፨
፨ከንፈሬን፨
በጆችሽ ዳሰሽ
የራስ ጸጉሬን
¶ዝም ብለሽ ስሚኝ¶
¶ዝም ብለሽ ሳሚኝ¶
ጽድቅ እስኪመስል
ፈውስ እስኪመስል
¶ከንፈር መንከሱ¶
¶ገላ መልበሱ¶
¶ልብስ ተቃደን¶
¶ከጭን ተጋምደን¶
ከላብ ከወዝሽ ጠብታ እስክትቀር
ነይ እንፋቀር
፨ከንፈር ከንፈርሽን፨
፨ከንፈር ከንፈሬን፨
¶ዝም ብዬ ልሳም¶
¶ዝም ብለሽ ሳሚኝ¶
¶ዝም ብለሽ ስሚኝ¶
እቅፍ አድርጊያት
ሽሽግ አድርጊያት
ቁስለኛ ነፍሴን
ሀጣን መንፈሴን
በነገርኩሽ ልክ
አልረዳውም እኔም እራሴ
መሸሸጊያ ነው
ገላሽ ለነፍሴ
ሀጢያት ነው ቢሉም
ኩነኔ ቢሉም
የነሱን መጽደቅ ተይው ለነሱ
ገላ ወዝሽ ስላልቀመሱ
ይኮንኑና ይጽደቁ በኛ
........እኛ..........
እኔና አንቺ
ዝም ብለሽ ሳሚኝ አንዳትሰለቺ
፨ከንፈር ከንፈሬን፨
፨ከንፈር ከንፈርሽን፨
ተጠምቄበት
ላቦት ወዝሽን
ቃላት እስኪያጥረን በፍቅር ሲቃ
ጨረቃ በሀፍረት በአሽሙር ስቃ
ገላሽን ትፈር
ከውበት እንጂ
አልሰራሽ ከአፈር
¶ዝም ብለሽ ስሚኝ¶
¶ዝም ብለሽ ሳሚኝ¶
፨ከንፈር፨
፨ከንፈሬን፨
የራስ ጸጉሬን
እቅፍ አድርገሽ
ሸሽጊኝ ከአሳር
ከህይወት ምሳር
<መዳፍሽ ዳሶኝ>
<ጥርሶችሽ ነክሶኝ>
¶በፍቅር ሲቃ¶
¶ጨረቃ ስቃ¶
ዘ-ፍጥረት አፍሮን
ጭጋግ ሰውሮን
ጽድቅ እስኪመስል
ፈውስ እስኪመስል
<ገላ መልበሱ>
<ከንፈር መንከሱ>
¶ዝም ብለሽ ስሚኝ¶
¶ዝም ብለሽ ሳሚኝ¶

@Yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
‎ያንድ ቀን ምሽት : ብርድ ቆፈን ሽሽት
‎ሌቱን ማነጋበት እግዜርን ጠይቄ
‎የሷን ቤት ጠቆመኝ አደርኩኝ ዘልቄ

‎ተንኮል እንደነበር ልቤ መች አጣው
‎ሌቱንም ፍቅሩንም አንግቼለት ወጣሁ።

By @yoseph_gezahegn

@getem
@getem
@paappii
አበቦችህ አሉ ጠንዝለው ደርቀዋል
አበቦችህ አሉ ግን የሉም ሞተዋል
ጠረናቸው ጎልቶ ካልጋየ አጠገብ ጠዋት ማታ ቢሸተኝ
አንተን ቢያስታውሱኝ
ሞተው ነው ሚኖሩት ሂወት የላቸውም
ደርቀዋል ግን አሉ ደሞ አልጣልኩአቸውም
ሄደሃል ላትመጣ አንተም እንደዚአው ነህ
አትለመልምም ከረፈደ ኋላ ውሃ እያጠጣውህ::

By lily

@getem
@getem
@getem
(የአብስራ ሳሙኤል)


¶እናቷን ብሏት ነው መሰል¶
ጨረቃም ሸ..ሸ..ች ከፍቁሩ
በኩሪፊያ ስትብሰለሰል
ለውበት ተዘጋ በሩ
የከዳ የሸ..ሸ ፍቅርሽ
ታትሞ ከፍጡሩ ሁሉ
አንጋጦ ገጽሽን ሲያይሽ
....... ይላል ይላሉ....
አጣልታው ከ-ዘፍጥረቱ
ጨለማ አደቀደቀ
...... ይላል ጨረቃን
ላንቺ <ቃል> ስላላወቀ
ክፉ <ቃል> አላስለመድሽው
በምን <ቃል> ቁስሉን ይናጋር
.......ይላል ጨረቃን
ለእግዜር ነው የአንቺን ነገር!።

By @Yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
ማህሌተ ገንቦ

ባጭር ቀረን ስንል፣ እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን

ቺርስ!!

ፊታችንን አይተው እንደተቸገርን፣
ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስከንለምናቸው፣
ቆመው ላልጠበቁ

ቺርስ!!

ወድቀው ለማይጥሉ፣ ነግሠው ለሚያነግሡ ነውራችንን አይተው፣ ልከ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው፣ ፈጥነው ለሚረሱ

ቺርስ!

ላባ ላረጉልን፣ የመከራ ሸከሙን
ቀልደው ላሳቁን፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ
ሥጋ ለበስ ትንግርት፣ ሆነው ላስደመሙን

ቺርስ!!!!

By bewuketu seyum

@getem
@getem
@paappii
( እግዜርና ሴት )
============

ምንም ብታማርር
ምን ብትበድላቸው
እግዜርና ሴት ልጅ
በዚህ አንድ ናቸው
:
ለይቅርታ ሲሹህ
ትወደኛለህ ወይ ??
ሁሌ ጥያቄአቸው !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
(የአብስራ ሳሙኤል)


¶ከህይወት ዳርቻ¶
¶የኔና የአንቺ ብቻ¶
<ሆነን>
<ደርሰን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
ትዝ አለኝ ትዝ አለሽ
ከትዝታ አይሸሽ
የመጀመሪያው ቀን
ደርሶ ያስተዋወቀን
ከፍጡር ነጥሎ ያውም ከወንድ ዘር
ያርባ ቀን እድሌ ባንቺ ሲመነዘር
መሄጃ ያጣውን እያንከላወሰ
...........ከደጅሽ ደረሰ
የሰናፍጭ ቅንጣት
አንቺን ላለማጣት
የተሳልኩ ይመስል
ውብ የሆነ ምስል
፨ከሙሉ ቀሚስ ጋር ከተሸነሸነ፨
፨የሚያምር ሹሩባ የተጎነጎነ፨
፨ከጉንጮችሽ መሀል፨
፨፨አለች ትንሽ ስርጉድ፨፨
አቤት የእግዚያብሄር ጉድ!!!
ምን ሲል ጋረደበት ?
የወንዱን ልቦና
አልተነካሽ ገና
ያ-ሁሉ ቦዘኔ ደጅሽ ሲርመሰመስ
ሴትነትሽ አይረክስ!።

፨፨፨
ከህይወት ዳርቻ
የኔና አንቺ ብቻ
<አልፈን>
<አሳልፈን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
ትዝ አለኝ ትዝ አለሽ
ጀንበር ፀንታ ስትሸሽ
እንዲው ስውተረተር
ሰው የመሆን ነገር
ሞልቶ ለማይሞላ
ሆዴ ስሻ መላ
ጉልበት ሲበዘበዝ
አንቺን አይቶ መፍዘዝ
ምን እድል አመጣሽ
የቱ እምነቴ ቃጣሽ
<ወደምሰራበት>
<ወደምትሰሪበት>
እግዜር ሲያገጣጥም
የዕጣ ፈንታ ግጥም
አንቺን ከኔ ጻፈ
...አንድ ቀን አለፈ...
...ሁለት ቀን አለፈ...
አይንሽን ለመድኩት
መተያየት በዛ
እንዲሁ እንደዋዛ
ተግባባን እንደቀልድ
ተያይዞ መንገድ
...መሸኛኘት በዛ....
....መገባበዝ በዛ....
እንዲሁ እንደዋዛ
¶ወደድኩሽ ወደድሺኝ¶
¶ጠየኩሽ እሺ አልሺኝ¶
በአብርሀም ጋብቻ
የኔና ያንቺ ብቻ
ጭብጨባ ያልበዛበት
ረብሻ ያልበዛበት
ተጸነሰች ህይወት።.....

፨፨፨
ከህይወት ዳርቻ
የኔና አንቺ ብቻ
<ሆነን>
<ደርሰን>
°°°°ስናይ ተመልሰን
መኖርም ያረካል
ውጥኔም ይሳካል
ውል ለሌለው ሀሳብ
ስለሆንሺኝ ርካብ
ዘመን ማሸገሪያ
ባህሩን ማስገሪያ
ከጉንጮችሽ መሀል
፨አለች ትንሽ ስርጉድ፨፨
ሳምኳቸው እንደጉድ ።

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
🌜🌜🌜🌜
.
.
.....ትዝ ይልሃል ያኔ
እቅፍህ ከተኸኝ ተቀምጠህ ከጎኔ፤

በተመስጦ ሆነን ጨረቃን ስናያት፤
ልባችን ያለዉን በሚስጥር ስንነግራት፤

ትዝ ይልሃል አይደል.......
ላልከዳህ ላትከዳኝ በስሟ ስንምል፤

ዛሬ ቀኑ ከፍቶ ቅናት ይሆን በደል፤
.....አመል አይሉት እድል፤
መሐላችን ጠፍቶ ተጓዝን ለየቅል፤

መገኘት ከፈለክ ከምንወደዉ ስፍራ
.....እጠብቅሃለሁ ከጨረቃ ጋራ።
.............................................


by ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
2025/06/27 10:28:20
Back to Top
HTML Embed Code: