መተላለፍ
------------------------------

“ሰው ሀገር ነው" ቢሉኝ ሀገሬ ነህ ብዬ፣
አንተ ስር ተገኘሁ ነገሬን ጣጥዬ፡፡
ለወሬ 'ማይመች የቸገረ ነገር፣
አንተ እኔን ታቅፈህ ትመኛለህ ሀገር።

By ሜሮን ጌትነት

@getem
@getem
@paappii

''ሌላ አዉነት የለኝም'' ሚለዉን የሜሮን ጌትነት ግጥም ገዝታቹ እያነበባቹ
71😁7👍3
ምን ይሻለዋል
--------------------

ሂድልኝ ሂጂልኝ
ብለን ተለያይተን

ከማነቀው ህይወት
አንቺም እኔም ገብተን

ይሄንን ልቤን ግን
ቆይ ምን ይሻለዋል

አንቺን ሲያስብ ጊዜ
እንባ ይቀድመዋል

@getem
@getem
@paappii
62😢11🔥7
    ግጥም ነው ምትመስዪው!
  ---------------------------------------
            

ከፊደል ማሳ ላይ ቃላት ለሚቃርም
ካገኘም ከትቦ እያደር ሚያርም÷
በአርኬው መባቻ  በመድፋት አባዜ
ከሃሳብ ባህር ላይ ሰጥሞ በትካዜ÷
በብዕሩ እንባ ስንኞች ሲቋጥር
ቤቱን በመዘንጋት ቤት ለመምታት ሚጥር÷
እቴ አትሞኚ ከቁብ ለማይቆጥርሽ
በፍቅር አጊጠሽ አምሮብሽ ቢያይሽ÷
በቃላት ስደራ የተሽቀረቀረ
በታሪክ ፍሰቱ ጎልቶ የዳበረ÷
ግጥም ነው ምትመስዪው
መምቻና መድፊያው ፍፃሜው ያማረ::
                     

By @Abuugida

@getem
@getem
@getem
32👍4😁1
ያ ሳቅሽ ሲጠፋ
--------------------------

አንቺ ስትስቂ
ከሰማይ ላይ ወፎች፣
እስከ ምድር ሰዎች፣
የገነት በር ደጆች፣
የቅዱሳን ፊቶች፣
አምረው ያበራሉ፤
ደስታን ያገኛሉ።

ትልቁ ጎልያድ
በሳቅሽ ተማሎ፣
ብላቴነው ዳዊት
ጠጠሮቹን ጥሎ፣
ያንቺን ሳቅ ነበረ
ተቃቅፈው ሚሰሙት፣
ፈገግታሽን ነበር
ሚያስቡት ሚያልሙት።

አንቺ ስትስቂ
ፀሃይ ከጨርቃ፣
ብርሃን ከጨለማ፣
ሰማይ ከምድር ጋ፣
ወፎች ከአረዊቶች፣
ክረምት ሳይቀር በጋ፣
አንድ አምሳል ነበሩ፣
በሳቅሽ ግዞት ውስጥ
አንድ ላይ ሚኖሩ።

ያ ሳቅሽ ሲጠፋ
ጎልያድ አቅራራ
ዳዊት ላይ ደነፋ፣
አባቶች ተከፍተው
መቋሚያ አነሱ፣
እንድትስቂላቸዉ
ፆም ፀሎት ሊያደርሱ።

ያ ሳቅሽ ሲጠፋ
ሰማይ አለቀሰ፣
ፀሃይ ተናደደች፣
ነፍሳትን አቃጥላ
ጨለማን ሰደደች።

እኔም ስጠባበቅ
በምኞት በተስፋ፣
ሳቅሽን ናፍቄ
ሳቅሽን ተርቤ
ግዜ ይዞኝ ጠፋ
ያ ሳቅሽ ሲጠፋ
ያ ሳቅሽ ሲጠፋ


@getem
@getem
@paappii
92😁6🔥5👎1
ፍቅር አለኝ ለአንተ!
-----------------------------

አደመጥሁኝ ቅኔ መልሴ መልሼ፣
ሙዚቃውን ሰማሁ ዓለሙን አስሼ።
ዜማ ሰለለብኝ ሥዕል ደበዘዘ ግጥም አነከሰ፤
ባሳይህ... ብኖረው... የልቤ አልደረሰ።
(አንደ ምን ልግለጸው?)
ጥበብ ያሳነሰው .
ቋንቋ ያኮሰሰው .
ፍቅር አለኝ ለአንተ፣
በፍጥረት ዘመን ልክ እየተጎተተ
አስከ ዓለም ፍጻሜ ደግሞ 'ሚዘረጋ፣
ብኖርም ባንኖርም
ምጽአት የሚጠብቅ በነፍስም በሥጋ።
ፍቅር አለኝ ላንተ
ምድር የሚሞላ፣
ከእግዜር የሚያስታርቅ ከእግዜር የሚያጣላ።

By Meron Ghetnet

@getem
@getem
@getem
49
ልጅ እያለሁ –··· ጨረቃ....
(በሌሊቱ ሰማይ ደምቃ ...)
ቁልቁል ዓይኔን እያየችኝ ፤
(እያልኩ –··· “ተከተለችኝ ”)
መስሎኝ የወደደችኝ...
(ሽቅብ... ሽቅብ.... እያየኋት)
ስራመድ አቅንቼ አንገቴን ፤
መች አየሁት እንቅፋቴን ?!
(ሲነቅልብኝ አውራ ጣቴን...)
ሲጥለኝ ከመሬት ጠልፎ ፤
ሲከነብለኝ አደናቅፎ ....!
(“ወደደችኝ” ካልኩት ይብስ...)
እዛው መሬት ላይ ወድቄ ፤
(ጨረቃ ከሰማይ ወርዳ...)
እስክታነሳኝ መጠበቄ ፤
ትልቁ –··· አለማወቄ ።
💧
ያኔ ታዲያ....
“አይዞህ ልጄን !
እኔን!” እያለች ፤
አንስታኝ እያባበለች ....
(በክንዶቿ ደግፋ )
አቧራዬን አራግፋ ...
ቁስሌን በጨረቅ ያሰረች ፤
እናቴ “ግጥም” ነበረች ።
💧
“ግጥም” ነበረች እናቴ ....
(አባባይ ለልጅነቴ....)
ዘቢብ ጠብታ — ለመሪር ቀኔ
ክፍተቴን መዝጊያ —  ክዳኔ ።
(ታዲያ ያኔ.....!)
ህመሜ ሲቀሰቅሰኝ...
(ጨረቃም ስትታወሰኝ....)
“እኔን ልጄን!” — መባል ሽቼ ፤
(“አመመኝ እናቴ” እያልኳት...)
እግሮቿ ላይ — ተደፍቼ....
ሲቃዬን በጨርቅ አፍኜ
(ፊቴን በቀሚሷ ሸፍኜ)
“ስቅስቅ” ያልኩት...
(“እሪ” ያልኩት...)
ልብሷ ላይ እስካሁን አለ...
እንደ ጥልፍ አምሮ –··· ተጥሎ ፤
(ዕምባዬ —··· “አበባ”  መስሎ ።)
____

የካቲት 8 — 2016 ዓም
By @Bekalushumye


@getem
@getem
@getem
60👍6🔥2
አይ አንቺ ጨረቃ
.
.
.
ስንቱን ሰዉ ታዘብሽዉ?

ስንቱን አደመጥሽዉ?

የከፋዉ እንደሆን

ላንቺ የሚያወጋዉ

በልቡ ያለዉን

ሚስጥራቱን ሁሉ.....

የሚዘረግፈዉ

እስቲ ልጠይቅሽ?

ምን ቢያይብሽ ነዉ?

   ✍️ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
54🎉7👎3👍1
ምስጋና
-------------------------

ባንቺ ተማምኜ እምነቴን ጥዬብሽ
አምኜሽ ቆይቼ ቃሌን ጠብቄልሽ፣
ዛሬ ትመጣለች ግድ የለም ወይ ነገ
ፀሃዩ ፍቅራችን ስል መች ገና አደገ፣
እልፍ አላፍ አመታት ጥሎኝ እያለፈ
መንፈቅ በመንፈቅ ላይ ሄዶ እየከነፈ፣
በዋሊት ትዝታ በሀሳብ እየኖርኩኝ
ስቀመጥ ስነሳ አንቺን እያሰብኩኝ፣
ያዘዙኝን ሳደርግ ያሉኝን ስሰራ
ስንቱን አለፍኳቸው ስንቱንስ መከራ፣

ቢሆንም

እንደው ብቅ ብለሽ ካጣሽኝ ከሌለዉ
ጆሮሽን አትስጪ ቸግሮታል ለሚለዉ
የመኖሬ ተስፉ አንቺ ነበርሽና፣
ዘግይተሽ ብትመጪም ይድረስሽ ምስጋና።

@getem
@getem
@paappii
47👍12😢5🔥2
ተመስገን🙏🙏🙏
.
.
.
መስከረም ሲያከታትም አልፎ ሲተካ ጥቅምት፤
ፀደይ ብራ ሲሆን ሰማዩ በዛች መጀመሪያ ዕለት፤

በእልልታ ታጅቤ ወደዚች ዓለም መጣሁኝ፤
የለቅሶን ሸማ ደርቤ ዛሬን ነው የተወለድኩኝ፤


አዲስ እድሜን ለንስሐ ጨመረልኝ፤
መከራዬን አሳልፎ ለዚች እለት አደረሰኝ፤


አንዳች ፍሬ ቢታጣብኝ ምንም ምግባር ባይኖረኝም፤
ከአጠገቤ ሳይለየኝ ለሴኮንዳት አልተወኝም።



ትናትናም አልሸሸኝም ሳማርረዉ በአንደበቴ፤
ዛሬም አለ ተነሽ ብሎ እያነሳኝ ከዉድቀቴ፤

ወዳጅ ያልኩት ሰዉ ቢርቀኝ፤
ለአፍታም እንኳ ቸል አላለኝ፤

በምሕረቱ አስጠልሎ ሳይገባኝ ስላኖረኝ፤
ተመስገን ነዉ እንጂ ሌላ ምን ቃል አለኝ።
🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊
🎂🎂01/02/2018🎂🎂
✍️ ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
34🎉31👍1
እኔም እንደ አዳም . . .
በገነት ገዳም
ሁሉ ተሟልቶ ፥ ኑሮ ሲመቻች
አድርጎኝ ታካች
ማለት ሲዳዳኝ "ከፀሐይ በታች..."
የዛኔ መጣች !

መጣች ...
"ንቃ" አለችኝ
ጎኔን እየወጋች ፥ ተፈታተነችኝ
ዝም አልኩኝ በግብሯ
ታገስኳት እንዴትም ፤
ለካ እንደመሳሳቅ ፥ ይጥማል ንዴትም ።

( ምቾት ብቻውን መች ያስደስታል ?
መስኩ ለምለም ነው
አፀዱ ሙሉ
ምግቡ ፥ መጠጡ በገነት ሞልቷል
ምስኪኑ አዳም ግን ትቶት ተኝቷል ።

ሳይጠፋበት ጥፋት ፥ ሳይጎበኘው ሐጥያት
ለካስ ይሰለቻል ፥ መንግስተ - ሰማያት ። )

እሷ ግን በቃ
እግዜር ያስተኛኝ በገነት አልጋ
እንዳልነቃበት ስለሚሰጋ
መሆኑን አውቃ
ህይወት ሰጠችኝ ፥ ምቾቴን ነጥቃ ።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
46🔥8👍1😁1
ገና ያኔ ድሮሮ
ከሩቅ ዘመን በፊት፣
አማኝ በሞላበት
ፈላስፎችም አሉ ብቻ ትንሽ ጥቂት፤

ታድያ በዛ ዘመን
መሬት ክብ ነበረች
ምጣድ ምትመስል፣
ለጥ ብላ ምትኖር
የማትዞር ማትዋልል፥

ያችኛዋ መሬት
አሁን ከነበረው በጣም ትለያለች፣
ምንም አድሎ የለም
ሁሉን ታበቅላለች፤

ታድያ እነዛ ጥቂት
የሚፈላሰፉ፣
ከንቱ ሀሰበቸውን
በሰው ውስጥ አስፋፉ፤

መሬት ክብ ሳትሆን
ሰማይ የምታክል፣
እንቁላል ነገር ነች
አሎሎ ምትመስል፤

ብለው ማይሆን ወሬ
ምድር ላይ በተኑ፣
ደበራት መሰለኝ
እንደዚ ሲሆኑ፤

አሁን በኛ ዘመን
ትንሽ መረጋጋት ያለ ከመሰላት፣
ለስሟ ነዉ መሰል
ድርቅና ቸነፈር
ጦርነት አይቀራት።

@getem
@getem
@paappii
👍3723😁11🔥4
‎ቀኑ ሲረፍድ
‎ ዱካክ አካሌ ላይ የሙጢኝ ሲሳፈር
‎ ድርጊቴን አጢነው ሲመጡልኝ ከንፈር
‎ ጥላው ሄደች ብለው እንደሳቀብኝ ሰው
‎ሀዘን ይሙላት ነፍስሽ ልብሽን ይውረሰው

‎ ባፍሽ ምላስ ያነሳሽው የማልሽልኝ ጠቅሰሽ ኪዳን
‎ መጨረሻሽ ይሁን የሄድሽበት ሁሉ እግርሽ ሄዶ አይደን
‎ በቀል የሱ ሆኖ ምን ባለደርግ ላንቺ በቀል
‎ ተራግሜሽ ይቁረጥልኝ
‎ በሄድሽበት ዝግጅት ላይ ሂውማን ሄርሽ ከቶ ይነቀል

‎የወደደሽ ልቤን
‎እንደተውሽው ከመንገድ ላይ
‎ከወደቅሽበት ማቅ ስትነሺ እንዳላይ!

‎አይበቃኝም ሰርክ መስደብ
‎  ገና ብዙ እረግማለሁ

‎ ግን

‎ እወድሻለሁ።


‎ ዮኒ
‎     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
14👍7
Audio
ተጓዡ ተራማጅ ሀሳቤ ልጓሙን እስኪያገኝ……………

እድሜ ወረተኛ ገስግሶ ገስግሶ
ትምክተኛ መልኬ በሽብሽብ ተወርሶ

ርግበ እምነቴ ማረፊያዉን ሲያጣ
ጠባቂ እንደሌለዉ እንደስጥ ተስፋዬ በወፎች ሲበላ

ጠብቀኝ…………..

ባጣ ቀየኝ…………….
ዘመንህን - እድሜ መኖርህን በኔ እድሜ ለዉጠኝ።


ትዝታ ወልዴ✍️


@Tizita21
@getem
33👍7👎7🔥3
ባቀፈሽ ካልቀናሁ፣
ካላማርሽ ካልከፋኝ፣
የያዝሽውን ካልያዝኩ - የጣልሽው ካልከፋኝ፤
ሲአቅፉሽም ሲአሻሹሽ - ፊቴ ካልዳመነ፣
ደግ አረግሽ ብቻ ምኑን ፍቅር ሆነ?

By @eyadermoges

@getem
@getem
@paappii
65👍8😢5🔥3👎2
( ከይቅርታ ኋላ )
============

ጆሮ እልፍ ቢያደምጥ
አይን ሺህ ቢያማትር
እግር ሩቅ ቢያስስ
እጅ ብዙ ቢጥር ....

ውብ ከቶ አያገኙም
ከይቅርታ ኋላ እንደሚኖር ፍቅር !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
45🔥7🤩2😢1


የመንገዴ ፍጻሜ ነሽ
ከአድማስ የአድማስ መጨረሻ 
የሀሰሳዬ ፍጻሜ የጉዞዬ መዳረሻ

✻‧‌

ባለፈው ወይኔ ጎድሎ
እቸረው (እሰጠው) ቢያጥረኝ
ማርያምን መስለሻት መጣሽ
በምልጃሽ ምልአትን ቸረኝ


"አይሆንም" ያልኩት ሆነልኝ
አያልፍም ያልኩት አለፈ 
"ከበደኝ ታከተኝ" ያልኩት በፍቅርሽ እየታቀፈ ።

✻‧‌

ነውሬን አንቺው ሸፈንሽው
ጋረድሽው የሀፍረት ታሪኬን 
የህይወት ማይ እየሆንሽኝ
አነጻው እድፋም መልኬን


ወደድኩሽ እስከ ጥ • ግ • ጥ • ጉ
ለፍቅርሽ ነፍሴን አስገዛሁ 
አንድ ሆኜ መኖር ያቃተኝ
ዕልፍ ሆኜ በፍቅርሽ በ • ዛ • ሁ ።

#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel

@getem
@getem
@getem
24👍3
ያላንቺ ይቅርብኝ!
(የሞገሴ ልጅ)
ዐየሽ የኔ ናፍቆት-
ካንቺ በፊት እኔ - ኖሬአለሁ ለናቴ፣
ቆንጥጣ አባራኝ - በሚናፈቅ ቤቴ።

ያኔ ግን - ልጅነት-
ከጎኔ ስትለይ - ናፍቆት ቢቀጣኝም፣
አቅፋኝ እየተኛች፣
በናፍቆቷ መራብ - - ጭራሽ አያውቀኝም።

ጭራሽ አደግ ስል...
እሷን መውደድ ሳልተው - አንቺን በልብ ይዤ፣
አጠገቤ ሆነሽ፣
ናፍቆትሽን ፃፍኩት - ማግኘቴን ሰርዤ።

እንደው ግን የምልሽ?

እለት እለት ጾሜ፣
ያለኝን መፅውቼ፣
ከገነት ለመግባት - የምጠባበቀው፣
ካንቺ ጋራ ስሆን፣
ከሚሰማኝ ምቾት - እንዴት ነው ሚልቀው?

እንጃ ያሳስባል-
ካንቺ በላይ ናፍቆት የሚያስይዝ ቢመጣ፣
ከሆነ ነው እንጂ፣
አንችው ሰማይ ሆነሽ - ልቤ በልብሽ ላይ ገነት ተቀምጣ።

በዛ አትበይ እንጂ...
ካንቺ ተለይቶ - መኖር የሳት ባሕር፣
ካንቺጋራ ሆኖ - ሲኦል መግባት ክብር፣
ከነ’ንትንሽ መሳም - የዘላለም እረፍት፣
ማፍቀርሽን መግፋት - ኦሜጋ ስህተት፣
አንችን አለማሰብ - የድርቀትም አያት፣
ፈልጎሽ መኳተን - የክብር ኁሉ አናት፤
ይመስለኛል እኔ.....
ለገነት ለሲኦል - አንቺ ነሽ ሚዛኔ፣
ጨርሼ መጽደቄ - ወይም መኮነኔ፣
ፈዋሿ መስቀሌም - ገዳዩዋ መብረቄ፣
የሰማዩን እማ.........አልተወለድኩኝም በፅንፀት አውቄ።

By @eyadermoges

@getem
@getem
@getem
14🔥4👎1
‎ያልታደልኩት እኔ
‎ አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
‎ ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም

‎የሚመሩን ሁሉ መምሪያ ሰነዳቸው
‎                    ምን ቢሆን አንድነት
‎በሬሳ አካላች ቄጤማ ነስንሰው ሰሩልን ሰገነት
‎ሰብከውን በኪዳን
‎ሰብከው በመንግስቱ
‎ተደመርን ብለው ምን ቢያጎበድዱ
‎የጀርባ ላይ እከክ ሆኑ አንዱ ጎሳ ላንዱ
‎በመስኮት በመስኩ ምንስ አሸብርቀው ፍቅር ፍቅር ቢሉ
‎እያቸው አለሜ
‎ጩቤ ተጨባብጠው ሰላም ሲባባሉ

‎ያልታደልኩት እኔ
‎ አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
‎ ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም

‎አዲስ ኪዳን ቢፈለሰፍ
‎አዲስ መንግስት ቢዋቀርም
‎ዱር ጫካ ገብቼ ሳላይሽ አልቀርም
‎የፈለገ ቢሆን ሰላም ለአደባባይ ለመንደሩ
‎ለሀገርህ ዝመት ብለው ገበሬን ነው ሚገብሩ
‎ሰርክ አራሽ መሬቱን
‎ሰርክ ቀዳሽ ታቦቱን
‎ነፍጠኛ ተኳሹን
‎ሀገር ሲሉት የሚነሳን
‎ወገን ሲሉት አለሁ የሚል
‎ምን ቢጨቆን አፉን ይዞ ትቅደም ባለ አንድ ሀገሩን
‎ሜዳ ላይ አጠፉት
‎ኪዳን ፍቅሩን ጥለው ሰበሩት ማገሩን

‎ያልታደልኩት እኔ
‎አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
‎ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም

‎አለሜ
‎አይንሽን ባላይም ቃልኪዳን አልፈታም
‎        ሁሌ    እወድሻለሁ
‎ሚያገናኘን መንግስት እስኪመጣ ድረስ
‎        እናውርድ እላለሁ


‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
19🔥4
መሔጃ የለኝ !
ካይኖችሽ ብሸሽ ፥ ቅንድብሽ ስር ነኝ ።
ወዴትም ብዞር
ገላሽ ብቻ ነው ፥ የሚያዋስነኝ ።
ቅርቤም - ሩቄ
ኩነኔም - ጽድቄ
ከህጎች በልጦ ፥ ልብሽ የሚያዘኝ
አይንሽ ብቻውን ፥ የሚያናዝዘኝ
ያንቺው ታሳሪ ፥ ግዞተኛሽ ነኝ ።

ካንቺው ቀምቼ ፥ ላንቺ ምሰጥሽ
ከገዛ ራስሽ ፥ የማስበልጥሽ
ምንም ቢሰማኝ ፥ የማላመልጥሽ
ወስልቼ ብሄድ ፥ ከገላሽ ምሕዋር
ተኝቼ ምገኝ ፥ ከትዝታሽ ጋር
ወዲህም ሳራ ፥ ወዲህም አጋር !

ካንቺ ጋር መሮኝ
ሌላ ሴት አምሮኝ
ጥዬሽ ለመሄድ ፥ አስር ብወራጭ
አንቺን ነው ማገኝ ፥ ልክ እንደ አማራጭ ።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@paappii
13
ያልወረደ እንባ
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ  ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን  የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....

በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤

መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤

በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤

አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍2215🔥7🤩1
2025/10/20 01:13:43
Back to Top
HTML Embed Code: