Telegram Web Link
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በአል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።በአሉ የደስታ፣የአንድነት፣የአብሮነት፣የመቻቻል፣የመከባበር ፣የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።
ወድ የዘፀአት ቴአትር እና ስነ-ፅሑፍ ቻናል ቤተሰቦች በእናንተ ጥያቄ መሰረት #የግጥም ውድድሩን በቻናላችን አዘጋችተናል። ስለዚህም መወዳደር የምትፈልጉ እና የግጥም ችሎታ ያላችሁ #ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ግጥሙን ከስማችሁ ጋር አያይዛችሁ በዚህ @Mmiki84 ይላኩልን #በተመልካች ምርጫ ብቻ አሸናፊ የሆነውን ግጥም እንሸልማለን ::

በዉድድሩ
#1ኛ_ለወጣ 100 ደቂቃ የድምፅ ጥቅል #2ኛ_ለወጣ 80 ደቂቃ የድምፅ ጥቅል
#3ኛ_ለወጣ 60 ደቂቃ የድምፅ ጥቅል

ምንሸልም መሆኑን በደስታ እንገልፃለን:: ማስጠንቀቂያ የራስ ያልሆነን ግጥም ለውድድር ማቅረብ ከውድድር ያሰርዛል::

@gxmee
@gxmee
@gxmee
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሰላም ለናንተ ይሁን እያልን አነሆ #የግጥም ተወዳዳሪዎች #ግጥሞቻቸውን እየላኩ ይገኛሉ አነሆ ውድድሩ በይፋ የሚጀመረው ማክሰኞ ማታ ስለሆነ ተጨማሪ ተወዳዳሪዎች ግጥሞቻችሁን በ @mmiki84 መላክ ትችላላችሁ

#ዘፀአት ቴአትር እና ስነ-ፅሑፍ አዳማ
👇👇👇👇
👉@gxmee👈
👉@gxmee👈
👉@gxmee👈
👆👆👆👆
ጠብቄሽ ነበረ


መንፈሴን አፅንቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ

ጠብቄሽ ነበረ ፤

ብትቀሪ ግዜ ፤
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ ፤

ብትቀሪ ጊዜ ፤
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ።

ከ(ደበበ ሰይፉ)
@gxmee
@gxmee
@gxmee
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሰላም ለናንተ ይሁን እያልን አነሆ #የግጥም ተወዳዳሪዎች #ግጥሞቻቸውን እየላኩ ይገኛሉ አነሆ ውድድሩ በይፋ የሚጀመረው ዛሬ ማታ 3:00 ሰዓት ስለሆነ ተጨማሪ ተወዳዳሪዎች ግጥሞቻችሁን በ @mmiki84 መላክ ትችላላችሁ

#ዘፀአት ቴአትር እና ስነ-ፅሑፍ አዳማ
👇👇👇👇
👉@gxmee👈
👉@gxmee👈
👉@gxmee👈
👆👆👆👆
..................አቦ ተዉኛ................

በዚች ዓለም በተሰጠችን:
ነፃ ሆነን ተፈጠርን::
ነፃ መሆናችን አባባል ሆነና;
ታስረን ከረምን አሳሪዉ በዛና::
አንዱ እንደኔ ሁኑ እያለን:
ሁለቱ እንደዚ በሉ ስለን:
ለራሳችን እኛዉ ባዳ ሆንን::
የቱን ኖርነዉ
ምኑን ዘለቅነዉ
መናገራችን ወረኛ አስባለ;
ዝም ማለት ኩራትን አዘለ::
ለኔ እኔን መሆኑ ስናፍቀዉ:
ምን ይሉኝን አስቦ ስጨንቀዉ:
እንደዚህ እየሆኑ ኑሮ:
አ'ልዋጥ አለኝ አልወርድ ከጉሮሮ::
SOLA🙏

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
. የአይኔ ደስታ
ከሰፈርሽ መጣሁ አንቺኑ ፍለጋ
ከቤታቹ ደጃፍ ከበሩ ስጠጋ
አይኖቼ ሲያዩሽ ልቤ ተረጋጋ
ሁሌም አይሻለው ስትወጪ ስትገቢ
ዛሬ ቀኑ ቀዝቃዛ ነው ጃኬቱን ደረቢ
ቀርቤ ወዳንቺ ልልሽ ፈለኩና
ሳልልሽ ቀረሁኝ በርቀት ቆምኩና
አላወራሽ ነገር ቀረቤታ የለን
ጋደኛ ፈለኩኝ ሰው ቢያስተዋውቀን
ላናግርልክ ሲለኝ ውዱ ጓደኛዬ
እራሴው ልሞክር አታናግራት ብዬ
ሳላወራሽ ቀረው ዝም አልኩኝ ሆድዬ

ከሳሚ ለማሂ የተፃፈ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
ፍቅርክ ልክ እንደ አሳት
ነበልባል ነው ውዴ
ውስጤን አቃጠለው
አንተን በመውደዴ
እሳቱን አይቼ መቅረብ ፈለኩና
ፍሙን እያየሁኝ ፈራው እንደገና
ግና ደፈር ደፈር እያልኩ ጠጋ ጠጋ
ከእሳቱም ደረስኩ ተጠጋው አንተጋ
ደርሼም ከፊቱ ከእሳት ነበልባሉ
ነደደች ደረቀች እያሉ ሲያወሩ
ብዙዎችን ታዘብኩ የእሳቱን ክብደት በውስጤ እያሰብኩ
ግን እድለኛ ነኝ ምንም አላረገኝ
በሙቀት ውስጥ ሆኖ ብዙ አናገረኝ
የውስጤን ተረድቶየውስጡንነገረኝ
የፍቅሩ ነበልባል ለኔ ውሀ ሆነልኝ
ያነደኛል ብዬ ፈርቼ በልቤ
የውስጡን ስሰማ ተረጋጋ ልቤ
ፍቅሬ እሳት ነበርክ ያኔ ማትደፈር
እኔ ግን አስቤ ፈርቼ ደፍሬ
አንተን በመቅረቤ
እድለኛ ሆንኩኝ ደስታንምፍቅርንም
በአንዴ አገኘሁኝ
አንተም ውዱ እሳት የድሮ አስፈሪ
አሁንማ የኔ ተፈቃሪ
የኔ ውድአፍቃሪ ❤️❤️❤️
ቤቲ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
====== አጣው======
ከፀሀይም በታች ከምድርም በለይ
ሀሳቤን ሰብስቤ ቆሜ ዙሪያዬን ሳይ
ምንአለ አዲስ ነገር ሳለን በምድርላይ
ምሽቱ ንጋቱ እንጂ ሌላ ምንም አላይ
አዲስ ነገር ፈለኩ ግን አጣው ላይኔ
አዲስ ነገር ካለ ስጡኝ እስኪ ለእኔ
ለማግኘት ፈልጌ አጥቻለው እኔ
ቁጭብዬ ልጠብቅ እሲከመጣ ወደኔ
ገጣሚ ልጅ ፓፒ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
፨014 :እሺ አትይም እንጂ …፨፨፨፨
ጨረቃን አውርጃት ፣ደቁሼ ፈጭቻት
በመዳፌ መሀል፣ አልቁጬ አልሜያት
ገፅሽን ነድፋለው ፣ከሰማይ ሸራ ላይ
ምትሃት መልክሽን ፣አለም ሁሉ እንዲያይ የኪሊዮፓትራን ስም ፣አለም ይገድፈዋል
ያንቺን ስም በምትክ ፣በልቡ ይፅፈዋል
አንቺ ግን ፈፅሞ እሺ አትይም እንጂ
ፀሀይን ቀፍፌ ወዟን አንጠፍጥፌ
አካሏን ቀርፌ
እጅግ አብረቅራቂ አክሊል አበጅቼ
እሰጥሽ ነበረ ብርሀን ሰውቼ
ግን አንቺ የኔ ውድ እሺ አትይም እንጂ
ፍላጎትሽ ሆኖ ወደሽ ብትፈቅጂ
ሺህ መአልቶች አልፈው መአልቶች ሲተኩ
ወንዞችም ተጉዘው ከባህር ሲጠልቁ
የውቅያኖስ ውሀ በትነት እስከሚያልቅ
ጠብታ ውሀ አቶ አሸዋው እስኪደርቅ
ከውሀው ዳር ቆሜ አንቺን እሰብካለው
ውበት ሚስጥርሽን እተነትናለው
ከልቤ ውስጥ ያለን ፍቅርሽን ጨምቄ
ህዝቡን አጠምቃለው
እንደውም ልንገርሽ እሺ አትይም እንጂ
ፍላጎትሽ ሆኖ ወደሽ ብትፈቅጂ
ያባይን ፏፏቴ ጭኔ ላይ ገምጄ
ቀስተ ደመናውን ከሰማይ አውርጄ
ሁለቱን ባንድ ላይ አመሳጥሬአቸው
ቀጭን ወገብሽ ላይ ነበር የማስራቸው
አንቺ ግን ፈፅሞ እሺአትይም እንጂ...
አይኖቼ እስኪፈሱ አልቅሼ አንብቼ
በትኩስ እንባዋች ውቅያኖስ ሰርቼ
ታንኳ አበጅቼ
በነፋሻው አየር አየቀዘፍኩልሽ
የፍቅርሽን ድርሳን እየተረኩልሸ
ሌሊቱን በሙሉ ማህሌት ቆሜልሽ
አንዴ ስዘምልሽ ሲለኝ ሳረግድልሽ
ዜማ ሳዜምልሽ ቅኔ ስቀኝልሽ
ሺህ አመት ላክብርሽ ሺህ አመት ላንግስሽ
ይሄን ሁሉ ትቼ ከሆነ ምይከፋሽ
ዘመን መለወጫ ካላንደር ላድርግሽ
ምናምን ቢሊዮን ወንዶችን ቀጥሬ
መስከረም አንድ ላይ በቁመት ሰድሬ
ባበዮሽ ፋንታ እንዲህ እንዲያዜሙ
በብርዳማ ጠዋት በርሽ ለይ ቢቆሙ.....
አንችን መሳይ የለም
አንችን መሳይ የለም
ድንቅ ተደርጋ እዩአት ተፈጥራ
የቆንጆ ንግስት ተብላ ትጠራ
እንኳን ስትስቅ ከቤት ውስጥ ሁና
እደጅ ያበራል ሳቅ ብርሀኗ
ከዋክብት ይርገፍ ከእግሯ ስር
ተቆጭም የለ በእሷ ግብር
አለሜ ያይኔ ሲሳይ ፈገግ በይ
ታድያ ይሄን ግዜ ፈገግታሽ ከታየ
ብሩህ ዘመን መጣ አዲስ ጮራ ታየ
አሮጌው አለፈ ዘመን ተለወጠ
ምድር በደስታ በሀሴት ተዋጠ
አንቺ አትይም እንጂ ላግኝህ ብትይኝ
በፈቀደሽ ጊዜ መርጠሸ ብትቀጥሪኝ
የምትስቅ ጨረቃን ከሰማይ አውርጄ
የህዋን ቀለማት በአንድ አዋህጄ
በከዋክብት ሰልፍ መምጫሽን አስምሬ
ከቤቴ ጣራ ስር ፀሀይን አስሬ
አንቺ ግን ፈፅሞ እሺ አትይም እንጂ
ፍላጎትሽ ሆኖ ወደሽ ብትፈቅጂ
ምኞቴና ህልሜ ሁሉም ከሰመረ
ከመኝታ ቤቴ እቀጥርሽ ነበረ።
(ናዝራዊው ቃዬል)

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
መኖር ብዙ ያሳያል

ሂወት ብለን ይዘን
ሁላችን አንድ ሆነን
በመዋደድ መሀል ፍቅርን አንግበን
በአበሮነት በፍቅር ጥላቻ አሶግደን
ተባብረን አንድ ሆነን በህብረት ስንቆም
በዚ ሁሉ መሀል ሂወት አላት ትርጉም
ግን የአንድቀን ስህተት ብዙዎችን ወክሎ
ፍቅራችንን ውጦ ጥላቻ ከልሎ
ወንድሙን ለመግደል ሀይልን አንስቶ
በወንድሞቹ ሞት እጅግ ተደስቶ
ግራ በመገባት ህይወት ቀጥላለች
በውስብስብ አለም መቆየት ችላለች
የመኖር ትንቅንቅ አሁንም ቀጥሏል
በዚ ሁሉ መሀል አንድ ድምፅ በዝቷል
ዘሬ ቋንቋዬ የሚል በርክቷል
በዚ ሁሉ መሀል አንድ የሰው ልጅ አለ
እኛን እዚ ለማድረስ ብዙ የታገለ
በስህተቱ ምክኒያት ከተድላ የወጣ
ዘር እና ቋንቋውን ሳያውቀው የመጣ
አዳምን ጠይቆ መረዳት ይቻላል
ፊት የነበረውን ዘሩን ይናገራል
ለዚህ መልስ ማግኘት እጅጉን ይከብዳል
በዚመሀል መኖር ብዙ ብዙ ያሳያል
ባለመግባባት ውስጥ መኖር ቦታ ይዟል
አንዱ አለም

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
እቁልልጭ አደኩ
እቁልልጭ አደኩ አሁን ትልቅ ሆኩኝ ወጥቼ መግባትን እየተለማመድኩኝ
ድሮ ህፃን እያለው ከረሜላ ይዜ እቁልልጭ ብዬ
ነበር የምበላው እደግ በል አቢዬ ወይልጅነት እብደት
ማፈር እኮን የለ የለ ዝም ብሎ መጫወት
የእቃቃ ባልናሚስት ሆነን
እኛ እኮን ሳናድግ ልጆችንም ወልደን እንጫወት ነበር አኩኩሉ ብለን
አስታውስሻለው ልጅነት ጥሩ ነው
እራቁታችንን ልብሳችን ውጪ ነው
ከዛ ትምርትቤት ኤልኬጂ ዩኬጂ ብለን
ድግሪ ይመስል ተምረን እንመረቃለን
ከዛደሞ አደኛ ክፍል እንማራለን
የዛኔም አላደግን ጭቃ እያቦካን
ጥፋት አይሰለቸን እንመታለን
ተመልሼ ብሆን አሁን ደስ ይለኛል
እርጅና መጣእና ተቀመጭ ይለኛል
አድጌ ሳስበው አሁን ትዝ ይለኛል
ደሞ ስንጣላ መደባደባችን
ትንሽ ቆየት ብለን የመታረቃችን
ወይ ልጅነት ሙዴ
ልጆችን መውደዴ
አሁን ትልቅ ሆኩኝ
ነብሴንም አወኩኝ
ከአድ እስከ ስምት ኤለመተሪ ነኝ
አሁን ደሞ አደኩ አይስኩል ገባሁኝ
ደሞ ስልኮችንም ያዝኩኝ
መጀናጀን ፍቅር ህይወትን ጀመርኩኝ
ግና የልጅነት ወዜን አጣሁት ዘድሮ
አብረውኝ ያደጉት ኩራትን ጀምሮ
መመለስ ያሻኛል
ማደግ መቀየር ነው አሁን ትዝ ይለኛል
ልጅነት ውበት ነው ልመለስ ደክሞኛል

አመሰግናለው ፀሀፊ ቤዛዊት ተስፈዬ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
#ክልሌን_ላስመታት
.
.
እኔ የሷን ፍቅር በቃል ፣ መግለፅ ቢያቅተኝ
መግጠም ጀመርኩ ፣ ሳልተኛ ቅኔ ልቀኝ
ታድያ ፍቅሬን ፣ በግጥም ብገልፅላት
ግጥምክ ቤት ፣ አይመታም አለቺኝ በንቀት
እኔ በሷ ፍቅር ሌት ፣ ቀን ስባክን ከርሜ
ከንግዲ በኋላ...............
ክልል ነው እንጂ ፣ ቤት አይመታም ግጥሜ
.
.
. @ham_hit

.
01/01/13
ገጣሚ ሀምዛ አጃኢብ
.
.
.
.
(ቤት ፈላጊ ገጣሚ)
ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee ዘፀአት
@gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
❤️የአንድ ቀን እብደት❤️

ለአንድ ቀን ሁካታ
ለንድ ቀን ፈሽታ
የአመት ሀዘን የዘላለም በሽታ
ለአንድ ቀን ጭፈራ
የዘላለም ስራ
ለአንድቀን ፈገግታ ጨዋታ
የማያልቅ የሃዘን በሽታ
ምነው ቢቀርብን
ለአንድ ቀን ብለን ሞት ሲቀልድብን
ለንድ ቀን እብደት
ፈጣሪን መጣላት
የዘላለም ሞት ማበጀት
ማወደሻ አፌ ስድብ ተሞልቶበት
ማጨብጨብያ እጄ ቢራ ተይዞበት
ለንድ ቀን ፈገግታ
ሺ የምት እንቢልታ


👌👌👌👌ሰው ስለሆንኩ ስተት አለኝ
እናተ በፍቅር አርሙኝ👍👍👍👍👍👍

ፀሃፊ አሹ ከወለንጮ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
የመጀመሪያዬ👬

የመጀመሪያዬ የመውደድ ሀሁዬ
ፍቅር የሰጠሁክ ከናቴ አካፍዬ
አትወጣም ከልቤ መቼም አትረሳም
የልቤ ተምሳሌት ከልብ አትጠፋም
የልጅነት ቀልቤ አይቶ ያረፈብህ
የልጅነት ቀልቤ መርጦ የወደቀብህ
የፍቅር መምህር የመውደድ ጅማሬ
ትዝታህ ይኖራል በልቤ ቀብሬ


በእፁብ የተፃፈ

ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
Hagi Beyu:
                             28/04/13
              ብቻ እስኪቆርጥልኝ
ስደውል አታንሳ ስፈልግህ አትኑር
የኔን ነገር ተወው እንደዘበት ይቅር
እሷ ማናት ሲሉህ አልምጣልህ ተወው
እኔን ማስታወሱን ፍቅራችንን እርሳው
እንቆይ ተገናኝተን ሳምንት ወራት ይለፍ
እኔን መናፈቅህ እንደዘበት ይለፍ
ዛሬን አመናጭቀኝ አንቋሸኝ እንዳሻህ
ከኔ ልብ ይሻገር ይርዘም መዳረሻህ
በስራህ ተወጠር ወዳጅህን ያብዛው
እኔ ስለማልደክም ናፍቆትህን ልቻለው
እዚህ ነኝ ብለሀኝ እዛ ሁን ግድ የለም
እኔ ለብቻዬ ስለፍቅርህ ላልም
በናፍቆትህ ልክሳ ልጥቆር ግድ የለም
የኔና ያንተ ነገር ጅምር ተረት አርገው
የፍቅራችን ጀምበር እሰይ አዘቅዝቀው
ይሄ ሁሉ ይሁን በተስፋ ላፍቅርህ
ብቻ እስኪቆርጥልኝ ከነብሴ ላውልህ
ግን ውዴ አደራ ስቆርጥ እንዳትመጣ
ለይቅርታዬ ብለህ ራስክን እንዳትቀጣ
የቆረጥኩብህ ለት ፍፁም እንዳትደውል
ልቤ ያስብሻል ፍቅሬ ነሽ እንዳትል ቁልምጫ አይጠራኝም
ልመና አያስቀረኝም
መልእክቴን አጠብቅ ድምፄንም አትናፍቅ
ስለፍቅሬ ብለህ ያለህን አትናቅ
በደካማ ልብህ ከቶ እንዳትፈልገኝ
ከቆረጥኩኝ ኋላ ስራራልህ አልገኝ
ፍቅሬ ያበቃል ተራዬን ጠፋለሁ
ካንተ ሀሳብ ሸሽቼ ባተሌ ሆናለሁ
አንተ ስታወራ እኔ ዝ......ም እላለሁ
አንተ ስትነቃ እኔ እተኛለሁ
አውቆ የተኛን ነውና ተረቱ ብጠራኝ አልሰማ
ከልብህ ይረዝማል የኔ መዳረሻ
ልብህ እንዳይሻ ከኔ ዘንድ መድረሻ
ገራሙ ፀባዬ አንተ የምታውቀው
በሌላ ይተካል በፍቅር ያየሀው
ብቻ የቆረጥኩ ለት ከኔም ዘንድ ይጠልቃል
የፍቅራችን ጀንበር ፈጥኖ ያዘቀዝቃል
የፍቅርህ ስንክሳር ከልቤ ይጠረጋል
ሁሉም ይቀየራል በአዲስ ይተካል
ከሌቤ ወለል ላይ ፍቅርህ ይጠረጋል
እኔ በተራዬ አንተን ሲጠይቁኝ
ጨርሶ ረስቼህ ማነው?እላለሁኝ
ግን አደራህን ውዴ ይሄ ሁሉ ሲሆን
እንዳታዝን በኔ እኔን እኔዳትኮንን
ስለፍቅርህ ኖሬ ለፍቅርህ የሞትኩኝ
ላንተነትህ ብዬ በፍቅርህ ያበድኩኝ
አፍቃሪህ ነኝና አንተን ያስቀደምኩኝ
ከእውነተኛው ቤትህ በክብር አኑረኝ
ሞቼ ስለሚሆን በድኔን ጠብቅልኝ።

#ዘፀአት ቴአትር እና ስነ-ፅሑፍ አዳማ
ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች እና ተወዳዳሪዎች እንደሚታወቀው ወድድሩ ዛሬ እለተ አርብ ነበር የሚያልቀው ሆኖም ግን አዳዲስ ተወዳዳሪዎች እንደተቀላቀሉ ይታወቃል ስዚህም በነሱ ጥያቄ መሰረት የማጠናቂያ ጊዜው ተራዝሟል ስለዚህ የማጠናቂያ ጊዜው በተጀመረበት እለት ማክሰኞ ማታ 2:30 ነው ፉክክሩ ይቀጥላል like👍 ማስደረግ ምትችሉት እስከ ማክሰኞ ማታ 2:30 ብቻ ይሆናል መልካም እድል

#ዘፀአት ቴአትር እና ስነ-ፅሑፍ አዳማ
ግጥም ለመላክ @mmiki84
Channel @gxmee @gxmee
ለመወዳደር @mmiki84
2025/07/03 14:37:18
Back to Top
HTML Embed Code: