Telegram Web Link
#ከልብ_የመነጨ_ደግነት| መሰለች ሻንቆ
#hawassa
ሐዋሳ ካፈራቻቸው ቅን ልቦች መሴን አለመጥቀስ ይከብዳል። አብዛኛዎቻችን በኮንቦኒ የሙያ ኮሌጅ እናውቃታለን። የሐዋሳ ትዝታን በቅርበት ከሚያንፁ፣ በስራዎቻችን ላይ በበጎነት ከሚሳተፉና ከሚደግፉ አንዷ ነች።
ሰው ሲቸገር ከሰማች እንዲ ብናረግስ፣ በማለት ከተረፋት ሳይሆን ያላትን ለማካፈል ሚቀድማት የለም። መሴ አቅመ ደካሞችን በተለይ አዛውንቶችን በራሷ ተነሳሽነት ስትደግፍ ብትቆይም ከሚያስገርመኝኛ ከሚደንቀኝ ነገሯ በገንዘብና በቁስ ብቻ ሳይሆን ከተጣበበ ጊዜዋ ቀንሳ እናቶች ቤት በመሔድ እንደቤተሰብ የምትጨይቀውና የምታጫውተው ልዩ ያደርጋታል።
በዚህ አመት ከሚጀመረው "ተማሪ ልጄ" ቻሌንጅ (በቅርቡ በይፋ የምንጀምረው ነው) በትምህርታቸው ጎበዝ ሆነው በችግር ውስጥ ያሉ ወላጆቻቸውን ያጡም ሆኑ አቅም የሌላቸውን በመሠልመል በተለያዩ ደረጃዎች በአባትነት/በእናትነት ተቀብሎ ሙሉ አሠታዊ የትምህርት ወጭን ከመሸፈን ጀምር በተለያየ የድጋፍ እርከን አንድ ሰው (በጎ ፍቃደኛ) ለአንድ ተማሪ ሙሉ ስፖንሰር እንዲሆን ያለመው "የተማሪ ልጄ ቻሌንጅ ስንወያይ ቀናዋ መሴ "አንድ ተማሪ እንደ ልጄ አድርጌ ለልጄ የሚያስፈልገውን ለሱ/ለሷም በማሟላት ለማሳደግ እፈልጋለሁ" በማለት የመጀመሪያ ሻማውን ለኩሳለች!
ይህ በርካቶች የጠየቃችሁ ስላላችሁ የልጆቹን የኑሮ ሁኔታ መረጃ ከነፎቷቸው አጠናቅረን ስንጨርስ በመረጣችሁት የስፓንሰርነት ደረጃ አንድ ልጅ ይኖራችኋል። በኛ ዘመን ያልተማረ ዜጋ እንዳይኖር የተለኮሰውን ሻማ ማቀጣጠል እንድትዘጋጁ በልጆቻችን ስም እንጠይቃለን።
ወደመሴ ልመለስ እኔ እና ጓደኞቼ የተማሪ ልጅ አለን። እነዚህ ሁለት ልጆች ሙሉ አመታዊ የትምህርት ወጫቸውን በመሸፈን፣ ት/ቤት ድረስ በመሔድና በመከታተል እንደ ልጆቼ የማስተምራቸው ነተማሪ ልጆቼ ናቸው። ታዲያ መሴ ይህን ስነግራት በድንገት የዩኒፎርም ወጭያቸውን ለኔ ተውልኝ በማለት ለተማሪ ፋሲካ 6ኛ ተማሪ የኔነሽ 5ኛ ክፍል በአዳሬ የቀድሞ ቤተክህነት ት/ቤት የሚማሩ ሲሆን ለሁለቱም ዩኒፎርም በማዘጋጀት አበርክታለች! የልጆቹ ደስታና የደካማ ታማሚ እናት ምርቃት ባንች ይደር!
መሴ ሰው ፈገግ ብላ ሰዎችን ፈገግ በማሰኘት የምትቀርብ፤ በማህበራዊ ህይወቷ ከህፃን እስከአዋቂ፣ ከሊቅ እስከደቂቅ በፍቅር የምትቀርብና የምትታወቅበት መገለጫዋ ነው። ስራ ላይ ቆፍጣና ታታሪ መሆኗን አልደብቃችሁም።
ውድ የሐዋሳ ምርጦች ስለ መሴ ነካካሁ እንጅ አልተናገርኩምና የምታውቋት ግለጿት የማታውቋት መልካምነቷን ተከተሉ አመስግኑልኝ!
#መልካምነት_ይለምልም
ሐገራችንን ሰላም ያድርግልን!
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
መስከረም 2015
#የተማሪ ልጄ መርሐግብር| የምናስተምረው አንድ ልጅ ቻሌንጅ ተጀመረ!
#በትዕግስት_ያንብቡት #ሼር ያርጉልን
በኛ ዘመን እኛ እያለን በአቅም ማነስ ምክንያት የማይማር ትውልድ መኖር የለበትም!
ውድ የሐዋሳ ቅን ልቦች ሰላማችሁ ብዝት ይበል። በናንተ መኖር በርካቶች በተለያዩ ችግሮች ያጡትን ፈገግታ ለመመለስ በቅተዋል። በችግር ውስጥ ያሉ ከህፃን እስከአዋቂ አዛውንቶች መስጠት የሚችሉት ምስጋናና ምርቃት ነውና ያላቸውን ሁሉ በፍቅርና በአክብሮት አድርሰዋል። እኛም በእናንተ ኮርተናል፤ አምላክ ያሰባችሁትን ያሳካላችሁ።
በከተማችን በርካታ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ አካላት እንዳሉ እሙን ነው። መሰረታዊ ፍላጎታቸውን (መጨለያ፣ ምግብና አልባሳትን) ማሟላት ቅንጦት የሆነባቸውን ዜጎች ተመልክተናል። እነዚህንም ዜጎች ለማገዝ የተለያዩ በጎ ፍቃደኞች በተለያየ መልኩ ለመደገፍ ያሳዩት መነቃቃት ደስ የሚያሰኝ ነው። የሐዋሳ ትዝታም ማህበራዊ ማዲያን በመጠቀም በከተማችን ግምባር ቀደም ሁኖ ስለ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት ከኋሊት እየቃኘ መልካምነትን በትዝታ እያወሳ በርካታ ቅን ልቦችን ልብ ለልብ እያቀራረበ ለሶስት አመታት በአብሮነት ዘልቋል።
በሒደትም ትዝታን ማውሳትና ባለውለታዎችን ከማመስገን፣ ከማክበር አልፎ ትዝታን መፍጠር፣ ባለውለታዎችን ማበረታታትና ማነቃቃት ደርሷል። አቅም ያጡ ባለውለታዎችን ቤት ለቤት በመሔድ መጠየቅ፤ የታመሙትን ማሳከምና ላበረከቱት አስተዋፅኦ ቢያንስም የሚገባቸውን ክብርና ትኩረት በመስጠት ከናንተ በተገኘ ድጋፍ ያከናወናቸው በጎ ተግባራት ለበርካታ ማህበራዊ ማዲያ ተጠቃሚዎች ተምሳሌት ለመሆን በቅተናል።
ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን መጭው ትውልድ ላይ አትኩሮት መስጠቱ ደግሞ ነገ በትዝታ የዳሰስናቸው መልካም እሴቶች ተረክበው የምንናፍቀውን ማህበራዊነት አስቀጥሎ ለማለፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
በተለይ ጥሩ ብቃት ኖሯቸው በቤተሰብ አቅም ማነስ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ወይም ገብተውም እኩዮቻቸው ያሟሉትን የትምህርት ግብአት፣ አልባሳትና ምግብ እጦት ለስለንቦና ጉዳት የተዳረጉ ትጉ ህፃናትን መታደግ ደግነትን ማሳደግ፣ ማብዛት በመሆኑ በጥልቀት ማሰብና ማገዝ አለብን።
****
ቢያንሰ አንድ ልጅ በዘለቄታ በማስተማር የምንኮራበት የምንመኘውን ትውልድ እንፍጠር። የትምህርት አባት/እናት በመሆን ተማሪ ልጄን በተለያዩ አማራጮች እንደአቅምዎ ሊወስዱ ይችላሉ። (ተማሪዎቹ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ ቀበሌዎችና አካባቢዎች የማስተማር አቅም ካላቸው ወላጆች የተመለመሉ ናቸው። የሚኖሩት ከቤተሰብ/ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር ሆኖ እርስዎ በመረጡት ፓኬጅ ልጁን ለማስተማር የወላጅነት ሐላፊነትዎን ይወጣሉ።)
የወላጅነት አማራጮች
1. #ተማሪዬ
የተማሪውን አመታዊ የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ነው። ይህ ዩኒፎርም፣ ደብተርና ብዕር፣ ቦርሳና የትምህርት ቤት መዋጮን ያጠቃልላል።
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ወቅታዊ (የ10 የትምህርት ወራ) በጀት 2800 ብር
2. #እንደ_ልጄ
ይህ ምርጫ በ #ተማሪዬ ፓኬጅ ከተጠቀሱት የትምህርት ግብአቶች በተጨማሪ እርስዎ ለተማሪ ልጅዎ የሚያደርጉትን ይበልጥ መሰረታዊ ፍላጎቶች አሟልቶ ማሳደግ ነው። የትምህርት ቁሳቁስ፣ ጫማና የክት ልብስ፣ ምግብ ሆኖ እርስዎ በፈቀዱትና ባሻዎ ጊዜ የሚያደርጓቸው ለምሳሌ ልደቱን ማክበር፣ የበአል ስጦታና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
#የጊዜ ወሰን--Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ወቅታዊ አመታዊ በጀት ግምት 2800 + 10,000 (ምግብ ለ10 ወራት በወር አንድ ሺህ) + ልብስና ጫማ 1500 = 14,300 ብር
3. #ድርሻዬ
ይህ ጥቅል አንድ ልጅ በጋራ ለማስተማር የተመቸ ነው። ለአንድ ተማሪ ለመማር ከሚያስፈልጉት አማካይ ዝርዝር ግብአቶች አንዱን ብቻ በመምረጥ በየአመቱ መደገፍ ነው። ለምሳሌ ዩኒፎርም፣ ደብተርና ብዕር፣ ብዕር፣ ቦርሳ፣ ጫማ፣ የክት ልብስ፣ የምግብ ግብአት የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁሉም እንደ አቅሙና ፍላጎቱ የተማሪውን ልደት ማክበር፣ በአላትን ጠብቆ ስጦታ ማበርከት ሌሎችም ሊካተቱ ይችላሉ ማለት ነው።
#ድርሻዬን_ለልጄ ጥቅል አመታዊ በጀቱ ከ250 እስከ አስር ሺህ የሚደርስ ይሆናል። እርስዎ ለአንድ ተማሪ አመታዊ ብዕርና እርሳስ ከመሸፈን እስከ ወርሐዊ ቀለብ ድረስ በሚችሉትና ለፈለጉት ጊዜ እንዲደግፉ ያስችልዎታል።
#የጊዜ ወሰን:-
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ Ⓔየ____ ወር ቀለብ Ⓕበአላት Ⓖልደት እርስዎ ያስፈልጋል የሚሉትን ሁሉ ገደብ የለውም።
4. #ቤተሰብ
ይህ ያልተገደበ የወላጅነት ሚና ነው። ከላይ ከተጠቀሰው #እንደ_ልጄ ፓኬጅ የሚለየው እርስዎ ለልጅዎ የሚያደርጉትን ሁሉ በማካተት ነው። ይሔም የትምህርት ቁሳቁስ፣ የክት አልባሳትና ጫማ፣ ልደትና በአላት፣ መዝናኛና #ህክምና ሁሉንም በአንድነት ማሟላት ነው። አንድ ልጅ ከቤተሰብ ትከሻ ሙሉ ለሙሉ ማቅለል ማለት ነው።
ይህ የቤተሰብ ፓኬጅ ምንም የበጀት ገደብ የለውም።
የጊዜ ወሰን
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ለማነኛውም ጥያቄ ሐሳብና አስተያየት ይፃፉልን፣ ይደውሉልን!
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
#አንድ_ልጅ_ለማስተማር_አላንስም!አንድ_ሰው_ለአንድ_ታዳጊ ቻሌንጅ ተጀምሯል
አሳውን መስጠት ጥሩ ነው። አሳ ማጥመጃውን ሰጥቶ አንዴት እንደሚጠመድ ያሰለጠነ ደግሞ በጣም ጥሩ ነው። ከመቀበል ወደመስጠት የሚያሻግር፤ ከጥገኝነት አስወጥቶ በራስ የሚቆም ትውልድ መፍጠሩ እጅግ በጣም ጥሩ ምግባር ነውና!
እኛም አሳውን ብቻ ሳይሆን ማጥመጃውን ሰጥተን አሰልጥነን #ከጥገኝነት_የተላቀቀቀንና መልካም የሆነ የምንመኘውን ትውልድ ወደ መፍጠሩ እንሻገር።
ሕያውና የስኬታችን ማሳያ የሆነ #ሳይሳቀቅ ትምህርት መማር የሚችል አባ፣ እማ ብሎ የሚጠራን የሚናፍቀንና የምንናፍቀው የተማሪ ልጅ ይኑረን። የተማሪ ልጅ ሲኖርዎ የአብራክዎ ክፋይ የሚኮራብዎት የወላጅ ተምሳሌት ያደርግዎታል።
በህይወትዎ ምን ሰሩ? ተምረዋል። ነግደው አትርፈዋል። አግብተው ወልደው ልጆችዎን ለቁም ነገር አብቅተዋል። የተወደዱና የተከበሩ የሐይማኖት አባት።ባለሙያ ወይስ አይጋፋ ስፖርተኛ? ጋዜጠኛ ወይስ የተቋም ሐላፊ! ለጋስ በጎ ፍቃደኛ!
አዎ ታይቶ የሚጠፋ ሰሞነኛ ድጋፍ አድርገን፤ አልያም ለራሳችንና ለኑሯችን ለፍተን ተሳክቶልን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ዘለቄታዊ የሆነ እድገቱና ለውጡ በውል የሚታይ፤ የእርስዎ መኖርና ስኬት ነፀብራቅ ሊሆን የሚችል፤ በተቸገሩ የነገ ሐገር ተረካቢዎችን አስተምሬ ለቁም ነገር አብቅቻለሁ እንደማለት #የሚያረካ_ስኬት የለም።
ለዚህም ነው የተማሪ ልጄ ቻሌንጅ እንዲቀላቀሉ በከተማችን ቤት ለቤት በመሔድ የተመረጡ በርካታ ልጆችን አምጥተን የፈለጉትን አንድ ተማሪ ወስደው ለአጭር ጊዜ አልያም ለዘሌቄታ እንዲያስተምሩ ያመጣንልዎ።
ቢያንሰ አንድ ልጅ በዘለቄታ በማስተማር የምንኮራበት የምንመኘውን ትውልድ እንፍጠር። የትምህርት አባት/እናት በመሆን ተማሪ ልጄን በተለያዩ አማራጮች እንደአቅምዎ ቤተሰብ ሆነው ይችላሉ።
(ተማሪዎቹ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ ቀበሌዎችና አካባቢዎች የማስተማር አቅም ካላቸው ወላጆች የተመለመሉ ናቸው። የሚኖሩት ከቤተሰብ/ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር ሆኖ እርስዎ በመረጡት ፓኬጅ ልጁን ለማስተማር የወላጅነት ሐላፊነትዎን ይወጣሉ።)
የወላጅነት አማራጮች
1. #ተማሪዬ
የተማሪውን አመታዊ የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ነው። ይህ ዩኒፎርም፣ ደብተርና ብዕር፣ ቦርሳና የትምህርት ቤት መዋጮን ያጠቃልላል።
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ወቅታዊ (የ10 የትምህርት ወራ) በጀት 2800 ብር
2. #እንደ_ልጄ
ይህ ምርጫ በ #ተማሪዬ ፓኬጅ ከተጠቀሱት የትምህርት ግብአቶች በተጨማሪ እርስዎ ለተማሪ ልጅዎ የሚያደርጉትን ይበልጥ መሰረታዊ ፍላጎቶች አሟልቶ ማሳደግ ነው። የትምህርት ቁሳቁስ፣ ጫማና የክት ልብስ፣ ምግብ ሆኖ እርስዎ በፈቀዱትና ባሻዎ ጊዜ የሚያደርጓቸው ለምሳሌ ልደቱን ማክበር፣ የበአል ስጦታና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
#የጊዜ ወሰን--Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ወቅታዊ አመታዊ በጀት ግምት 2800 + 10,000 (ምግብ ለ10 ወራት በወር አንድ ሺህ) + ልብስና ጫማ 1500 = 14,300 ብር
3. #ድርሻዬ
ይህ ጥቅል አንድ ልጅ በጋራ ለማስተማር የተመቸ ነው። ለአንድ ተማሪ ለመማር ከሚያስፈልጉት አማካይ ዝርዝር ግብአቶች አንዱን ብቻ በመምረጥ በየአመቱ መደገፍ ነው። ለምሳሌ ዩኒፎርም፣ ደብተርና ብዕር፣ ብዕር፣ ቦርሳ፣ ጫማ፣ የክት ልብስ፣ የምግብ ግብአት የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁሉም እንደ አቅሙና ፍላጎቱ የተማሪውን ልደት ማክበር፣ በአላትን ጠብቆ ስጦታ ማበርከት ሌሎችም ሊካተቱ ይችላሉ ማለት ነው።
#ድርሻዬን_ለልጄ ጥቅል አመታዊ በጀቱ ከ250 እስከ አስር ሺህ የሚደርስ ይሆናል። እርስዎ ለአንድ ተማሪ አመታዊ ብዕርና እርሳስ ከመሸፈን እስከ ወርሐዊ ቀለብ ድረስ በሚችሉትና ለፈለጉት ጊዜ እንዲደግፉ ያስችልዎታል።
#የጊዜ ወሰን:-
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ Ⓔየ____ ወር ቀለብ Ⓕበአላት Ⓖልደት እርስዎ ያስፈልጋል የሚሉትን ሁሉ ገደብ የለውም።
4. #ቤተሰብ
ይህ ያልተገደበ የወላጅነት ሚና ነው። ከላይ ከተጠቀሰው #እንደ_ልጄ ፓኬጅ የሚለየው እርስዎ ለልጅዎ የሚያደርጉትን ሁሉ በማካተት ነው። ይሔም የትምህርት ቁሳቁስ፣ የክት አልባሳትና ጫማ፣ ልደትና በአላት፣ መዝናኛና #ህክምና ሁሉንም በአንድነት ማሟላት ነው። አንድ ልጅ ከቤተሰብ ትከሻ ሙሉ ለሙሉ ማቅለል ማለት ነው።
ይህ የቤተሰብ ፓኬጅ ምንም የበጀት ገደብ የለውም።
የጊዜ ወሰን
Ⓐ ለአንድ አመት Ⓑ አንደኛ ደረጃ Ⓒሁለተኛ ደረጃ Ⓓዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ
ለመሳተፍ ምን ያስፈልጋል?
ይደውሉ።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ጥቅምት 2015
#ተምሳሌት| በሀይሉ ጌታቸው
#hawassa
ሐላፊነት ምን ማለት እንደሆነ የገባው፤ ብዙ ከማውራት ማዳመጥና መስራት ልዩ መለያው የሆነ፤ ታታሪ፣ ስራው ሰውነትን ማዕከል ያደረገና ማህበራዊነቱ፣ አዛኝነቱ፣ ችግር ፈችነቱ ለስራው ስኬትን በተገልጋዩ ተወዳጅነትን አጎናፅፎታል።
በተለያዩ የስራ ሐላፊነቶች ተሰማርቶ ህዝብን እያገለገለ የቆየው ይህ ወጣት ተምሳሌት ዛሬ ላይ የሐዋሳ ከተማ የመሐል ክ/ከተማ አስተዳደር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ቅንነቱን ውሳኔ ሰጭነቱ "አዎ ቢል ሚቀበሉት፤ አደለም ቢል የማይቃወሙት የተወደደ ያደረገው ሁሉን አክባሪና አድማጭ በመሆኑ ነው።
ይህን ስራውን የተለከተ ይገባዋል ብሎ ሽልማት ሲሰጠው በእውነት ደስ የሚያሰኝ ነው። ባዬ ስኬቱ በመንግስት ሐላፊነቱ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ተባርኮ ምርጥ ባልና አባት መሆኑ ታላቅ ማሳያ ነው።
ውድ ቤተሰቦች ስለበሐይሉ ከኔ ይልቅ እናንተ ግለፁለት። እሱን የመሰሉ ታታሪዎችን ማመስገንና ማበረታታት ለሐዋሳ ቅን ልቦች የሚነገር አይደለም።
ሰላሙን ሁሉ ተመኘሁ!
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ጥቅምት 2015
#እናመሰግናለን!| ኤደን በቀለ
#hawassa|TEMARI_LIJE
በሐገራችን ብሩህ ተስፋ ማየት የምንፈልግ ከሆነ ባለ ተስፋ ትውልድ መፍጠር ከቻልን ነው። አቅምና ችሎታ ኖሯቸው በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት የሚሳቀቁና ከትምህርት ገበታቸው ለመራቅ የሚገደዱ ተስፈኞችን እኛ ካልደረስንላቸው የመኖራችን ትርጉምና የምንጠብቀውን ብሩህ ተስፋ ዋጋ አይኖረውም።
ኤዲ በ #ማሪ ልጄ ፓኬጅ ተስፈኛ ልጅ ለማስተማር መወሰንሽ ሐገር ወዳድነትሽን አሳይተሻልና እናመሰግናለን!
!!ሼር ማድረግም የድጋፉ አካል ነው!!
ለትውልድ እንሰራለን!
#መረጃ| Smart City
#hawassa
ከተማችን ሐዋሳ ከፍቅር ከተማነቷ ባሻገር በከተማ ፅዳት እንዲሁም በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ዘርፎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። በጅምር የነበሩና አዳዲስ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ እየተከናወኑ ሲሆን ይህንንም በቅርቡ በፎቶና ቪዲዮ አስደግፈን ከተማችንን የምንቃኝበት ፕሮግራም ይኖረናል።
ዛሬ በከተማችን ከንቲባ ረ/ፕ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የቀረበውን መረጃ እንደሚከተለው አቅርበናል። ከተሞችን ከቴክኖሎጂ ጋር የማዋዛቱ ስራ ይበልጥ የሚያዘምን ነውና ከተማችን የስማርት ሲቲ ባህሪያትን በመላበስ ላይ ትገኛለች!
" #Smart_City_Hawassa ን ዛሬ በቴክኖሎጂ አስተሳስረናል።

ስማርት ሲቲ የመገንባት ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል። ለከተሞች ዘመናዊነትና እድገት መሰረቱ ተቋማትን በቴክኖሎጂ ማስተሳሰርና በእውቀት ማዘመን ተቀዳሚ ተግባር እንደመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ የተገነባዉን እጅግ ዘመናዊ አርቴፊሻል ኢንቴሌጂንሲ መቆጣጠሪያ የደህንነት ካሜራ አሰገንብተን ዛሬ ለአገልግሎት አብቅተናል።

ሀዋሳ እንደ ስሟ የዘመነች፣ ዉብ፣ አረንጓዴ፣ ጹዱና ስማርት ከተማ እንድትሆን ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም በላቀ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ ለማስገንዘብ እወዳለሁ!!"
ሐዋሳ በእድገት ጉዳና!
ሰላም ለሐገራችን!
ጥቅምት 2015
#ቃል_በተግባር #ተማሪ_ልጄ
#hawassa
ውድ የሐዋሳ ምርጦች፤ ትውልድ ካልተማረ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ይገጥሙታል። ለዚህም በኛ ዘመን ያልተማረ ትውልድ መኖር የለበትም ብላችሁ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች በኢኮኖሚ ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ላይ የተቸገሩ ተማሪ ልጆችን መልምለን ያቀረብናቸውን በሙሉ በእናንተ ተወስደዋል/የሚያስተምር አግኝተዋል። እናመሰግናለን።
ትውልድ ወደፊት ሊገጥመው የሚችለውን ችግር ለመቅረፍ ዛሬ ላይ መስራት ይገባል በማለት ለመሳተፍ ጠይቃችሁ የነበራችሁ በርካታ ተማሪዎችን በመመልመል ጊዜ ወስደን ዛሬ ይዘን ቀርበናልና የዚህ በጎ ተግባር አካል ትሆኑ ዘንድ ጋብዘናል።
ቃል በተግባር ህዳር 21 ጀምሮ ልጆችዎን መደገፍ የሚጀምሩበት ነውና እንኳን ደስ አላችሁ። በተለያዩ የስራ ዘርፍ ያላችሁ በዓመት ከ250 ብር ጀምሮ ልጅን ማስተማር እንደሚቻል አውቀን ታሪክ እንስራ። ከምዕራባውያን ጥገኝነት ለማላቀቅ እኛው ለኛው እንደጋገፍ እንላለን።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ህዳር 8/2015
#እናመሰግናለን!| ኤደን በቀለ
#hawassa|TEMARI_LIJE
   በሐገራችን ብሩህ ተስፋ ማየት የምንፈልግ ከሆነ ባለ ተስፋ ትውልድ መፍጠር ከቻልን ነው። አቅምና ችሎታ ኖሯቸው በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት የሚሳቀቁና ከትምህርት ገበታቸው ለመራቅ የሚገደዱ ተስፈኞችን እኛ ካልደረስንላቸው የመኖራችን ትርጉምና የምንጠብቀውን ብሩህ ተስፋ ዋጋ አይኖረውም።
    ኤዲ በ #ማሪ ልጄ ፓኬጅ ተስፈኛ ልጅ ለማስተማር መወሰንሽ ሐገር ወዳድነትሽን አሳይተሻልና እናመሰግናለን!
   !!ሼር ማድረግም የድጋፉ አካል ነው!!
ለትውልድ እንሰራለን!
2025/10/25 01:37:52
Back to Top
HTML Embed Code: