Telegram Web Link
#እናመሰግናለን!| ቢኒያም በቀለ
#hawassa #temarilije
እኛ እያለን! በኛ ዘመን ተማሪ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታው አይቀርም! የሚሉን የሚደንቁ ቤተሰቦች ናቸው። በቅንነት እህት ወንድም ሁሉም አንድ አቋም አላቸው። ይህም መደጋገፍ ያደጉበት ስብዕናቸው ሁኖ ሁሌም መልካምነት ባለበት ይከሰታሉ።
የሚገርመው ከኢኮኖሚ ባለፈ በሐሳብ በምክር አብረውን ከመጀመሪያው ከኛ ጋር ነበሩ። ፈጣሪ በህይወት አቆይቶ የመልካምነታቸውን ፍሬ ለማየት ያብቃን።
ወንድማችን ቢኒያም እህቱ ያቀረበችለትን ሐሳብ ያለማንገራገር የተቀበለው በእርግጠኝነት መልካም ልቦና ቀድሞ የታደለ በመሆኑ ነው። በኔ አላበቃም ሲል አንድ ተማሪ #በድርሻዬ ፓኬጅ ሊያስተምር ወስኖ አላቆመም፤ ይልቅ ለማስቀጠልም የበኩሉን በማድረግ ላይ ይገኛል።
እኛም በተማሪዎቹና በሐዋሳ ትዝታ ቤተሰብ ስም በወጣ ይተካ ፈጣሪ ያክብርልን እንላለን።
ነገን ዛሬ እንስራ!
ህዳር 2015
#እናመሰግናለን! ቶም| Thank you!
#hawassa #temarilije
"መልካምነት ድንበር የለውም!" እንዲሉ ከዚህ ቀደም ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊዎችን በመደገፍ የመልካምነትን ህሊናዊ ርካታ ተጎንጭቷል። ዜጋ፣ ሐይማኖት፣ ዘር፣ ብሔር ... ምናምን የማይለየው ቅንነት ሰውን ሰው በመሆን ብቻ በመደገፍ ያምናል።
ቶም የማስተምራቸው ሌሎች አሉኝ በቃኝ ሳይል በዚህ ቻሌንጅ የበኩሌን አንድ ተማሪ #በድርሻዬ ፓኬጅ ለማስተማር መወሰኑን በእሌኒ በቀለ በኩል አብስሮናል፤ ከልብ እናመሰግናለን!
በዚህ አጋጣሚ ከሐገር ውጭ ያሉ ወገኖች እንዲሳተፉ በማስተባበር ሁነኛ ሐላፊነት በመወጣት ላይ የምትገኘው እሌኒን እንዲሁም ጊፍቲ ከልብ ማመስገን እንወዳለን!
#ተማሪ_ልጄ
ህዳር 2015
“የሐዋሳ ትዝታዎች”

በአለምሸት ግርማ

ብዙዎችን ከተደበቁበት በማውጣት ችግራቸውን ሰዎች እንዲጋሩና ድጋፍ እንዲያገኙ አድርገዋል። የታመሙ ጠያቂ እንዲያገኙ፣ ተስፋ ቆርጠው ትምህርታቸውን የተዉትን እንዲቀጥሉ ዕድል አመቻችተዋል። ካላቸው ለሌለው በማካፈልም እንዲሁ፡፡

እኚህ ባለታሪካችን መምህር ፍፁም በላይ ናቸው፡፡ ትውልዳቸውም ሆነ ዕድገታቸው በሀዋሳ ከተማ ነው። የቄስ ትምህርት ቤት ገብተው የፊደል ገበታን ከቆጠሩ በኋላ በኮምቦኒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብተው የተማሩ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

“ኮምቦኒ ትምህርት ቤት በመልካም ስነ-ምግባር እንድታነፅ ያደረገኝ ነው” ሲሉ ነበር ያስታወሱት። ከዚያም በሆሳዕና የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህርነት በዲፕሎማ መርሀ-ግብር ተመርቀው በመምህርነት ስራ ተሰማሩ።
ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ http://srta.gov.et/index.php/en
#ምስጋናው_የናንተ_ነው!| እናመሰግናለን
#hawassa| ሐይቅ ት/ቤት
ትውልድ ላይ መስራት ነገን ብሩህ እንዲሆን መሰረት ነው። እናንተም በቅንነት እንደ አቅማችሁ ተረባርባችሁ በከተማችን ለሚገኙ በኢኮኖሚ አቅመ ደካማ ለሆኑ፣ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ላላቸው (አካል ጉዳተኛ) ህፃናትን ጨምሮ ለ2015 የትምህርት ዘመን ከ600 መቶ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የደብተርና ብዕር ድጋፍ አድርጋችኋል።
ከድጋፉ ተጠቃሚዎች መሐከል የሐይቅ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መደበኛና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ተማሪዎች ይጠቀሳሉ።
በዛሬው እለት ህዳር 23/2015 የሐይቅ ት/ቤት የአካል ጉዳተኛና ተጋላጭ ልዶች ቀንን የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ የት/ቤቱ አስተዳደር ሐላፊዎች፣ በጎ አድራጊ ተቋማትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት "አካታች የፈጠራ ስራና ሽግግራዊ መፍትሔ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
በእለቱም ለተማሪዎች ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች የምስጋናና የምስክር ሰርተፍኬት ከት/ቤቱ ር/መምህር አቶ እያሱ ብርሐኑ እይዲሁም የክላስተሩ ተዘዋዋሪ መምህር አቶ እይድሪስ ከድር እጅ ተሰጥቷል።
የሐዋሳ ትዝታም ይህ የምስክር ሰርተፍኬት ሲሰጠው ትውልድ ላይ መስራት ተገቢ መሆኑን ባመናችሁና በቅንነት መልካምነትን ላስተማራችሁ የከተማችን እንቁዎች ምስጋናው የናንተ ነውና ክበሩልን ለማለት እንወዳለን።
#ጥቆማ
1. ማነኛውም ልዩ ፍላጎት (አካል ጉዳት ያለበት) ልጅ ያለው ቤተሰብ ልጁን ያለምንም ክፍያ (የደብተርና ቁሳቁስ ወጭን ጨምሮ) በከተማችን በሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች በማስገባት፤ ማስተማር የምትችሉ መሆኑን
2. መስማት የተሳናቸው ልጆች ካሉ ያለምንም ክፍያ በበቂ ባለሙያ ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ ቄራ ሜዳ በሚገኘው ቪዥን ግሎባል ኢምፓወርመንት በመላክ ማስተማር ትችላላችሁ
*
ነገን ዛሬ እንስራ!
#ምስጋና
የሐይቅ ት/ቤት አስተዳደርና እንድሪስ ከድር
#ምርጥ_ተሞክሮ| ያ ትውልድ
#hawassa
#የሐይቅ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት

የሀዋሳ ሀይቅ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት መሠረት ተጣለ።
በትምህርት ቤት ያላለፈ የለም። ለተማርንበት ት/ቤትና ላስተማሩን መምህራን ምን አደረግን? ምንስ ይጠበቅብናል? የዛሬ 30 እና አርባ አመት የነበሩት ት/ቤቶች ዛሬም ይኼ ነው የሚባል ለውጥ አላመጡም። ክፍሎቹ፣ ወንበሮቹ፣ ግቢው ባጠቃላይ ድሮ በነበሩበት ይስተዋላሉ። ዛሬ በአካል መጥቶ ላያቸው የቧረቅንበት ሜዳ፣ የዘለልነውን አጥር፣ የተቀመጥንበትን ወንበርና በርካታ ኩነቶች ባሉበት እናገኛቸው ይሆናል። ክኛን ለውጠው ላልተለወጡ ... ባለውለታዎች ምላሽ ይኖረን ይሆን?
ለዛሬ በተሞክሮ ለማቅረብ የወደድኩት ከ29 አመታት በፊት የተማሩበትን ሐይቅ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የነበሩ ዛሬ ከነትውስታቸው በልጅነት ቤታቸው ተገኝተው ለዛሬ ያበቋቸውን ጭምር ጋብዘው ተከስተዋል። መምህራኖቹም በኩራት "እንኳን መምህር ሆንኩ..." የሚል ስሜት ፈጥረውባቸዋል። ሌሎቻችሁ ይህን ህብረት በየተማሩባቸው ት/ቤቶች በማቋቋም ውለታችሁን ለመመለስ የሚያዘጋጅ ታላቅ የማንቂያ ደውል ሆኖ ታይቶኛል።
ጋዜጠኛ እንዱ ስሜቱን እንዲህ ነው በማህበራዊ ገፁ የገለፀው።
"ዛሬ በሀዋሳ ሀይቅ ትምህርት ቤታችን ከ29 ዓመት በፊት ጀምሮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስተማሩንን መምህራን(እነ ጋሽ ተሼንና ሞርሼን የመሣሠሉትን) በማየቴ እንባን የቀላቀለ ልዮ ስሜት ተሰማኝ!

እንባ የቀላቀለ ደስታ እንዴት ደስ ይላል ግን!

ያ ትውልድ ትዝታችንን ዳግም መለስ ብለን በበጎ ምግባር ጭምር ለመቃኘትና ለማጀብ ልዩ ምክክርን በተሳካ ሁኔታ ዛሬ አርጓል!

ምስክር እሸቱ ማሙሌ... ሌሎችም ልትመሠገኑ ይገባል።
የሐዋሳ ትዝታ ይህን ታላቅ ተሞክሮ ሲያቀርብ በታቦር፣ ቤተክህነት፣ ኢትዮጵያ ትቅደም .... ወዘተ እንዲሁም በግል የተማራችሁ ህብረት በማዋቀር ለዛሬ ያበቋችሁን ት/ቤትና መምህራን በመጎብኘት ውለታችንን እንመልስ ለማለት እንወዳለን!
የፍቅር የሰላምና የአንድነት ከርበኞች!
ህዳር 2015
@እንዱሽ_ግርማ😍
#እናመሰግናለን!| ቃልኪዳን ግርማ
#hawassa | ኑ ነገን ዛሬ እንስራ
በኛ ዘመን ትምህርት እየፈለጉ ነገር ግን በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መማር ቅንጦት የሆነባቸው እንዳሉ ያውቃሉ? አዎ ነገ ብሩህ ተስፋ እንዲታያቸው በቀላል በጀት ልጆችን ማስተማር እንችላለን። ከተረፈን ብቻ ሳይሆን ካለን ላይ ቀንሰን ነገን ዛሬ እንስራ!
ወጣት ቃልኪዳን እኔንም ይመለከተኛል በማለት ከመለመልናቸው በርካታ ተማሪ ልጆች ከንድ ተማሪ በተማሪዬ ፓኬጅ ለማስተማር ወስዷል። እጅግ እናመሰግናለን!
ለሌሎቻችንም ጊዜው አልረፈደምና አንድ ተማሪ በማስተማር የዚህ ወሳኝ ታሪክ ተሳታፊ ይሁኑ።
ነገን ዛሬ እንስራ!
#ተማሪ ልጄ
ህዳር 24/2015
#እንኳን_ደስ_አለን!| ቢሮ ተሰጥቶናል
#hawassa| ተማሪ ልጄ አፈፃፀም
እስከ አሁን ቋሚ መገኛ አድራሻ አልነበረንም። በርካቶችም አስተያየት ስትሰጡን ነበር። በተለየይ የምናከናውናቸውን በጎ ተግባራት በተለያየ መልኩ ስትደግፉን የነበራችሁ ይህ የምስራች ይድረሳችሁ።
በተለይ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ ሊለዩ ከጫፍ የደረሱ ታዳጊዎችን ለመመለስና ከጭንቀታቸው ለመገላገል ያቀረብነውን ጥሪ በቅንነት በማመን ለተቀበላችሁ ክብረት ይስጥልን።
ይህን እንቅስቃሴ በቻልነው አቅም ከግብ ለመምታት የምናረገውን ጥረት በመመልከት በሐዋሳ መሐል ክ/ከተማ አስተዳደር አቶ በሐይሉ፣ የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር አቶ መሐሪ ንጉሴ እንዲሁም የቤተልሔም ትምህርት ቤት ር/መምህርት ወ/ሮ ምህረት በቃል ለመግለፅ በሚከብድ በጎነት አላማችንን ከመደገፍ ባሻገር በትናንትናው ቀን በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ ክፍሎች አንዱን በቢሮነት እንድንጠቀም በይፋ ቁልፍ አስረክበውናል።
እኛም ተበታትኖ የመስራትን ፈተና ዛሬ ለሁሉም ግልፅ በሆነ ቋሚ አድራሻ ማግኘታችን ይበልጥ ስራችንን የሚያሳልጥ፤ ተአማኒነትና ግልፀኝነትን ከማጉላት አንፃር ከፎተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። አሁን በአድራሻችን በመምጣት ስራችንን መጎብኘትና ማገዝ ይቻላል።
#ተማሪ_ልጄ ከምን ደረሰ?
የሰሩትን ማክበር እውቅና መስጠት ይቀጥላል። አዲሱን ትውልድ ደግሞ ነገ ከሚገጥመው የህይወት ፈተና መታደግ/ቅድመ መከላከል ስራ በማስተማር ነገን ዛሬ እንሰራለን። ዛሬ በየጎዳናው የምናገኛቸውን ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍል ከጎዳና ማንሳት፤ መመገብና ማልበስ ወዘተ መልካም ስራዎች እንደሆነ ይታወቃል። ነገር ግን በቋሚነት ለውጥ ማምጣት የሚቻለው ወደ ጎዳና እንዳይመጡ መከላከል ላይ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ተገቢ ነው። ማስተማር ደግሞ ከመፍትሔዎቹ ዋናው ነው።
እስከአሁን ከ50 በላይ ስፖንሰር/ቤተሰብ፤ ከ70 በላይ ተማሪዎችን ለመያዝ ቃል ተገብቷል። ከዚህ ውስጥ በ23 ቤተሰቦች ወደ 40 ለሚሆኑ ልጆች በገቡት ቃል መሰረት አመታዊ በጀታቸውን ፈፅመዋል።
ከ27 በላይ የሆኑ ቃል የገቡና ተማሪ የጠየቁ ስፖንሰሮች (ፓስት የተደረጉና ያልተደረጉ) ከ30 በላይ ተማሪዎችን ቢይዙም አመታዊ በጀት ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡ (በአካል ለመገኘት እንዲያዩ አልያም ሐሳባቸውን እንዲገልፁልን በመጠበቅ ህዳር 21 ይጀመራል ያልነው እስከዛሬ ሊቆይ ችሏል።
በመሆኑም በቤተልሔም ት/ቤት ከተመለመሉ ከ35 በላይ ተማሪዎች ለ23ቱ በጀት ተፈፅሞ የተቀሩትን ደግሞ ስፖንሰሮቻቸው ምላሽ ሲሰጡ የሚካተቱ አድርገን በዛሬው እለት የፍላጎት ዝርዝርና አጠቃላይ አሰራራችን፤ ስፖንሰር የማስተዋወቅ ወዘተ ተግባራትን ፈፅመናል።
በቀጣይ ቀናት በሐይቅ ት/ቤት፤ በሕዳሴ እና በየአካባቢ የሚኖሩ ተማሪና አሳዳጊዎችን በመጥራት ተመሳሳይ ውይይትና አፈፃፀም የሚከናወን ይሆናል።
ውድ ቤተሰቦች ለካ ምግብ ሳይበላ የሚማር ተማሪ አለ? ለካ የት/ቤት መዋጮ መክፈል ባለመቻል ት/የሚያቆም አለ? ለካስ እናትና አባት የሌላቸው በለጋነታቸው በሰው ቤት እያገለገሉ ለትምህርት ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ህፃናት አሉ? ለካ.... ብዙ ብዙ እውነት የማይመስሉ ንፁህ እውነቶች በየቤቱ በፈገግታ ተሸፍነው ኖረዋል?
የእውነት ከጠበቅነው በላይ ለተማሪዎች ስነልቦና ስንል የማንፅፈው አሳዛኝ ቤተሰብ በማህከላችን አለ።
#ቃል_የገባችሁ_ ልጆቻችሁ_በተስፋ እየጠበቁ ነውና ለሌላ ሲሰጥ ቆመው ከማየት ይታደጓቸው። ሌሎች በርካታ ተማሪዎች ስላሉ ዛሬም #አልረፈደም_አንድ ተማሪ ያስተምሩ።
የሐዋሳ ትዝታ እያንዳንዱን የተማሪ ፕሮግሬስ ለስፖንሰሮቻቸው የምናሳውቅ ይሆናል።
#በሳምንት አንድ ቀንም የህይወት ክህሎት እና ስነምግባር ስልጠና ለተማሪዎች ይሰጣል። በዚ የሙያ ዘርፍ ያላችሁ አለን በሉን።
በመጨረሻ ለዚህ ስኬት የናንተ ድርሻ ዋናው ነውና እግዜር ያክብርልን። አቶ በሐይሉ፣ መ/ር ሱፐርቫይዘር መሐሪ ንጉሴ እንዲሁም ር/መምህርት ትዕግስት፣ ር/መምህርት ፍጥረትና ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን።
ነገን ዛሬ እንስራ!
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ታህሳስ 17/2015
#እንኳን_አደረሰን_አደረሳችሁ| የገና ስጦታ
#hawassa| ይሳተፉ
ውድ የሐዋሳ ቤተሰቦች፤ የቅን ልቦች ስብስብ፤ የመልካምነት አርአያ የሆናችሁ እንደተለመደው ገናን አምስኪን እናቶች ጋር እናሳልፋለን። ፆም መፍቻው ሳያስጨንቃቸው በፆም የቆዩ እንዲሁም በአል በባዶ ለማሳለፍ የቆረጡ እናትና አባቶችን ፈገግ እናሰኛለን።
ሁለተኛው ደግሞ አልባሳት ለተቸገሩ ለማድረስ ከየቤቱ ከየተቋሙ በመሰብሰብ ላይ ነን። የህፃን የአዋቂ ሁሉም አይነት መጠን ያላቸው የትኛውም አልባሳት ሳይጠቀሙበት በቤታችሁ ካለ አንድም ቢሆን በመስጠት በመስጠት ፈገግ አሰኝተው በአልዎን በደስታ ያሳልፉ።
ለተሳትፎ
በኢንቦክስ ያናግሩን። ወይ ከቨር ፔጅ ላይ ባለው ስልክ ይደውሉ።
የአቅምዎን ይለግሱ።
@አለማየሁ
2025/10/22 09:43:03
Back to Top
HTML Embed Code: