#አይረሴው_መምህር| መምህር ፀጋዬ
#hawassa| እስኪ አመስግኑልን
ሰለ እሳቸው የታቦር ት/ቤት ዛፎች ዛሬም ይመሰክሩላቸዋል! የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድሮች ይመሰክሩላቸዋል!! በተለይ ዩኒት ሊደር ሆነው ለእኛ በብዙ ደክመዋል! ዛሬ በሐዋሳ ትዝታ ዛሬም አስታውሰናቸዋል!!!! ትዝታችሁን አጋሩን እናክብራቸው።
ስለ መምህር ፀጋዬ በርካቶች ከመሰከሩት መካከል የሚከተለውን አጋርተናል። ጠምሩበት
"በእውነት መነሳት ካለባቸው መምህሮቻችን መካከል አንዱ እና ዋናው መምህር ፀጋዬ ናቸው።እሳቸውን ከመምህርነታቸው እና አባትነታቸው በተጨማሪ ለሀዋሳ ከተማ እስፖርት እድገት ያበረከቱት አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ነው።"
"ጋሽ ፀጋዬ ለስፖርቲ ሌሊት ወጥተው ሲሰሩ ውለው እቤታቸውን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ እንደውም ሳስበው እንቅልፍም የሚተኙ አይመስለኝም፡፡ ምክራቸው፣ ለስፖርት በተለይ ለእግር ኳስ ያላቸውን ፍቅር በምን ልንለካው እንችላለን?"
" ልጆቻቸውን አሳድገው ለወግ ለማዕረግ ያበቁበት መንገድ ግርም ይሉኛል! ጠዋት ከቤት ሲወጡ ብታይ አንተ በመኪና ወደ አንዱ የከተማው ጥግ ብትሄድ እርሳቸው እዛ ከልጆች ጋር ሀነው ኳስ ሲመለከቱ ታገኛለህ፡፡ "
"የሚወደዉን ስራ በፍቅር የሚሰራና በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንደርሳቸው አይቼ አላውቅም፡፡ ጋሽ ፀግሽ ረዥም እድሜ ከጤና ጋር!"
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
መልካም ስራ በትውልድ ይዘከራል!

#ተጫዋች_አምራቿ_ሐዋሳ| ከየት ወዴት?
#hawassa| በቼቼ ጳውሎስ
@ርዕሰ አንቀፅ "ልብ ያለው ልብ ይበል!
የኢትዮጵያ የእግርኳስ ታሪክ ከረጢት ነች፤ በየትኛውም ዘመን የትውልድ ቅብብሎሿ ሳይቋረጥ ላለፉት በርካታ ዓመታት እንደ ሃገር የበርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማምረቻ የኢትዮጵያዋ ብራዚል ነበረች ብል አላጋነንኩም።
ለብሄራዊ ቡድን ጥሪ ሲደረግ ለግማሽ የቀረበው ቁጥር ከዚህችው ዕንቁ ከተማ ከሐዋሳ ነበር ጥሪ የሚደረግላቸው። ከዋናዋ የሃገሪቱ መዲና አዲስአበባና ከበርካታ የክፍለሃገር ከተሞች በተሻለ ተጫዋቾችዋን ስትቸርና በአፍሪቃ መድረክ አብሪ ኮከብ ሆነውላት ኢትዮጵያ በሃዋሳዊያን ተወድሳለች። ያለፉት ደማቅ ታሪክ ፅፈው አልፈዋል፥ ያሉትና የቀሩት በቻሉት ሁሉ ለክለብና ለሃገር ያላተውን ችረዋል።
በሀዋሳ ልጆች ያልደመቀና ያልተዋበ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ፈልገህ አታገኝም፤ ብቻ ግን ሀዋሳ ትውልድ ሳይነጥፍባት ኳሰኞችን ሳታርጥ ከውብ ማህፀንዋ ውብ እግርኳሰኞችዋን ለኢትዮጵያ ሳትሰስት ሰጥታለች።
የዛሬው የፅሁፌ ዋነኛ ነጥብ ግን የከተማዋ የእግርኳስ አሁናዊ ገፅታ ላይ ያለኝን ታላቅ ስጋት የሚገልፅ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አራቱም የሃገሪቱ ማዕዘናት ለሚገኙ ክለቦች የሚጫወቱ ሃዋሳዊያን ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ከዓመታት በፊት ጀምሮ የጉዳት ሰለባ ሆነው ቀርተዋል። ሀዋሳ ከተማ ተወላጆችዋን ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ ልጆችን ማስመረጥ የተሳናት ይመስላል። ከሃገር አልፎ ለአህጉርና ለዓለም ዓቀፍ ውድድሮች የጠበቅናቸው በርካቶች በጉዳት ሰበብ ካለ ዕድሜያቸው ተቀምጠዋል። የከተማው ተወካይ በሆነው በሀዋሳ ከነማ ዋናው ቡድን እንኳን ሳይቀር ቋሚ ተሰላፊ የሆኑ የሀዋሳ ልጆችን ማየት ተስኖናል። በርካታ ዕንቁ ልጆችዋ ካለምንም ግጭትና አደጋ ከእግርኳሱ ዓለም ሸሽተዋል፤ ያሉትም ፈታኝ ጊዜ እያሳለፉ ነው።
ለኢትዮጵያ በርካታ ውለታን የዋለችው ሀዋሳ ዛሬ ዛሬ ላይ በፕሪሚየርሊግ ደረጃ ሳይቀር በየክለቦቻቸው ቋሚ ተሰላፊ የመሆን ዕድላቸው መመናመን በከተማዋ ላይ አንዳች መንፈሳዊ አሰራር መኖሩን እንዳስብ አድርገውኛል። አሁን አሁን ላይ አዳማ (ናዝሬት) ለኢትዮጵያ እግርኳስ ዕድገት ከአሰልጣኝ እስከ ተጫዋች ድረስ በርካቶችን የምታፈራ ከተማ ሆናለች የቀደመችውን ሀዋሳዬን የሚያስታውስ የእግርኳስ ትውልድ ፈጥራለች። በርካታ ኳሰኞችዋ ለብሄራዊ ቡድን ጥሪ ተመራጮችም ጭምር ሆነዋል።
ሀዋሳ ለምን የእግርኳስ ትወልድዋ ተመናመነ?
ለሀዋሳዊያን እንቁ እግርኳሰኞች ከሌሎች በተለየ የጉዳት ሰለባ መሆን ምክንያቱ ምን ይሆን?
በኩራት የምንጠራቸው የአሁን ቀን የከተማችን ውድ ተጫዋቾችስ አሉን?
ይሄ ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የኢትዮጵያዋ ብራዚል የሆነችው ከተማችን ታዳጊዎች ዕጣፈንታ ምንድነው?
ሁላችሁም በየግላችሁ ከራሳችሁ ጋር አውሩበት ሀዋሳ እንደ ክለብ ሳይሆን እንደ ከተማ ዘግናኝ የተጫዋች ድርቅና የጉዳት መፈንጫ የሆኑ ልጆች የሚወለዱባት ከተማ ሆናለች ለኔ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል መፍትሄን የሚሻ ሳይሆን በመንፈሳዊ መነፅር የሚታይ ሆኖ ስላገኘሁት እጅግ አስፈርቶኛል።
ሌላው ሁሉ ቀርቶ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ ባለፉት ዓመታት የሞቱ ከተማዋ ያፈራቻቸው እግርኳስ ተጫዋቾች ቁጥር ቀላል አይደለም። ከኮረም፥ከውቅሮ፥ ከጎድጓዳ በቀላሉ ያጣናቸው ወንድሞቻችን ጉዳይ በመንግስትና በውይይት የሚፈታ ጉዳይ አይደለም።
ነገር ግን አንዳች በከተማዋ ስፖርተኞች ላይ የተሰራ ክፉ አሰራር ከተማዋ የተጫዋች ድርቅ እንዲጎበኛትና ትወልድ እንዲመክንባት አድርጓታል።
" ልብ ያለው ልብ ይበል።"🙏🙏🙏
የትናንቷን የእግርኳስ ምድር ሀዋሳዬን አጥብቄ እናፍቃለሁ።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ህዳር 2016

#የዜሮ_ሶስች_ትዝታዎች| በጋዜጠኛ ተስፋዬ ታደሰ| አቹሜ
#hawassa| ክፍል አምስት|
ነበር❗ነበረ❗
የዚያኔ የነበሩ የጥበቃ ጓዶች "ከየት ነው የምትመጣው?" ሲሉት የነበረ ጎረምሳ ""ሻውር ወስጄ" ሲላቸው ""ቶሎ መልስ በአስቸኳይ መልስ"" ያሉት የትም አይደለም 03 ቀበሌ ነበረ❗
በአሳ እና በአሳር ላደግነው የ03 ህፃናት የትምህርት ቤት ውጤታችን ከፍተኛ ነበር❗ነበረ❗
ቁጣ ቁምጣና ቂጣ ለተዛመደው ለወቅቱ የ03 ህፃናት የሚወጡ ስሞች አብዛኛውን ጊዜ ተቃርኗቸው ያይላል.....ሀብታሙ በረከት ገንዘቤ በረከት አትክልት... ወዘተ....አሁንም አለ በፊትም ነበር❗ነበረ❗
("በአይነ-ሥጋ"") እስከምንገናኝ በሚለው ደብዳቤ ..."(የግብረ-ሥጋ") ግንኙነት ዙሪያ በሚሰጡት ምክር...ስለ-ሥጋ በፅሁፍና በድምፅ
ብቻ እንጂ ከመስቀል በዓል ውጪ አያውቀንም አናውቀውም ነበር❗ነበረ❗
መርፌ ቁልፍና ምላጭ በኪሳቸው......ቁራጭ ጨርቅ ቢጤ መሐረብ በእጃቸው የ03 ሽማግሌዎች መስፈርት ይመስል ነበረ❗ነበር❗
አብሾ-ጎዳ ሲባሉ መጠሪያ ስማቸው ሳይሆን መግነጢሳዊ ብሽቀት የሚፈጥርባቸው አዛውንት ...አብሾ-ጎዳ ብሎ ለጠራቸው በጅምላና በችርቻሮ እርግማን ያዘንቡ ነበረ......የጩሌ አባት የሚባሉ ሰውዬ እርምጃቸው መቼም አይረሳም ...ብራኬት ናቸው.....ሸንኮራ ሲነግዱ ውለው ያድራሉ ....ከሁሉም የሚገርመው በማሽን የመሰለ አቆራረጣቸው ነበር❗ነበረ❗
እንደ ጋሽ አያሌው Spar part የሴት ልጆቻቸው ቁንጅና....እንደ ዶዳ ጎበና የአለባበስ ስታይል (መሽቀርቀር)......እንደ ጳውሎስ ሒንጂሮ ወታደራዊ አቋም ....እንደ ጋሽ አበበ(ጆሆቫ) የቴክኒክ ችሎታ ....ተብሎ ይነገር ይወራ ይዘከር ነበረ❗ነበር❗
4በ*4 በሆነች አንድ ክፍል ቤት 3 አባወራዎች ከነልጆቻቸው በተአምር የሚኖሩበት ነበረ❗ቀበሌያችን......ኬሻ ተዘርግቶ እንደ አጠና በሚደረደሩት የምሽት መኝታቸው ...አንደኛው ከእህቱ የወለደው እዚያው 03 ነበረ....ይህንን የሰማው አንድ የሰፈሬ ልጅ ...በአዳራቸው ተገርሞ "ከወንድምህም ትወልዳለህ" ብሎን ነበር❗
ሕርቢኪ ባቶ ሚሊ አሳኖ አቴ ሌዶ አይ ታላማኖ--ሲዳምኛውን
ጦሳይ ታማ ዲርሳን ባናቱዮ ኦኔ ዳንዳኤና ጦናናዮ- ወላይትኛውን
በአንድ ላይ የዘመርን ........መሐመድን ከእታገኝ በትዳር ያጣመርን ......ጌታሁንን ከአሊ ያዛመድን 03ቶች ነበርን❗
የዜሮ ሶስት ትዝታዎች ክፍል 6 ይቀጥላል ....ይቀጣጠላል
| በዚህ አምድ የሚቀርቡ ሐሳቦች ቁም ነገርን በትዝታ እያዋዙ ለማዝናናት ብቻ የቀረቡ ናቸው። የከተማችን ማነኛውንም ሰፈር ሌላውን በማይነቅፍና በማይተች መልኩ አዋዝቶ ማቅረብ ይችላል። የሐዋሳ ትዝታ|

#ህዳር_30_ደረሰ| ነገ በጠዋቱ
#hawassa| የሜሪጆይ መልዕክት ይነበብ😍
የዘንድሮው የሜሪ ጆይ እግር ጉዞ አረጋዊያንን አከብራለሁ! በምርቃታቸውም እባረካለሁ! በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ህዳር 30 ዕለተ ዕሁድ የሚካሄድ ሲሆን፣
የጉዞው መነሻና መድረሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት ሱሙዳ አደባባይ ነው።
የጉዞው መስመር ከሱሙዳ አደባባይ ወደ ፍቅር ሀይቅ በሚወስደው መንገድ በሴንትራል ሆቴል ታጥፎ ተመልሶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት ያበቃና በአረጋዊያን ምርቃት የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ይሆናል።
👉የተጓዦች ከጉዞ ስፍራ መድረሻ ሰአት ማለዳ 12::30
👉በጉዞው መነሻ ስፍራ የሰውነት ማማሟቂያ እና በዕለቱ የክብር እንግዳ መክፈቻ ንግግርና ጉዞውን ማስጀመር ይካሄዳል።
👉 በጉዞው መሀል የሰርከስ ና የስካውት አባላት ትርኢት ይኖራል እንዲሁም የንጉስ ማልት ቅምሻም ተካቷል
🙏ማሳሰቢያ
👉 ማንኛውም ስለትእና የጦር መሳሪያ መያዝ አይቻልም
👉 ከበጎ አድራጎቱ አላማ እና ከማዝናናት ውጭ የሆኑ ንግግሮችና ሌላም ማንፀባረቅ አይፈቀድም
👉 አደንዛዥ ዕጾችንና አልኮል መጠቀምም ሆነ ተጠቅሞ መጓዝ አይፈቀድም
በመጨረሻም ሁላችንም አረጋውያኖቻችንን በማክበርና በመደገፍ ከምርቃታቸው በረከት ተንበሽብሸን እንድንመለስ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏