Audio
👉በዐብይ ጾም ለምን የንሰሐ መዝሙር ብቻ ሆነ
👉በዐብይ ጾም ለምን የቸብቸቦ መዝሙር አይዘመርም

👉🏾በዐብይ ጾም ለምን ከበሮ አይመታም
👉🏾በዐብይ ጾም ለምን ፅናፅል አንጠቀመም
👉🏾በዐብይ ፆም መብላት የሌለብን ምግቦች
       🍂ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ድምፀ🍂
#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ

‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ›› #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

    
ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።

ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።

በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።

ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
" እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "
@haymanotanednat
@haymanotanednat
​​​ገብርኄር

ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ​​​

‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ -25፥10 የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡

#አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡

👉# ፩ኛ: አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ፣ ዐሥር አድርጎ፣ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ›› ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡

👉# ፪ኛ: ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ፣ ወርዶ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው ‹‹አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡

👉# ፫ኛ: አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ ‹‹አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት፤ እነሆ መክሊትህ!›› ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት!›› ብሎ አዘዘ፡፡

#በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው (ክርስቲያን) ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም፣ በጎ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ (አገልጋይ) ይባላል፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡

#ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ፣ መክሊታቸውን (ጸጋቸውን) ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡

መክሊትን (ጸጋን) መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡


እንኳን ለዓቢይ ጾም ስድሰተኛ ሳምንት አደረሰን አደረሳችሁ።
🕊


†      [      ገ ብ ር ኄ ር      ]       †

🕊                     💖                   🕊

" አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ፤ እነሆ ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

ጌታውም። መልካም ፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ ፤ በጥቂቱ ታምነሃል ፥ በብዙ እሾምሃለሁ ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ፤ እነሆ ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

ጌታውም። መልካም ፥ አንተ በጎ ፥ ታማኝም ባሪያ ፤ በጥቂቱ ታምነሃል ፥ በብዙ እሾምሃለሁ ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።" [ ማቴ.፳፭፥፳ ]

🕊

[ 🕊 የሰንበት ምስባክ 🕊 ] ፦

" አቤቱ ፈጣሪዬ ወደህ የሠራኻትን ሕግ አስተምር ዘንድ ወደድኩ:: አንድም ሕግህን እጠብቃለሁ ብዬ መጥዎተ ርእስን ለማድረግ ወደድኩ:: አንድም ነውር ነቀፋ የሌለበትን እንከን የማይወጣለትን ፈቃድህን እፈጽም ዘንድ ወደድኩ ፤ አንድም ፈቃድህን ከፈቃዴ ሐሳብህን ከሐሳቤ ምኞቴና ከምኞትህ ጋር ለማዋሐድ ወደድኩ፡፡ አንድም የራሴን ፈቃድ ትቼ በአንተ ፈቃድ ልኖር ወደድኩ::

ፈቃድህን ለማደረግ ከመውደዴ የተነሣ የፈቃድህ መገለጫ የኾነው ሕግህ በልቡናዬ ሰሌዳ ላይ ተጽፎ ይኖራል። አንድም ሕግህን ዘወትር በልቤ ሳስብ ስዘክር እኖራለሁ::

ቸርነትህንና ከሃሊነትህን ለብዙ ጉባኤ ተናገርኩ። አንድም ያደረክልኝን የቸርነት ሥራ የዋልክልኝን ውለታ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት እግዚአብሔር እንዲህ አደረገልኝ ብዬ መስከርኩ። መዝ ፴፱ ፥ ፰

†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

💖

🕊                       💖                   🕊
ረድኤት በረከታቸው ይደርብንና በዛሬዋ ዕለት ሚያዝያ 9 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ያደረጉት ተአምር ይኽ ነው፡- ነፍሰ ገዳይና ሌባ ዝሙተኛ የሆነ አንድ ክፉ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በአባታችን በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የበዓል ቀን ወደ ቤ/ክ ሔደ፡፡ ከዚያም ደርሶ ሚያዝያ 9 ቀን ለዕረፍቱ በዓል የተዘጋጀውን ፍርፋሪ ቀመሰ፡፡ ከጽዋውም ጠጣ፡፡ መቃሩም ካለበት ከቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት ቆሞ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ተማጸነውና ወደቤቱ ሔደ፡፡
ከጥቂት ቀንም በኋላ በድንገት ታሞ በክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ የጨለማ አጋንንት ከበዋት እያዳፏት እያጋፏት ወደ ሲኦል ወሰዷትና ወደ ጥልቅ እሳት አወረዷት፡፡ ያንጊዜም አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ከመንበረ ጸባዖት ፊት ደርሶ ሰማይንና ምድርን በውስጧ ያለውንም ሁሉ ለፈጠረ ለልዑል እግዚአብሔር ገደገ፡፡ ‹‹አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ! በአንተ ስምና በእናትህ በድንግል ማርያም ስም ተማጽኛለሁና ይህችን ክፉ ነፍስ ማርልኝ በጸሎቴ ተማጽናለችና ለመታሰቢያዬም የተደረገ ፍርፋሪ ቀምሳለች ሥጋዋም ቦታዬ ተቀብሯልና ማርልኝ…›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ውሻ ይማራልን? በእኔ ላይ እጅግ በደል አድርሷልና ለአንተስ ያደረገልህ ምን ሥራ አለና በምን እምርልሃለሁ?›› አለው፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ‹‹…ስለገባህልኝ ቃልኪዳን ስለእኔ ስትል በቸርነትህ ማርልኝ፣ የሰጠኸኝ ኪዳን እንዳይታበል የመታሰቢያዬን ፍርፋሪ ቀምሳለችና ማርልኝ›› አለው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ቅዱስ ሚካኤልን ያችን ነፍስ ያመጣት ዘንድ አዘዘው፡፡ እርሱም ሔዶ አመጣት፡፡ ጌታችንም ያችን ነፍስ ‹‹ለወዳጄ ለእስትንፋሰ ክርስቶስ ምን አደረግሽለት? ያደረግሽለት ነገር ምን አለ?›› ብሎ ጠየቃት፡፡ ያችም ነፍስ ‹‹…በበዓሉ ቀን ወደ እርሱ ቦታ ሔጄ ለመታሰቢያው ለበዓሉ የተደረገውን ፍርፋሪ ቀምሻለሁ፣ ከአባታችን ፍቅር የተነሣ መታሰቢያውን ለማድረግ አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ቤቴ በሔድኩ ጊዜ ድንገት ሞቼ ወደዚህ መጣሁ›› ብላ መለሰች፡፡ ጌታችንም ለአባታችን ‹‹ወዳጄ ምሬልሃለሁ ወደዘላለም ደስታ ትግባ›› አለው፡፡ አባታችንም ሰግዶ ያችን ነፍስ ተቀብሎ ወደዘላለም ቤቱ አስገባት፡፡
የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸሎቱና በረከቱ ለዘላለሙ ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን፡፡
+ + +

ዳግመኛም ብርሃነ ክርስቶስ የተባለ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስይህን ታላቅ ተአምር አደረገ፡- እንደዛሬ ባለችው ቀን ሚያዝያ 9 ቀን አንድ የአባታችን ወዳጅ የሆነ ሰው የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ መታሰቢያ ወደሚደረግት ቦታ ሲሔድ ዳግመኛም ሚስቱ ልጇ ጋራ ለመመታሰቢያው የሚሆን እንጀራና ወይን ተሸክማ ስትሔድ በድንገት ከትልቅ ገደል ላይ ወደታች ወደቀች፡፡ ያንጊዜም ‹‹…የእስትንፋሰ ክርስቶስ አምላክ አድነኝ›› ብላ ጮኸች፡፡ ከወደቀችም በኋላ እግሯና እጇ ምንም ሳይሆኑ ዳነች፡፡ ወይኑም ሳይፈስ፣ እንጀራውም ሳይቆረስ፣ ወጡም ምንም ሳይፈስ ያች ሴት በሰላም ከልጇ ጋር ከወደቀችበት ገደል ውስጥ ተነሥታ የአባታችንን ተአምሩን እያደነቀች ተሸክማ ሔደች፡፡ እርሷና ልጇም ወደ አባታችን ገዳም ሔደው መካነ መቃብሩን እጅ ከነሡ በኋላ በአበምኔቱ እጅ እንጀራው ለሰው እንዲቀርብ አደረጉ፡፡ ከዚያ ያሉት ሰዎችም ከወደቀችበት ትልቅ ገድል ውስጥ ምንም ሳትሆን በደህና መውጣቷንና ለዝክር የተዘጋጀውም በተአምራት ምንም እንዳልፈሰሰ በነገረቻቸው ጊዜ ሁሉም የአባታችንን ተአምር አደነቁ፡፡ የወይኑንም እንስራ ለምስክር እንዲሆን እዚያው ገዳሙ ውስጥ አስቀመጡት፡፡ ከዚህም በኋላ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ዝክር እስከ ዕለተ ሞታቸው ሲዘክሩ ኖሩ፡፡ እንደዚሁም አባታችን እኛን ከወደቅንበት የኃጢአት ገደል ውስጥ ያንሣን፣ ምልጃው አይለየን አሜን!!!
+ + +

ዳግመኛም ረድኤት በረከታቸው ይደርብንና አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ‹‹ይህች ዕለት አትጠቅመኝም›› ብለው በመነኑባት በዛሬዋ ዕለት መጋቢት 9 ቀን ያደረጉት ተአምር ይኽ ነው፡-
አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ በሕይወተ ሥጋ ሣለ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከደቀ መዝሙሩ ከአባ ልብሰ ክርስቶስ ጋር በጎዳና ሲሔዱ የደረቀ የሰው አጥንት አግኝቶ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ፈጽሞ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፡፡ ያንጊዜም በጸሎቱ ኃይል ያ የሞተውና የደረቀው አጥንት ነፍስ ዘርቶ ተነሣ፡፡ ያንጊዜም አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ‹‹ከወዴት ነበርክ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ሞቶ የተነሣውም ሰው ‹‹…እኔ አስቀድሜ ያልተጠመቅሁ አረመኔ ስሆን የሰውን ገንዘብ የምቀማ ሽፍታ ወንበዴ ነበርኩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በገንዘብ ፍቅር የተነሣ ከጓደኞቼ ተጣልቼ ከበው ደብድበው ገድለው በዚህ ቦታ ጣሉኝ፣ ሥጋዬንም በከንቱ የዱር አራዊት በሉት፣ ነፍሴንም የጨለማ አጋንንት እያዳፏት እየገፏት ወስደው ወደ ሲኦል ወረወሯት፡፡ በሲኦል ውስጥ ሆኜ ብዙ ብዙ መከራና ሥቃይን አየሁ፡፡ በኃጢአታቸው ተፈርዶባቸው ወደ ሲኦል የገቡ ሕዝበ ክርስቲያን ዕለተ ሰንበትን የሚያከብሩ ከሆነ ዐርብ ዕለት በሰርክ በዘጠኝ ሰዓት ወጥተው እስከ ሰኞ ጠዋት በዕረፍት ቦታ በገነት ይቆያሉ፡፡ እናንተም የእግዚአብሔር ወዳጆች የሆናችሁ ቅዱሳንና መላእክት በሰንበት ዕለትና በበዓላት ነፍሳትን ከሲኦል አውጥታችሁ ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደገነት ታስገባላቸሁ፡፡ ሰንበትን የሻሩ ግን ከዓመት እስከ ዓመት ዕረፍት የላቸውም፣ መከራ ይበዛባቸዋል፡፡
እኛም ከእኛ በታች ካለ ጥልቅ እሳት ውስጥ ከሚኖሩ ጋር ያለዕረፍት ስንሠቃይ እንኖራለን፣ ዕረፍት የለንም፡፡ ከእናተ መካከል በቅዱሳን በዓላትና በሰንበት ነፍሳትን ከሲኦል እሳት የሚያወጡ አሉ፤ በፈረስም ሲኦል ገብተው ነፍሳትን የሚያወጡ አሉ፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ ዘውድ የደፉ አሉ፤ በክንፍ ወደ ሲኦል ገብተው ብዙ ክርስያንን የሚያወጡ አሉ፡፡ እንደእኛ ያለውን ግን የሚያወጣ የለም፡፡ እኛም ‹‹..ለዘመዶቻችን ስለኃጥአን በተሰቀለ ሞቶ ከሙታን ተለይቶ በ3ኛው ቀን በተነሣ በክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ማን በነገራቸው!?..›› እንላለን፡፡ በቀናች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አምነው በመልካም ምግባር ጸንተው ያሉ ከዘላላም ሥቃይ እሳት ይድናሉ፡፡ አባት ሆይ በክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ አንተን ተማጽኛለሁ ዳግመኛ ወደ ሥቃይ ቦታ ወደ ሲኦል እሳት እንዳልመለስ በጸሎትህ አድነኝ አለው፡፡ ያንጊዜ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ፊቱን አቅንቶ እጁን ዘርግቶ በመጸለይ ወዲያውኑ ለአንተ አሥራት ይሆንህ ዘንድ ሰጥቼሃለሁ አጥምቀው ታላቅ መነኩሴ ይሆንልሃልና›› የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ፡፡ በዚያን ጊዜም አባታችን መሬቱን እረግጦ ውኃን አፍልቆ ባርኮ አጥምቆ ከዚያም ‹‹..ተከተለኝ›› ብሎ አስከተለውና ወስዶ ፊደልን መዝመረ ዳዊትን አስተማረው፡፡ ስሙንም መከየደ ክርስቶስ ብሎ ሰየመው፡፡ እርሱም በጸሎት በጾም ተጠምዶ ዓመት ተቀምጦ በአባታችን በእስትንፋሰ ክርስቶስ ጸሎት አፍሮ ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደገነት ገባ፡፡
አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ አስቀድሞ ከሞት ማስነሣቱ፣ ዳግመኛም ውኃን አፍልቆ ማጥመቁ፣ ሦስተኛም ማስከተሉ፣ አራተኛም ከሲኦል አውጥቶ ወደገነት እንዲገባ ማድረጉ እጅግ ድንቅ ነው፡፡
ጸሎቱና በረከቱ ለዘላለሙ ከሁላችን ጋር ይሁን!
@haymanotanednat
@haymanotanednat
ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ማለት የሕዝብ ድል (የሕዝብ አለቃ ) ማለት ሲሆን ስሙ በዮሐንስ ወንጌል ብቻ ተጽፏል። የሳን ሕድሪን (የአይሁድ ሸንጎ ) አባል ሲሆን  ምሁረ ኦሪት ነበር። ከጌታም በቀጥታ የተማረ ነው። ጥያቄ ጠይቆ የተመለሰለት፡ ከገማልያል ንባብ ከጌታ ምስጢር ያደላደለ።

አንዳንድ ምሑራን ኒቆዲሞስን ተከራርካሪ ነው የሚሉት አሉ ነገር ግን ተከራካሪ ብቻ ሳይሆን ጠያቂም ነው። እንደ ዘካርያስ ሳይጠራጠር ያመነ ነው፡፡ መምህርነቱን ለማጽናት መጣ ግን አላዋቂነቱ ተነገረው። በአይሁድ ዘንድ የተከበረ የተማረ ባለጠጋም ነበር። ወደ ጌታ መጣ ካልታወቀ መምህር ዘንድ ለመማር ቀረበ። ጌታን እንደ ታዋቂ መምህር ስለማያዩት “ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦”

ኒቆዲሞስ እውነትን ለማወቅ የሚጓጓ ነበር። በሌሊት መጣ። በሌሊት የመጣበትን ምክንያት አንዱ ፍርሃት ሲሆን ፦ ያልተማረ እንዳይባል ነቀፋ ፈርቶ ነው፡፡ ኒቆዲሞሰ መምህር ይሁን እንጂ ከፍርሃት ነጻ አልነበረም፡፡ ከርሱ ጋር የታየውን ሰው ከምኩራብ ይለዩት ነበር፡፡ “ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፤ እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና” ዮሐ.9:25

ሌላው ምክንያት መምህርነቱ ካልተመሰከረለት መምህር መገኘቱ ሲሆን ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ  ቀን ለውይይት አይመችም ሕዝብ ጣልቃ እንዳይገባ ብሎ ነው ይላሉ መተርጉማነ ወንጌል፡፡ ኒቆዲሞስ ጌታን የቆጠረው እንደ አንድ ጻድቅ  ነበር እንጂ መሲህ አልመሰለውም  “በሕዝብም መካከል ስለ እርሱ ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዱም፦ ደግ ሰው ነው፤ ሌሎች ግን፦ አይደለም፥ ሕዝቡን ግን ያስታል ይሉ ነበር።” ዮሐ.7:12

ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ኒቆዲሞስ ሲናገር “ጌታ ኒቆዲሞስን በነቀፋ አልተቀበለውም አላሳፈረውም አልገሰጸውም ይልቁንም ትልቁን እና ጥልቁን ነገረ ሃይማኖትን አናገረው እንጂ” ይላል፡፡ ኒቆዲሞስ ስለ ጌታ የተወሰነ እውቀት ቢኖረውም ገና ያልጠራ ሰብአዊ ሐሳብ ነበረው። ተአምራቱን ስላየ እንደ ነቢይ አይቶታል። ጌታ ታዲያ ለምን በቀን አልመጣህም አላለውም  “አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።” እንዲል ኢሳ.42፡2 “አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም”ማቴ 12፡19   ዮሐ. 12፡47

የኒቆዲሞስ የንግግር መነሻ

“መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።”ኒቆዲሞስ ያላወቀው ነገር ቢኖር ተአምር ያደረገ ሁሉ ከእግዚአብሔር አለመሆኑን ነው። ዮሐንስ አፈወርቅ ሲተረጉመው፦ “ጌታ የመጣው ተአምራት ሊያደርግ ሳይሆን ነቢያትን እና ሕግን ለመፈጸም ነው” ይላል  “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” ማቴ.5፡17

 ጌታችን ለኒቆዲሞስ ሲናገር መምህር ብቻ መሆኑ ቀርቶ ከሁሉ አስቀድሞ መድኃኔ ዓለም እንደሆነ አረጋገጠለት፡፡ ከክርስቶስ ጋር ለመሆን አስፈላጊው ነገር ተገቢ መሆን ሳይሆን ዳግም መወለድ አስፈላጊ መሆኑን ማወቅ እንዳለበት ነገረው፡፡

ጌታችን ለኒቆዲሞስ “ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው” ዮሐ.3፡3 
ኒቆዲሞስ የሚያስፈልገው ነገር እንደገና መወለድ ስለነበር  ጌታ “ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ” አለው። በዚህ ንግግር ውስጥ መንፈሳዊ ህይወት ከሥጋዊ ሕይወት ወይም ከአእምሮ እውቀት በላይ መሆኑን የሚያሳይ መልእክትን ይዟል።

 ይኽንን መልስ ኒቆዲሞስ መሸከም የሚችለው አልነበረም፡፡ “እንደገና መወለድ ሲል ሌላ መወለድ፤ ሌላ እውቀት ከምድር ከተፈጥሮ አስተሳሰብ በላይ የላቀ እንዳለ ነገረው ” “ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው” ቁ.4

ሰው እንዴት ዳግመኛ ሊወለድ ይችላል አለው፡፡ ኒቆዲሞስ ምስጢሩ የረቀቀበት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ባለማወቁ ነው፡፡ የመወለዱን ምስጢር ሳይሆን መንገዱን ጠየቀ እንዴት? ይህ ሳራን ያስታውሰናል ትወልጃለሽ ስትባል ሳቀች በጣም ስላረጀች የሚሆን አልመሰላትም፡፡ ሁለተኛ ወደ ማሕጸን እንዴት ሊገባ ይችላል? አለ፡፡ ይኽ መንፈሳዊ ነገሮችን እንዴት ወደራሳችን ሀሳብ እንደምንጎትት ያሳያል።

ሌላው ኒቆዲሞስ በወቅቱ የመናፍቃንን ጥያቄን ይዞ ነበር የመጣው። ለጥያቄውም መልስ አላገኘም ነበር። “አይወለድም፣ እንዴት ሥጋ ሊለብስ ይችላል” የሚል ክርክር በአካባቢው  ነበር። ስለሆነም በራሳቸው መረዳት ተጉዘው ይስቱ ነበር። ኒቆዲሞስ መልሱ አልገባው ቢል ጥያቄውን ወደ ታች ወሰደው፡፡ “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም” 1ቆሮ.2፡14

ኒቆዲሞስ መምህር ነው ነገር ግን ሁለት ነገር ከበደው
  ፩.ዳግም ስለ መወለድ ፦ ለመምህር በሚያምነው መሠረታዊ ነገር ላይ እውቀት ማጣት ትልቅ ውድቀት ነው። ዛሬም ይኽው ነው። መምህራን ነን ብለው ከመሰረታዊ ትምህርት የሚጎድሉ በርካታ ናቸው፡፡ በየጠበል ሰፈር የአጋንንት ልፍለፋ ብቻ ሰምተው ራሳቸውን መምህራን ያደረጉም ያየንበት ዘመን ነው፡፡ ዘይት በመቀባት የሚነግዱም በመምህር" ስም ነጋዴዎች ናቸው። ሃይማኖትን ከድንቁርና አስተሳሰብ ማላቀቅና በቲዎሎጂ መምራት ይገባል፡፡ 

    ፪. “የእግዚአብሔር መንግሥት” ኒቆዲሞስ ይኽንን  ቃል  በአይሁድ ትምህርት ሰምቶ አያውቅም፡፡ በብሉይ ትምህርት ውስጥም የለም፡፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚመሠርተው እርሱ ነው። እነርሱ የሮማን መንግሥት መወደቅ ነው የሚጠብቁት፡፡ “ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” ኒቆዲሞስ የጥያቄው መልስ አስገረመው፡፡

ኒቆዲሞስ “አይችልም” ሲል ጌታ “ይቻላል” አለ። የመሬቱን እና የሰማዩን ልደት የሚለየው “መንፈስ” ነው።  ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ጌታ ሰው ዳግመኛ መወለድ እንዳለበት አስተማረው ።

የቀደመው ፍጥረት ውሐ፣ አፈር፣ ነፋስ ነው። የአሁኑ ፍጥረት ከውኃና ከመንፈስ ነው፡፡ ሰው እንዴት ከውኃ ይወለዳል ለሚለው ጥያቄ “ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው” የእኔ ጥያቄ “ሰው እንዴት ከአፈር ይፈጠራል” የሚል ይሆናል። ያ አፈር አጥንት፣ ቆዳ፣ ክፈለ አካል ሆኗል ቀለሙ ይለያያል፡፡

 ከውኃ መወለድ የሚታየው በእምነት ነው “ውኃው የሚለወጠው በእምነት ነው” “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ" ሲል ዘፍ.2፤7 

“ሕይወትን በሚሰጥ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን” ጸሎተ ሃይማኖት “ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” ይላል።
ጌታ ኒቆዲሞስን ሲያስረዳው ውኃ ከዚያም ነፋስ በማለት አስረዳው። ውኃ ከመሬት ይቀላል ነገር ግን ከአየር ይልቅ የተጠቀጠቀ ነው (denser than air) ቀድሞ ፍጥረት ካለቀ በኋላ ሰው ተፈጠረ(አሮጌ ሰው)። አሁን ግን አዲሱ ሰው ከተፈጠረ በኋላ አዲሱ መንግስት ይከፈታል። በጥንቱ ተፈጥሮ ሰው እግዚአብሔር መስሎ ተፈጠረ። አሁን ግን እግዚአብሔር ራሱን ከሰው ጋር አንድ አደረገ።

 ሰው ከተፈጥረ በኋላ ምድርን ይገዛ ገነትንም ይጠብቅ ዘንድ ሰጠው። አሁን ግን መንግስተ ሰማይን ይገባ ዘንድ ከፈተለት። በመጨረሻው በስድስተኛው ቀን ሰውን ፈጠረው። አሁን ግን በመጀመሪያ ሰውን አዘጋጀው። (መጀመሪያ ብርሃን እንደ ተፈጠረ) ሁሉ  የመጀመሪያው ሰው አዳም ከመሬት ከዚያም ሔዋን ከጎኑ አጥንት ከዚያም አቤል እያለ ይቀጥላል። ይህ ተፈጥሮአዊው ነው። የዳግመኛው በጥምቀት የተፈጠረው የዘር ሐረግ ግን አይታይም። አይቆጠርም (እገሌ እገሌን ወለደ) አይባልም። unseen generation by baptism። ስንጠመቅ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ይፈጸማል። ተሳታፊ እንሆናለን። ሞትና ትንሣኤ እንሳተፋለን።  ‘ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ….” የምንለው ለዚኽ ምስክር ነው፡፡

ሰው ወደ ውኃ ራሱን ከቶ ማውጣት ይችላል ለእግዚአብሔርም አሮጌውን ሰው ወደ ውኃ ከቶ አዲስ አድርጎ ማውጣት ቀላል ነው። ጥምቀቱም ሶስቴ በመደጋገም ይፈጸማል ፦ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም (Theocentric) “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን” ሮሜ.6:4 በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን ይላል። ጥምቀት መስቀል ተባለ መስቀልም ጥምቀት ተባለ። “እነርሱም፦ እንችላለን አሉት። ኢየሱስም፦ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ” ማር.10:39

በቀላሉ በውኃ ገብተን እንደምንወጣ በፈቃዱ ሞተ በቀላሉ ከሞት ተነሳ፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ለጽንስ ማሕጸን መፈጠሪያው ነው። ውኃ ለአማኞች ዳግም መወለጃ ነው። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል”     2. ቆሮ.5:17

ኒቆዲሞስ እስከ አሁን ግር ያለው ተገለጠለት “ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው” ይህ መንፈሳውያን የሚወለዱት ነው። “እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም” ዮሐ.1:13

 “ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው። ኒቆዲሞስ መልሶ፦ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው” ኒቆዲሞስን ወደ ረቀቀ ነገር አመጣው “አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን” ተባለ።

ነፋስ ወደ ፈቀደ ይነፍሳል ተባለ። ሴቷ ከአዳም ጎን መውጣቷ፣ ኤርትራ ተከፍሎ እስራኤል መሻገሩ። ኤልሳዕ ብረት በውሃ ማንሳፈፉን፣ ንእማን በውሃ ለምጽ ማንጻቱን….. ይህ ሁሉ ከውኃ መወለድ አምሳል ነው።

ኒቆዲሞስ

 መሰከረ :-  በሌሊት ተምሮ በቀን መሰከረ “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው” ዮሐ.8:51 በሕጋቸው ሌሊት ፍርድ አይሰጥምና ተቃወመ።

 በመጨረሻም የጌታን ሥጋ ገንዞ ቀበረ። ጸሎተ ኪዳን ተደረሰ  “ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ” እንደ በፊቱ ወደ ጌታ ለመምጣት ምሽት አልጠበቀም፡፡
ሆሣዕናችን ጌታ ኢየሱስ
✞ ጋሜል - ዘ ኦርቶዶክስ ✞
✞ ሆሣዕናችን ጌታ ኢየሱስ ✞
🌾🌾🌾🌾🌾🌿🌿🌷🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🎤🎤🎤🎤🎤🎤
የሰላም ንጉስ በአህያ ላይ
በእየሩሳሌም ታየ ፀሐይ
ደዌን ሊሸከም ሊያድለን ፈውስ
ሆሣዕናችን ጌታ ኢየሱስ
🥀🥀🌸🌸🌸🌸🌷🌷🌷🌷🌷🌿🌿🌷🌷🌹🌺🌺🎤🎤🎤🎤🎤🍃🍃🎋🎋🎋🥀🥀🥀🥀💐🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🕯🕯🕯🕯🌸🥀🥀🕊🕊🕊🕊🕊🕊🌾🌾🌾🌾🌾🥀🥀🌷🌷🕊🌹🌹🌹አጥንትን የሚያለመለም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን አሜን አሜን አሜን🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌾🌾🌾ስለ ዝማሬው የዝማሬ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌷🌷🌷🥀🥀🌿🤲🤲🤲🌾🌾🍃🍃🍃🍃🍃🌿🌾🌾🌾🌾🌿🌿
🌾🌾 #ሆሳዕና 🌾🌾

#የዐቢይ_ጾም_ስምንተኛ_ሳምንት(#ሆሳዕና)
#እንኳን_ለሆሣዕና_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ!
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
👉🏻 ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ  ቃል ሲኾን “ሆሻአና” ስሆን ትርጉሙ " እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን " ማለት ነው።
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ፡፡ ኅበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር፡፡ ወተቀበልዎ ሕዝብ በዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅ ዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበኃሤት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡

ትርጉም፡ የፋሲካ በዓል ሳምንት ሲቀረው የእውነተኛው አምላክ ደቀ መዛሙርት የእግዚአብሔር አገር ወደ ሆነችው ደብረ ዘይት ቁልቁለት ሲደርሱ ወደ እርሱ ለመታዘዝ ቀረቡ፤ ብዙ ሕዝብ፣ ልጆችና ሽማግሌዎችም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፡፡ በአህያ ተጭኖ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸው ዘንድ በፍጹም ደስታ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡

መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ)

ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ)

ምስባክ
"ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡

ወንጌል

ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም “ በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና ከረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህ በዚሁ በዓለ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርአየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካሪያስ እንደተነገረው ‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ ዘካ.9፣9። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናገሮ ነበር። ሲመጣም ‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።’’ በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። 2ኛ ነገ. 9፣13 ።

የሆሣዕና በዓል በቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡርክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር – በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ መዝ.117፣26 በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ታድላለች። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚመለከቱ የቅዱስ ማቴዎስ (ማቴ. 21፣1-17)፤ የቅዱስ ማርቆስ፣(ማር.11፣1-10)፤ የቅዱስ ሉቃስና (ሉቃ.19፣29-38)፤ የቅዱስ ዮሐንስ (ዮሐ.12፣12-15) ወንጌላት ይነበባሉ ።

ታዲያ አኛ ይህን ዐቢይ በዓል የምናከብረው እንዴት ነው? በነቢያቱ ከላይ እንደተገለጠው በወንጌላቱም አንደተፈጸመው እርሱ ወደ እኛ የሚመጣበት ጊዜ መቼ ነው? ሲመጣስ ምን እናድርግ? የእግዚአብሔርን መምጫ ጊዜ ማሰብና መዘጋጀት ያለብን እንዴት ነው? ምክንያቱም


በዓሉ ከምንም በላይ የሚጠቅመን ለእኛ ነውና ።

ስለዚህ ይህን በዓል ስናከብር ሰላምንና ፍቅርን የእርሱን የክብር አመጣጥ እያሰብን ልንተገብረው ይገባል። ለጌታ የማያስፈልግ ፍጥረት የለም ይልቁንም የክብር ዘውድ አድርጎ በመልኩ የፈጠረው ሰው ያስፈልገዋል።ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጠረ ማንም የለም።እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ዓላማና ዕቅድ የተፈጠርን እንደመሆናችን መጠን እግዚአብሔር የሚከብርበትን ሥራ ልንሠራ ይገባል።አህያ በሰው ሰውኛ ሲታይ የንቀትና የውርደት ሲመስል ይችላል ።የአህያን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት ግን

 በለዓም በሥጋዊ ገንዘብ መንፈሳዊ ዓይኑ ታውሮ እግዚአብሔር ያልረገማቸውን እስራኤላውያንን ሊራገም ሲሄድ እስራኤላውያንን እንዳይራገም ለመንገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው መልአክ በሚሄድበት መንገድ ላይ ቆሞ ሳለ ከበለዓም ይልቅ ያየችው የበለዓም አህያ ነበረች ። አህያይቱም መልአኩን አክብራ መንገዱን እንደለቀቀችለት ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ዘኅ.22፣23።
 በትንቢተ ኢሳያስ 1፣3 ‘ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጪ በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ እሥራኤል ግን አላወቀም’’ እንደተባለው ጌታ በተወለደ ጊዜ ትንቢቱን ምሳሌውን የሚያውቁ እሥራኤላውያን ባላወቁ ባለተቀበሉ ሰዓት በዚያ በብርድ ወራት እናቱ የምታለብሰው ልብስ አጥታ ቅጠል አልብሳው በነበረ ጊዜ ለጌታ ሙቀት የገበሩለት እረኞቻቸውን ተከትለው የመጡ ከበቶች ላሞችና አህዮች ናቸው። ‘ወአስተማወቅዎ አድግ ወላህም’’ እንዲል አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም።

በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይ.ራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)
#ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
#በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
#በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ
#በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
................................................................

=> ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው ?

ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው ?

1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡
=> ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም ?
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)

=> በአህያ መቀመጡ፦
👉 ትህትናን ለማስተማር
👉 የሰላም ዘመን ነው ሲል
👉 ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
👉 አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ
=> ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው ?
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ምን ምን ?
=> ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡
=> ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ ?
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና
@haymanotanednat
@haymanotanednat
Channel photo updated
👉🏾# ሥርዓት_ ዘሰሞነ_ ህማማት


ሥርዓት_ዘሰሙነ_ሕማማት ( ከሰኞ እስከ ዓርብ )
 
✍️ሰሙነ ህማማት ማለት :- "ሰመነ፣ ማለት ሳምንት አደረገ ማለት ነው " ይሄውም ከእለተ ሆሳዕና ሰርክ፣ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ እና ቀናት" የሚያመለክት ነው ፡፡

ሀመ - ማለት "ታመመ" ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዳያቢሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ፅዋተ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፣ "የሰሙነ ህማማት እለታት የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው" ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት፣ ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ አምላካቸውን የሚማፀኑበት፣ ጠዋት ማታ አምላካቸውን ደጅ የሚጠኑበት ፥ ኃጢያታቸውን በቤተክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት፣ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው ፡፡ 

መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፣ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፣ ምክራቸው የተፈፀመው ረቡዕ ነው፣ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ “እንስቀለው፣ እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር" ይህንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፣ "መስቀልም አንሳለምም" ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡

ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነውና ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው፣ ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም፣ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፤  የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፣ "ሔዋንን ሰላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት" የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፣ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ህማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፣ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፣ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል።

በህማማት ሳምንት "ሥርዓተ ፍትሀት አይደረግም"፣ ይኸውም ይህ ሳምንት "ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት፣ ከጨለማ ወደ ብርሀን የተጓዝንበት" የመሸጋገሪያ ወራት ምሳሌ በመሆኑ ነው፣
በእለተ ምፅአት መላእክት የመለከትን ድምፅ እንደሚያሰሙ፤ የዳግም ምፅአትን እለት በማሰብ ምዕመናን ጥሪውን ሰምተው፣ ከዚያም አስቀድመው የበአሉ ታዳሚዎች መሆናቸውን ለማጠየቅ "በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭሉን እያቃጨለ ምዕመናኑን ያሳስባል"

በዚህ የህማማት ሳምንት የስግደት የፀሎትና የፆም ስርዓታችን እንደሚከተለው ነው።

"ስግደት"
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ፣ 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል፣ ይህም ክርስቶስ ስለ እኛ በደልና ኃጢአት በሰው እጅ ተይዞ የቀበለውን መከራና ስቃይ ለማሰብ ነው፣ ክርስቶስ ለእኛ ፍቅሩን አንዴ ሞቶ ገልፆልናል፣ እኛ ግን ስለ በደላችን፣ በፍርድ ሰዓት በግራ እንዳንቆም አብዝተን ንስሐ በመግባት ሥጋችንን እናደክማለን።

"ጸሎት"
በሰሙነ ህማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ፣ እኒህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3 ሰዓት ፣ 6 ሰዓት ፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት፣ 3 ሰዓት፣ 6 ሰዓት፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት ናቸው፣ በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር "መዝሙረ ዳዊትና፣ ግብረ ሕማማት፣ ድርሳነ ማህያዊ አብዝተው ይጸለያሉ" ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚደረግ የጸሎት ሥርዓት ሲሆን ምዕመናን ተገኝተው ፀሎቱን ተካፋይ ይሆናሉ፣ "የግል ጸሎታቸውም ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ከውዳሴ ማርያምና ከውዳሴ አምላክ ፣ ከሰይፈ ሥላሴና፣ ሰይፈ መለኮት" ሲሆን፤ "መልክዓ መልክእና ድርሳናት እንዲሁም ተአምራት በህማማት ሳምንት ባሉ ቀናት ውስጥ አይጸለዩም

ይልቁንም ከቅዱሳን መጻሕፍት የጌታችን የአምላካችንን መከራውንና ድካሙን የሚያስታውሱ "ከትንቢተ ኢሳይያስ፣ ከትንቢተ ኤርሚያስ፣ ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ህማማት" በየሰዓቱ ይነበባል፡፡

       "ጾም"
በሰሙነ ህማማት "ብዙ አዝማደ መባልዕት አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም" ይልቁንስ በመራብ፣ በመጠማት፣ በመስገድ፣ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የአምላካችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውን ህማሙን ግርፋቱን ድካሙን በማሰብ ይዋላል። በዚህም "ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም" ይኸውም ቆሎ፣ ዳቦ፣ ውኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

በሰሞነ ህማማት የሚጸለዩና የማይጸለዩ የጸሎት መጽሐፍት አሉ

  "በሰሞነ ሕማማት የማይደገሙ የማይጸለዩ የጸሎት መጽሐፍት" :-

1.ድርሳናት
2.ገድላት
3.መልክአ መልክእዎች

"የሚጸለዩት ደግሞ:-"

1. ውዳሴ ማርያም፣
2.መዝሙረ ዳዊት በብዛት ከወትሮ በተለየ ቢያንስ የየዕለቱን ሙሉዉን፣
3. ሰይፈ መለኮት፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ውዳሴ አምላክ
4. ድርሳነ ማኀየዊ የጌታችን ሕማማትና እንግልቱ ያደረጋቸው ተዓምራትና፣ ዐርኬ መልከአ ማኀየዊ አንድ ላይ የየዕለቱ አለው፣
5.ላሓ ማርያም የእመቤታችን ለቅሶ ሐዘን

እነዚህ የጸሎት መጽሐፍቶቹ ያለን ሰዎች በርትተን እንጸልይባቸው፣ የጌታችንንም የእመቤታችንን ስቃይ እንግልት ሐዘን እንካፈል፣ በረከት እናግኝ ለአገራችንና ለዓለም ሰላም ለቤተክርስቲያናችን ፍቅር፣ አንድነት ተግተን እንጸልይ"
@haymanotanednat
@haymanotanednat
            " መልካም ሰሞነ ሕማማት "
2024/04/29 02:37:38
Back to Top
HTML Embed Code: