Telegram Web Link
በ ሰዕሊ ዘሪሁን ገብርወልድ የተሳለ ትክክለኛ ስዕል
#ዓርብ_ስቅለት

ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ በመሆን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምሕረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#አሥራ_ሦስቱ_ሕማማተ_መስቀል

#ተኰርዖተ_ርእስ (ራስና በዘንግ መመታት)

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በዘንግ መመታቱንና መቀጥቀጡን የሚገልጥ ነው፡፡

‹‹ተኰርዖት›› የሚለው ቃል ኩርዐ – መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፤ ርእስ ደግሞ ራስ ማለት ነው፡፡

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ የእሾህ አክሊል ጐንጉነው ራሱ ላይ ደፍተውበታል፤ ራሱንም በዘንግ መትተውታል ።
ማር ፲፭፥፲፱

የሰው ዘር ከአዳም ጀምሮ በጠላቱ በዲያብሎስ በተጐነጐነ የኃጢአት እሾህ ራሱ ተይዞ ነበርና ይህንኑ ለማስወገድ ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ የሆነ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ ተንኮል የተጐነጐነ አክሊለ ሦክ እንደ ዘውድ ደፋ፡፡

በሲኦል ወድቆ በዲያብሎስ ተረግጦ ራሱ የሚቀጠቀጠውን የሰውን ልጅ ለማዳን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱን በመቃ ተቀጠቀጠ፤ ከራሱ ላይ በሚወርደው ደም ፊቱ ተሸፈነ፡፡

#ተፀፍዖ_መልታሕት (በጥፊ መመታት)

‹‹ተፀፍዖ›› የሚለው ቃል ፀፍዐ በጥፊ መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፤ መልታሕት ደግሞ ፊት ጉንጭ ማለት ነው፡፡

ጌታችን ለሊቀ ካህናት ቀያፋ እውነትን መናገር እንደ ስድብ ተቆጥሮበት መላልሰው ፊቱን በጥፊ መትተውታል፤ ፊቱንም በጨርቅ ሸፍነው ‹‹ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማነው ትንቢት ተናገርልን›› እያሉ ዘብተውበታል፡፡

በጠላት ዲያብሎስ እጅ ወድቆ በነፍሱ ይቀለድበትና ይንገላታ የነበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ብሎ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ ወድቆ ተጐሰመ፤ ተንገላታ፤ በጥፊም ተመታ።
ማቴ ፳፯፥፳፯

ጲላጦስ አሳልፎ ከሰጠው በኋላም አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ አኑረው ቀይ ልብስ አልብሰው ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን›› እያሉ እየተሳለቁበት በጥፊ መትተውታል።
ዮሐ ፲፱፥፪-፬

#ወሪቀ_ምራቅ (ምራቅ መተፋት)

❖ ‹‹ወሪቅ›› የሚለው ቃል ወረቀ ካለው ግእዛዊ ግሥ የተገኘ ነው፤ ትርጉሙም እንትፍ አለ፣ (ተፋ) ማለት ነው፡፡ 

ርኩሳን አይሁድ በብርሃናዊው የክርስቶስ ፊት ላይ በሚያስጸይፍ ሁኔታ ምራቃቸውን እንደተፉበት የሚገልጥ ነው፡፡

በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ‹‹ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኩም›› ተብሎ እንደተነገረ እየዘበቱበት ምራቃቸውን ተፉበት።
(ኢሳ ፶፥፮፤ ማቴ ፳፯፥፳፱-፴ ፣ ማር ፲፭፥፲፱)

በኃጢአት የቆሸሸውን የሰውን ሕይወት ለማጥራት የመጣው ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፋበት፤ በሥራው ከገነት ተተፍቶ ተንቆ ተዋርዶ የነበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ ጌታችን ያለ ኃጢአቱ ተተፋበት ተናቀ ተዋረደ፡፡

#ሰትየ_ሐሞት (መራራ ሐሞት መጠጣት)

‹‹ሰተየ›› ማለት ጠጣ ማለት ነው፤ ሐሞት የሚለውም አሞት ተብሎ በቁሙ ይተረጐማል፡፡

ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሳለ ተጠማሁ ባለ ጊዜ መራራ ሐሞት መጠጣቱን የሚገልጥ ነው፡፡

‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ ነቢዩ ዳዊትን ትንቢት ያናገረ የነቢያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ‹‹ተጠማሁ›› ባለ ጊዜ ሆምጣጤ ተሞልቶበት ተቀምጦ ከነበረው ዕቃ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡
መዝ ፷፰፥፳፩

ጌታችንም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
( ማቴ ፳፯፥፵፰፤ ማር ፲፭፥፴፮፤ ሉቃ ፳፬፥፴፮ ፤ ዮሐ ፲፱፥፳፱ )

ቢጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ ውኃ የሚሰጥ አምላክ፤ የተጠማችውን ነፍስ የሚያረካ ጌታ፤ ለዘለዓለም የሚፈልቅ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሚያድል ፈጣሪ በተጠማ ጊዜ የፈጠረውን ውኃ እንኳን የሚያጠጣው የሚያቀምሰውም አላገኘም።
ኢሳ ፶፭፥፩

የዝናማት የባሕርና የውቅያኖስ ጌታ በውኃ ጥም ተቃጠለ፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሲኦል በረሃ ወድቀው በሕይወት ውሃ ጥም የተቃጠሉትን ነፍሳት ለማርካት ሲል እርሱ ተጠማ፡፡

በኃጢአት ወድቀው፣ በበደል ረክሰው፣ በነፍሳቸው ተጐሳቁለው፣ መራራ መከራን የሚቀበሉትንና ምረረ ገሃነም አፉን ከፍቶ ሆዱን አስፍቶ የሚጠብቃቸውን ሁሉ ለማዳን መራራ ሐሞትን ቀመሰ፤ ሆምጣጣውንም ጠጣ፤ የመረረውን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማጣፈጥ የመረረውን መጠጥ ተቀበለ፡፡

#ተቀሥፎ_ዘባን (ጀርባን መገረፍ)

‹‹ተቀሥፎ›› የሚለው ቃል ቀሠፈ- ገረፈ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፤ ‹‹ዘባን›› ደግሞ ጫንቃ፣ ትከሻ፣ ጀርባ ማለት ነው።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀርባው እስኪላጥ ያለ ርኅራኄ የመገረፉን ነገር የሚገልጥ ነው፡፡

በአይሁድ ልማድ የተገረፈ አይሰቀልም የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም ነበር። ጲላጣስ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን አስገረፈው፤ ከደሙ ንጹሕ ነኝ ብሎ ከታጠበ በኋላ ክርስቶስን ያለ ኃጢአቱ በመግረፍ ለአይሁድም አሳልፎ በመስጠት ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› እንዲሉ የታጠበ እጁን መልሶ አቆሸሸው።
(ማቴ ፳፯፥፳፰ ፤ ማር ፲፭፥፲፭ ፤ ዮሐ፲፱፥፩)

መድኃኒታችን መንፀፈ ደይን ወድቆ በእግረ አጋንንት ተጠቅጥቆ በእሳት አለንጋ የሚገረፈውን የሰው ልጅ ለማዳን ሲል ጀርባውን ለግርፋት ሰጠ፤ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገረፈ፡፡
#ተዐርቆተ_ልብስ (ከልብስ መራቆት)

አምላካችን ኢየሱስ ክርስስቶስ ልብሱን መራቆቱን የሚገልጥ ነው፡፡

‹‹ተዐርቆተ›› ማለት ታረዘ፤ ተራቆተ ማለት ነው፤ ፀሐይና ከዋክብትን ብርሃን አልብሶ የፈጠረ አምላክ ተራቆተ፤ ጸጋውን ለዕሩቃን የሚያለብስ አምላክ ልብሱን ተገፍፎ ዕራቁቱን ቆመ፡፡

የሲኦል ወታደሮች የሆኑት አጋንንት የሰውን ልጅ ጸጋ ገፍፈውት ነበርና ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ በሰጣቸው ሰዓት ወታደሮች ልብሱን ገፍፈውታል።
ማቴ ፳፯፥፳፯

#ርግዘተ_ገቦ (ጎንን መወጋት)

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ጎኑን በስለታም ጦር መወጋቱን የሚገልጥ ነው፡፡

‹‹ርግዘት›› የሚለው ቃል ረገዘ- ወጋ ከተሰኘ የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፤ ገቦ ማለት ደግሞ ጎን ማለት ነው፡፡

ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ በግራና በቀኙ ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ነበር፤ ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር ጭናቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ አይሁድ ጲላጦስን በለመኑት መሠረት ጭፍሮቹ የሁለቱን ወንበዴዎች ጭን ጭናቸውን ከሰበሩ በኋላ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ሲመጡ ፈጽሞ እንደሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ስለወጋው ወዲያው ከጎኑ ደምና ውኃ ፈሰሰ
ዮሐ ፲፱፥፴፫

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ያደርገው ዘንድ ሞተ፤ የሰው ልጅ በዘለዓለማዊ ሞት ተይዞ ነበርና፤ ትልቁ ሞት በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር መለየት ነው፤ በጌታችን ሞት ግን ሞት ራሱ ድል ተነሣ፡፡

ከተወጋው የጌታችን ጎን ደምና ውኃ መፍሰሱም የእግዚአብሔርን ልጅነትና የዘለዓለምን ሕይወት አጥቶ የነበረው ሰው ልጅነቱና ሕይወቱ እንደተመለሰለት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ምክንያቱም ከጎኑ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቆ ልጅነትን ደሙንም ጠጥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛልና።
( ዮሐ ፫፥፭፤ ዮሐ ፮፥፶፬ )

#ተአሥሮተ_ድኅሪት (ወደ ኋላ መታሠር)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እጆቹን ወደኋላ የፊጥኝ መታሠሩን የሚገልጥ ነው፡፡

‹‹ተአሥሮት›› የሚለው ቃል አሠረ (ሲነበብ ይላላል) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አሠረ ማለት ነው፡፡

‹‹ድኅሪት›› የሚለው ቃል ደግሞ ተድኅረ- ወደኋላ አለ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ በሰጠባት በዚያች ዕለትና ሰዓት ሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች እጁን የኋሊት አሥረው መሬት ለመሬት ጎትተውታል፤ አፍገምግመውታል።
ዮሐ ፲፰፥፲፪

#አምሥቱ_ቅንዋተ_መስቀል መድኃኒታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረባቸውን ጠንካራ የብረት ችንካሮች (ምስማሮች) የሚገልጥ ነው፡፡

❖ ‹‹ቅንዋት›› የሚለው ቃል ቀነወ- ቸነከረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፤ መስቀል ማለት ደግሞ ዝም ብሎ የቆመ ግንድ ሳይሆን አሁን በየሥፍራው እንደምናየው ምልክት የተመሳቀለ እንጨት ነው፡፡

🔹 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች
❖ ሳዶር፣
❖ አላዶር፣
❖ ዳናት፣
❖ አዴራ፤
❖ ሮዳስ ይባላሉ፤ እነዚህም የአምሥቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌዎች መሆናቸውን አበው ያስተምራሉ፡፡

ምንጭ
ማኅበረ ቅዱሳን

እንበለ ደዌ ወሕማምእንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ አመ ከመ ዮም እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሰላም

@haymanoteabew
@haymanoteabew
@haymanoteabew
" ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተቀመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ፤ ሁሉን የያዘውን ያዙት ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት የሕያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤ በቊጣ ጐተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተላቸው ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በዐደባባይ አቆሙት ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት
በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ ዘውድ
አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው ፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ ይህን ያህል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው?፤ ይህን ያህል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው?፤ ይህን ያህል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው?፤ ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?፤ ኀያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወት የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት፤ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤. . . የወልድ መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል፤ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ "

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ቅዳሜ_ቀዳም_ስዑር

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሏት

#ቀዳም_ሥዑር_ይባላል ፡- የትንሣኤ ዋዜማ የሆነችው ቀዳሚት ሰንበት ከወትሮው በተለየ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል ፤ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች ቅዳሜ/ ተብላለች። የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምና ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ከእህል ውኃ ርቀው በጾም አክብረዋታልና ነው።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜ ይባላል ፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡

#ቅዱስ_ቅዳሜ ይባላል፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

#ሰንበት_ዓባይ_ይባላል፦ይኸውም የፊተኛይቱ ቅዳሜ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከሥራው ያረፈባት ዕለት ስትኾን ይህቺ ግን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሦስት ዓመት ከሦስት ወር የማዳን ሥራውን በመስቀል ፈጽሞ በከርሠ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት ስለሆነች ነው፡፡

#ቀዳም_ስዑር_ርጥቡ_ቄጤማና_የኖህ_ርግብ

በዚች ዕለት ክርስቲያኖች ጠዋት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ሥርዓተ ጸሎቱ ሲፈጸም “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ- ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ፤ ሰላምን ፈጠረ፤ የምሥራች” ይባባላሉ፡፡ ለተሰበሰበ ሁሉ የምሥራች ምልክት የሚሆን ቄጤማ ይታደላል፡፡ ምእመናንም ይህን እየሰነጠቁ በራሳቸው ያስሩታል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላልመጡት ደግሞ ካህናት በየበኩላቸው ልብሰ ተክኅኗቸውን ለብሰው መስቀልና ቃጭል ይዘው ቄጤማውን “የምሥራች” እያሉ ይሰጣሉ፡፡

ቄጤማው የምሥራች ምልክት መሆኑ ከታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ዓለም በንፍር ውሃ በተጥለቀለቀች ጊዜ ኖኅ ርግብን የውሃውን ሁኔታ ለመረዳት በመስኮት አሾልኮ ወደ ምድር ይልካታል፡፡ እርሷም በአፏ ቄጤማ ይዛለት መጥታለች፡፡ ኖኅ የውሃውን መጉደል በቄጤማው ተረድቶ ተደሰተ፡፡ መርከቢቱንም ለማሳረፍ ተዘጋጀ፡፡ ቄጤማው ለውሃው መጉደል ለኖኅ የምሥራች እንደሆነለት አሁንም ክርስቶስ የኃጢአትን ውሃ እንደደመሰሰው ለማስገንዘብ ምእመናን ቄጤማ አስረው፣ ቄጤማ ይዘው ይታያሉ፡፡ የምሥራች ይባባላሉ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ለፈቀደ ለሰላም አለቃ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር የክብር ክብር ለእርሱ ይሁን አሜን::

በዚሁ ዕለት ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላም እንደሰጠን እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም ገጸ በረከት ያቀርባሉ፤ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ አንድም የምዕመናኑ በእራሳቸው ላይ ቄጠማ ማሰር አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው፤ ቃጭል ሲያቃጭሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቁ ምእመናን ትልቅ ብሥራት ነው፡፡

በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃየማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

@haymanoteabew
@haymanoteabew
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።

መልካም የትንሣኤ በዓል
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እም ይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

#በዓለ_ትንሣኤ_ፋሲካ_እየተባለ_የሚጠራበት_ምክንያት

የፋሲካ በዓል በዕብራይስጥ ቋንቋ ‹ፓሳህ› ይባላል፤ ትርጉሙም ‹ማለፍ› ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በዓለ ትንሣኤ አንደኛ ሞት፣ ከእስራኤል መንደር ያለፈበት ስለ ኾነ ነው፤ ግብፅ በረሃብ እንዳትመታ ፈርዖናቸው ያደረገው ነገር ባይኖርም መጻተኛውና ወደ ወኅኒ የወረደው ዮሴፍ ግን የረሃብ ሞትን ወደ ግብፅ እንዳይገባ ከለከለው፡፡ ዳሩ ግን ዮሴፍ ሲያልፍ የዮሴፍን ታሪክ የማያውቅ ሌላ ፈርዖን ተሾመና በእስራኤል ላይ የሞት ሕግ አወጣ (ዘፀ. ፩፥፲፩)፡፡

‹‹በአንተና በሴቲቱ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፡፡ እርሱ ራስ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰና ሰኰናውን ትነድፋለህ››(ዘፍ. ፫፥፲፭) ተብሎ የተነገረለት ዲያብሎስ ራስ ራሱን የሚቀጠቅጥ ወንድ እንዳይወለድ በማሰቡ ሕፃናትን ከማኅፀን እያስቀረ፤ ለመቃብርም እያቀበለ እስከ ሙሴ ዘመን ደረሰ፡፡ ከሙሴ መምጣት በኋላ ሞት የእስራኤልን መንደር ለቅቆ ወደ ግብፃውያን መንደር እንዲገባ ምክንያት የኾነው ዕለትም ፋሲካ ይባላል፡፡ በዚህ በዓል ላይ እስራኤላውያን የበግ ጠቦት አርደው የቤታቸውን ጉበን የቀቡትን ደም የተመለከተው ሞት እነርሱን ትቶ የግብፃውያንን የበኵር ልጆች ገደለ፡፡ እስራኤላውያን ‹‹ቀሣፊያችን ተቀሠፈ›› ሲሉ በዓላቸውን ‹ፋሲካ› አሉት፡፡

እኛም በሐዲስ ኪዳን የጌታችንን ትንሣኤ ፋሲካ የምንለው ሞት ከእኛ ያለፈበት የመጀመሪያው በዓላችን በመሆኑ ነው፡፡ ስለ ብዙዎች ይቅርታ የፈሰሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም በግብፅ ከተሠዋው በግ ይልቅ የከበረ መሥዋዕት ነውና ያሉትን ከማዳኑም ባሻገር የሞቱትንም ከመቃብር አውጥቷል፡፡ በእርሱ ትንሣኤ ሞት ከእኛ ማለፉንና የሰው ባሕርይ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱንም ‹‹ለምንት ተኀሥሣሁ ለሕያው ምስለ ምዉታን፤ ሕያዉን ከሙታን ጋር ስለ ምን ትፈልጉታላችሁ›› ከሚለው ኃይለ ቃል እንረዳለን (ማቴ. ፳፰፥፮)፡፡ ምዉታን ያላቸውም አጋንንት ናቸው፡፡ በጌታችን ትንሣኤ ሰው ከሙታነ ሕሊና ከአጋንንት ተለይቶ ተነሥቷል፡፡ ‹‹ኦ! አዳም መሬት አንተ ወትገብዕ ውስተመሬት፤ አዳም ሆይ ቀድሞም መሬት ነህ፤ ወደ መሬትነትህም ትመለሳለህ›› የሚለው አዋጅ አሁን ተቀይሯል፡፡ የጌታችን ትንሣኤ ከሚያረጀው ወደማያረጀው፣ ከሚበሰብሰው ወደማይበሰብሰው ሰውነት የተሸጋገርንበት በዓል ነው፡፡ ይህ ዂሉ መሸጋገር የተፈጸመው በፋሲካው በግ ምክንያት በመኾኑ ክርስቶስን ፋሲካችን እንለዋለን (፩ኛ ቆሮ. ፭፥፯)፡፡

ሁለተኛ ‹‹መሥዋዕተ ኦሪት አለፈ፤ መሥዋዕተ ወንጌል ደረሰ›› የምንልበት ወቅት ስለ ኾነ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለደቀ መዛሙርቱ በሰጠበት ዕለት በፋሲካ የተጀመረችውን ሕግ በፋሲካ ይሽራት ዘንድ የሚያልፈውን መሥዋዕተ ኦሪት አስቀድሞ፣ የሚመጣውን መሥዋዕተ ወንጌል አስከትሎ ፋሲካን አደረገ፡፡ ለደቀ መዛሙርቱም ‹‹ዝ ውእቱ ደምየ ዘይትከአው ለሐዲስ ሥርዓት በእንተ ቤዛ ብዙኃን፤ ስለ ብዙዎች ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው›› (ማቴ. ፳፮፥፳፰) በማለት ወደ ሐዲስ ኪዳን መግባታቸውን አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ትንሣኤ አሮጌውን ትተን ወደ አዲስ ሕይወት የተሸጋገርንበት በዓል በመኾኑ ፋሲካ እንለዋለን፡፡

ሦስተኛ የደስታችን ማረጋገጫ ስለ ኾነ ነው፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት በግእዝ ቋንቋ ‹ደስታ› ማለት ነው፡፡ ደስታችን የተረጋገጠው በጌታችን ትንሣኤ ሲኾን ፍጻሜውን የሚያገኘው ደግሞ በትንሣኤ ዘጉባኤ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን በዕለተ ዓርብ በቈረሰው ቅዱስ ሥጋውና ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ተመሥርታለች፡፡ ምንም እንኳን በሕዝብና በአሕዛብ ፊት ደስታዋን የምትገልጥበት ጊዜ ገና ቢኾንም፣ በትንሣኤው ግን በዝግ ቤት ውስጥ ኾና የክርስቶስን ሰላምታ ተቀብላ ተደስታለች (ዮሐ. ፳፥፲፱)፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ደስ ትሰኛለች›› እያልን የምንዘምረው፡፡

#ጌታችን_በኵረ_ትንሣኤ_የተባለበት_ምክንያት

የመጀመሪያው አዳም ለሞትና ለኀጢአት በኵር ሆኖ ነበርና ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ሞት ሲገዛን ኖሯል (ሮሜ. ፭፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ክርስቶስ ላንቀላፉት (ለሙታን) በኵራት ኾኖ ከሙታን ተነሥቶአል” በማለት ጌታችን የትንሣኤያችን በኵር መኾኑን ነግሮናል (፩ኛ ቆሮ. ፲፭፥፳)፡፡ ከጌታችን በፊት የሞቱና ከሙታን የተነሡ አሉ፡፡ ነገር ግን የጌታችን ትንሣኤ ከሌሎች ትንሣኤ የተለየ ነውና በኵረ ትንሣኤ (የትንሣኤ መጀመሪያ) ይባላል፡፡ ጌታችን በኵረ ትንሣኤ መባሉም፡-

አንደኛ ሞቱ፣ ሞትን ስላጠፋ ነው፡፡ የጌታችን ሞት ከሌሎች ሙታን የተለየ ነው፡፡ ሞትን በመግደል ድሩን ሳይኾን የችግሩን ምንጭ ሸረሪቱን አጥፍቶታል፡፡ ኀጢአት፣ ሞት፣ መቃብር እነዚህ ሦስቱ ተያያዥ ነገሮች ናቸው፡፡ ኀጢአት ከሌለ ሞት፣ ሞትም ከሌለ መቃብር አይኖርም፡፡ ሞት ሲሞት ሙታን ተነሡ፤ የሞት ጥላ ሲገፈፍ መቃብራት ተከፈቱ፡፡ በክርስቶስ ሞት ኀጢአት ከሥሯ እንደ ተነቀለች ዛፍ ላታፈራ፣ ላትለመልም ለዘለዓለም ተነቀለች፡፡ ሞትም ሙታንን ለቆ ጠፋ፤ መቃብርም ባዶ ኾኖ ተከፈተ፡፡ ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋ ‹‹ሞተ ዘቦአ ቀዳሚ ውስተ ዓለም በቅንዓተ ሰይጣን አብጠልከ በምጽአቱ ለዋሕድ ወልድከ መድኃኒነ፤ በሰይጣን ተንኮል ከልጅህ መምጣት አስቀድሞ ወደ ዓለም የገባ ሞትን በልጅህ ሰው መኾን አጠፋህ›› እያለች የምታመሰግነው (ሥርዓተ ቅዳሴ)፡፡

ጌታችን በኵረ ትንሣኤ የተባለበት ሁለተኛው ምክንያት የጌታችን ትንሣኤ የመጀመሪያው ሐዲስ ትንሣኤ ስለ ኾነ ነው፡፡ ከእርሱ በፊት ከሙታን የተነሡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በሚበሰብስ ሥጋ ተዘርቶ በማይበሰብስ ሥጋ መነሣት የቻለ ማንም አልነበረም፡፡ ሌሎቹ ሙታን ለዘለዓለም ሞትን ማሸነፍ በሚችል ሞት የተነሡ አልነበሩምና (፪ኛ ነገ. ፲፫፥፳፩)፡፡ ክርስቶስ ከመጣ በኋላ የተነሡት እንደነአልዓዛር ያሉትም ዳግመኛ መሞትና መነሣት አለባቸው፡፡ የጌታችን ትንሣኤ ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ እኛም ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እንደ መላእክት ኾነን እንኖራለን፡፡ በሚፈርስ፣ በሚበሰብስ ሥጋ ተዘርተን (ሞተን)፣ በማይፈርስ፣ በማይበሰብስ ሥጋ እንነሣለን፡፡ የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ነውና፡፡

ጌታችን በኵረ ትንሣኤ የተባለበት ሦስተኛው ምክንያት፣ ትንሣኤው ስለ ዂላችንም ቤዛ የተደረገ ትንሣኤ ስለ ኾነ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ስለ ዂላችን (ለዓለም) የሞተ የለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እስመ ኵሉ ፆሮ ይፀውር፤ ዂሉም የራሱን ሸክም ይሸከማል›› ብሎ እንደ ተናገረው (ገላ. ፮፥፭)፣ አባቶቻችን በራሳቸው ዕዳ ሲሞቱ ምንም ዕዳና በደል የሌለበት ክርስቶስ ግን ለፍጥረት ዂሉ ዕዳ ሊደመስስ በፈቃዱ ሞተ፡፡
ሞቱ ስለ ሁላችን እንደ ኾነ ሁሉ ትንሣኤውም የሁላችን ሕይወት ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚኾነን የአይሁድ ፍርሃት ነው፡፡ አይሁድ ‹‹በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ ማለቱን ሰምተናል፤ ደቀ መዛሙርቱ ሌሊት መጥተው እንዳይሰርቁት፣ ‹ተነሣም› ብለው ለሕዝብ እንዳያስተምሩ ...›› ነበር ያሉት (ማቴ. ፳፯፥፷፪-፷፭)፡፡

ይህ የአይሁድ ፍርሃት የዲያብሎስም ጭንቀት ነው፡፡ ጌታችን ክብርት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ሲለያት ዲያብሎስ ነፍሱን በሲኦል ውጦ፣ ሥጋውን በመቃብር ረግጦ ማስቀረት እንዳልተቻለው ስለ ተረዳ አይሁድን እንዲህ እንዲሉ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ትንሣኤውን ዐይተው ያምኑ ዘንድ ይህን ማለታቸው የጌታ ፈቃድ ነበር፡፡ አምነው ባይጠቀሙበትም የጌታ ትንሣኤ ላመኑትም ላላመኑትም ሕይወት ነውና፡፡ ስለዚህ ነው የጌታችንን ትንሣኤ በኵረ ትንሣኤያችን የምናደርገው፡፡

#ትንሣኤ_ዘጉባኤ

በእሳት ተቃጥለው፣ በአራዊት ተበልተው ወደ ዐመድነትና አፈርነት የተለወጡ ሰዎች፣ በዕለተ ምጽአት ከሞት የሚነሡት እንዴት ነው? እንደ ገና ሰው ኾነው ይፈጠራሉ ማለት ነው?

በመጀመሪያ ካለመኖር ወደ መኖር እንድንመጣ ያደረገን ጥበበ እግዚአብሔር ነው፡፡ ያለዚያማ እንዴት ኾኖ ነው ከአባት የተከፈለው ዘር ከሴት ደም ጋር ተዋሕዶ፣ ብጥብጥ የነበረው ረግቶ፣ የአጥንት ምሰሶ የጅማት ማገር ተሠርቶለት ቅዱስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚኾነው? በእርግጥ እንዲህ ኾኖ የተጀመረው ህልውናችን በሞት ሲቋረጥ እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በመቃብር ውስጥ ቀልጦ ለመቅረት እንጂ ተመልሶ ለመብቀል አልነበረም፡፡ የሰው ልጅ እንደ አዝርዕት ከሞተና ከፈረሰ በኋላ አካል ኖሮት የሚነሣ ነው፡፡ ያለ ዝናም የአዝርዕት ምን ትንሣኤ አላቸው? ያለ ክርስቶስ ደም መፍሰስስ የሰው ልጅ ማን ከሞት ሊያስነሣው ይችላል? የጌታችን ደም ሲፈስ ግን መቃብራት ተከፈቱ፤ ዐለቶች ተሰነጣጠቁ፤ ከሙታን ወገን ብዙዎቹ ተነሡ፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለኵሉእጓለ እመሕያው፤ በውኑ ሰውን ዂሉ ለከንቱ ነገር ፈጥረኸዋልን?›› የሚለው የአባቶቻችን ጥያቄ ምላሽ አገኘ (መዝ. ፹፰፥፵፯)፡፡

ሞት እንደ ገበሬ፣ መቃብር ደግሞ እንደ እርሻ ኾኖ የሰው ልጆች በዚህ ምድር በመበስበስ በመፍረስ እንዘራለን፡፡ እንዲህ ካልኾንን ትንሣኤ የለንም፡፡ በኋላም ተለውጠን በአዲስ ሥጋ እንነሣለን፡፡ ባሕርይ መልአካዊ፣ ባሕርይ ሥጋዊ፣ ባሕርይ እንስሳዊ ለዂላችንም በተፈጥሮ ይሰጡናል፡፡ ስንሞት ባሕርይ እንስሳዊ እና ባሕርይ ሥጋዊ ይለዩናል፡፡ ባሕርይ መልአካዊ ግን በባሕርዩ ሞት ስለ ሌለበት አብሮን ይኖራል፡፡ በምንም ዓይነት ሞት ብንሞትም ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው (፩ኛ ቆሮ. ፲፭፥፴፭-፵፬)፡፡ ትንሣኤ፣ የሰው ልጅ ፍሬ ሠላሳ፣ ስልሳና መቶ ፍሬ አፍርቶ የሚታይበት ወቅት ነው፡፡

ዕፅዋትና አዝርዕት ከፈረሱ፣ ከበሰበሱ በኋላ አንዱ በራሱ፣ ሌላው በጎኑ፣ ሌላው በሥሩ ያፈራል፡፡ ከሥሩ የሚያፈራው የባለ ሠላሳ፣ ከጎኑ የሚያፈራው የባለ ስልሳ፣ ከራሱ የሚያፈራው የባለ መቶ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያናችን ‹‹ዳግም ልደት›› ተብሎ ይጠራል፡፡  የሰው ልጅ ተፈጥሮዎች ሁለት ዓይነት ሲኾኑ፣ እነዚህም ጥንተ ተፍጥሮና ሐዲስ ተፈጥሮ ይባላሉ፡፡ ጥንተ ተፈጥሯችን በአዳም በኩል የተደረገው ተፈጥሯችን ሲኾን፣ ሐዲስ ተፈጥሮ የምንለው ደግሞ በክርስቶስ በኩል የተደረገውን የባሕርያችንን መታደስ ነው፡፡ ልደታችን ግን ሦስት ወገን ነው፡፡ አንደኛው ሥጋዊ፣ ሁለተኛው መንፈሳዊ፣ ሦስተኛው ደግሞ ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው፡፡ ይህም “ልደተ ሙታን እመቃብር” ይባላል፡፡ ይኸውም የሙታን ከመቃብር መወለድ ማለት ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት ማለትም በትንሣኤ ዘጉባኤ ከሞት የምንነሣውም በዚህ መልኩ ነው፡፡

(በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ)

@haymanoteabew
@haymanoteabew
@haymanoteabew
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እም ይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

#ሰሙነ_ትንሣኤ_የትንሣኤ_ሳምንት

ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታት "ሰሙነ ፋሲካ" ወይም "ሰሙነ ትንሣኤ" እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜ አላቸው።

በዓለ ኃምሳ ከትንሣኤ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ድረስ ያሉት የኃምሳ ዕለታት መጠሪያ ነው። በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘችውን ዕረፍተ ነፍስ በምልዓት ትሰብካለች። ዕረፍተ መንግስተ ሰማያትን ታስባለች።

በነዚህ ዕለታት ረቡዕና ዓርብ አይጾምም ፤ ቀኖና ለተነሣሕያን አይሰጥም ፤ በደላችን ሁሉ በትንሣኤው ተሽሯልና በስግደት በድካም የሚኖሩ ሁሉ በዕረፍት ድካም በማያስከትል አምልኮ ያሳልፏታል።

ጌታ የትንሣኤያችን በኩር ነው። እኛም ከተነሣን በኋላ ረኃብ ፣ ጥም ፣ ድካም ፣ ሕማም ፣ ፈተና ፣ ሞት ፣መቃብር የሌለበትን ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን ስንል ነው። ቀኖና የማይሰጠውም በሥጋም ሆነ በነፍስ ከመበደል ጌታ ነጻ ያወጣናል ፤ ሕይወታችን ከበደል ተለይቶ የምንኖርበት ዘመን ይመጣል። በአጠቃላይ ድኅነተ ነፍስ ድኅነተ ሥጋ በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቶናል ፤ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትና የዘላለም ሕይወት ተዘጋጅቶልናል ለማለት ነው።

#የሰሙነ_ትንሣኤ_ሰኞ
የትንሣኤ ማግስት ሰኞ ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ስትሆን "ፀአተ ሲኦል" ወይም "ማዕዶት" ትባላለች።

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባርነት ወደ ነጻነት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣ ከሲኦል ወደ ገነት እንዳሸጋገረን እናስባለን።

ይህች ዕለት ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች አሏት።

#ማዕዶት_ትባላለች
ማዕዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። ታሪኩም ቀድሞ እስራኤላውያን ባሕረ ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስትን ገብተዋል። በዚህም ፈርዖን የዲያቢሎስ ፣ ሠራዊቱ የሠራዊተ ዲያቢሎስ ፣ ግብፅ የሲኦል ፣ ባህረ ኤርትራ የባህረ ሲኦል፣ እስራኤል የምዕመናን ፣ ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር በትረ ሙሴ ደግሞ የመስቀል ምሳሌ ነው። እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት ባህረ ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስት እንደገቡ ፤ ነፍሳትም በክርስቶስ መሪነት ባህረ ሲኦልን ተሻግረው ገነት የመግባታቸው ምሳሌ ነው። በዚህም ማዕዶት ተብላለች።

#ዕለተ_አብርሃም_ማዕዶተ_ለአብርሃም_ትባላለች
አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከነዓን ገብቷል። አንድም አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ቢሄድ መልከጼዲቅ ኅብስተ አኮቴት ጽዋ በረከት ይዞ ተቀብሎታል። ነፍሳትም ባህረ ሲኦልን ተሻግረው ቢሄዱ ኅብስተ አኮቴት ጽዋ በረከት ወልድን የማግኘታቸውና ወደ ቀድሞ የበረከት ርስት የመመለሳቸው ምሳሌ ነው። ስለዚህ ትንቢቱም ምሳሌውም መድረሱን ለማጠየቅ ዕለቷ ማዕዶት ትባላለች።

" ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥እርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው"
፩ጴጥ ፫÷፲፰

@haymanoteabew
@haymanoteabew
@haymanoteabew
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት?

ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ።

ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን።

ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!!

ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እም ይእዜሰ
ኮነ
ፍስሓ ወሰላም

እንኳን ለታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ለቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ የክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ኢትዮጽያዊው_ሊቅ_ቅዱስ_ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ በሚያዝያ ፭ ቀን ፭፻፭ ዓመተ ምሕረት ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) እንዲሁም ከአባቱ ይስሃቅ (አብዩድ) በአክሱም ከተማ በምድረ ኢትዮጵያ ተወለደ፡፡

ያሬድ ማለት ርደት፣ ወሪድ ማለትም መውረድ ማለት ነው፡፡ ሰማያዊውን ጣእመ ዜማ ወደ እኛ የሚያወርድ ነውና፡። ‹‹ዋይ ዜማ !!! ዘሰማዕኩ እመላእክት ቅዱሳን ›› ‹‹ ከሰማይ ከቅዱሳን መላእክት የሚያስደንቅ ዜማ ሰማሁ›› በማለት እንደተናገረ።

ያሬድ ማለት - ንብ ማለት ነው፡፡ ንብ የማትቀስመው መልካም አበባ እንደሌለ ኹሉ ቅዱስ ያሬድም ከቅዱሳት መጻሕፍት - ከብሉይ፣ ከሐዲሳት እና ከሊቃውንት የማይጠቅሰው የለም፡፡ ከንብ የተገኘ ማር ጣፋጭ ከመኾኑም በላይ ሰሙ መብራት ኾኖ ጨለማን በማራቅ ብርሃንን አግዝፎ በማሳየት ልብን ደስ እንደሚያሰኝ ኹሉ የቅዱስ ያሬድም ዜማ ንባቡ ከምሥጢሩ ጋር ተዋህዶ ልቡናን በቅን መንፈስ ከማደሱም በላይ ለምዕመናን ደስታን የሚያበሥር፤ ኃይለ ቃሉም ጨለማ ክኅደትን የሚያርቅ ነው።

ያሬድ ማለት - ምሥጢር ተመልካች ምሥጢርን ገላጭ ማለት ነው፡፡ ምሥጢር ተመልካች መባሉ የመላእክት ምሥጢር የነበረውን ሰማያዊ ዜማ አምልቶ፤ አስፍቶ ተናግሯልና ነው፡፡ ምሥጢር ገላጭ መባሉ ደግሞ ኅቡዕ (ሥውር) የኾነ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን፣ የነቢያትን እና የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶ ስለሚናገር ነው፡፡

ያሬድ ማለት - እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው፡፡ እነዚኽ በስልት በስልት በቤተክርስቲያን ለአገልግሎት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንደሚያሰኙ፤ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ዐደባባይ በቤተክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፣ ሰውና እንሰሳትን ኹሉ ደስ ያሰኛል፡፡

አባቶቻችንም ጥዑመ ልሳን፣ ንሕብ፣ ሊቀ ሊቃውንት፣ የሱራፌል አምሳያ፣ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፣ ካህነ ስብሐት፣ መዘምር ዘበድርሳን፣ ማኅሌታይ፣ ልዑለ ስብከት እያሉ ይጠሩታል::

ያሬድ ሰባት ዓመት ሲሆነዉ አባቱ ስለሞቱበት እናቱ ት/ቤት ለማስገባት ወደ አጎቱ መምህር ጌዲዮን ጋር ወሰደችዉ፡፡አባ ጌድዮንም በአክሱም ቤተ ቀጢን(ቤተ ጉባኤ) መምህር ነበሩ፡፡ ያሬድ በትምህርቱ የሚያሳየዉ ዉጤት ደካማ ስለነበር ከሌሎች ህጻናት ጋር ሊወዳደር አልቻለም፡፡

መምህሩ ጌዴዎን ለተግሣጽ ቢቀጡትም መታገስ ተስኖት ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ወለል ተጓዘ፡፡

ቅዱስ ያሬድ ከዛፍ ስር ተቀምጦ በምን ምክንያት ከጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሲያዝን ሲተክዝ ቆየ፡፡ አንድ ትል የዛፉን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛዉ ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፡፡

ያሬድም የዚህን ትል ተስፋ አለመቁረጥ ትዕግስቱንና ጽናቱን ተመልክቶ " እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረግሁ እንደዚህ ሊሳካልኝ ይችላል" ብሎ ወደ መምህሩ ለመመለስ ወሰነ።

ያሬድ የአጎቱ ምክርና ተግሣጽ ለሕይወቱ የሚጠቅም መሆኑን በመረዳቱ ትምህርቱን በትጋት ቢማርና ቢያጠና ያሰበዉ ደረጃ ለመድረስ እንደሚችል በመገንዘብ ወደ መምህሩ ጌዲዮን ጉባኤ ቤት ተመለሰ፡፡ መምህሩም ተቀብለዉ አስተማሩት፡፡

በአጭር ጊዜ አልገባ ያለዉ ትምህርት ተገልጾለት ትምህርቱን በሚገባ አጠናቀቀ፡፡ በኋላም የብሉይና የሐዲስ መምህር ሆኖ በመምህሩ በጌዲዮን ወንበር ተተካ፡፡

እግዚአብሔርም በቅዱስ ያሬድ መመስገንን በወደደ ጊዜ ቅዱስ ያሬድ ኅዳር 5 ቀን በ527 ዓ.ም በዕለተ ሰኑይ ሦስት አእዋፍ ተልከው የመላእክትን ዜማ ሊያሰተምሩት ወደ ሰማይ ነጥቀው አሰተማሩት በነጋታውም ኅዳር 6 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ወደ ምድር ተመለሰ፡፡

ከዚያም ኾኖ ፊቱን ታቦተ ጽዮን ወዳለችበት ወደ ምሥራቅ አዙሮ፥ እጆቹን ዘርግቶ እንዲህ ብሎ ሰማያዊ ዜማውን ለመጀመሪያ ጊዜ በአኲሱም አደባባይ (ዐውደ ምሕረት) ዘመረ ፡፡

ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ ብሎ በዓራራይ ዜማ አዜመ፡፡ (አርያም፣ጾመ ድጓ)

ይህም ማለት ዓለም ሳይፈጠር ለነበረና ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም ለሚኖር ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው ማለት ነው፡፡ (ኦሪት ዘፀ. 25፥8-10 ፤ 26፥30)

ይህንንም ዜማ ሊቃውንተ አክሱም ተማሩ ቢባሉ ምን ምልክት አይተን ተቀብለን እንማር ቢሉ ከታኅሣሥ 1 ቀን እስከ ታኅሣሥ 7 527 ዓ.ም ሱባኤ እንዲያዝ አጼ ገብረ መስቀል አዘው በሰባተኛው ቀን ታኅሣስ 7 ቀን በ527 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ከጉልላቱ በላይ አምላከ ቅዱሳን በዕለተ አርብ እንደተሰቀለ ሆኖ ታያቸው።

በዚህም ምስክርነት ካህናቱና ሕዝቡ ተቀብለው መማር ጀመሩ ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀን ጀምሮ አገልግሎቷ ሁሉ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ሆነ፡፡

ቅዱስ ያሬድ በግእዝ፣ በዕዝልና በዓራራይ ዜማ ዝማሜ እየደረሰ እያለ ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል ተገኝተዉ ነበር።

በዜማዉ ተመስጠዉ አይን አይኑን እያዩ እንደ እርሱ እዘምማለሁ ብለዉ በያዙት የብረት ዘንግ ሳያዉቁት ቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ቸከሉት፤ ሁለቱም በተመስጦ ስለነበሩ የሆነዉን ነገር አላስተዋሉትም ነበር፤ ዜማዉ አብቅቶ ሁለቱም ከተመስጧቸዉ ሲነቁ የቅዱስ ያሬድ እግር ዘንጋቸዉ ተሰክቶ ብዙ ደም ፈሶት ነበር፤ ንጉሡም ደንግጠዉ እጅግም አዝነዉ
‹‹ደምህን አፍስሻለሁና የምትፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር ጠይቀኝ እሰጠሃለሁ››ሲሉ ቃል ገቡለት፡፡

ቅዱስ ያሬድም ‹‹ይምለምነዉ አንድ ነገር አለ እርሱን ፈጽምልኝ›› አላቸዉ ‹‹የፈለከዉን ጠይቅ ፈቅጄልሃለሁ›› አሉት

እርሱም‹‹እስካሁን እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መሰረት በዚህ ከተማ ከእርሰዎ ጋር ቆይቻለሁ ብዙ ደቀ መዛሙርትም ተክቼያለሁ ከእንግዲህ በኋላ የቀረኝን ዘመን በጸሎትና በብሕትዉና መኖር እንድችል ከከተማዉ ራቅ ወዳለ ቦታ ሔጄ ፈጣሪየን ማገልገል እፈልጋለሁ› ብሎ የንጉሡን ፈቃድ ጠየቀ፡፡

አፄ ገብረ መስቀልም የቅዱስ ያሬድን ቃል ሰማተዉ በገቡለት ቃል መሰረት ፈቀዱለት።

ከዚያም ጉዞዉን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ተራሮች አደረገ፤ በዚያም አሁን በስሙ የታነጸዉ ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ በምናኔ ተወስኖ ፈጣሪዉን በብሕትዉና እያገለገለ ኖረ፤ ደብረ ሐዊ ከተባለዉ ተራራ ላይ በምናኔ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በአንዱ ግንቦት 11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰወረ፡፡


@haymanoteabew
@haymanoteabew
ስንት ዓመት ተማርክ?

አሁን የምትሰራው ስራ ለሥጋዊ ኑሮ የሚሆን የሚጠቅም ነው በዚች ምድር ላይ ሳለህ እንዳይርብህ እንዳይጠማህ እንዳይበርድህ ኑሮህን ለማመቻቸት ትወጣለህ ትወርዳለህ ከሕፃንነትህ ጀምሮ ትማራለህ ሦስት ዓመት ጊዜ ወስደህ መዋእለ ሕፃናት ተምረሃል አስራ ሁለት ዓመት ጊዜ ሰጥተህ 12 ክፍል ጨርሰሃል ከአምስት ዓመት በላይ ጊዜ ሰጥተህ በድግሪ በማስተር ተመርቀሃል በአጠቃላይ የሥጋ ሥራ ለመያዝ ከሃያ ዓመት በላይ ተምረሃል እንደዚህም ተምረህ ስራ አጥተህ በስራ ፍለጋ ደክመሃል ወንድሜ ሆይ አሁን ከ20 ዓመት በላይ የተማርከው ትምህርት ለስንት ዓመት ያሰራሀል ?


ጡረታ እስክትወጣ ነው ከዛ በኋላ የተማርከው ትምህርት አያገለግልህም ከ20 ዓመት በላይ ስትማር የፈጀኸውን ጊዜ አስብ ጭንቀቱን ፣ ድካሙን ፣ እንቅልፍ ማጣቱን ከትምህርት ቤት ለመድረስ የእግር ጉዞውን ሁሉ አትርሳ ያ ሁሉ ደክመህ የተማርከው ስትሞት አይጠቅምህም ሥጋህ መቃብር ሲገባ ምድራዊ እውቀትህ አብሮ ይቀበራል በሕይወት እያለህ ጡረታ የምትወጣው መስራት አችልም ተብለህ ነው ከ20 ዓመት በላይ በተማርከው ትምህርት ብሰራበት 30 ዓመት ቢሆን ነው ያም እድሜ ከታደለህ ነው። ወንድሜ ሆይ እስቲ ልጠይቅህ ለሥጋህ ስራ ለመስራት ከ20 ዓመት በላይ ተምረሃል ለነፍስህ ስንት ዓመት ተማርክ??????


ለነፍስህ የተማርከው ትምህርት ጡረታ የለውም በሥጋ የተማርከው የመንግሥት ስራ ያስይዝሃል በነፍስ የተማርከው የእግዚአብሔር ስራ ያስይዝሃል የነፍስ ትምህርት ቃለ እግዚአብሔር ነው የእግዚአብሔርን ቃል በወር ስንት ሰዓት ተምረሃል? በዓመት ስንት ቀን ይሆናል የተማርክበት ጊዜ እስቲ ደምረው? በአጠቃላይ የተማርክበት ጊዜ እስክትሞትስ ስንት ዓመት ይሆናል? መቼም የሥጋውን የትምህርት ጊዜ አያክልም በነፍስ የተማርከው ትምህርት ስንት ዓመት እንደሚያሰራህ ታውቃለህ ? ቁጥር የማይደርስበት ጊዜ ነው ዘመናት አልፈውም ትሰራበታለህ ለዘላለም ጡረታ አያወጣህም:: አንተ ግን ይሄን ረስተሃል ቀኑን ሙሉ ለሥጋህ ትሮጣለህ ለነፍስህ የምትማርበት ጌዜ አጥተሃል በሚያልፈው ነገር ራስህን ቢዚ አርገሃል::


ሁለት ሰዓት ቁጭ ብለህ ፊልም ታያለህ 30 ደቂቃ ቁጭ ብለህ ወንጌል መማር ይሰለችሃል:: ሁለት ሰአት ቁመህ እያጨበጨብክ ኳስ ትደግፋለህ አንድ ሰዓት ተኩል ቁመህ ቅዳሴ ማስቀደስ አቅቶህ በዕለተ ሰነበት ተኝተህ ታረፍዳለህ ልብ ወለድ የሆኑ መጻሕፍትን ታነባለህ የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍን ለማንበብ ይሰለችሃል ለዘፈን የተከፈተው አፍህ ለምስጋና ይዘጋል ለሀሜት የሚፈጥነው አፍህ ለጸሎት ይዘገያል ለስፓርት የጠነከረው ጉልበትህ ለስግደት ይዝላል ለስርቆት የሚላከው እጅህ ለምጽዋት አይታዘዝም ወደ ጭፈራ ቤት የሚገሰግሰው እግርህ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይተሳሰራል
ሀሜት የሚሰመው ጀሮህ ወንጌል ለመስማት ይደነቁራል ጫት የለመደው አፍህ ሥጋውን እና ደሙን ረስቶአል አልኮል የለመደው አፍህ ፀበሉን ተፀይፎታል ቂም የሚቋጥረው ልብህ ፍቅርን ረስቷል ስታጣ እግዚአብሔርን ትቀርበዋለህ ስታገኝ ግን ትርቀዋለህ ስትጨነቅ አምላክህ ትጠረዋለህ ስትደሰት ትረሳዋለህ

ወንድሜ ሆይ በሕይወትህ አትቀልድበት ካንተ በፊት የነበሩት
ምሁሩ
ሊቁ
ሳይቲስቱ
ዶክተሩ
እንጂነሩ
ንጉሡ
ጳጰሱ
ቄሱ
ገበሬው
አርቲስቱ


ታዋቂው አዋቂው ሁሉ የት አሉ? መቃብር ውስጥ አይደሉምን ? ይህንን አስበህ ከፈጣሪህ ጋር የሚየገናኝህን ስራ ስራ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂደህ ዘወትር ወንጌል ተማር ለማስቀደስ ትጋ ለንስሐ ተዘጋጅ ቅድሚያ ለነፍስህ ሁሉን ነገር አድርግ አንደበት ለጸሎት ይትጋ እጅህ ለምጽዋት ይዘርጋ ልብህ ለምሕረት ይነሳሳ ሥጋውን እና ደሙን ለመቀበል ወስን፡፡

@haymanoteabew
@haymanoteabew
@haymanoteabew
"መጽሐፍ ቅዱስ"

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም የአያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀመረ፡፡
አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደ ወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው”
ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው
ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ ! እንዲሁ ነው የምደክመው እንጂ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በእጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡
ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እንደርሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን
አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

@haymanoteabew
@haymanoteabew

መልካም ምሽት ይሁንላቹ
#ሦስቱ_ባልንጀሮች........


#ለሌሎች_ያካፍሉ


👉ሦስት ጓደኞች የነበሩት አንድ ሰው ነበረ ይህ ሰው ለሦስቱም ጓደኞቹ ያለው ፍቅር የተለየ ነበር
አንደኛውን ጓደኛውን ከራሱ አብልጦ ይወደው ነበር
ሁሌም እርሱን ያከብረዋል ይንከባከበዋልም::

ሁለተኛውን ጓደኛውን ደግሞ እንደ እራሱ አድርጎ ይወደዋል::

👉ሦስተኛውን ከእራሱ አሳንሶ ዝቅ አድርጎ ይወደዋል ።ሊጋብዘው ሲፈልግ እንኳን ከእነዚያ ከሁለቱ የተረፈውን ነበር::
👇👇👇👇👇👇👇

ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሦስት ጓደኛ የነበረው ሰው ወደ ንጉሥ እንድመጣ ከንጉሡ አስቸኳይ ጥሪ ይደርሰዋል ይሄ ሰው ደግሞ በጊዜው ምንም ነገር የለውም ነበር፤ እናም ወደ ንጉሡ ዘንድ ሲቀርብ ምን ለብሶ እንደሚቀርብ ተጨነቀ እራቁቱን መቅረብ ስለማይችል ማልቀስ ጀመረ::

👉ከዚያም አንድ ሃሳብ መጣለት
መቼም ጓደኛ የሚለካው በመከራ ሰዓት ነውና """እንዲህ
ከማለቅስ ከራሴ አስበልጬ ከምወደው ጓደኛዬ ለምን አልሄድም ከዚያም እርሱ ጥሩና ዋጋው ውድ የሆነ ልብስ ይሰጠኛል ያነንም ለብሸ ወደ ንጉሡ እሄዳለሁ""ብሎ ከእራሱ አስበልጦ ወደ ሚወደው ጓደኛው ቤት ሄዶ የደረሰበትን ችግር ነገረው "እባክህን ንጉሥ አስጠርቶኛልና ወደ ንጉሡ ስሄድ የምለብሰው ልብስ ስጠኝ"
አለው:: ጓደኛው ግን ገና ሲመጣ ሲያየው ፊቱን አዞረበት "ምንም ልረዳህ አልችልም " አለው::

ያኔም ይህ ከእራሱ አብልጦ የሚወደው ጓደኛው ባዶ እጁን
እንደሰደደው ባየ ጊዜ እያዘነ
"እስኪ እንደ እራሴ አድርጌ ወደምወደው ጓደኛዬ ቤት ልሂድ እርሱ ይሰጠኛል" ብሎ ተማምኖ ሄደና "" እባክህ ንጉሥ በአስቸኳይ ወደ እርሱ እንድሄድ ና ስላለኝ ከነጉሡ ፊት የምለብሰው ስጠኝ"አለው::
እንደ እራሱ አድርጎ ይወደው የነበረው ጓደኛውም አዝኖ አልቅሶ
ምንም ሳይሰጠው ሸኝቶ ሰደደው::


አሉኝ ያላቸው የተማመነባቸው የተመካባቸው እነዚህ ከእራሱ አስበልጦ የሚወደው እና እንደ እራሱ አድርጎ የሚወደው ሁለት ጓደኞቹ ምንም እንዳረዱት አወቀ
ከዚያም ያ ምንም የለውም ብሎ በጣም ንቆ አቃሎ ከእርሱ በጣም ዝቅ አድርጎ ወደሚወደው ጓደኛው ቤት ሄደ ይህ ጓደኛው ግን እንደነዚያ እንደሁለቱ ጓደኞቹ አልነበረም:: ገና በርቀት ሲያየው እሮጦ ተቀበለው ስለሆነው ነገርም ጠየቀው:: ባዕለ ጸጋ የነበረው ሰውም ለዚህ ከእርሱ ዝቅ አድርጎ ለሚወደው ጓደኛው ችግሩን ነገረው::
.
""አይዞህ አትዘን እኔ ጥሩና ዋጋው ውድ የሆነ ልብስ አለኝ እርሱን እሰጥሃለሁ
ደግሞ በንጉሡ ዘንድ እኔ # ወዳጅ ነኝ::

እናም ወታደሮቹ እንዳያሰቃዩህ እኔ በነጻነት እንድታልፍ በንጉሡም ዘንድ መወደድን እንድታገኝ ለንጉሡ እነግርልሃለሁ"አለው::
እና ይናቅ ዝቅ ተብሎም ይወደድ የነበረ ጓደኛው ይሄንን መልካም
ሥራ ሠራለት:: ያ ባዕለ ጸጋ የነበረ ሰውም ሁለቱ ጓደኞቹና ይህ ጓደኛው ያደረገውን ባየ ጊዜ አለቀሰ::



፠ባለ ጸጋ የተባለ = # የሰው ልጅ ነው::

፠ከእራሱ አብልጦ የሚወደው = ገንዘብ ነው::

፠እንደ እራሱ አድርጎ የሚወደው = #ባል # ሚስት # ቤተሰብን ነው::

፠ዝቅ ናቅ አድርጎ የሚወደውም = # ነዳያንን ምንም የሌላቸው
ሰዎችን ነው::

፠ንጉሥ የተባለም= # እግዚአብሔር ነው:: ባለ ጸጋ የተባለ ሰው በሞት በተጠራ ጊዜ ምንም የሌለው ድሃ
ይሆናል። በእግዚአብሔር ፊትም ባዶ ሆኖ ይቀርባል።

👉ያኔም ከእራሱ አስበልጦ የሚወደው ጓደኛ የተባለ ገንዘብ በዚህ
ዓለም እንጂ በዛኛው ዓለም ምንም የማይጠቅም ሆኖ ከእነ ነዌ ጋር ያሠልፋል።

"በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።"(ማር. 10:24)


፠እንደ እራሳችን አድርገን የምንወዳቼው ባል ሚስት ልጅ ቤተሰብም በሰማይ ስላለው ሕይወት ምንም የማይጠቅሙ
ይሆናሉ:: ልክ አዝኖ አልቅሶ እንደሸኜው ቤተሰብም እስከ መቃብር ድረስ አዝነው አልቅሰው ይሸኙናል እንጂ ከዛ በኋላ ምንም አያደርጉልንም::

👉ከእራሱ ዝቅ አድርጎ የሚወደው ጓደኛ የተባለ ድሃ ግን በዚህ አለም እርሱ ድሃ እንደነበረ አይቀርም በዚያኛው አለም በዕለ ጸጋ ይሆናል:: እኛ እንደ ነዌ ካልጨከን እጃችን ከዘረጋንለት እርሱ በዛኛው አለም በጽድቅ ይቀበለናል::
እርሱ የንጉሡ የእግዚአብሔር ወዳጅ ነውና መንግሥተ ሰማይን
እንድንወርስ ያደርገናል::
:
👉የእኛን ፍርፋሪ ለማገኜት ከእኛ በር ላይ ይቀመጡ የነበሩ ድሆች በዛኛው ዓለም እንደ አላአዛር በአብርሃም እቅፍ ሆነው
እኛ ደግሞ በዚህ ዓለም ሳለን እያለን ሳንሰጣቸው ቀርተን በዛኛው ዓለም ነዌን ሆነንን ሲዖል ገብተን እንዳያስተዛዝበን
ድሃዎችን ልንረዳ ይገባል::

ያለዚያ እኛ ነዳያን ቤታችን እንዳይገቡ በግንብ እንዳጠርንው ሁሉ እነርሱም
""ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ # በእኛና # በእናንተ #መካከል_ታላቅ_ገደል_ተደርጎአል """ይሉናል::
(የሉቃስ ወንጌል 16:26)

#ተወዳጆች ሆይ
የሚጠቅመንና የሚረባንን ለሰዎች መልካም በማድረግ
ገንዘባችነን በድሃ ሆድ ውስጥ እናስቀምጥ:: እነርሱ ታማኞች ስለሆኑ በችግራችን ጊዜ ይሰጡናልና::

👉 መልካም የሆነውንም ያለመመካት እንሥራ የታዘዝነውን እያደረግን
" የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል ።"እያልን
(የሉቃስ ወንጌል 17፥10)

👉በኃላፊው ገንዘብ ሰማያዊ ወዳጅ እናብጅበት:: እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 16፥9
.
# ምንጭ የአባቶቻችን አንደምታ ወንጌል

ክብር ለአባቶቻችን በቃልና በሕይዎት ላስተማሩን

@haymanoteabew
@haymanoteabew
#ደብረ_ታቦር



ነሐሴ13 በዚች ቀን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።

ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።

ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።

በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።

ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።

የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት።

ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።

ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።

ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።

ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።

እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ።

ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

@haymanoteabew
@haymanoteabew
ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡


#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
….” ይላሉ
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡

@haymanoteabew
@haymanoteabew
ሰላም ስላም ውድ የትምህርተ ሐይማኖት ቻናል ተከታታዪች በተለያየ ችግር ምክንያት ጠፍቼ ነበር አሁን በአዲስ መልክ መጥቻለሁ በቅርብ ቀን መንፈሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ እውቀታችንን የሚያሳድጉ ነገሮች አዘጋጅቻለሁ እናንተም ባለን ጊዜ 5 ደቂቃም ቢሆን ከልብ ከሆነ ብዙ እናነባለን መልካም ነገሮች ላይ እንድናተኩር የሰራዊት ጌታ ይርዳን ስላማችሁ ይብዛ እግዜር ያክብርልሽ መልካም ነገር ነው ብላቹ ካሰባቹ ለምትፈልጉት ሰው ሊንኩል ላኩላቸው ስናይ ጊዜ ተመኝውላቺ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@haymanoteabew
@haymanoteabew
@haymanoteabew

👆👆👆👆👆👆👆


ክፉ ሰው ክፋትን ለመስራት ደፍሮ ሲሄድ መልካም ሰው በጎ ነገር ለማድረግ ፈሪ ሆነ።
አስታውስ

ደካማነትህን አስታውስ፦ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።

የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፦ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።

የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፦ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል።

ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።

በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፦ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም “በዋጋ ተገዝታችኋልና” 1ኛ ቆሮ. 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፦ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ ኃይል ታገኛለሕና።

በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፦ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፦ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።

ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፦ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።

የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፦ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።

የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፦ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።

@haymanoteabew
2025/10/22 11:02:48
Back to Top
HTML Embed Code: