እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! #መልካም_በአል!
ገሀድ, ከተራ
ገሀድ ምንድን ነው?
ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ ይምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሀድ ጾም ነው ማለት ነው!
ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
• በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመኼዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ምሳሌ ሲኾን ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ሲኾን መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
• በባሕረ ጥምቀቱ ላይ በሚንሳፈፍ ነገር መብራት መደረጉ በርግብ አምሳል ለወረደው መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። " ኢያሱ 3:3
@haymanoteabew

ሰሙነ ሕማማት
ዘረቡዕ🗣👥
1. ምክረ አይሁድ
ጌታ ሆይ እውርን በማብራትዕ ተማከሩብህ፣ ጎባጣውን በማቅናትዕ ቀኑብህ፣ አምላካችን ሆይ ፴፰ዓመት ያልጋ ቁራኛ የሆነን ሰው በማስነሳትዕ ሰንበትን ሻሪ ብለው ተማከሩብዕ፣ ክርስቶስ ሆይ ስለ መልካም ሥራ ክፋትን አደቡብዕ፣ ፍቅርን ስትሰብካቸው ክፋትን ያደርጉ ዘንድ ልባቸውን አፈጠኑ፣ አቤቱ ክርስቶስ ሆይ በፍቅር አቅፈዕ ከሐዋሪያት ቁጥር የከተትከው ስለ ፍቅረ ነዋይ ብሎ ይለውጥዕ ዘንድ እግሩ ቸኮለችበት፣ ጌታ ሆይ ይሰቅሉዕ ዘንድ፣ ይገርፉዕ ዘንድ እየተቻኮሎ መጡ አቤቱ ለዚህ ትዕትናዕ አንክሮ ይገባል።
ይሁዳ ሆይ እኔስ አንተን እጠይቃለው ስለምን ክፋትን አሰብክ? መልስልኝ አንተ ታምራቱን እያየዕ ከአንደበቱ የሚወጣውን ቃል ለ ፫ ዓመት ተመግበዕ ፍሬ ክፋት ስለምን ሆነብዕ፣ እንዴትስ ልብህ ደነደነ፣ አቤቱ ይሁዳ ሆይ ያንተ ድፍረት እንዴት ያለች ናት፣ ተማክረህ መተህ እንኳን የጌታን ፊት ስታይ አታፍርም? ምን አይነት የልብ መደንደን ነው፣ ቅዱሳን መላዕክት ሊያዩት የማይቻላቸውን ተማክረህ አሳልፈዕ መተህ ከፊቱ አንዳች መሆኑን እንዴት ቻልከው፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ባየው ጊዜ በአፍረት ከደጅ ወቶ እንባውን ያነባለትን ጌታ እንዴት በድፍረት አይን ተመለከትከው።
ጌታ ሆይ አቤቱ የይሁዳ ድፍረት በእኛም እንዳይሆን አድለን።
2. የመልካም መዓዛ ቀን
ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን በዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረች ማርያም እንተ እፍረት /ባለ ሽቶዋ ማርያም/ የአልባጥሮስ ሽቶ አምጥታ በራሱ ላይ በማፍሰሷ የመልላም መዓዛ ቀን ተብሎ ይጠራል።
ተወዳጆች ይህ እንዴት አይደንቅ፣ እንዴትስ አይገርም ይሁዳ በክርስቶስ መዓዛ መኖርን ሲጠላ የክርስቶስን መዓዛ ልትቀምስ፣ ውድ የሆነ ሽቱ ይዛ መጣሽ፣ ይሁዳ ከጌታ ጋር ያከማቸውን ፍቅር ባለሽተዋ ማርያም ትቀይረው ዘንድ መጣች፣ ይሁዳ ክርፋቱ ናፍቆታልና ከማዕዛ ክርስቶስ ሲወጣ ማርያም እንተ እፍረትን ሊለውጥ ተቻኮለ፣ የዓለም አጢያት ስልችት ብሏት ወደ ጌታ ማርያም እንተ እፍረት ስትኳትን ይሁዳ በዓለም ፍቅር ተነደፈ፣ ይቺም ማርያም መፅሐፍም እንደሚለው በዝሙት ዘመኗን ሙሉ ስትገፋ ብሎ ይገልፃል።
ግን ወንድሞች ይቺ ሴት ያላትን ሁሉ ብር አውጥታ ውድ የተባለ ሽቶ ገዝታ ስትመጣ ይሁዳ ደግሞ ለ30 ብር ያስገምተው ነበር። ግሩም ነው ከክርስቶስን እርቃ ያለችው ማርያም እንተ እፍረት ውድ ለሆነ ክርስቶስ ውድ የሆነ መዓዛው ያማረ ሽቱ ስታዘጋጅ ይሁዳ እርካሽ በሆነ ብር ሊሸጥ ልቡ አሰበ፣ ይቺ ማርያም ውድ በሆነ ዋጋ ክርስቶስን ልትገዛ ስትወጣ ይሁዳ በረከሰ ብር ይሸጠው ዘንድ ገበያ ወጣ፣ ጌታን በሰላሳ ብር የሚገዛ እያለ ሲለፍፍ ይቺ ማርያማ እባክ እኔ የያዝኩት ብዙ ብር ነው ግን ቢሆንም ስለምፈልገው በብዙው ልግዛህ ብላው ክርስቶስን ሸጠላት እሷም አጢያቷን ሰጠችው ግሩም ነው።
ፍቅረ ክርስቶስን ላወቀበት ገንዘቡ ማዳኛ ነው። ለይሁዳ አይነቱ ደግሞ መጥፊያ ነው።
አቤቱ ጌታ ሆይ ብዙ አጢያት ያለባት ማርያም እንተ እፍረት ብዙ በመሻቷ በብዙ የማርካት ነህና የእኛንም ክፋት ይቅር ትል ዘንድ፣ እንደ ማርያም እንተ እፍረት ልባችንን ታነፃ ዘንድ ፍቃድህ ይሁን አሜን!!
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ጻማ ወድካም
አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር እስከ ትንሣኤሁ በፍሥሐ ወበ ሰላም አሜን!

💠አይለፉት ይጠቅሞታል🩸 ##በቤተክርስቲያን
1 👉 እግዚአብሔር ስራውን ሰርቶ በ 7ኛው ቀን ፈፅሟል'
2 👉7ቱ ሊቃነ መላእክት የሚባሉት
1 ቅዱስ ሚካኤል
2 ቅዱስ ገብርኤል
3 ቅዱስ ኡራኤል
4 ቅዱስ እራጉኤል
5 ቅዱስ እሩፍኤል
6 ቅዱስ ፍኑኤል
7ቅዱስ ሳቁኤል
3 👉 7ቱ ኪዳናት የሚባሉት
1 ኪዳነ አዳም
2ኪዳነ ኖህ
3 ኪዳነ መልከ ፀድቅ
4 ኪዳነ አብረሀም
5ኪዳነ ሙሴ
6ኪዳነ ዳዊት
7ኪዳነ ምህረት ናቸው
4👉 7ቱ አፆማት የሚባሉት
1 የአብይ ፆም
2 የሀዋርያት ፆም
3 የፍልሰታ ፆም
4 ፆመ ነብያት
5 ፆመ ገሀድ
6 ፆመ ነነዎይ
7 ፆመ ድህነት ።ናቸው
5 👉7ቱ የፀሎት ጊዜያት
1 ነገ ወይምጧት ወይም 12ሰአት
2 ሰለስቱ ሰአት ወይም ጧት 3ሰአት
3 6 ሰአት ወይም እኩለቀን
4 ከሰአት ወይም ከቀኑ 9 ሰአት
5 ሰርክ ወይም ከምሽቱ 11ሰአት
6 ንዋም ወይም ከምሽቱ 3 ሰአት
7 መንፈቀ ሌሊት ወይም ከሌሊቱ 6ሰአት
6👉7ቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት
1ሚስጥረ ጥምቀት
2ሚስጥረ ሜሮን
3ሚስጥረ ቁርባን
4ሚስጥረ ክህነት
5ሚስጥረ ተክሊል
6ሚስጥረ ንሰሀ
7ሚስጥረ ቀንድል ናቸው
7👉7ቱ ሰማያት የሚባሉት
1 ድህረ አርያ /ከሰማያት ሰማያት
2 መንበረ መንግስት /መንበረ ብረሀን መንበረ ፀባዎት መንበረ ስበሀት
3 ሰማይ ውድድ /መንበረ መንግስት የተዘረጋበት
4 እየሩሳለም ሰማያዊት (መንግስተ ሰማያት)
5 ኢዮር
6 እራማ
7 ኤረር /የመላእክት ከተሞች ናቸው
8👉7ቱ አባቶች የሚባሉት
1የሰማይና የምድርም አባት ልኡል እግዚአብሔር
2 የንሰሀ አባት/የነፍስ አባት
3 ወላጅ አባት
4 የክርስትና አባት
5 የጡት አባትማለትም /ያልወለደውን እንደልጅ የሚያሳድግ
6 የስልጣን አባት /የአገር መሪ
7 የቀለም አባት በመንፈሳዊይም/ ሆነ በአለማዊ የሚያስተምር ናቸው
9👉7ቱ እኔ ነኝ
1 የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ_ ዮሐንስ 6÷35
2 እኔ የአለም ብረሀን ነኝ____ ዮሐንስ 8÷12
3 በሩ እኔነኝ___ ዮሐንስ 10÷ 9
4 መልካም እረኛ እኔነኝ_ ዮሐንስ 10÷11
5 የትንሳኤ ህይወት እኔ ነኝ____ ዮሐንስ 11÷25
6 እኔ መንገድ እውነት ህይወት ነኝ_ ዮሐንስ 14÷ 6
7 እውነት የህይወት ግንድ እኔነኝ ዮሐንስ 15÷1
10👉7ቱ ጌታችን በመስቀል ላይ የተናገራቸው
1 አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ማቴ 27÷46
2 አባቶይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው_ ሉቃ 23÷34
3 እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ። _ሉቃ 23÷43
4 አንች ሴት እነሆት ልጅሽ እነሆት እናትህ_ ዮሐንስ 19÷26--27
5 ተጠማሁ____ ዮሐንስ 19÷30
6 አባቶይ ነፍሴን በእጅህ ስጥቻለሁ____ ሉቃ 23÷46 ና
7 ተፈፀሙ _ዮንሐስ 19÷30
11👉7ቱ የክርስቶስ ማንነት የሚመሰክሩ
1። የባህሪ አባት ምስክርነት ዮሐ 5=34÷37 8÷18
2 እራሱ ወልድ የክርስቶስ ምስክርነት_ ዮሐ 8 ~18~58
3 የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት____ ዮሐ 15፦ 26 ÷16 ÷12
4 የሰራተኞቹ ምስክርነት____ ዮሐ 5÷36--10-- 25
5 የመፅሀፍ ቅዱስ ምስክርነት____ ዮሐ 5÷39 ~46
6 የመጥምቁ ዮሀንስ ምስክርነት_ ዮሐ 1 ÷7--5--33
7 የተማሪዎቹ ምስክርነት ዮሐ 15÷27~ 19~35ናቸው
12 👉7ቱተአምራት ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ
1 ፀሀይ ጨለመ
2 ጨረቃ ደም ለበሰ
3 ከዋከብት እረገፋ
4 አለቶች ተሰነጣጠቁ
5 መቃብሮች ተከፈቱ
6 ሙታን ተነሱ
7 የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ