Forwarded from ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
የመንግሥት ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ጉዳይ እንዳይዘግቡ መከልከላቸው ተሰማ።
ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተቃጣውን የመፈንቅለ ቅዱስ ሲኖዶስ ሙከራ እንዳይዘግቡ የመንግሥት ሚዲያዎች መመከልከላቸው ተሰምቷል።
አዲስ ማለዳ ደርሶኛል ብሎ ባወጣው መረጃ መሠረት ከመንግሥት ኃላፊዎች በመጣ ትእዛዝ ምክንያት የተከሰተውን ድርጊትም ሆነ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን እንዳይዘግቡ ሚዲያዎቹ መከልከላቸውን ገልጿል። ይህንንም ከሠራተኞቹም መገንዘብ መቻሉን አስረድቷል።
የመንግሥት ሚዲያዎች በሆኑት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና የዋልታ ሚዲያ ላይ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጠረውን ዐቢይ ጉዳይ ባለመዘገባቸው በምእመናን ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል።
የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ኢብኮ፣ ፋና እና ዋልታ ሚዲያዎች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም።
ምንጭ
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል©
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

እንዴት ሰነበታቹ ተወዳጆች ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሁላችንም ሼር እና የፕሮፍይል ላይ በማድረግ አንድነታችንን እናሳይ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏በማርያም ልለምናቹ ቸል እንዳትሉት
እኔ ጥቁር እለብሳለሁ እናተስ
የነነዌ ጾም 3ቱን ቀን ጥቁር በመልበስ ለቤተክርስታናችን እና ለአባቶቻችን ድጋፍ እናሳይ
ለ10 ሰው እናጋራው ለራሳችን ለህሊናችን ስንል።

መንግስት በ48 ስዓት ውስጥ ህግ ካላስከበረ ሰልፉ እንደሚደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳወቀ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ::
#Ethiopia | በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡
በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡
በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡
ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡
እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡

ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡
ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡
ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡
በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡
በመግለጫውም፡-
፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡
፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡
በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡
ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡

መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡
መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡
ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ሁላችሁም ለምታውቋቸው ሁሉ VPN እንዲያወርዱ ንገሯቸው። መልእክቱን አዳርሱት። ይህንን ካላደረግን መረጃ መለዋወጥ አንችልም።
https://www.tg-me.com/onesinod
https://www.tg-me.com/onesinod
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ!
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ
ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግእያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን”
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት
በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡
በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤ በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡
በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤
ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም
የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡
በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖት ተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና
በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ፍጹም ሰላማዊ ና ሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ጋር የደረስንበትን ውጤት በየጊዜው የምናሳውቃችሁ ስለሆነ እንደዚህ ቀደሙ ፍፁም በሆነ መንፈሳዊ ጨዋነት የቅዱስ ሲኖዶስን መልእክት እንድትጠባበቁ፤ አሁንም ቢሆን ያለመዘናጋት ቤተክርስቲያናችሁን በጥብቅ ሁኔታ እንድትጠብቁ እና ቤተክርስቲያናችሁ ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሁሉ በተዋረድ ላለው መዋቅራችሁ እንድታሳውቁ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሰበር ዜና
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውምሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።
በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ክርስቶስ የሚወደው ደቀመዝሙር የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል
የፀሐፊው ስም -ዮሐንስ
የተወለደበት ቀን -በ፩ኛው ክፍለ ዘመን በ፲ኛው ዓመት
የተወለደበት ቦታ- ቤተሳይዳ
ሥራው- ወንጌል ሰባኪ ፀሐፊም
ያረፈበት ቀን -ሞትን አልቀመሰም
(ተነጥቋል)
ንግሥ ጥር ፬
#መታወቂያው
የሚከበረው በመላው የክርስትና እምነት ተከታይ
የጻፈው ወንጌል- ፳፩ ምዕራፍ
በተጨማሪ የፃፋቸው የዮሐንስ ራእይ
ታዐምረ ኢየሱስ
#ዮሐንስም ረቂቅና
ጥልቅ የሆነውን ትምህርት ያስተምር ነበር። እነዚህም:
"እግዚአብሔር ፍቅር ነው"
"እግዚአብሔር ብርሃን ነው"
"እግዚአብሔር ሕይወት ነው"
🙏🙏 🙏🙏🙏🙏
@haymanoteabew
ውብ ምሽት ይሁንላቹ
የፀሐፊው ስም -ዮሐንስ
የተወለደበት ቀን -በ፩ኛው ክፍለ ዘመን በ፲ኛው ዓመት
የተወለደበት ቦታ- ቤተሳይዳ
ሥራው- ወንጌል ሰባኪ ፀሐፊም
ያረፈበት ቀን -ሞትን አልቀመሰም
(ተነጥቋል)
ንግሥ ጥር ፬
#መታወቂያው
የሚከበረው በመላው የክርስትና እምነት ተከታይ
የጻፈው ወንጌል- ፳፩ ምዕራፍ
በተጨማሪ የፃፋቸው የዮሐንስ ራእይ
ታዐምረ ኢየሱስ
#ዮሐንስም ረቂቅና
ጥልቅ የሆነውን ትምህርት ያስተምር ነበር። እነዚህም:
"እግዚአብሔር ፍቅር ነው"
"እግዚአብሔር ብርሃን ነው"
"እግዚአብሔር ሕይወት ነው"
🙏🙏 🙏🙏🙏🙏
@haymanoteabew
ውብ ምሽት ይሁንላቹ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ተዝካረ_ስቅለቱ_ለመድኃኔዓለም
ጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት መጋቢት 27 ቀን አምላክ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ለዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠው መጋቢት 27 ቀን በ33 ዓ.ም ነው፡፡ ይህም ሐሙስ የሐዋርያቱን እግር አጥቦ ራት ከበሉ በኋላ በአምስት ሰዓት ስለራሱ በጌቴሴማኒ ጸለየ፤ ከዚህም በኋላ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በአይሁድ እጅ ተያዘ፡፡ አይሁድም ልብሱን ገፈው አስረው እያዳፉና እየገፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሐና ወሰዱት፡፡ ሊቀ ካህናቱ ሐና ምን እያልክ ታስተምራለህ ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲጠይቀው በስውር የተናገርኩት የለም የሰሙትን ጠይቅ አለው፡፡ አንዱ ጭፍራ (በወንጌል አንደምታ መጻጉዕ ተብሎ ተጠቅሷል)) ‹‹ሊቀ ካህናቱን እንዲህ ትመልስለታለህ?›› ብሎ የጌታን ፊት በጥፊ መታው፤ ጌታም ‹‹ክፉ ከተናገርኩ መስክርብኝ እንጂ እንዴት በዳኛ ፊት ትመታኛለህ?›› አለው፤ (ዮሐ 18፥19-23)።
👉 ከዚያ በኋላ ደግሞ ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት ከሐና ወደ ቀያፋ ወሰዱት፡፡ ከዮሐንስ ወንጌላዊው በቀር ሐዋርያት ጥለውት ተበተኑ፤ ጴጥሮስም ከሩቅ እየተከተለ ገብቶ እሳት ከሚሞቁት ጋር ተቀምጦ ነበር፡፡ ከካህናቱ አለቆች ገረዶች አንዲቱ ጴጥሮስን እሳት ሲሞቅ አየችው፤ ‹‹አንተም ከገሊላዊው ከኢየሱስ ጋር ነበርክ›› አለችው፡፡ ጴጥሮስም ደንግጦ አንቺ የምትይውን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ከቅጥሩም ወደ ውጭ ወጣ ዶሮም ጮኸ፡፡ ዳግመኛ ሌላይቱ ገረድ አየችው፤ ከዚያ ቁመው ላሉት ‹‹ይህም ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበር›› አለቻቸው፤ ሁለተኛ ካደ፡፡ ጥቂትም ቆይቶ ቆመው ያሉት ጴጥሮስን ‹‹አንተም በእውነት ከእነርሱ ወገን ገሊላዊ ነህ፤ አነጋገርህም ያስታውቃል›› አሉት፡፡ የምትሉትን ሰው አላውቀውም እያለ ይምል ይገዘት ጀመር፡፡ ያን ጊዜም ዶሮ ጮኸ፤ ጌታ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ብሎት ነበርና ዘወር ብሎ አየው፡፡ ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ አለቀሰ፤ (ማር 14፥66-72 ፣ ሉቃ 22፥54-61 ፣ ማቴ 26፥69-75 ፣ ዮሐ 18፥25-27)።
👉 አይሁድም በጥዋት ወደ ጲላጦስ ወስደው ሊያሰቅሉት መከሩ፤ ይሁዳም ሲወስዱት አይቶ ተጸጸተ፡፡ እርሱ በተአምራት ይድናል እኔ ገንዘቤን ይዤ እቀራለሁ ብሎ ነበርና እንደማይለቁት ተረድቶ ሔዶ ገንዘባችሁን እንኩ አላቸው፡፡ እነርሱም የምንሻውን ሰጥተኸናል የምትሻውን ወስደሃል አሉት፡፡ ብሩን በቤተ መቅደስ በትኖ ሊታነቅ ሔዶ ከዛፍ ተሰቀለ፤ ዘፏም ‹‹እንደ ወንድምህ ጴጥሮስ ንስሐ ግባ›› ብትለው ከሌላ ዛፍ ተሰቀለና ገመዱ ተበጥሶ በመውደቁ ሰውነቱ ቆስሎ ከዐርባ ቀን በኋላ ሞተ፡፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ጌታ ተይዞ ወደ ጲላጦስ ሲገባ ከበር ቁመው የነበሩ ጦሮቹ ሰገዱለት፤ በሌሎች ኃያላን ቢያስይዟቸውም አሸንፈው ሰገዱለት፡፡ ጲላጦስ ይህን ሲያይ ፈራና በውኑ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? አለው፤ ጌታም ‹‹አንተ አልክ›› አለው፤ (ዮሐ 18፥37)፡፡ አይሁድ ግን ሰንበትን የሻረ፣ ኦሪትን ያቃለለ፣ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገና ለቄሳር ግብር የከለከለ ዐላዊ ነው እንጂ ንጉሥ አይደለም አሉ፡፡ ጌታ ዝም ሲል ጲላጦስ ይህን ያህል ሲያሳጡህ አትመልስም ልገድልህም ላድንህም ሥልጣን አለኝ አለው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር ምንም ምን በእኔ ላይ ሥልጣን የለህም›› (ዮሐ19፥11) ይህን ተናግሮ ዝም አለ፡፡ ይህን በተናገርክበት እስኪ ንገረኝ አለው፤ መንግሥቴስ በዚህ ምድር ብትሆን ኖሮ ለአንተ ተላልፌ ባልተሰጠሁ ነበር፤ አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ወደ ገነት ልመልሰው ከሰማይ ወርጄ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልጄ በዚህ ምድር ወንጌልን እያስተማርኩ ሳለሁ አይሁድ ይዘው ለአንተ አቅርበውኛል ብሎ ሁሉን ነገረው፡፡ ጲላጦስም ይህን ሰው በደል አላገኘሁበትም ብሎ ልልቀቀው? አላቸው፡፡ እነርሱም ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ ሲያውክ የነበረ ነው አሉ፡፡ ጲላጦስም ከገሊላ ሲሉ ሰምቶ ወደ ገሊላው ገዥ ወደ ሄሮድስ ላከው፡፡ ሄሮድስም ዝናውን እየሰማ ሊያየው ይወድ ነበርና ሲያየው ደስ አለው፡፡ ነገር ግን ቢጠይቀው የማይመልስለት ሆነ፡፡ ሄሮድስም ይህስ ቢቻል ሁለት ሞት ይገባዋል ብሎ አስገርፎ ቀይ ግምጃ አልብሶ ወደ ጲላጦስ ሰደደው፡፡ ጲላጦስ ግን ብዙ እንዳስገረፈው አውቆ አዘነ፡፡ አይሁድንም ሦሰት ጊዜ አመጣችሁት በደሉ ምንድን ነው? አላቸው፡፡ ገርፌ ልልቀቀው በርባንን ልስቀለው አላቸው፡፡ አይሁድ ግን ሕዝቡን አስተባብረው ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮሁ፡፡
👉ያን ጊዜ የጲላጦስ ሚስት አብሮቅላ ደብዳቤ ላከችበት፤ ዲዳ የነበሩ ልጆቹ መካራና ዶርታ አንደበታቸው ተፈቶ የሆነውን ነግረዋት ነበርና ይህን አይቶ ሊፈታው ፈለገ፡፡ ‹‹ይህን ብትፈታው የቄሳር ወዳጅ አይደለህም›› አሉት፤ (ዮሐ 19፥12)፡፡ ስለዚህ ውኃ በኩስኩስት አስመጥቶ ‹‹እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› ብሎ እጁን ታጠበ፤ እነርሱ ግን ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ይሁን ብለው ተቀብለው #6666 ጊዜ ዐጥንቱ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ገርፈውታል፡፡ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በራሱ ደፉበት፤ ራሱንም በዘንግ መቱት፡፡ ቁመቱ ሰባት ክንድ ከስንዝር ወርዱ ሦስት ክንድ ከስንዝር አድርገው መስቀል ሠርተው አሸክመው ከሊጦስጥራ ወደ ቀራንዮ ወሰዱት፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይም ሰቀሉት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ግራ ዳክርስን በቀኙ ደግሞ ጥጦስን አብረው ሰቅለዋል።
👉 ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ሰባት ተአምራት ተደርገዋል፡፡ እነዚህም፦
👉- ሦስቱ በሰማይ፦ ፀሐይ ጨለመ፣ ጨረቃ ደም ሆነ፣ ከዋክብት ረገፉ (ሚልክያስ 4፥2 ፣ ዘካ 14፥7 ፣ ኢዮ 3፥15 ፣ ኢሳ 13፥10 ያለው ትንቢት ተፈጸመ)፡፡ ‹‹ፀሐይን አጨለመ፤ ገዳዮቹን ግን አልተቀየመም›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘዓርብ 6 ሰዓት)
👉
- አራቱ በምድር፦ መቃብራት ተከፈቱ፣ ሙታን ተነሡ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ፣ ዓለታት ተሰነጣጠቁ (ኢዮ 2፥10 ያለው ትንቢት ተፈጸመ)፡፡
❤❤❤❤❤❤❤❤❤
👉
ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ መከራን የተቀበለ ሲሆን በጥቅሉ ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ተብለው ይጠራሉ፡፡ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል ተናግሮ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ፡፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
👉 ሰባቱ አጽርሐ መስቀል የሚባሉትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቀራኒዮ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፡፡ እነዚህም፦

- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ)…ማቴ 27፥40
- አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው…ሉቃ 23፥39
- ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ…ሉቃ 23፥39
- አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ…ሉቃ 23፥46
- እነሆ ልጅሽ እነሆ እናትህ…ዮሐ 19፥26
- ተጠማሁ…ዮሐ ፥28
- ተፈፀመ…ዮሐ ፥19፥30