Telegram Web Link
🥇 ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ #ኩክ የለሽ_ማርያም እና #ሰሚነሽ_ኪዳነምህረት

🥈 የፊታችን እሁድ ጥር 29/05/2014

🥉 የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 250 ብር ብቻ

🏅መነሻ:- መገናኛ እና ጣፎ አደባባይ

🎖 ፈጥነው ቦታ ይያዙ ደውሉ ለበለጠ መረዳት
📞 ስልክ:-0911285173
📩 @Henokaas
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ታምረኛዋ #አርቱ_ቅድስት_አርሴማ

👉 ጻበሉ ፍል የሆኑና ብዙዎች በእንፋሎቱ ብቻ የዳኑበት

👉 ሙስሊሞች ድነው ምስክርነት የሚሰጡበት

👉 ለዘመናት እጃቸውን እግራቸውን የተቆለፈ በ አንድ ቀን የሚፈቱበት

👉 ብዙ ታምራትን የምናይበት ቦታ ነው

👉 የጉዞ ቀን እሁድ የካቲት 6/06/2014 ደርሶ መለስ

👉 የጉዞ ዋጋ 250 ብር መስተንግዶን ጨምሮ

👉መነሻ:- መገናኛ , ቃሊቲ ማሰልጠኛ እና አየር ጤና

👉 ፈጥነው ቦታ ይያዙ ደውሉ ለበለጠ መረዳት
📞 ስልክ:-0911285173
📩 @Henokaas
🙏 ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ # ሰላማዊት ኪዳነምህረት እና  #ሰሚነሽ_ኪዳነምህረት

↪️ የፊታችን እሁድ በ15/12/2014

↪️ የጉዞ ዋጋ 300 ብር ብቻ

↪️ መነሻ:- ጦር ሃይሎች, ሜክሲኮ,አየር ጤና  ልደታ, መገናኛ  እና ጣፎ አደባባይ

↪️ ፈጥነው ቦታ ይያዙ ደውሉ ለበለጠ መረዳት  
   
          📞  ስልክ:-0911285173
                        :-  0943070920

           📩  @Henokaas
የመስከረም ፬  #ግጻዌ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ዘነግህ ምስባክ

‹‹አጽምኡ ሕዝብየ ሕግየ። ወጽልዉ እዝነክሙ ኀበ ቃለ አፉየ። እከስት በምሳሌ አፉየ።››

‹‹ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ››
🌻📖 መዝሙር ፸፯፡፩

የዕለቱ ምንባባት

🌻📖 ማቴዎስ ፲፩፡፯-፳
፯ እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?
፰ ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።
፱ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።
፲ እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።
፲፩ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።
፲፪ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።
፲፫ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤
፲፬ ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።
፲፭ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
፲፮ ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ።
፲፯ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል።
፲፰ ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት።
፲፱ የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።
፳ በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦

🌻📖 ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፫፡፩-፰
፩ ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው።
፪ እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
፫ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥
፬ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤
፭ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?
፮ በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።
፯ በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።
፰ እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥

🌻📖 ፩ኛ ጴጥሮስ  ፭፡፱-ፍጻሜው
፱ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
፲ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።
፲፩ ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
፲፪ እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።
፲፫ ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
፲፬ በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።

🌻📖 ሐዋርያት ፯፡፵፬-፶፩
፵፬ እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤
፵፭ አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።
፵፮ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።
፵፯ ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት።
፵፰-፶ ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።
፶፩ እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
2025/06/28 10:15:03
Back to Top
HTML Embed Code: