Telegram Web Link
መንፈሳዊ የዩቱብ ቻናል
መግዛት የሚፈልግ
ካለ ሞኒታይዝ የሆነ ክፍያ የጀመረ
2119 ሰብስክራይብ ያለው
ዋጋ 60,000(ስልሳ ሺ ብር)

@Henokaas
አድራሻ:-
ምክረ አጋንንት

በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ

ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።
# በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
# ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
# እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።
ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
# ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሔር ተመልሰን ንስሐ እንግባ።።
+ ጻድቅ ሆኖ ተመለሰ +

አባ ፕሮፎርዮስ እንዲህ ሲሉ ገጠመኛቸውን ያስታውሳሉ ፦

‘በጥምቀት በዓል ሰሞን ውኃው ተጸልዮበት ከተባረከ በኋላ ለካህናት ወደ ሰዉ ቤት መሔድና ጠበል መርጨት የተለመደ ሥርዓት ነው፡፡ የሆነ ዓመት ላይ ይህንን ጠበል እየረጨሁ ምእመናንን ለመባረክ ከቤተ ክርስቲያን ወደ መንደር ወጥቼ ነበር፡፡  በየቤቱ በር አንኳኳና ‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ /ጌታ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ.../ እያልሁ እያዜምሁ እገባለሁ፡፡

ብዙ መኖሪያ ቤቶች ወዳሉበት መንደር እንደዘለቅሁ አንድ በብረት በር የተዘጋ ትልቅ ጊቢ ጋር ደረስሁ፡፡ ከፍቼ ዘልቄ ገባሁ ፤ ጊቢውን የሞላውን መንደሪን ፣ ሎሚና ብርቱካን የተተከለበት የአትክልት ሥፍራ አልፌ ቀጥ ብዬ ገባሁ፡፡ ሕንጻው ወደ ምድር ቤትና ወደ ላይኛው ፎቅ የሚያስወጡ ሁለት ደረጃዎች አሉት፡፡ ወደ ላይ ወጥቼ አንዱን በር ሳንኳኳ አንዲት ሴት ብቅ ብላ በሩን ከፈተች፡፡ ‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ ብዬ ማዜም ስጀምር በፍጥነት አስቆመችኝ፡፡ ይሁንና ድምፄ በደንብ ተሰምቶ ስለነበር ከግራ ከቀኝ ካሉት ክፍሎች ውስጥ ወጣት ሴቶች ወደ ኮሪደሩ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ነገሩ ገባኝ ፤ ‘አሃ ዘልዬ የገባሁት ለካ መሸታ ቤት ከሚሠሩ ሴቶች ቤት ኖሯል?’ አልኩኝ በሆዴ፡፡

‘እባክዎን ይሒዱ አባ’’ አለች ቀድማ የወጣችው ሴት ‘እነዚህ ሴቶች መስቀል መሳለም የሚገባቸው አይደሉም ፤ እኔን ያሳልሙኝና ቶሎ ይሒዱ’ አለች በችኮላ፡፡

ኮስተር አልኩና ‘ካህን ነኝ ቤቱን ሳልባርክ አልሔድም’ አልኳት
‘እሱን ይችላሉ እነዚህ ሴቶች ግን መስቀሉን አይሳለሙም’ ብላ ፍርጥም አለች፡፡

‘መስቀሉን መሳም የሚገባው አንቺ ሁኚ እነርሱ በምን እናውቃለን? እግዚአብሔር  መስቀሉን መሳለም የሚገባው ማን ነው ብሎ እኔን ቢጠይቀኝ ኖሮ መስቀል መሳለም የሚገባው ለአንቺ ሳይሆን ለሴቶቹ እንደሆነ በነገርሁት ነበር፡፡ ምክንያቱ ከምትመጻደቂው ከአንቺ ይልቅ የእነርሱ ነፍስ ትሻላለች’ ብዬ ገሠጽኋት፡፡ ደንግጣ ዝም አለች ፤ እኔም ሴቶቹን ወደ እኔ እንዲመጡ ጠራኋቸው፡፡

ከዚያም ‘‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ እያልኩ ከመጀመሪያው በበለጠ ኃይል መዘመር ቀጠልሁ፡፡ እግዚአብሔር ወደ እነዚህ ምስኪን ነፍሳት እንድመጣ እንዳመቻቸልኝ ስላወቅሁ ውስጤ በደስታ ተሞልቶ ነበር፡፡

ሁሉም መስቀሉን ተሳለሙ፡፡ ሁሉም ያጌጠ ልብስ ለብሰው ሊወጡ ተዘጋጅተው ነበር፡፡ እንዲህ አልኳቸው ፦ ልጆቼ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፤ እግዚአብሔር የሚወደው ሁላችንንም ነው፡፡ እርሱ መልካም ነውና ለኃጢአተኞችም ለጻድቃንም ዝናምን ያዘንባል፡፡ እርሱ የሁላችን አባት ነውና ለሁላችን ይጨነቃል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ወደ እርሱ መምጣት እርሱን መውደድና መልካም መሆን ብቻ ነው፡፡ እርሱን ውደዱ ምንኛ ደስተኛ እንደምትሆኑ ታያላችሁ’’

በመደነቅ ይመለከቱኝ ነበር ፤ በተጨነቀች ትንሽ ነፍሳቸው ውስጥ የሆነ ነገር እንደቀረ ያስታውቅ ነበር፡፡

‘እናንተን ለመባረክ እግዚአብሔር ዛሬ ወደዚህ ቤት የመምጣትን ክብር ስለሠጠኝ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ’ አልኳቸው፡፡ ለመሔድ ስነሣ ‘እግዚአብሔር ለዘላለም ይባርካችሁ’ አልኳቸው ፤ ‘አሜን አባ’ ብለው በአንድነት መለሱ ፤ ጉዞዬን ቀጠልሁ፡፡ 
                    💒💒💒💒💒

ይህንን አጭር ታሪክ በኦርቶዶክሱ ዓለም እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ እጅግ ውብ መጻሕፍት አንዱ ከሆነው ‘Wounded by Love ፤ The Life and the Wisdom of Saint Porophyrios’ ከተሰኘው የአንድ መነኩሴን ሕይወት የሚተርክ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

               💒💒💒💒💒
              

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‘እግዚአብሔር በጽድቁ ከሚመካ ጻድቅ ይልቅ ስለ ኃጢአቱ የሚያለቅስ ዘማዊን ይወድዳል’  ይላል፡፡  በእርግጥም ራስን አጽድቆ የሌላውን ሰው ኃጢአት የማሰብን ያህል ኪሳራ በክርስትና ሕይወት የለም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበው የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት ሲቆጥር ሳይሆን የራሱን በደል ሲቆጥር ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‘እኔ መተላለፌን አውቃለሁና ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና’ እንዳለው እግዚአብሔር ኃጢአትህ ተሰረየችልህ የሚለው ሰው የራሱን ኃጢአት ዘወትር የሚያስብ ሰው ነው፡፡

የነነዌው ቅዱስ ማር ይስሐቅ ‘መላእክትን ከሚያይ ሰው ይልቅ የራሱን ኃጢአት የሚያይ ሰው ይሻላል’’ ይላል፡፡ ባለ በገናው ‘እባክህ ጌታዬ ሥጠኝ መስታወት ፤ የሰው ሥራ ትቼ የእኔን አይበት’ እንዳሉ የራሱን በደል ማየት ከሚችል በቀር ይቅርታን የሚያገኝ የለም፡፡ ለብዙዎቻችን ከራሳችን ይልቅ የሰው ጉድፍ ማውጣት ይቀልለናል፡፡ ሰው ሆኖ ሌላ ሰውን ኃጢአተኛ ነህ የማለትን ኃጢአትና ትዕቢት ግን የለም፡፡ የሰዎችን ድክመት ባየን ጊዜ ከመሳደባችን በፊት እኛ ከዚያ ሰው በኃጢአት ብዛት በምንም እንደማንሻል ማሰብ አንደበታችንን ይሰበስብልናል፡፡

አባ ሲድራስ የተባለ አባት አንድ ወጣት መነኩሴ የወይን ፍሬ ሰርቀሃል ተብሎ ከገዳም ሲባረር አይቶት ተከትሎት ወጣ፡፡ አባታችን ወዴት ትሔዳለህ ሲሉት ‘እሱ ወይን ሰረቆ ከተባረረ እኔ የሠራሁት በደል ብዙ ነውና አብሬው ብወጣ ይሻላል ብዬ ነው’ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት መነኩሴውን ከመባረር አዳኖታል፡፡ ወዳጄ እኔና አንተ በወንድማችን የምንፈርደው ከእርሱ የባሰ የተሸሸገ በደል ተሸክመን መሆኑን አንርሳ፡፡ ‘እኔ እንኳን ብዙ ኃጢአት የለብኝም’ የምንል ከሆነ ግን በድሏል ካልነው ሰው የከፋ ለንስሓ መንገድ የሌለው በደል ውስጥ ነን፡፡  እግዚአብሔር ሊያድነን የሚችለው ከምናምነው ኃጢአታችን እንጂ ከመመጻደቃችን አይደለም፡፡

በወንጌል ጌታችን ከተናገራቸው ታሪኮች እጅግ የተዋቡት ምንባባት ኃጢአታቸውን ያልደበቁና ያልተመጻደቁ ኃጢአተኞች ታሪክ ነው፡፡ የዘኬዎስ ፣ የባለ ሽቱዋ ማርያም ፣ ልትወገር የነበረችው ሴት ወዘተ ታሪኮች ኃጢአታቸውን አምነው ይቅርታ ያገኙ ሰዎች ታሪኮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ ታሪክ ስለ አንድ ቀራጭ ይናገራል፡፡ በቤተ መቅደስ ፈሪሳዊውና ቀራጩ ጎን ለጎን ቆመው ይጸልያሉ፡፡

ፈሪሳዊው በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እንኳን ራሱን ዝቅ አያደርግም፡፡ አፉን ሞልቶ ጽድቁን ያወራል፡፡ ጽድቅን ተናግሮ የሚገኝ ነገር ያለ ይመስል ‘እጾማለሁ ፣ ዐሥራት አወጣለሁ’ እያለ ይመጻደቃል፡፡ አልፎ ተርፎ ‘እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ’ ብሎ የቀራጩን ኃጢአተኝነት ለእግዚአብሔር አሳሰበ፡፡ ወዳጄ ሺህ ጊዜ በጎ ብትሠራ እንዲህ አደረግሁ ያልህ ቀን ዋጋ ታጣለህ ፣ ስለ ሌሎች ሰዎች ኃጢአት ማውራትና ማሰብ እስካልተውህ ለእኔ ፈሪሳዊ ነህ እያለን ነው መሐሪው ጌታ፡፡

ቀራጩ ግን ‘‘በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ’’ ይላል ጌታችን፡፡ በእውነት እንዴት ያለ ቃል ነው፡፡
#ጾመ_ነቢያት_የገና_ጾም ✞ 

👉🏽 ገና ሚባል በተለምዶ ነዉ ጌና ነዉ ትክክለኛዉ ጌና  ብሂል ልደተ ክርስቶስ አምላክ እንዲል፡፡

❖ ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡

✤ ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡

❖ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡
    
✤ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡
      
❖ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

@Terha_Tsion

#የጾመ_ነቢያት_መግቢያ

የጾመ ጌና መግቢያ ሁልጊዜ (በአራቱም ወንጌላውያን) ኅዳር 15 ቀን ይገባል፡፡ ይህን አስመልክቶ የሕጉ መጽሐፍ #ፍትሐ_ነገሥት
"ወጥንተ_ዚኣሁ_መንፈቀ_ኅዳር_ወፋሲካሁ_በዓለ_ልደት" መጀመሪያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካውም የልደት በዓል ነው ይላል (አን 15) እኩሌታ የሚለውን ይዘው የኅዳር እኩሌታ 16 ነው የሚሉ አሉ፡፡ ለዚህ ምላሽ የሚሆነን!

*15+15=30 ይሆናል እንጅ 15+16=30 አይሆንም፡፡

* መንፈቁ ለኅዳር ዝ ውእቱ ሚናስ ይላል #የቅዱስ  ሚናስ  በዓሉ ነገ መሆኑ ልብ እንበል። (በ15)

*ስንክሳሩ ወበዛቲ ዕለት አመ ፲ወ፭ ጥንተ ባዓለ ጌና በኅዳር 15 ቀን የገና ጾም መጀመሪያ ነው ይላል፡፡ (ስንክሳር ዘኅዳር 15)

@Terha_Tsion

*ፍትሐ ነገሥቱ የኅዳር እኩሌታ ብሎ በማለቱ

*ቅዱስ ሲኖዶስ በ1983 ጾሙ በአራቱም ወንጌላውያን በኅዳር 15 ብቻ እንዲገባ ወስኗል፡፡

ሌላኛው በኅዳር 19 ይገባል የሚለው የተቀብዐ ወገኖች ሐሳብ ነው ስንክሳራችን ግን በዚህችም ዕለት የሮም፣ የአፍርንጊ፣ የሶርያ፣ የአርማንያ ክርስቲያኖች ከግብጽ፣ከኢትዮጵያና ከኖባ በቀር   የጌናን ጾም የሚጀምሩበት ነው ይላል  (ስንክሳር ዘኅዳር 19) ስለዚህ የ19 መግቢያ የኛ ባሕል አይደለም፡፡
                         
                        
Forwarded from 💖ማርያም ሆይ እንወድሻለን💖
ሐዋርያው መነኩሴ

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ(ጻድቁ) ለነፍሴ
አዝ
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አዝ
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/
አዝ
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተምረናል /2/
አዝ
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ቅዱስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አዝ
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/
Forwarded from ♌️ⓁⒾⓈⒶⓃ♌️
ውድ የተዋህዶ ልጆች ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ።አንድ የማስቸግራችሁ ነገር አለኝ መምህር ሄኖክ ነኝ አዲስ የዩቱብ ቻናል ከፍቻለሁ ኦርቶዶክሳውያን ሰብስክራይብ አድርጉኝ ለሌችም በማስደረግ እግዛችሁ ያስፈልገኛል🥺🙏 ሰብስክራይብ ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ 🙏🥺

      የዩቱቡ ሊንክ👇
https://www.youtube.com/@tilamedia
ውድ የተዋህዶ ልጆች ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ።አንድ የማስቸግራችሁ ነገር አለኝ መምህር ሄኖክ ነኝ አዲስ የዩቱብ ቻናል ከፍቻለሁ ኦርቶዶክሳውያን ሰብስክራይብ አድርጉኝ ለሌችም በማስደረግ እግዛችሁ ያስፈልገኛል🥺🙏 ሰብስክራይብ ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ 🙏🥺

      የዩቱቡ ሊንክ👇
https://www.youtube.com/@tilamedia
2025/06/28 06:53:11
Back to Top
HTML Embed Code: