አባባን ሐጅ ወስደዋቸው ነው.... ሐጁ እየተከወነ ሶፋና መርዋ መካከል የሚሮጥበት ሰአት ደረሰ። እናም ሰዎች አንዲሮጡ ነገሯቸው ....« አባባ ዱብ ዱብ በሉ » አሏቸው
.... «የእስማኤል እናት ብትሮጥ ለልጇ ውሃ ፍለጋ ነው እኔ ምን ገዶኝ እሮጣለሁ» አሉ ይባላል ።
ወላጆችን ሐጅ ለማስደረግ መቋመጥ የሁሉም መልካም ልጅ ምኞት ነው።ነገር ግን ሐጅ ዒባዳህ እንጂ የቱሪዝም መዳረሻ አይደለምና ልክ እንደ ሶላት አፈፃፀሙን መማርና ማስተማር ግዴታ ነው።
ሐጅ የምታስደርጋቸው ጀነትን በመፈለግ እንጅ መካን ለማሳየት አይደለም። ረሱለላህ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ኩልል ያለ ሐጅ ጀነት እንጅ ክፍያ የለውም» (ቡኻሪይ 1773)
ኩልል ያለ ሐጅ ማለት ፦
① ከወንጀል የፀዳ
② ከይዩልኝና ይስሙልኝ የፀዳ (ኻሊስ)
③ ማእዘናቱና ዋጂቦቹ የተረጋገጡበት ማለት ነው።
ከነርሱ ጋር ካዕባ ዘንድ ሰልፊ መነሳትኮ ሀጅ አይደለም! ማስደሰት ከሆነ የፈለግከው በዚያው ወጪ በሌላ ነገር ማስደሰት ይቻላል። አላህ ለኛም ለቤተሰቦቻችንም ኩልል ያለን ሐጅ ይወፍቀን!!
@heppymuslim29

የዐረፋ ቀን ታላቁ የአላህ ቀን ነው። ኃጢኣት ይሰረዝበታል። በእለቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል። ከምንም ጊዜ በበለጠ የአላህ እዝነት ለባሮቹ ቅርብ ይሆናል።
:
የተውበት ቀን ነው። ምህረት የሚታደልበት ቀን ነው። ለአላህ የሚዋደቁበት የዱዓ ቀን ነው። የለቅሶና የተስፋ ቀን ነው።
ሰዎች በብዛት ከእሳት ነጃ የሚባሉበት፡ ኢብሊስም አንሶና አፍሮ የሚውልበት ዕለት ነው።
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ አምናለሁ።»
ዙል-ሂጃ 9 ነገ ነውና ዕለቱን በፆም፣በዚክርና መልካም በተባሉ ስራዎች እናጅበው።
እኔንም በዱዓ አትርሱኝ ‼️

ሳንሰለች እንደጋግማት!
اللّٰہ أڪبَر .. اللّٰہ أڪبَر .. اللّٰہ أڪبَر
لاَ إلہ إلاّ اللّٰہ

وللّٰہ الحمّد
አብዛኞቻችን በነዚህ አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ተክቢራን ዘንግተናል እና ሁላችንም በነዚህ የተወደዱ ከዱንያ በላጭ በሆኑ ቀናቶች ተክቢራን እንደጋግም።

የኡዱሕያ መስፈርቶች
1ኛ, ከቤት እንስሳት መሆን አለበት።
እነርሱም ፡- ግመል ከብት በግ እና ፍየል
2ኛ, በሸሪዓ ለተገደበው እድሜ መድረስ አለበት።
ግመል ከኾነ 5 ዓመት
ከብት ከኾነ 2 ዓመት
ፍየል ከኾነ 1 ዓመት
በግ ከኾነ 6 ወር የሞላው
3ኛ, ከነውር (ከዓይብ) የጠራ መሆን አለበት።
አንድ ሰው ኡዱሕያ ማረድ ከፈለግ በሚያርደው እንስሳ ላይ የተጠቀሱት ነገሮች መሟላት አለባቸው።
🛖ቅርጫ ማድረግ የፈለገ ሰው
በግ ወይም ፍየል ከኾነ ለ1 ሰው ብቻ
በሬ ወይም ግመል ከኾነ ለ7 ሰው መካፈል ይቻላል
👉 እንስሳቶችን ስናርድ ደግሞ አስተራረዳችንን ማሳመር አለብን። እነሱም ነፍስ አላቸው አይናገሩም ብሎ እነሱን ማሰቃየት ተገቢ አይደለም።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ﴾
👉አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ። 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1955

ኢዱን ሰዒድ…… የቀናት ምርጦችን አንድ ሁለት እያልን አስረኛው ላይ አገባደድን ። የኢብራሂምን ቆራጥነት ፣ የኢስማዒልን ታዛዥነት ፣ የሀጀራን ፅናት ና ተወኩል እያወሳን ለህይወታችን ማጣፈጫ እና መመሪያ ይሆነን ዘንድ ጣርን ። የጌታዬን ቤት ካዕባ ፣ የውዱን ነብይ ትውልድ ፣ የሀይማኖት አባት የሆኑት የኢብራሂምን ሱና አላህ ያደላቸው እዝነቱን ያንቧቧላቸው በቦታው ተገኝተው የእድሜ ዘመናቸውን ህልም በእነዚህ ቀናት አሸበረቁበት ። በሚና ተራራ ላይ ፣ በሙዝደሊፋ እድረት ፣ በአረፋ ተራራ ዱዐ ፣ በታላቁ የአረፋና የጁምዐ ኹጥባ ፣ በኡድሂያ እርድ ፣ በዒድ አልአደሀ ሰላት …ለበይክ ያአላህ እያሉ ፣ ምንኛ መታደልን ታደሉ በቤትህ የከተሙ ። መካን መምጣት ባይችሉ መዲናንም ባይጎበኙ በፆም በዱዐ ፣ በአዝካሩ ነገን ተስፋ ያደረጉ ምርጥ የአላህ ባሪያዎች አለምን በዒድ ሰላት በተክቢራ ድምፅ አሳምረዋት ዋሉ ። የተራራቀ ዘመድ የተረሳሳ ወዳጅ ታላቅ ዒድ ነውና ሲዘያየር ሲተዋወስ ዋለ ። ለህፃናት መቦረቂያ ለአዋቂውም የቀልቡ መደሰቻ ነው ዒድ አልአደሃ …… የዘመናት ታሪክ ፣ የህይወት ዘመን ተምሳሌት ፣ የቤተሰብ ፅናት …… አደም(ዐ.ሰ)…… ኢብራሂም(ዐ.ሰ)…… ኢስማዒል(ዐ.ሰ)…… የሴትነት ተምሳሌት ሀጀራ…… ዉዱ ነብያችን ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)የአለማት እዝነት…… እና እኛ የአለማቱ እዝነት ዑማ የሆንን…… ሁሌም ታሪክ ያነሳናል።
ኢድ ሙባረክ
@heppymuslim29
ኢድ ሙባረክ
@heppymuslim29
"በሕይወታችን የሚጎዱን ከባድ ነገሮች ምን ይመስሉሻል?" በጫወታችን መሀከል ድንገት ከጓደኛዬ የመጣ ጥያቄ ነበር
"እንደዚህ አይነት ድንገተኛ ጥያቄ" አልኳት.. ፈገግ አለችና "አልቀለድኩም አንቺ ደሞ" አለችኝ.. "እምም እሺ ቆይ" ብያት ትንሽ አወጣው አወረድኩና እንዲህ አልኳት..
"በሕይወታችን የሚጎዱን ከባዶቹ ነገር የራሳችን ጉጉት Expectation እና የፍላጎታችን መብዛት ይመስለኛል" አልኳት። ማብራርያ የፈለገች ትመስላለች በተመስጦ እያየችኝ "like how?"አለችኝ
"እንዴት መሰለሽ For example አንድን ሰው እንደማታገኝው እያወቅሽ.." ስላት ሳታስጨርሰኝ "Oww የሞተን ሰው ምናምን ነው እንዴ" አለችኝ
"No No የሰውን ልጅ የማታገኝው ስለሞተ ብቻ ነው እንዴ ?Ofc አይደለም አጠገብሽ ሆኖ ሀሳቡ ልቡ ሌላ ጋር የሆነን ሰው መናፈቅ ፣በራሱ የዓለም ባህር ውስጥ የሰመጠን ሰው መናፈቅ ፣መቼም እንደማትገናኙ የምታቂውን ሰው መናፈቅ አየሽ እንደዚህ አይነት ሰዎችን አብረሻቸው ለመሆን እነሱን ያንቺ ዓለም ውስጥ ለማስገባት መጓጓት የሕይወትሽ ከባዱ ነገር ነው።መጓጓት መጥፎ ነው ከጓጓሽ ትጠብቂያለሽ ጠብቀሽ ካላገኘሽ ደሞ ውስጥሽ፣ቅስምሽ ላይጠገን ይሰበራል ድብርት ውስጥ ትዘፈቂያለሽ ሕይወት ማታጓጓው ስልቹ እና careless ሰው ትሆኛለሽ እንደዚ ከሆንሽ ደሞ ምንም motive የሌለው ሰነፍ ሰው ትሆኛለሽ..። በግርምት እያየችኝ "እንዴት እንዴት አድርገሽ አገናኘሽው አንቺ" ብላ ሳቀች።
እንዴት እንዳገናኘሁት እኔም አልገባኝም ግን ይሄ የሁላችንም ትክክለኛ ስሜት መሰለኝ ዝም ብያት ፈገግ አልኩኝ "So መፍትሄውስ አለችኝ" "መፍትሄውማ ከባድ ነው ይሄን ያነሳውልሽ ለምሳሌ ያክል ነው የሰው ልጅ ስትሆኚ በሆነ means የሆነ ነገር ላይ መጠበቅሽ መጓጓትሽ አይቀርም ግን መፍትሔው ለፍላጎትሽ ገደብ መስጠት እና ለበጎ ነው የሚለውን ብሂል አለመረሳት እና ለበጎ መሆኑን አምኖ እንዲቀበል ራስሽ ላይ መስራት ነው" አልኳት። አተኩራ አየችኝ እና ማክያቶዋን በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደረገችው እና "አዋ ለበጎ ነው" ብላ በውስጧ እያጉረመረመች ፈገግ አለች ባትነግረኝም ለጥያቄዋ መልስ እንዳገኘች ከface expressionዋ ተረዳውና እኔም ሁፈይይ አልኩ።

"ስልችት ብሎኛል!"
"ምኑ?"
"የሚመረጥ የለውም... መኖር አሰልችቶኛል?"
"ጓዝ አበዛሽ እንዴ?"
"የምን ጓዝ?"
"ተጥሎ መረሳት የነበረበትን ያለፈ ታሪክ ዛሬም ያለ እና የሚኖር እስኪመስልሽ ተሸክመሻል?"
"እንዴ? ... ወዴት ይጣላል? የኔ እኮ ነው። የኖርኩት። ማንነቴ የተገነባበት ነው። ወደ የት ነው የምጥለው? አያስፈልገኝም ልጣለው ብልስ ግማሽ አያስቀረኝም?"
"ወጣት ነሽ አይደል? ህፃን እያለሽ የነበሩሽን የምትወጃቸውን እና በምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የምትምነሰነሽባቸው ልብሶችሽን ፤ ያለ ምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የለበስሻቸውን ሁሉ አሁንም ትለብሻቸዋለሽ?"
"አይሆኑኝም እኮ ልኬ አይደሉም እንዴት እለብሳቸዋለሁ? በየጊዜው እየተካካሁ አስወግጃቸዋለሁ"
"ያለፈ ታሪክም እኮ እንደዛ ነው ለዛሬው አንቺነትሽ ያዋጣው ነገር ይኖራል እንጂ ለዛሬው አንቺነትሽ ግን ላይበቃሽ ይችላል። ልክ እንደልብሶችሽ በጊዜ ሂደት ወደሚሆንሽ እየተቀየረ በአዲስ መተካት ይኖርበታል!"
"የማይጠቅመኝን ያለፈ ነገር ማስወገድ ከመሰላቸት የሚያድነኝ ከሆነ በደስታ አደርገዋለሁ! ቀላል ይመስልሻል ግን?"
"ለአመታት በወጉ ያልተያዘን ቤት በደቂቃዎች ውስጥ ማሳመር ቀላል ነው?"
"እንዴት ቀላል ይሆናል?"
" ይሄም ቀላል አይደለም። ለመሞከር መነሳት ግን በግማሽ መንገዱን ይጠርገዋል!"
"በጉጉት መኖር ምን እንደሚመስል ማወቅ እና መኖር እፈልጋለሁ።"
"እንዲሆንልሽ ምኞቴ ነው።"

ዐሹራ (عاشوراء)
.
➊አሹራ ሚባለው ምን ቀን ነው?
.
➪አብዛኛዎቹ ኡለሞች ባሉበት አቋም መሰረት አሹራ የሚባለው ከሙሀረም አስረኛው ቀን ነው። አሹራም የተባለበት ምክንያት አስረኛው ቀን ለማለት ተፈልጎበት ነው።ልክ እንደዚሁ ዘጠናኛው ቀን ታሱአ ይባላል።
.
➦አንዳንድኡለሞች የሙሀረምን ዘጠነኛው ቀን ነው አሹራ ሚባለው ቢሉም ከቋንቋ አንፃር እንኳን ስናየው ትክክል አለመሆኑን እንረዳለን።
.🏷የዘንድሮ የዐሹራ ቀን (ሙሐረም10) ቅዳሜ ሰኔ 28 /2017 ላይ ይውላል። አሏህ በሰላም ያድርሰን
.
❷አሹራ ሚፆመው ለምንድነው?
.
➪የአሹራ ቀን የሚፆምበት ዋነኛ ምክንያት አላህ ሙሳን እና በኒ ኢስራኢሎችን ከፊርአው ነፃ ያወጣበት ቀን ስለሆነ ነው።
.
▩ማስረጃው
ኢብንአባስ እንዲህ ይላል
((የአላህ መልእክተኛ ﷺ መዲና ሲገቡ አይሁዶች የአሹራን ቀን ሲፆሙ አዯቸውና
"ይህ ምንድነው?"ብለው ጠየቋቸው ከዛም የሁዶች ሲመልሱ
" ይህ ደግ ቀን ነው አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው። ሙሳ ለምስጋና ፆሞታል" አሉ
የአላህ መልእክተኛም ﷺ "እኔ በሙሳ ከናንተ ይበልጥ ተገቢ ነኝ" አሉና ፆሙት በመፆምም አዘዙ
❸የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፆመውታል?
➩አዎ የአላህ መልእክተኛ ﷺ የአሹራ ፆምን ይፆሙት ነበር
.
▩ማስረጃው
አኢሻ እንዲህ ትላለች
(የአሹራቀን ቁረይሾች በጃሂሊያ ግዜ ይፆሙት ነበር የአላህ መልእክተኛም ﷺ ይፆሙት ነበር...)
📚ቡኻሪናሙስሊም ዘግበውታል
.
❹ከሙስሊሞች ውጪ ይህን ቀን ሚፆሙት አሉ?
.
➪አዎ ከሙስሊሞች ውጪም ይህን ቀን ሚፆሙት ነበሩ እነሱም
.
➀ሙሽሪኮች ፦ማስረጃው ከላይ በተራ ቁጥር ❸ ላይ ያሳለፍነው የአኢሻ ሀዲስ ነው
.
➁አይሁዶች ፦ማስረጃው ከላይ በተራ ቁጥር ❷ ላይ ያሳለፍነው የኢብን አባስ ሀዲስ ነው
❺ ግዴታ ነው ወይስ ሱና?
.
➪ረመዳን ከመደንገጉ በፊት የአሹራ ፆም ሙስሊሞች ላይ በግዴታነት መልኩ ተደንግጎ እንደነበር የሚጠቁሙ ሀደሶች አሉ ከነዛህ መሀከል ኢማም ቡኻሪ የዘገቡት የሰለማ ቢን አውከአ ሀዲስ አንዱ ነው። በዛ ሀዲስ ላይ መልእክተኛው ﷺ ሳያቅ ጠዋቱን የበላ ሰው የተቀረውን የቀን ክፍለ ግዜ እንዲፆም አዘዋል።
.
➪ይህ የግዴታነት ትእዛዝ ግን በሗላ ላይ ተሽሮ በበርካታ ሀዲሶች ላይ እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ የፈለገ ሰው ይፁም ብለው ተናግረዋል።
.
▩በመሆኑም የአሹራ ፆም የጠነከረ ሱና እንጂ ግዴታ አደለም።
.
❻አስረኛው ቀን ብቻ ነው ሚፆመው?
.
➪የአሹራን ቀን ብቻውን ነጥሎ ከመፆም ይልቅ ከሱ በፊት አንድን ቀን አስቀድሞ ፆሞ የአሹራንም ቀን አንድ ላይ መፆሙ የተወደደ ነው።
.
➦ይህ ማለት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን ማለት ነው።
.
➦ወይ ደግሞ አስራ አንደኛውንም ቀን አስከትሎ መፆሙ ይወደዳል።
.
▩ማስረጃውም
.
አብደላህኢብን አባስ ባወራው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል
"አላህ ካለ የሚመጣው አመት ዘጠነኛውን ቀን እንፆማለን"
ነገር ግን የሚቀጥለው አመት ሳይመጣ መልእክተኛው ሞቱ
📚 ሙስሊም ዘግቦታል
.
▤አንድ ቀን አስቀድሞ ወይም ደግሞ አንድ ቀን አስከትሎ መፆሙ የተደነገገበት ምክንያትን ኡለሞች ሲያብራሩ ብዙ የሚጠቅሷቸው ነገሮች ቢኖሩም በዋነኝነት ግን ከአህለል ኪታቦች ለመለየት ሲባል የሚለው ይበልጥ ሚዛን ይደፍል።ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሚቀጥለው አመት ብደርስ ዘጠነኛውን ቀን ጨምሬ እፆማለው ያሉት አስረኛውን ቀን አህለል ኪታቦች እንደሚያልቁት ሲነገራቸው ነው።
.
➪አንዳንድ ኡለሞች አስረኛውን ቀን ብቻ ነጥሎ መፆሙ የተጠላ እንደሆነ ይገልፃሉ።
.
➦ነገር ግን ሸይኹል ኢስላም ዘጠነኛውን ወይም አስራ አንደኛውም መፆም ላልቻለ ሰው አስረኛውን ብቻ ቢፆምም እንደማይጠላ ይገልፃል። የሚችል ሰው ግን አስረኛውን ብቻ መነጠሉ ተገቢ እንዳልሆነ ይጠቅሳል።
.
❼የሚወደደው አፇፇም
.
➪የሚወደደው አፇፇም በቅደም ተከተል ሲቀመጥ
.
⓵ዘጠነኛውን አስረኛውንና አስራ አንደኛውን ቀን ሶስቱን በተከታታይ መፆም (3ቀኖች)
.
⓶ዘጠነኛውንና አስረኛውን መፆም (2ቀኖች)
.
⓷አስረኛውን ቀን ብቻ መፆም (1ቀን)
.
📚ይህንንቅደም ተከተል ኢብኑል ቀይም ዛደል መአድ ላይ እንዲሁም ኢብን ሀጀር ፈትሀል ባሪ ላይ መርጠውታል። ኢብን ተይሚያም ኢቅቲዳ ኪታቡ ላይ ከኢማም አህመድ የዚህን አምሳያ ጠቅሷል።
.
➦በርግጥ ሌሎች ኡለሞች የመረጣቸው ሌሎች ቅደም ተከተሎች ቢኖሩም ከመጡ ሀዲሶች አንፃር ከላይ የጠቀስነው ቅደም ተከተል ይበልጥ አመዛኙ አቋም ነው።
.
❽የአሹራ ፆም ያለው ትሩፍት
.
➪ ኢማሙ ነሳኢ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ የአሹራ ፆም ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብለዋል።
.
✍🏾ኻሊድ ሙሀመድ (አቡሱለይማን)

Forwarded from Sumeya sultan
"የትዳር መስፈርትሽ ምንድነው?" አለችኝ ለሷ እና አብሮን ላለው ጓደኛችን ጥቁር ቡና ለኔ ነጣ ያለ ማኪያቶ ካዘዝን በኋላ
" መግባባት፣ ሃላፊነትን ማወቅ እና መዋደድ" አልኳት።
ከት ብላ እየሳቀች "የዛሬ 5አመት ስጠይቅሽ ብዙ መስፈርቶችን ዘርዝረሽ ነበር ከምኔው 3ላይ ደረስሽ?" አለችኝ።
እውነቷን ነው ከመልክ እስከ ስራ እያንዳንዱን ልኬት አስቀምጬ ነበር።
" ሴቶች እድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር መስፈርቶቻችሁን እያጠፋችሁ ነዋ ምትሄዱት? መጨረሻ ላይ "የሚተነፍስ ወንድ ይሁን ብቻ"ማለት ነው 'ሚቀራችሁ"። ድጋሚ ሳቅን።
" አይደለም ባክህ በ እድሜ መጨመር ውስጥ እነዚህ መስፈርት ብዬ አስቀምጬ የነበሩት ነገሮች የወዳጀነት መተሳሰሪያዎች ሳይሆኑ የፊልም ግብዓት እንደሆኑ ስለገባኝ ነው" አልኩት
በመኖር ውስጥ ተምረን ያሳጠርነው መስፈርታችን ያለመፈለግ ያመጣው አይደለም።
እስቲ ደህና እንደር😍
@sumeyasu
@sumeyaabot

ያቺ ቁንጅናዋ የዘመኗን ሴቶች በማይለካ እጥፍ በልጦ የተገኘው ራህመት ቢንት አፍረኢም ቢን ነቢዩሏህ ዩሱፍ
ከብዙ የተትረፈረፈ ፀጋ በኋላ ታላቁን የአሏህ ነብይ አዩብ መከራ አጋጠማቸው ሀብታቸው ልጆቻቸው ጠፉ አስቀያሚ በሽታም መፈናፈኛ አሳጣቸው በጎ ይውሉለት የነበረው ህዝባቸውም አውጥቶ ቆሻሻ መጣያ አካባቢ አረጋቸው ህዝባቸው ፊት ነሳቸው ሰውነታቸው ከዳቸው ምላሳቸው ብቻ በዚክር ቀረች
ግን እሷ ያንን ሌሎች ሴቶችን አንገት ሚያስደፋ ሙሉ ውበት ይዛ አልተቀየረችባቸውም ይልቁኑም ከመቼውም በላይ ቀረበቻቸው አዘነችላቸው ኻደመቻቸው ለሰዎች በደሞዝ ስራ እየሰራች ለውድ ባሏ ምግብን ታመጣለችውና ታበላቸው ነበር ።ግን ይህም አልቀጠለም ሰዎች ይሄ በላእ(በሽታ) ይተላለፍብናል በሚል እሷንም ማሰራት አሻፈረኝ አሉ ውድ ባሏን ምታበላቸው ነገር ብታጣ ቢጨንቃት ቢጠባት ትልቅ ውሳኔን ወሰነች ፀጉሯን ሁለት ጉንጉን አድርጋ አንዱን ጉንጉን ለታላላቅ ሰዎች ሸጠችውና ለባሏ ምግብን አመጣች ማያልቅ የለምና አለቀ....!
አሁንም ቢጨንቃት የቀረውን አንድ ጉንጉን ቆርጣ ለባሏ ምግብን አመጣች ታላቁ የአላህ ነብይ አያዉቁም ግን ኬት ነው አሉ ካልነገርሽኝ አልበላም አሉ በዚህም ጊዜ ኺማሯን ከጭንቅላቷ ላይ ወረድ አደረገችው በዚህም ጊዜ ታላቁ የአሏህ ነብይ ያንን መስዋእትነት አዩ ውስጣቸው አዘነ ፣ተሰማቸው በዚህም ጊዜ ዝንት አለም በአሏህ ቃል ሚቀራውን ፍፁም ታዛዥነት ተናናሽነት ለአሏህ ውሳኔ ጥላቻ የሌለበትን ንግግር ተናገሩ፦
وَأَیُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥۤ أَنِّی مَسَّنِیَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّ ٰحِمِینَ
አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
አሏህም ታላቁ ባርያውን አላሰፈረውም የወሰደባቸውን መለሰላቸው አዋብ ብሎ አወደሳቸው እስከመጨረሻው የትእግስት ተምሳሌት አደረጋቸው።
#ራህመት ቢንት አፍረኢም ቢን ዩሱፍ ቢን ያዕቁብ ቢን ኢስሃቅ ቢን ኢብራሂም አል ኸሊል ዐለይሂሙሰላም

ኢማም_አህመድ_ኢብን_ሀንበልን በቁርአን ላይ ያላቸውን አመለካከት ከቀየሩ ከፍተኛ ሽልማት ሊሰጣቸው ካልቀየሩ ግን የከፋ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ቢዝትም ኢማሙ ከአቋማቸው ፍንክች ሳይሉ ቀሩ።
አል-ሙዕተሲም በማባበሉና በማስፈራራቱ ውጤት ሲያጣበት #ኢማም_አህመድ እንዲቀጡ አዘዘ።
በዚህም ጀርባቸው በደም እስኪጨቀይ
ድረስ ተገረፉ። በየመሃሉ አል-ሙዕተሲም ወደ #ኢማሙ እየቀረበ ሃሳባቸውን ቀይረው እንደሆነ ለማረጋገጥ "አህመድ ሆይ! ይህቺን አንዲት ዐረፍተ ነገር ተናገርና ከዚህ ስቃይ ነፃ አወጣሃለሁ" ሲላቸው ይሰጡት የነበረው ምላሽ
"እንደዚያ እንድናገር ከፈለግክ ከቁርአንና ከሃዲስ ያንተን ሃሳብ የሚደግፍ አንዲት ማስረጃ አቅርብልኝ" የሚል ብቻ ነበር።
ጨካኙ መሪ አል-ሙዕተሲም #ኢማም_አህመድ በያዙት አቋም መጽናታቸውን ሲያስተውል ግርፊያው እንዲበረታባቸው ጭፍሮቹን አዘዘ።
#ኢማም_አህመድ ከመጠን በላይ ሲሰቃዩ ይመለከት የነበረና አል-ሙዕተሲም አጠገብ የነበረ አስመሳይ ዓሊም ለኢማም አህመድ ""አላህ በራሳችሁ ላይ መከራ አትፍጠሩ ብሏል"" እያለ ሊመክራቸው ሲቃጣም #ኢማም_አህመድ ለሰውዬው "ሂድና ከበሩ በስተጀርባ ያለውን ተመልከት" አሉት። በሩን ከፍቶ ሲወጣ በደጃፉ ላይ መጻፊያና ወረቀት የያዙ እጅግ በርካታ ሰዎች ተሰብስበዋል ፡፡
ለሕዝቡ "እዚህ ምን ትሠራላችሁ?"ሲላቸው "ኢማማችን ኢማም_አህመድ የሚናገሩትን ለማድመጥና የሚሰጡትን ምላሽ ( አስተምህሮት ) ለመመዝገብ ነው፡፡ የሚል ምላሽ ሰጡት፡፡
ሰውዬው ወደ ኢማም_አህመድ በመመለስ ያየውንና የሰማውን ነገራቸው እሳቸውም ታዲያ እንዲህ አሉት ይህንን ሁሉ ሕዝብ ወደ ጥመት እንድመራቸው ትፈልጋላችሁን ? እነርሱን ወደማይሆን መንገድ ከመምራቸው በርግጥ ሞትን እመርጣለሁ" አሉት።
ኢማም_አህመድ_ኢብን_ሀንበል በቀን ውስጥ 300 ረከአ ሰላት ይሰግዱ ነበር። ንጉሱ አል-ሙእተሲም ሲያሰቃያቸው በነበረ ጊዜም ሶላታቸውን አልተውም በቀን 150 ረከአ ሰላት ይሰግዱ ነበር።

ወጣቶች እንደሚተናኮሏትና እንዳስቸገሯት ለወንድሟ ነገረችው። እሺ ነይ ብሎ ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫ ወስዶ ለፊትና የማያጋልጥ ኢስላማዊ ልብስ ገዛላትና መልበስ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ " አሁንም ወጣቶቹ ያስቸግሩሻል? በማለት ጠየቃት። የእህቱ ምላሽ "በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ልብስ ከገዛህልኝ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ያከብረኛል" የሚል ነበር። ወንድሟ ይህን ሲሰማ እንዲህ አላት « የሚፈታተን ልብስ በመልበስ አንቺ ነበርሽ ማለት ነው የምትለክፊያቸው። እነሱ ቢሆኑ ኖሮ የጨዋ ልብስ ከለበስሽ በኃላም ማስቸገራቸውን ይቀጥሉ ነበር»።
[ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞ ﻷَِّﺯْﻭَاﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ ﻭَﻧِﺴَﺎءِ اﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦ ﺟَﻼَﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰٰ ﺃَﻥ ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼَ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ] الأحزاب 59
«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» አል አህዛብ 59

አንድ በጎ አድራጊ እንዲህ ይላል:-
"...መራመድ የተሳናቸው ህፃናት ላሉበት አንድ ድርጅት መንቀሳቀሻ ዊልቸሮችን አበረከትኩ። የድርጅቱ ባለቤትም አብሬው ሄጄ ዊልቸሮቹን በአካል እንድሰጥ አጥብቆ ጠየቀኝ። ተስማምቼም ሄድኩ። በልጆቹ ፊት ላይም ትልቅ ደስታን ተመለከትኩ። ጨራርሰን ለመሄድ እያልኩ ሳለሁም ከህፃናቱ አንዱ እግሬን አጥብቆ ይዞ አይኖቹን ፊቴ ላይ ተክሏቸው አገኘሁት። ጎንበስ ብዬም; 'ሳልሄድ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገው ሌላ ነገር አለ?' ስል ጠየኩት። እሱም እንዲህ ሲል ሰውነቴን ውርር የሚያደርግ መልስ ሰጠኝ; 'ፊትንህን በደምብ መሸምደድና ማስታወስ እፈልጋለሁ፣ ጀነት ውስጥ ደግሜ ሳይህ እንዳውቅህና አላህ ፊት ደግሜ እንዳመሰግንህ' "

ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ رضي الله عنه ጀናዛውን መላዒካዎች የተሸከሙት እና ዓርሽ የተንቀጠቀጠለት ሰሃባ በእስልምና ውስጥ የቆየው 7 ዓመታትን ብቻ ነበር። እኛ ስንት ዓመታትን ቆይተን ልባችን አለመርጠቡ ያማል።
@heppymuslim29
@heppymuslim29
ልባቸው በመስጂድ ፍቅር ከተጓጠለጠሉ ሸይኾች መካከል የአንደኛው ልጅ እንዲህ ሲል ነግሮኛል
“ ከዕለታት በአንዱ ቀን ከባድ ዝናብና አደገኛ
ንፋስ ነበር፡፡ አባቴ እንዳይቸገር በማለት በቤት አንዲሰግድ ጠየኩት። አባቴ ግን እንዲህ ሲል መለሰልኝ " ወላሂ እየዘነበ ያለው ድንጋይ እንኳ
ቢሆን መስጂድ መስገድን አልተውም:: "
አየህ በሰላት ጉዳይ ድርድር የማይቀበልን ጠንካራ ስብዕና?

የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹አሁን የማላያቸው ለወደፊት የሚመጡ አሉ፤ የጀነትን ሽታ አያሸቷትም፤ ለብሰው ያለበሱ ›› አሉ፡፡
ዛሬ ዛሬ ‹‹ኢስላሚክ ስታይል›› እየተባለ ሴቶች እህቶች የሚለብሱት በጣም አስገራሚ አላህን አይፈሩም ወይ፤ ምንድን ነው ከሌሎች ልብሶች ያለው ልዩነት የሚያስብል ልብሶች ‹‹ኢስላሚክ እስታይል›› የሚባሉ ልብሶች ውስጥ ሲሸጡ ይታያል፡፡
ወገባቸው ጋር ሰፋ ብሎ የመጣውን አባያ፤ ቅርፃቸውን ‹‹8 ቁጥር›› እንደሚሉት ያሳይላቸው ዘንድ ያስጠብቡታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሆነ አካላታቸውን ለሰዎች ጎልቶ እንዲታይ ከውስጥ እስፖንጅ የሚያደርጉም እንዳሉ፤ ልባችንን ቢከፋው እና ብናዝንም ለመስማት ተገደናል፡፡ እነዚህ ሂጃብ ከመሰሉሽ ሂጃብ አይደሉም ‼️
ቀሚስሽን በእጅሽ ከፍ አድርገሽ እግርሽን ለአጅነቢ ወንዶች ላሳየሽው ሁሉ ነገ አላህ ፊት ትጠየቂያለሽ፡፡ ዛሬውኑ ቶብቺ እህቴ ፡፡ ሂጃብሽን አስተካክይ
ለአላህ ታማኝ የሆነ ባል የሚገኘውም አላህን በመፍራት እንጂ እንዲህ በየአደባባዩ አላህ የጠላውን ተገላልጦ መሄድ፤ ጥብቅብቅ ያለ ልብስ መልበስ፤ ዊግ መቀጠል ፤ ቅንድብ መቀንደብ አይደለም፡፡
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹እናንተ ሴቶች ሆይ! ጀሃነም ውስጥ በዝታችሁ ተመለከትኳችሁ ብለዋል››፡፡
@Heppymuslim29

ከአስር አመታትና እንደዛ በፊት መስጂድ ውስጥ ኪታብም ቁርዐንም የምታስቀራን ሴት ነበረች። የሑላችንም ሴት ልጆች የመጨረሻ የመዳረሻ ምኞታችን ነበረች። እንደሷ ዓሊም ፡ እንደሷ ታጋሽ ፡ እንደሷ ስታወራ የሚያምርባት ፡ እንደሷ ትልልቅ እናቶችን ሰብስባ አሊፍ የምታስቆጥር ፡ እንደሷ ሑሉም ሴት ጉዳዩዋን የምታማክራት ፡ እንደሷ ሰላቷ የሚረዝምላት መሆን!
ከሑሉም ከሑሉም ይደንቀኝ የነበረው የሱጁዷ እርዝመትና ከሰላቷ ኋላ ያለው የፊቷ ስክነት። እውነት ጥያቄ ይሆንብኝ የነበረው ሱጁዷ ውስጥ ምን ብታወራ ነው እንደዛ ይረዝምላት የነበረው? አያልቅባትም? መች ነው የምትቃናው? የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ ። ያኔ በቻልኩት ሱጁዴን ለማርዘም እሞክር ነበር... «ሱብሃነ ረቢየል አዕላ ወቢሐምዲህ» የሚለውን እስከሚደክመኝ በመደጋገም።
ከጥቂት አመታት በፊት ነው የገባኝ... ጌታዬን የማወራው በዝቶ ሱጁዴ አልበቃኝ ማለቱን...🌼

የሕይወት ግብህን ቅረፅ @heppymuslim29 .pdf
32.2 MB
📚ርዕስ:- የሕይወት ግብህን ቅሬፅ (sit and set your goal in life)
📝 ኡስታዝ ያሲን ኑር አሊ
📖የገፅ ብዛት:- 274
📆ዓ.ም:- 2007
📚1 @heppymuslim29
📝 ኡስታዝ ያሲን ኑር አሊ
📖የገፅ ብዛት:- 274
📆ዓ.ም:- 2007
📚1 @heppymuslim29
በጠዋት አንድ ሰአት ላይ አንድ ጓደኛዬ ደውሎ እርዳታ ከምንሰጣቸው ሰዎች አንድ ደካማ አሮጊት በጣም ታመዋል፤ ከጎናቸው ማንም የለምና እባክህ አጅሩን ከአላህ እናገኛልን ሀኪም ቤት እናድርሳቸው አለኝ።
ልምዴ ሆኖ በረመዳን ከፈጅር ሰላት በኋላ እንቅልፍ የምተኛበት ወቅት ነው ሆኖም አንድ ኡዝታዜ ተጨማሪ (ናፊላ) የሆኑ ኢባዳዎችን ከመስራት የሰዎችን ጉዳይ (ሀጃ) መፈፀም ይቀድማል ሲል የተናገረውን አስታወስኩና እያመነታሁ አንድ እግሬን ወደ ፊት ሌላኛውን ወደ ኋላ እየጎተትኩ ከቤቴ ወጣሁ። ወደ አዛውንቷ ሴትዮ ቤትም ሄደን ሀኪም ቤት ወስደናቸውና በአላህ ፍቃድ አስፈላጊውን ህክምና ካደረግንላቻው በኋላ ጤንነታቸው መለስ አለ። እናም ወደ ቤታቸው ይዘናቸው ተመለስን። አዛውንቷ ምላሳቸው ዱዓእ ከማድረግ አልቦዘነም ነበር። መንገዱን ሙሉ ዱዓእ ሲያደርጉልን ቆዩና ከቤታቸው አድርሰናቸው ጓደኛዬን ተሰናብቼ ወደ ቤቴ አመራሁ፤ ቤት ስገባም እናቴ የመኝታ ክፍሌን ስታፀዳ አገኘኋትና ፦ እማዬ ምን ነው!? ምን ሆነሻል!? ምን እየሰራሽ ነው? ስል ጠየቅኳት።
እሷም፦ ተኝቼ ሳለ ከክፍልህ ከባድ ድመፅ ሰማሁ ልጄ ላይ ምን ወድቆ ነው ብዬ እየጮህኩ ስሮጥ ወደ ክፍልህ መጣሁ አልሀምዱሊላህ አንተ የለህም ቁም ሳጥኑ ግን አልጋህ ላይ ተደፍቶ አገኘሁት ቆይ ግን የት ነበርክ !? ብላ ጠየቀችኝ። ይህን ግዜ ፈገግ አልኩና እንዲህ የሚለውን የረሱልን ﷺ ቃል አስታወስኩ፦
《 (ለሰዎች) መልካምን መስራት ከመጥፎ አደጋ (አሟሟት) ይጠብቃል።》